እውን ለውጡ በማሸንፍ ወይንስ በንቃቃት ላይ?
ስቅዛት በፈቃድ።
„ጋሜል። ቀበሮች እንኳን ጡታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ።
የወገኔ ልጅ ግን እንደ ምደረ በዳ ሰጎን ጨካኝ ሆነች።“
ሶቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፫
ከሥርጉተ©ሥላሴ
22.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
- መነሻ።
Ethiopia: በቡራዮ ከተካሄደው ጥቃት የተረፉ ዜጎች ፖሊስ ሦስት ቀን ሙሉ ስንጨፈጨፍ አልደረሰልንም
አሜኑ! ይቻላል ወይ በጃዋርውያን/ በኦነግውያን መንፈስ አገር እየታመሰ?
እንዴት ናችሁ ውዶቼ አንድ ኢሜል አንድ ወዳጄ ላኩልኝ። እኔ እኮ መሬት ላይ የጋሞ አዛውንታት የሠሩትን ማቃለሌ አይደለም። ያ መልካም ነገሩ ኦሮምያ ላይ ካልሠራ ምንድነው ፋይዳው ነው ጉዳዩ።
እነኛ ቅኖች መበደልን በበቀል አለመመለሳቸው በፈጣሪ ዘንድ ያስደግፋቸዋል። ነገር ግን መንግሥት የተጠቀመበት የቄሮ ወንጀል እንዲሸፈንለት መሆኑ ነው እኔ የማይመቸኝ፤ ሌላው አባገዳዎች ኦሮምያ ላይ ጉዳት ሳይደርስ ለቃችሁ ውጡ ማለታቸውን ከኦሮምያ የተፈናቀሉ የአማራ ልጆች ከ6ወር በፊት ገልጸዋል።
አባ ገዳዎች እንደ ጋሞዎቹ መሆን ተስነቿው ነው የማዬው። አባ ገዳዎችም የኦነጋውያን መንፈስ እንጂ ለአብይ ካቢኔ ክብካቤያቸውን አላዬሁም። ቡራዩ ላይ አባ ገዳዎች የሉንም? ቢያንስ ሬሳ አስነስተው በክብር ለማስቀብር ምን አገዳቸው? ሞትስ ቢሆን ምን አለ ቢቀበሉት። ሰማዕትነት ነው። ሊቢያ ላይ አኮ አንድ ሙስሊም ሰማዕት ራሱን ቀራኒዎ አውሏል ከወገኖቹ ጋር።
አባገዳዎች ከተጠቂዎች ቀደመው ቢሰው የአቡነ ጴጥሮስ ትውፊታቸውን ከወኑ ነበር። ግን የሆነው የሚሆነው ነገር ሁሉ እኮ ወንጀለኛን መደበቅ፤ ንጹሃንን በአደባባይ መረሸን ነው። ይህ ደግሞ አሊ አይባልም። ሌላው ቀርቶ ለተጎዱ እርዳታ የሚያደርጉ የአዲስ አባባ ቅን ወጣቶችን እስር ቤት አስገብቶ ተረጅዎች በራብ እንዲያልቁም እዬተደረገ ነው።
ሰቆቃው እኮ ድርብ ነው። ቄሮ ሲጎዳ ጉዳቱን እንዳይሰማው የተጎዳው ወገን ከጎን ሆኖ መርዳት እኮ ኦሮምያን ማገዝ ነው። እነሱ ላጠፉት ነገር፤ ላቃጣሉት አብሮነት ወገኖች ሆድ እንዳይብሳቸው የበኩልን ማድረግ በራሱ ወንጀል መሆን አልነበረበትም። እንዲያውም ኦሮምያን ማገዝ ነው። ብቻ ምን ዓይነት ህሊና እንደሆን ግራ ያጋባል። ያገዘህን እንዴት ትዘምትበታለህ፤ አሁን በቴዲ ላይ የሚፈሰውም ማዕት ይኸው ነው።
በአዲስ ዓመት ዋዜማ ደግሞ ጠ/ ሚር አብይ ሳይቀሩ ለደካሞች ድጋፍ ሲያደርጉ ነበር። አብነቱ እኔን ተከተሉኝ ነው። የአዲስ አባባ ወጣቶች ግን የተገለበጠ ዕጣ ነው የገጠማቸው። ቴዲም እንዲሁ። ይህም ወንጀል ነው በጃዋርያኑ ዘንድ። ስለዚህ ጃዋርያን አረመኔያዊ ድርጊታቸው እሰከ መጨረሻው ይቀጥል፤ ያን የሚያስታግስ የበጎ ነገር ምልክቶች መታዬት የለበትም ነው ጉዳዩ። በቀጥታ ፀረ አብይ ዘመቻ ላይ ራሱ የአብይ ካቢኔ እዬተገበረው ነው፤ ሽፋንም እዬሰጠው ነው። ኦህዴድ በስተጀርባ ሙሉውን ሃላፊነት ለጃዋር አስኳድ አስረክቧል። ይህ በሳል የሆነ የፖለቲካ ቻሌንጅ በጥሞና ሊመረመር ይጋባል።
እኔ የጠ/ሚር አብይ አህመድ „አይደገምም“ ሲሉ ራሱ የትኛው ፕላኔት ነው ያሉት ሁሉ ብያለሁኝ። ሁሉ እንደሳቸው ቅን ይመስላቸዋል። በሳቸው ሥልጣ ኦነግ ነው እየመራ ያለው። አማካሪዎችም ወደዛ ነው እዬገፉ ያሉት።
"አይደገምም"ያ ከሆነ ረጂ የበጎ አድራጎት ወጣቶች ስለምን ነው የታሰሩት። የተጠቁትን መርዳትም ወንጀል ሆኖ „በደል አይደገምም“ ማለት ምን ማለት ነው። የኦሮሞ ፕሮቴስት እና የአማራ የህልውና ታገድሎ ተነስቶ በነበረበት ጊዜ ሳጅን በረከት ስምዖን „አይደገመም“ በማለት ቲሸርት እስረኞችን ሲፈቱ አስለብሶ ነበር። ግን የነፃነት ተጋድሎው የቀረ ነገር አልነበረም። አሁን ያን ነው እማዬው።
"አይደገምም"ያ ከሆነ ረጂ የበጎ አድራጎት ወጣቶች ስለምን ነው የታሰሩት። የተጠቁትን መርዳትም ወንጀል ሆኖ „በደል አይደገምም“ ማለት ምን ማለት ነው። የኦሮሞ ፕሮቴስት እና የአማራ የህልውና ታገድሎ ተነስቶ በነበረበት ጊዜ ሳጅን በረከት ስምዖን „አይደገመም“ በማለት ቲሸርት እስረኞችን ሲፈቱ አስለብሶ ነበር። ግን የነፃነት ተጋድሎው የቀረ ነገር አልነበረም። አሁን ያን ነው እማዬው።
ሌላው „የጥፋች ሃይሎችን“ አሁን እኮ ቁልጭ ያለው የጥፋት ሃይል ቄሮ ነው። መሪው ጄኒራላቸው አቶ ጃዋር መሃመድ እና ቡድኑ ነው። አጋዡ ደግሞ ኦህድድ/ ኦዴፓ ነው። እንግዲህ ቲም ለማ ቀርቶ ቲም ጃውርውያን ራሱ ቲም ለማ ከሆነም ይነገረን። እሱን በቢአይፒ ደረጃ እያቀማጠልክ ሌላው አንተ ተጸይፎ ሲያብጠልጥልህ የነበረውን፤ አሁን ህውከት በመፍጠር እዬመራ ያለውን የአቶ አብዲ ኢሌን ቅጅ አዲስ አባባ ላይ አክብረህ፤ እንደ ታቦት የለውጥ ቀልባሽን መንፈስ ጀብጅበህ አብይ ፍቅሬ ነው ያለውን ባለውለታህን፤ ላማ የ እኔ ነው ያለውን ህሊና፤ ላንተ ሲል አካሉንም ህይወቱንም ላጣ፤ መንፈሱን የሸለምህን ታስራልህ፤ በአደባባይ ትረሽናለህን?
የኦዴፓ ጉባኤ ማሸነፍ መሬት ላይ ካለው ዕውነት ጋር አልተገናኘልኝም - ለእኔ፤ ዕውነት እኮ ነው አሁን የጠ/ ሚር አብይ አህመድን እዬሞገተ ያለው እንጂ ሥርጉተ ሥላሴ አይደለችም። በቀል በቀልን መውለድ የለበትም። ጥላቻ ጥላቻን አያክመውም። የጋሞ አባቶች ያደረጉት ይህንን ነው።
አህዴድ/ ኦዴፓ መንግሥት ላይ ተቀምጣችሁ ዕውነት በአደባባይ የሚለውን ህግ ማስከበር አልተቻለም። በዳይ ተቀምጦ ተባዳይ ይታሠራል ይረሸናል። ዛሬም ድምጽ አልባዎቹ እናቶች ያለቅሳሉ። ያነባሉ።
ነገ ኢትዮጵያን ሶርያ ለማድረግ የተሰናዳው ህዝቃኤልውያን፤ በቀላውያን፤ ጃዋርውያን፤ አራርሳውያን መንፈስ ንጹህ ነው ጻድቃን¡ለአብይ ካቢኔ እና ሚዲያ ያለተደፈረው እውነት ይህ ነው። ግን ዶር ለማ መገርሳ ከዬትኛው ወገን ናቸው? በማን ፈቃድ እና ቸርንት ነው ይህ የህግ ጥሰት እዬተከወነ ያለው።
የጋሞ አባቶች ያደረጉትን የዶር ለማ መገርሳ አስተዳደር ሆነ አባ ገዳዎች ሊያደርጉት አልቻሉም። እነሱ ተግባሩን ባልደፈሩት ቁጥር ለአረመኔዎች የልብ ልብ ይሰጣሉ ማለት ነው። ባለፈው ጊዜ ኦቦ በቀለ ገርባ በፎቶ ሪከርድ እያደረጋችሁ ያዙ ሲሉ ውስጥ ለውስጥ ያደራጁት ሃይል እና በጠ/ ሚር አብይ ካቢኔ መወገድ የሰጡት ብልህ መረጃ አለ።
ቀጣዩ በቀል በሁሉም ዘርፍ ቀጣይ ነው። ጭካኔ ነው አሁን ኢትዮጵያን እዬመራት ያለው። ጃዋርውያን የፈለጉትን እያስደረጉ ነው።
በዶር አብይ አህመድ ላይ ጨክነን ወቃሳ እንድንጽፍ እኮ እያስገደዱን ነው። ደግፈን ስንጽፍ ኦነጋውያን ያበዱትን ያህል አሁን ደግሞ የሚፈልጉትን ምርቃና ምርቃት ጀባ እያልናቸው ነው - ተገደን። ስለምን አብይ ራሱን የመከላከል አቅሙ ስስ ስለሆነ። ቢያንስ የቁም እስር ስለምን አያደርጋቸውም እነዚህን ሰዎች፤ አሁን እኮ እኔያ የተከበሩ አቶ ደጀኔም ጣፋም ታከለው እያዬሁኝ እኮ ነው።
ዲሲዎች ለዶር ማራራ ጉዲና የራት ግብዣ እንዳሚያዘጋጁ ሰምቻለሁኝ። በውነቱ ሥራ ፈቶች ናቸው። አውሮፓ በ90ዎቹ አጋማሽ ብዙ ደክመንብታል፤ እንሱ ከቁብ ባልቆጠሯቸው ጊዜ። አሁንም እርሾውን እናስቀጥላለን ያሉ በተለይ አምሰተርዳም አያለሁኝ። በታሠሩ ጊዜም እንሱ ሳይሆኑ እኛ ነው የተጋንላቸው፤ አሁን ግን ዘምድ ከዘመዱ ነው የሆኑት። ጊዜ ማባከን አያስፈልግም። በቃ ሁለመናችን ሰጥተን አየናቸው አስከ አለፈው ቅዳሜ ድረስ። ሰማይ ሰማይ እንጂ መሬት አይሆንም። መሬትም መሬት እንጂ ሰማይ አይሆንም።
አንድ አብይን አምኖ ነገን ማሰብ ምጥ ነው … አብይ ራሱን ከነቤተሰቡ ካተረፈም መልካም ነው … ማሸነፍ በድርጊት እንጂ በወኔ አይደለም። ተሸናፊው ሃሳብ መሬት ላይ የቱ እንደሆነ መንግሥት እየወሰደ ካለው የህግ ጥሰት እርምጃ ማዬት ይቻላል። ለመንግሥት ቄሮ ብጽዑን ነው ያለ እለት በሃሳብ ተሸንፏል፤ ችግሩን ለሥም የለሽ የሰጠ ዕለትም እንዲሁ።
„አዲስ አበባ በቀለበት ውስጥ ነበረች አሁንስ ማን ከልካይ አለን“ ማለት በብቁ ሁኔታ ስኳድ እንዳላቸው፤ መደረጃታቸውን ያሳያል፤ ለዛውም እያሾፈ ነው አንዲህ ያለው። ከዚህ ቀድም አንድ ብርቱ የአባ ገዳ ተናጋሪ የሰላም ኮንፈረንስ እነ ሳጅን በረከትን ባዘጋጁት ዶር አብይ አህመድን ባትመርጡ ኖሮ እንተያይ ነበር ነው ያሉት።
አባ ገዳዎች ለዶር አብይ አህመድ ወግነው ነበር መደራጀታቸውን የነገሩን ያን ጊዜ። ያ ውገና ዛሬ አለ ብሎ መናገር አይቻልም። ሁሉም በመንፈሱ ከዶር አብይ አህመድ ጋር ነው ማለት የማያስችሉ ምልክቶች አሉ። ሥርዓተ አልበኝነቱን ላለማጋለጥ እኮ የራሳቸውን ደም እና ሥጋቸውን ላለማሳጣት የሚያደርጉት መንኮራኩር ድንቡልቡል ነው።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅናቱም፤ ምቀኝነቱም፤ ኢጎም፤ ሴራውም ታክሎ። አንድ የ42 ዓመት ወጣት ይህን ያህል ብቃት እና አቅም ከርህርህና ከቅንነት ጋር ማዬት አለተለመደም፤ በዘመናችን ተጽዕሞ ፈጣሪያን እኮ ከስመው ነው የቀሩት። አሁን ይሆናል ተብሎ ባልተገመተ ሁኔታ ኤርትራንም ደመረ እና ይህ ደግሞ ያ መከረኛ አራት እግር አላሚውን ሁሉ አሳባደ። ጉዳዩ ይህ ነው። ቅናት ነው አገር ምድሩን እያሰባደው ያለው።
ሌላው የግራኛውያን መንፈስ ነው። ግራኛውያን የሚያርመጠምጣቸው ጉዳይ ደግሞ አለ። ኢትዮጵያ ላይ እስላማዊ መንግሥት የመገንባት ጉዳይ። ይህም ልብ ያልተባለው ፍሬ ሃሳብ ነው። ለነገሩ ከፌድራል ጀምሮ ባሉ መዋቅሮች ሁሉ ያለው ዕውነት ግን ከፍተኛውን የፖለቲካ ዕወቅና ያገኘው እስላማዊነት ነው። አቅም ያላቸው ሊሂቃን አያለሁ። ለዛውም ሴቶች ይህም ሆኖ ለጃዋርውያን አላረካም። ኢትዮጵያ በቁራዕን መመራት አለበት።
በምድር ማንን ትጠላለህ ቢባል አቶ ጃዋር መሃመድ አብይን ነው የሚለው። ኢንፈረሪቲ ኮንፕሊክስ አለበት። እሱ ብቻ አይደለም የምናከብራቸው ሁሉ የሚያስማማ መንፈስ አላቸው አብሶ ሊሂቃኑ ወገኖቻቸው በአብይ ኩራት የላቸውም። ስለምን? ሰለሚበልጧቸው።
በዬደቂቃው እኮ አቶ ጃዋር መሃመድን ሲያሳብደው የነበረው የአብይ አቅም አደባባይ ሲወጣ አጀንዳ አልባ መሆኑን ስላወቀ ነበር። 100 ቀኑን ከመሰሎቹ እኩዮወች ጋር ሆኖ ጥላሸት ቀብቶታል። ብቻ በገርዳሜም በወልቻሜም የፈለገው አገር መግባት ብቻ ነበር። ገብቷል ከገባ በኋዋላ ለሃጅነት አረብ አገር ነበር።
ኢትዮጵያ ከመሄዱ በፊት ኬንያ ነበር። ጄኔባም የሚያሰጠጋው ባይኖርም አንድ ፌካዊ ጉባኤ አካሄድን ብለው ከአጋሩ ከስታሊናዊው ፕ/ ህዝቃኤል ጋር አንድ ትዕይንት ፈጽመዋል። መግመለጫው በእንግሊዘኛ ነበር።
ኢትዮጵውያን የሚወዱትን እንደ አማራጭ ያዩት የነበረውን ህብር ራዲዮን በምን ሙሉ አቅም ሲጠቀምቡት እንደ ነበር እንደ እኔ ልብ ያለው አልነበረም። ቢቢኤን ዞቢዞ። ይህ ሁሉ የአሸባሪዎችን ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ለማሰገባት ቃል ለመፈጸም ነበርን ያሰኛል? ያን ያህል የሚዲያ ሽፋን ካለማስተዋል ከሰጡ ድምጽ ከሆኑ በኋዋላ ደግሞ ለቅሶ ብዙም እርጂ አይደለም፤ „ቁጭ ብለው የሰቀሉትን ቁሞ ማውረድ“ እንደሚሉት ማለት ነው … ። አቶ ጃዋር አለሳችለው እያለ ነው ትቢቱ ሞልቶ ሲተርፈረፍ እርግጠኝነቱን የማድረግ አቅሙን የሚተነፍሰው።
ኦዴፓ አመራሬን ቀይራለሁ ይላል። ማዕከላዊ ኮሜቴ በተወሰን ጊዜ የሚገናኝ፤ ጉባኤው እስኪሰበሰብ ድርስ የጉባኤውን ተግባር ተክቶ የሚሰራ ሴሪሞናዊ አካል እንጂ ዕለታዊ የፓርቲው ተግባር ላይ ሚና የለውም።
ዕለታዊ የፓርቲውን ተግባር የሚመሩት እንደ ኢሠፓ ዛሬ ፕሬዚዲዬም ተብለዋል ሥ/አስፈጻሚዎች የትኞቹ ይሆኑ የአብይ መንፈስ ደጋፊዎች? መቼም በኦሮምያ ታላቅነት እና አፍሪካዊ አንበሳነት የሁሉም እድምታ ነው። ጠረኑ ቅይጥ ዝንቅንቅ እና ጥምልምል ነው።
እስኪ በምልሰት OMN ወደ አገር ሲገባ የነበረው መሰናዶ ፍጥነት እንዴት እንደ ነበር አስተውሉት። ቤቱ እንዴት ከጸሐይ ብርሃን በፈጠነ መንገድ እንደተገኜ። ራሱ ኦህዴድ/ ኦዴፓ እኮ ነው የኦነግን መንፈስ ተቀብሎ እያስተናገደ ያለው። ኦህዴድ / ኦዴፓ እኮ ከራሱ ሚዲያ OBN እና ከራሱ ዓርማ ይልቅ ኦነጋዊ ልሳን ነበር ቀልቡን የገዛው። ወደፊትም ውሳኔ ላይ እንዲህ እንደሚሆን ቅንጣት አልጠራጠረም።
እሰቡት ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ ወደፊት ሲመጡ የዶር ነገሬ ሌንጮ መንፈስ እና አሁን የሰጡትን ቃለ ምልልስ አዳምጡት። አሸንፈናል ሲሉ ዶር አብይ አህመድ በሳቸው ድልድይነት የኢትዮጵያን ህዝብ ለማረጋጋት ካልሆነ በስተቀር ከሰሜን አሜሪካ ከተመለሱ ጀምሮ መሪው ሃይል ኦነጋዊነት ነው። የአብይ ካቢኔ ያልገባውም ይህን ነው።
የሳቸውን ኢትዮ አፍሪካዊነት ከጥጋቸውም አያደርሱትም ኦነጋውያን፤ የቤታችን ሥራ አስቀድመን መሥራት ነው ባይ ናቸው እነ አቶ ደጀኔ ጣፋ። እንዲያውም ለውጡ ተቀልብሷልም ባይም ናቸው።
አንዳቸውም ለውጡ ከቄሮ ውጪ የመጣ ነው ብለው አያምኑም። አብረው ታስረው የአማራ የህልውና ተጋድሎ አባላት አይተው እንኳን። ድራማው እኮ ቀላል አይደለም። ነገ አገር የገቡት ከ ኦሮሞ ውጭ ያሉት አክቲቢስት በሉት፤ የፖለቲካ ድርጅቶች በሙሉ እኮ ተራ በተራ ይለቀማሉ። በተለያዬ መንገድ ጥቃቱ ቀጣይ ነው። ገራሚው ነገር ዛሬ አንዱ የኢህአፓ ክንፍ ይህን እዬሰማ አገር ገባ ይላል ዘጋባው። እኔ የገቡት እንዴት ትሆን ነፍሳቸው ጭንቅ ይዞኛል አሁን ተጨማሪ ታሳሪ ደግሞ ገብቶላቸዋል። ጃዋርውያን ከህሊናው ያለ ቡድን አይደለም።
የአሁኑ የ ኢህአፓ አንዱ ከንፍ የማንኛው እንደሆን አይታወቅም ያው አማራ መሬት ቻል ተብሎ ወደ ዛ ይጋፋል። በቃ ሌላ ቦታማ የቧልት ክልል አይደለም። የሁሉም ነገር ማከማቻ ጉርድ በርሚልነቱን ድርሻ ብአዴን/ አዴፓ ይወጣው … ያው ቀጣዩ ሥያሜ ይሄው ነው ለዚህ መሰል ሴራ ነው አቶ ተስፋዬ ጌታቸው ቀደመው የተገደሉት። በህመም አይደለም ቆሞሱ የተለዩን። በምግብ በብክለት ነው። ይህን ማን እንዳደረገው የዛሬ ብአዴኖች የነገ አዴፓዎች ይናገሩት። ቀልፍልፍ - ጥምልምል - ጥምንምን ያለ ጉዳይ የመንፈስ ቁርጥማት ነው ያለው።
የቆመስ ኢንጂነር ስመኘው አሟሟትም ከዚህ ጋር የሚታይ ነው። ድፈረቱ የሚያንሰውም ለዚህ ነው የአብዩ ካቤኔ። አንተ በሌለህበት ከሆነ ትደፈረዋለህ። ስለሌብነት ጠያፊነት ሲነገር በመንግሥት ሚዲያ እና ስለሚጣፈው ነፍስ ሲነገር ቶኑ አንድ አይደለም፤ የተሳሰረ ጉድ ስላለ። እኔ አሁን ስለፈለጉኩት ድርጅት የልቤን እናገራለሁኝ እጽፋለሁኝ። ምክንያቱም የምንም ዓይነት ፍርፋሪ ልቅምቃሚ ተዋሽ ሳላልሆንኩኝ። ዘማዊ ሆኜ ስለዘማዊነት ጸያፊነት መናገር አልችልም። በገዳማዊ ህይወት ወስጥ ሁኜ ግን እንዳሻኝ መናገር እችላለሁኝ።
- · የበሰለው ዕቅድ።
ደጋግሜ ስጽፍ ሰዉ ሊያዳምጠኝ አልፈቀደም። ግንቦት 7፤ አቶ ታማኝ በዬነን፤ ኢሳትን አትሂዱ ወደ አገር ሁሉ ብዬ ጽፌያለሁኝ። ኢሳት ወኪል ብቻ ይኑረው ነበር ምኞቴ ይህን መልካም አድርገዋል።
እስኪ አውሮፓው ህብረት ጉባኤ ይጥራቸው እና ግንቦት 7 ለመውጣት ይሰቡ ካቻሉ? ቴስት ያድርጉት እስቲ … 97 ዳግሚ ነው እዬታዬ ነው ያለው። ምርጫ ሳይኖር በምርጫ የተሸነፉ ዓይነት ነው የሚናገሩት ኦነጋውያን። „አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ“ እያሉ እዬተረቱ ነው፤ ለዛውም እነሱ አና ባሉበት በነገዉበት ሁኔታ፤
እስኪ አውሮፓው ህብረት ጉባኤ ይጥራቸው እና ግንቦት 7 ለመውጣት ይሰቡ ካቻሉ? ቴስት ያድርጉት እስቲ … 97 ዳግሚ ነው እዬታዬ ነው ያለው። ምርጫ ሳይኖር በምርጫ የተሸነፉ ዓይነት ነው የሚናገሩት ኦነጋውያን። „አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ“ እያሉ እዬተረቱ ነው፤ ለዛውም እነሱ አና ባሉበት በነገዉበት ሁኔታ፤
የመጪው ምርጫ ጉዳይም እርማችሁን አውጡ … በካቢኔው በኩል እዬተስተዋለ ነው። ለነገሩ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአበሄርን የግንባሩ ጉሮሮ የጽ/ቤት ሃላፊ፤ በመንግሥት በኩል ደግሞ የዶሞክራሲ ግንባታ ቅብጥርሶ ምንትሶ ሚ/ር አድርገህ እንዴት ተብሎ። መመኘት እና መፍቀድ አንድ አይደሉም። የሚዲያ ነፃነት ራሱ መንግሥት ያልደፈረው ነው። የግሎቹ ቢጀምረቱ አይቀጥልም። ጥቂት ጊዜ ነው … እየተለቀመ የሚሆነው ይሆናል።
ጃዋርውያን የአብይን መንፈስ ልቅና፤ የአብይን አቅም ልዕልና፤ ለአብይ የተሰጠው ግሎባል ክብር እና ፍቅር ቀጣይነት እኮ እንደ እብድ ነው የሚያደርጋቸው። አብዩን እኮ እንደ ወገናቸው በፍጹም አያዩትም። የኢጎ አርበኞችም እንዲሁ። ተያይዘው ምሾ ቤት ነው የባጁት። አሁን በስልት ገብተው ጉድ እዬሠሩት ነው፤ አማካሪውም ወደ ገድል እዬመራው ነው። ስለምን አብይን መፈንቀል የሁሉ ህልም ስለሆነ።፡
… ታሥረህ እንደ አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ተቀምጥ ነበር እኮ ሲሉ የነበሩት። ስለምን በህዝብ አውሮፕላን አትጓጓዝም ተብሎ እንዲጻፍ የተደረገው እኮ በኦነጋውያን መንፈስ ነው። ሞታቸው ይፈለግ ነበር። አሁንም የሚሠሩት በቅድመ ሁኔታ ነው።
ቄሮ ጀግና ነው ግን ከቄሮ ገዳይም አሸባሪ አይደለም¡ ጀግና ሳለም ጽፈናል ጨካኝ ሲሆንም እንጽፋለን። ዕውነት እንጂ ዕብለት የህሊና ዳኛ እንዲሆን ስለማይፈቀድለት፤ የታሪክም ስርቆትም ዝርፊያም ነው።
እስካሁን አንድም ገዳይ አልታሠረም። ቢታሰርም ይፈታል። ቀድሞ ነገር ማነው አሳሪውስ? ማንስ ተደፍሮ? የሚታሠረው ባለቤት የሌለው ንጹሃን ነው፤ ወገኖቻችን ሞቱብን ህግ ይከበር ሲባል በአደባባይ ነው የተረሸኑት፤ የኢንጂነር ስመኘው ቀባሪ በአደባባይ ነበር የተደበደበው፤ በአብይ ዘመን ቀብር እኮ አልተፈቀደም። ከኑሯቸው የተፈናቀሉትን ወገኖች እረዳችሁ ተብለው የአዲስ አባባ ወጣቶች እኮ ነው እዬታሠሩ ያሉት።
የአዲስ አባባ ኮንሰርት ጠቢቡ ቴወድርስ እንዳይካሂድ፤ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ እንዳይታይ መጀመሪያ እንዲራዘም ተደረገ፤ ቀጥሎ ይህ ቀውስ ተፈጠረ። „ኢትዮጵያን“ አይፈልጓትም። ከሆነም እያረዱ ለመግዛት ነው ኦነጋውያን ሆኑ ግራኛውያን ምኞታቸው።
ይህ በቀል ስለምን አብይን የአዲስ አበባ ህዝብ ወጥታችሁ ደጋፋችሁ ነው። አሁን እኮ ውጊያው ኢትዮጵያዊነት እና የኦሮሞ ኢንፓዬርነት ነው። እውነት የሆነ ነገር እኮ ነው ይህ። እግዚአብሄርን የማመሰግነው ኢሳት ሙሉው አካል አገር ቤት አለመግባቱ ነው። ለዚህም ነው እርሾ ይኑረን የምለው።
አሜሪካን አገር በነበረው ዝግጅት ላይ „የእኔ አልትሜት ግብ ቀጣዩን ምርጫ ዴሞክራሲ ማድረግ ነው“ ሲሉ ዶር አብይ አህመድ ከዙሪያቸው ያለውን ጉዳይ ብዙም የተመለከቱት አይመስለኝም። ማነው ከሳቸው ጋር ያለው አሁን? ማነውስ የሚታመነው?በሌላ በኩል ያን ጊዜም ጽፌዋለሁኝ ሊሂቃኑ ሁሉ ውሃ የባለው ቅል ነው የሆኑት። ሞጋች ነው የጠፋው ቢያንስ ነገረ ፈትወርቅ እንዴት አይነሳም?
እንኳንስ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ፤ ተንፈሶ ማደርም፤ ያሻውን ዕምነት መከተልም ቀኗ መቀኖ የምታጣባት አውሎ ነው ያለው። ይህን የኢትዮጵያ ህዝብ በማስተባባያ ዜናዎች ሳይታለል ከልቡ ሆኖ ማሰብ ይኖርበታል።
ትናንትም ህግ መጣስ፤ ዛሬም ህግ መጣስ ከሆነ ዜግነት የት ላይ ነው? አንድነት ኢትዮጵያዊነት እምኑ ላይ ነው። የአብይ መንፈስ ቢያንስ ዕውነቱን ለህዝብ ቢያሳውቅ ከጎኑ ቅኖቹን ማሰለፍ ይችላል፤ ከሸፈነው ግን ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር መሰደዱን ልብ ሊለው ይገባል። እኔ እንዲያውም አጤ እያሱን ነው የሚመስሉኝ ነገረ ሥራቸው ሁሉ። የዘመን ልዩነቱ እንደ ተጠበቀ ሆኖ።
የወያኔ ሃርነት ትግራይ እና ጃዋርውያን/ ኦነግውያን ግንኙነት የላቸውም ብለው ማስብ ይከብዳል። ጊዜያዊ ስምምነት ሊኖር ይችላል። አቅምን ለማዘናገት፤ ልክ ኦዴፓ ያሉ ኦነጋውያን ግርባውን ብአዴንን አንደሚያታልሉት ማለት ነው። ጃዋርውያን ካሸነፈ ተራፊ ተጋሩም አይኖርም፤ መንፈሱ እኮ ናዚዝም ነው።
አረመኔያዊነት እኮ ነው የሚታዬው፤ እንሰሳዊነት ነው የሚደመጠው። ጀብደኝነትን ነው እያደማጥን ያለነው ከሊቅ እስከ ደቂቅ። አብዩ ግን ከኦዴፓ ጥገኝነት ከወጣ የተሻለ ዕድል ኢትዮጵያ ይገጥማታል። ለዚህ ደግሞ ዕውነት ላይ መቆም ከተቻለ ብቻ ነው። በስተቀር „አለባብሰው ቢያርሱት ባረም ..“ ነው የሚሆነው።
ለውጡን እንደግፍ ሲባል ለውጡ ሁሉንም ዋስትና ሰጪ ከሆነ እንጂ ወንጀሎኞችን አንግሶ ከሆነ የአረመኔነት ምርጫ የለም። ለምን አቶ ጃዋር መሃመድ አይታሠረም? ለነገሩ ኦዴፓ ላይ ጃዋርያን መልሰው መመረጣቸውን አዳምጫለሁኝ። የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ከአለቁ በኋላ ነው የሚያውቁት። አሁን የተመረጡት አፍቅሮተ ጃዋርውያን ናቸው።፡
የት ገባ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ በቃ ለእኛ አሸከምኖ እሱ ኮበለለን? ከዛች ቀን በኋላ ተደግሞ ተደምጦ አያውቅም እኮ። መቼም ንጹሃንን መግደል፤ ሴቶችን መድፈር፤ በአደባባይ መረሸን፤ ህጻናትን ማረድ፤ ጡት መቁረጥ፤ ህጻናትን አስገድዶ መዘረፍ፤ ቁሶችን መዝረፍ ኢትዮጵያዊነት አለመሆኑን አስተርጓሚ አያስፈልግም።
ነጻነት ተገድሎ ተዘቅዝቆ በሚሰቀልበት አገር ኢትዮጵያዊነት ማለት የቂሉ ማሞ ተቋም በህሊናችን ተንፈራሰሰ እንደማለት ይሆናል። ያ የተደረገው አብይ አቅም የለውም ለማለት ነበር። ደግሞም ነው። ግን ኦሮምያ ላይ ፌድራል መንግሥት የመምራት አቅም አለውን? የለውም!!!!!!!!!!!!
እውነተኛው ዶር ለማ መገርሳ ከአብይ ጋር ስለመሆናቸው፤ ዶር አብይ አህመድ ከዶር ለማ መገርሳ ጋር ስለመሆናቸው ምን እርግጠኛ የሚያደርግ ነገር አለ። ሴሪሞናዊ ነገር ብቻ ነው እኔ ያዬሁት፤ ያን መሰል አብርሃም ወአጽብሃ ድባባ እኔ በዚህ ጉባኤ ላይ አላዬሁም። እርግጥ በጨረፍታ ነው ነገር ግን የእነሱ አብረው ሲቀመጡ አገኝ የነበረውን ምቾት ፈልገሁት አላገኘሁትም። ያን ናፍቆቴን በውነቱ አላገኘሁትም።
- · ጥሪትን …
የአብይ ካቢኔ ግምት አቶ ጃዋር መሃመድ እኮ ምንም እንዳለሆነ ነው፤ የፕ/ ህዝቃኤል ጋቢሳ ምንም እንዳለሆኑ፤ ኦቦ በቀለ ገረባ ምንም እንደማያደርጉ ነው „ስትራቴጂዊ ተግባር“ ሰንከውን ቆይተን ማለት ምን ማለት ነው?
የኦህዴድ /ኦዴፓ አልትሜት ግብ እኮ እንደምንም ተሟሙቶ የኦሮሞን አክቲቢስቶች፤ ጋዜጠኞች፤ ሊሂቃንን፤ የፖለቲካ ድርጅቶች አገር ማስገባት፤ ማሰባሰብ እና አቅሙን ማጠናከር፤ ማጎልበት ነው የነበረው፤ ይህን አሳክቷል። አሁን ለእነሱ ሽፋን በመስጠት አብይን መፈንቀል ነው ዋንኛ አልትሜት ግቡ እንጂ ነፃ ምርጫ ምንትሶ ቅብጥርሶ አይደለም። „ፊንፌኔ“ አገር ገባ የሚባለውንም አብዛኛውን ወደ አማራ ክልል ነው የሚልከው።
የአማራን ብሄርተኝነት የፈራው በጽኑ ኦህዴድ/ ኦዴፓ ነው። በዓዋጅ እስኪያግደው ድረስ አሁን በመንፈስ እዬታገለው ነው። ከዚህ በተጨማሪ የራስ ተሰማ ናደው ጠረን ስል ነበር አብዝቼ አሁን አደባባይ ወጥቷል „የሽዋ ፓርቲ“ ብሎ። ይህ ሲንተከተክ ለረጅም ጊዜ የቆዬ ሌላው ፈታኝ ጉዳይም ነው። ፈተና ሲጣፋ በፈተና ... ፈተና እስኮዬር ሆነ።
- · ትእግስታዊ ጥበቃ።
ቡራዩ ላይ፤ አስኮ ላይ፤ አሸዋ ሜዳ ላይ እኮ ድርጊቱ እንዲፈጸም ሲደርግ ቁጥር አንድ እኮ ዲፕሎማቶችን ለማስደንገጥ ነው። ቁጥር ሁለት ደግሞ የቴዲ አፍሮን ኮንሰርት ማስተጓጎል ነው፤ መጀመሪያ ዝግጅቱ የተስተጓጎለውም ለዚህ ነው። ቁጥር ሦስት ግንቦት 7 ቀለበት ውስጥ ለማስገባት ነው። ቁጥር አራት አስገድዶ አዲስ አባባን መቆጣጠር ነው፤ ቋንቋውን ኦሮምያ ማስደረግ፤ ሲቀጥል „መጤን“ ማፈናቀል፤ ሃይማኖቱም ይቀጥልላል … ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ!
የቴዲ ኮንሰርት ግን ደግ አምላክ እንኳንም አደረገው። እንኳንም ቀረ። ለበጎ ነው። ፈንጂ ይጠምዱ ነበር። ለመሆኑ የሰኔ 16 ጥቃት በማን ነበር የተፈጸመው? ተርብ እና ቧልት ቢቆም መልካም ነው። ለዚህ ነበር እኔ አስቀድሜ የአዲስ አባባ ድጋፍ ሰልፉ እንዲቀር ተማጽኜ የነበረው።
አሁንም አደባባይ ከመውጣት የቤት ውስጥ ዝምታ መልካም ነው። ለምሳሌ በተመሳሳይ ሰዓት ሁሉም ቤት ውስጥ ሆኖ „ህግ ይከበር“ ድምጽ ቢያሰማ መልካም ነው። ድሬ ላይ ምልክት የተደረጋባቸው ቤቶች አሉ ሞትን የሚጠበቁ። አሰላ ላይም ባለቤት የሌላቸው ወገኖች ኤሉሄ እያሉ ነው።፡ብታምኑም ባታምኑም የበኮ ሃርም መንፈስ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቷል። አሸባሪነት ኢትዮጵያ የመግባት ዕድል አልነበረውም፤ አሁን ግን ዕድሜ ለመደመር ዝንቅ ፖለቲካ¡ይህን አስፈጻሚው ደግሞ ኦህዴድ/ ኦዴፓ ነው።
ብዙ ሰዎች የተደመሩትን ስታመሰግኝ አንቺ ስለምን አልተደመርሽም ይሉኛል? የድምጽ አልባዎችን የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ የት ሁን ብዬ ነው እኔ እመደመረው ብየ እጽፍላቸዋለሁኝ። አደብ ገዝቼ እምከታተለው እኮ አብዩ ሆኖብኝ እንጂ እስከ አሁን ስንት ቦታ እደርስ በነበረ። እርግጥ ስንፍና ብዙ ዋጋ እንደሚያስከፍል ባውቅም የአብይን ሰብዕና አውደዋለሁኝ። ቅንነቱ ያሳዝነኛል። ርህርህናው ይመስጠኛል። ቸኩዬ ላሳጣው አልሻም።
- · ግድፈት መደፈር አለበት።
ከዚህም ባሻገር እጅግ የምሳሳላቸው ለስላሳው ፈላስማው ዶር ዳኛቸው አሰፋ „አብይ የቅኖና አስረኛ አይደለም ግራ ዘመም አይደለም“ ቢሉም እኔ ግን ከዚህ አለያለሁኝ፤ አማራን በሚመለከት ዶር አብይ አህመድ የቅኖና እስረኛም ግራ ዘመም ናቸው። እሳቸው የቅኖና እስረኛ የማይሆኑት ኦሮሞ ቅዱስነቱን በማስከበር ላይ ነው።
ኦሮሞ ታላቅነቱን ወደፊት አምጥቶ አፍሪካን የሚያስንቅ ማህበረስብ በማድረጉ ላይ ነው። ኢትዮጵያንም ይወዷታል። ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንደ አሻው ሳይጠዬቅ ወረራውን በማስቀጠል ላይ ጉዳያቸው ነው በቀል ጥሩ አይደለም ስለሚሉ።
ወያኔ ሃርነት ትግራይ በወንጀሎቹ ሁሉ ተጠያቂ እንዳይሆን ቀዳዳዎችንም በምህረት በይቅርታ በፍቅር እንድፈነው ባይ ናቸው … ይህ ግራ ዘመም በደመመን መግፋት ቢሆንም ለ አጥቂዎቻቸው በድርብ ተደራጅተው አንዲሰናዱ ደግሞ አድርጓል። ከሃሳብ በላይ ቢሆኑን አንድ እንጨት አይነድም አንድ ሰው አይፈርድም አይነት ነው ... አብሶ እናት ድርጅታቸው ውስጥ ያለው ኦነጋውያን መንፈስ በቀላል ቀመር እሚወገድ አይደለም።
ወያኔ ሃርነት ትግራይ በወንጀሎቹ ሁሉ ተጠያቂ እንዳይሆን ቀዳዳዎችንም በምህረት በይቅርታ በፍቅር እንድፈነው ባይ ናቸው … ይህ ግራ ዘመም በደመመን መግፋት ቢሆንም ለ አጥቂዎቻቸው በድርብ ተደራጅተው አንዲሰናዱ ደግሞ አድርጓል። ከሃሳብ በላይ ቢሆኑን አንድ እንጨት አይነድም አንድ ሰው አይፈርድም አይነት ነው ... አብሶ እናት ድርጅታቸው ውስጥ ያለው ኦነጋውያን መንፈስ በቀላል ቀመር እሚወገድ አይደለም።
እኔ የወደደድኳቸውን ሁሉ ውደዷቸው ብሎ በመስበክ መልካም ቢሆንም በጅምላ ድጋፍ እና ተቃውሞ ደግሞ እንደ ሰው ለተፈጠረ አይመቼ ነው።
ለእኔ የግራ ዘመም ፖለቲካ አንኳሩ አማራ ላይ ያለው ጠናና አመለካከት ብቻ ሳይሆን ነፃነቱን መጫን ነው። ይህን ደግሞ ከሥልጣን መባቻ ጀምሮ የሚታይ አመክንዮ ነው። መጀመሪያ ነገር የአማራን ነፃ ሆኖ መፈጠር መቀበል ግድ ይላቸዋል ዶር አብይ የቅኖና እስረኛ አይደሉም ለመባል።
ለእኔ የግራ ዘመም ፖለቲካ አንኳሩ አማራ ላይ ያለው ጠናና አመለካከት ብቻ ሳይሆን ነፃነቱን መጫን ነው። ይህን ደግሞ ከሥልጣን መባቻ ጀምሮ የሚታይ አመክንዮ ነው። መጀመሪያ ነገር የአማራን ነፃ ሆኖ መፈጠር መቀበል ግድ ይላቸዋል ዶር አብይ የቅኖና እስረኛ አይደሉም ለመባል።
ከግራ ዘመም ፖለቲካ አወጣቸው ሊበል የሚችለው ሃሳብ የገለጸን በአደባባይ ባይረሸን ነበር። የአዲስ አባባን ጉዳይም ቢደፍሩት ነበር። የወያኔ ሃርነት ትግራይን ማንፌሰቶ ፖሊሲ ጸረ አማራ መሆኑን እራሱ አያምኑበትም። አማራ ኢትዮጵያዊነት ያቀንቅን፤ ጥያቄው በኢትዮጵያ ማህለቅ ይፈታል ነገር ግን ኦሮሞ አፍሪካ የመምራት ሃይሉን ያስከብራል፤ ኦሮሞዎች ብቁ አመራሮች ወደፊት ይመጣሉ፤ አማራ መሬት ግን አቅም ያለው የሌላ ብሄረስብ ከሆነ ችግር የለም፤ ከሆነ የቅኖና እስረኛ ያልሆኑበት ፍልስፍና ለእኔ አይታዬኝም።
እርግጥ ነው የራሳቸው መንገድ አላቸው፤ መንገዳቸው ደግሞ በራሳቸው ወገኖችም ራሱ ከውጥኑም አልተደገፈላቸውም፤ እኛም ብርቱ ዳጋፊዎች ደግሞ እንደ አገር ወዳድ ሞጋችነታችን ሂደቱን ከእውነት ጋር ፊት ለፊት አስቀመጥን በልሃ ልበልሃ ማለታችን አይቀሬ ነው።
እሳቸውም ሰው ናቸው መላዕክ አይደሉም። ለዛውም ገና ወዳጅ ጠላታቸውን በውል ያላዩ ግን ሩቅ አላሚ ናቸው። ለመሆኑ ዶር አብይ አህመድ ይቀናቀነኛል የሚሉት የሚጠረጥሩት መንፈስ እንኳን አላቸውን? ሁሉም ፍቅር ነው ላሳቸው። ከኣናታቸው ላይ ያለውን ጸጉር ቁጥር ማወቅ እና የኢትጵያን የሴራ ፖለቲካ ሃዲድ ማወቅ እጅግ ከባዱ ጉዳይ ነው።
አሁን እኛ የምንጽፈው ለሳቸው ጥላሸት መቀባት ሆኖ ሊታያቸው ይችላል። ዲያቢሎስ ከሰማዬ ሰማዬት ወርዶ ነው ሻሸመኔም ላይ ሰው ተገድሎ ተዝቅዝቆ የተሰቀለው፤ ቡራዩ፤ አስኮ፤ አሻዋ ሜዳም የተፈጸመው እንዲሁ ዲያቢሎስ ነው የሠራውን? የራሳቸው ልጆች ናቸው። የራሳቸው እናት ድርጅት ተባባረው ነው ያስፈጸሙት። ፍልስፍናው ግን ቄሮ የለውጥ ሐዋርያ፤ የለውጥ ዘውድ እንጂ እንዲህ ዓይነት ነገር አይነካካውም ነው የሚባለው። ዕውነት እንጂ ፕሮፖጋንዳ ጤዛ መሆኑን አሳምሬ አውቃዋለሁኝ። የኢትዮጵያ ሚዲያ ቢደብቀው የ ዓለም ሚዲያ እያወጣው ነው።፡
ስለእውነት የኦሮምያ መንግሥታዊ አካላትም ቅደስት ቅዱሳን ናቸው በሳቸው አመራር ሥርም ናቸውን? እሳቸው የሚሰጧቸውን ትእዛዝ ይቀበላሉ በትክክል እነ ዶር ለማ መገርሳ እና አመራራቸው አካቢያቸውን እዬመሩ ነውን ወይንስ በቸለልታ አብይን በማሳጣት ጉዳይ ተጠምደዋል?
ለመሆኑ ኦሮምያ ከአብይ ጋር ተደምራለችን¡ ስለምን በሁሉ ቦታ አብረው የሚገኙት ዶር ለማ መገርሳ ከጎናቸው ሰኔ 16 ቀን ጠፉ? ሞትን የፈቀዱ ካቢኔ አባሎቻቸው ብቻ ነበር የተገኙት።
ለመሆኑ ኦሮምያ ከአብይ ጋር ተደምራለችን¡ ስለምን በሁሉ ቦታ አብረው የሚገኙት ዶር ለማ መገርሳ ከጎናቸው ሰኔ 16 ቀን ጠፉ? ሞትን የፈቀዱ ካቢኔ አባሎቻቸው ብቻ ነበር የተገኙት።
መቀሌ ብቻ ሳይሆን ያመጸው የራሳቸው አካል ስለመሆኑ እንናገራለን … ለዚህ ነው የአብይ ካቤኔ ሌላ ቦታ እንደማይችል ስለሚያውቀው እንዳሻቸው በግራባው ብአዴን/ የነገ አዴፓ የሚወራኙት። በዛም አቶ ንጉሡ ጥላሁን የሳቸው የአብይ መንፈስ እንዲያርፍባቸው የሚፈቅዱ አይደሉም። አቶ ንጉሱ ጥላሁን ጃዋራውያን ናቸው። የጃዋር ፈን ናቸው። ጣምራ ድርሻ አላቸው።
ግንቦት 7 አገር ባይገባ ግን ሚዛኑን የሚጠብቅ ሁኔታ ይኖር ነበር። ይፈሩም ነበር። እራሱ ኦህዴድ/ ኦዴፓ እኮ ነው የአብይን ካቢኔ እዬሞገተው ያለው። እመኑኝ አልላችሁም ግን ብአዴን ሥያሜውን ነገ አዴፓ ይለዋል አዲሱን ሥያሜው፤ ትናንት ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ዛሬ ደግሞ ለጃውራውያን … ያረግርግ። አቅም ያላቸውን ሲያሻው በመርዝ ያሰወግድ፤ ሲያሻው ዝሃ እና ግራ ሆኖ ያሳፍን …
አቶ ጃዋር መሃመድ ሚሊዬነም አዳራሽ ላይ በአዲስ ዓመት ዋዜማ አልተገኘም። ለነገሩ ድባቡም ስላልተመቸኝ ብዙም አልተከታተልኩትም። ከዛ ቢሄድ ፖለቲካል ትርፍ የለውም። ለማያተርፍበት ነገር አለመድከም ብልህነት ነው። አሁን እኔ አዲስ ተመሠረተ ስለሚባል ፓርቲ ጉዳዬ አይደለም - እኔ። አድሮ ጥጃ መሆኑን ስለማውቅ መድከም አያስፈልግም። የሆነ ሆኖ ጅማ ላይ ግን ተገኝቷል። የተቀመጠው አባ ገዳዎች ጋር አሻባሪነትን ለማስደመር ነበር። ባገኛት ደቂቃ ሁሉ ናዚዝም ፍልስፍናውን ያስጠናል። ወዮልሽ ቤተሳይዳ!
ብዙዎቹ እንዲያውም ላያውቁት ይችላሉ። የእሱ አቅም እኮ አንቦ አካባቢ እንጂ ከዛ ያለፈም አልነበረም። ለውጡን እኔ አስነሳሁት ቢል ባሌ ላይ ቢሆን ነበር፤ ግንጫ ሽዋ ውስጥ ነው ያለው ለውጡ። ከዛ እኮ ሄዶ „የእናንተ እርዳታ ያስፈልገኛል“ ብሏል። ይህም ከጉዳይ አልጣፈውም የአብይ ካቢኔ። ከጃዋር በስተጀርባ ያለው ከ ኦነግ በላይ የትናንቱ ኦህዴድ የዛሬው ኦዴፓ ነው።
አሁን ያን ለማዋህድ ይመስላል የዶር አብይ ካቢኔ አቶ ታከለ ኡማን ፊት ለፊት በማውጣት ላይ የሚገኙት ነፍሰ - አንቦን። ግን እሳቸውን ከብክቦ ለሥልጣን ያወጣው መንፈስ ዕውን ከሳቸው ጋር ነው ወይ አብዩ ጥያቄ ይህ ነው። እኔ አይመስለኝም።
ወደፊት የመጣው የሚባለው ወጣት አመራር በአብይ መንፈስ ሳይሆን በታላቋ ኦሮምያ ፍልስፍና ውስጥ የተጠመቀ ነው። ሃቁ ይህ ነው። ጫን ያለ መከራ ፊት ለፊት አለ። የአብይ የመንፈስ ክህሎት ግን ኢትዮጵያ በ100 ዓመትም ደግማ አታገኘውም። ዲታ ናቸው ለሁለገብ ክህሎት፤ ግን ምን ይሆናል ሴራው ከረፋ።
ሌላው የመስቀል ባዕልን በሰላም እንደሚከብር በወኔ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ገልጸዋል። ያድርግልን ነው። ከሆነ ጥሩ ነው። ምን አልባት ኦህዴድ ውስጥ ያሉ ጃዋርውያን ይህቺን ቀን ለማሰተባባያነት ሊታገሱም ከቻሉ አንደ ነገር ነው እንጂ ዘመነ የኦሮሞ የበላይነት በእጥፍ ድርብ መከራ ቀጣይነቱ አይቀሬ ነው … ወዮልሽ አንቺ ቤተሳይዳ!
ጠ/ ሚር አብይ አህመድ መወገን ያለባቸው ለእውነት እና ለህግ መሆን ይገባዋል። በስተቀር „የመንታ እናት ተነጋላ ሞተች ነው“ የሚሆኑት። የበፊቱ ትእግስት እና የአሁኑ በፍጹም ሁኔታ ይለያል። የ ኢትዮ ሱማሌ ትእግስትና የ ኦዴፓ ትእግስት አንድ አይደሉም። ይህኛው እንኳንስ እሳቸውን ኢትዮጵያን እንደ አገር የሚያሳጣ ነው።
ከመጋቢት 24 ቀን ጀምሮ ሴራዎች ነበሩ፤ የአሁን አሸባሪነት ነው። የቀደመው የሥልጣን ግልበጣ ነው። የሥልጣን ግልበጣ ሊሂቃን ላይ ነው የሚቀረው። አሸባሪነት ግን ጽንስ ላይ ያለውን ህጻን ብቻ ሳይሆን መልካምድራዊ ጸጋዎችን፤ ትውፊት፤ ትሩፋትን ሁሉ ነው የሚጠፋው፤ የሚያነደው። አፍሪካ ቀንድም ይታመሳል፤ ሶሪያ እኮ የለችም። ደመነፍሷን ነው ያለችው። ቀጣዩ መካራ ይሕው ነው።
ከመጋቢት 24 ቀን ጀምሮ ሴራዎች ነበሩ፤ የአሁን አሸባሪነት ነው። የቀደመው የሥልጣን ግልበጣ ነው። የሥልጣን ግልበጣ ሊሂቃን ላይ ነው የሚቀረው። አሸባሪነት ግን ጽንስ ላይ ያለውን ህጻን ብቻ ሳይሆን መልካምድራዊ ጸጋዎችን፤ ትውፊት፤ ትሩፋትን ሁሉ ነው የሚጠፋው፤ የሚያነደው። አፍሪካ ቀንድም ይታመሳል፤ ሶሪያ እኮ የለችም። ደመነፍሷን ነው ያለችው። ቀጣዩ መካራ ይሕው ነው።
ዶር አብይ አህመድ ወይ ከህዝብ መከራ ጋር ወይ ደግሞ ከጃውራውያን ህዝቃዬላውያን፤ ግራኛውያን በቀለውያን ጋር መቆም ነው ምርጫቸው። ከአዲስ አባባ ጋር ስለመቆማቸው እዬታዩ ያሉ ምልክቶች ግርዶሽ አለባቸው … አንድ ሰው ሁለት እግር አለኝ ብሎ በአንድ ጊዜ ሁለት ዛፍ ላይ መውጣት አይችልም። ምርጫው አንድ ነው። አንዱን መምረጥ ነው። ቢያንስ አወዳደቃቸውን ማሳመር ይኖርባቸዋል። በስተቀር የልጅ እያሱ እጣ አይቀሬ ነው።
ከመፍንቀለ መንፈስ ኩዴታ የዘለለ ካቢኔው አቅም አለው ነው የሚሉት፤ ነገር ግን ከዛ የዘለለ የእርምጃ አወሳሰድ ደረጃ ላይ ካቢኔዎች አያሳይም፤ ንጹሃን መግደል ለጃዋርውያን ድርብ አቅም ቢሰጥ እንጂ የዶር አብይን ሌጋሲ ሊያሰቀጥል አይችልም።
ሁለት ነገር አለው። አንደኛው የጃዋርውያን መንፈስ የበላይነት፤ የማድረግ አቅም ያሳያል፤ ሁለተኛው ደግሞ ህዝብ በአደባባይ ስትገድል ሉላዊው ዓለም ዝም አይልም፤ እኛ እንኳን ዝም ብንል። እዛው ቤተ መንግሥት ውስጥም የሲአይኤ ሰዎችም እንዳሉም ማወቅ ይጠቅማል። አብይ የመምራት አቅም የለውም አንዲባል ይሻሉ የራሳቸው እናት ድርጅታቸው ውስጥ ያሉ ጃዋርውያን።
ግን እስኪ ይነገሩን አዲስ አባባ የማን ናት? አዲስዬ የኦሮምያ ወይንስ የኢትዮጵያውያን? ወይንስ ዝቅ ሲል የአዲስ አበቤ ከፍ ሲል የአፍሪካ? ከትልቁ ሃሳብ መጀመረዎትን አውቃለሁኝ። አፍሪካውያን ጠላቶቻቸው የሠሩላቸው መስመር ነው ብለውናል። አሁን ግን የማንክደው ሉዕላዊ አገር ናቸው። እንኳንስ ሌላው ኤርትራም። የሆነ ሆኖ አሁን እሳቱ እዬነደደ ያለው ማህል አገር ነው። ወስጡ ከተሸረሸረ እኮ ውሃ ልኩን ቤት ማቆም አይቻልም አይደለም አፍሪካ ኢትዮጵያም እንደ አገር ወዮ ነው።
ያልደፈሩትን ዕውነት ካልደፈሩ ቀጣዩ የጭካኔ ካቢኔ ጠረን እንዳይኖረው ሩህሩህ መንፈሰዎትን ስጋት አለኝ። ግን ዶር ለማ መገርሳ መንፈሳቸው የት ላይ ነው? አድርሻው ጠፍቶብኛል። ስለምሳሳላቸው ከደሃ ድምጽ ጋር ቢሆኑ ምርጫዬ ነው። ወስጣቸው ግን እጀግ ርቆኛል። ንቃታቸው ሁሉ አላዬሁትም።
ኢትዮጵያን መዳፈር ከተፈጥሮ አደጋም ማምለጥ አለመቻሉን ማወቅ ብልህነት ነው። አሁን ሁሉም ነገር አቅም ሊመሰል ይችል ይሆናል። ነገር ግን አማኑኤል ከተቆጣ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው። አንድ የሰማይ ቁጣ ይበቃዋል። ትምክህት ጥሩ አይደለም ለማንም ግለሰብ ይሁን አገር ይሆን ቀዬ ይሁን። ኢትዮጵያ ደግሞ አምላክ አላት የማይሞት የማያንቀላፋ። ጭንቁ በዚህ ውስጥ ተጎጂዎች እናቶች መሆናቸው ብቻ ነው።
አንድ ነገር፤ //// በተፈናቃዮች ዙሪያም ዶር ለማ መገርሳ ብቅ አላሉም፤ ኗሪዎቻቸው አይደሉንም ተይህ ላይ ሞጋሳ፤ ጉድፊቻ ገዳ አይሠራም ማለት ይሆን? በሌላ በኩል በሙያሌ እልቂት ውስጣቸው ተነክቶ ጥቁር ለበስው ነበር በኢህዴግ ስብሰባ የተገኙት አሁን ደግሞ ይህን አላዬሁም? የህሊና ምስከር ለስላሳው ለማ፤ የምዕቱ ቅኔ፤ የዴሞክራሲ የተራራው ስብከት የት ሄዱብን? ምን ገጠማቸውስ?
ክፉዎችን ልዑል እግዚአብሄር ያጥፋልን። አሜን!
ውዶቼ ኑሩልኝ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ