ለሦስተኛ ጊዜ የሰማይ ምልክት።
እዩት እስኪ ውዶቼ።
„በረድኤታችን
በእግዚአብሄር ደስ ይበላችሁ፤ ለያዕቆብ አምላክ እልል በሉ“
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፹ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ© ሥላሴ
23.09.2018
ከገዳማዊቷ ሲውዘርላንድ።
በ2015 መግቢያ ወር ላይ ሰማይ ላይ ብዙ ሠረገላዎች
የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለብሰው አያለሁኝ። ለአንዲት መነኩሲት እህቴ ደውዬ ነገርኳት። ለቤተሰቦቼም ሲደውሉልኝ ውጪ አገር ለሚኖሩት
እንዲሁ ነገርኳቸው።
ከዛ የካቲት 24 ቀን እዚህ ሲዊዘርላንድ የኢትዮጵያ አዬር መንገድ በጀግና ሃይለመደህን አበራ አማካኝነት ካለምንም
እንከን ጄኔባ አረፈ። ያው አዬር መንገዳችን ነጹሁን ሰንደቅ ተሸላሚ ስለሆነ ከቤተሰቦቼ ጋር ይህን ነው ያሳዬሽ ተባብለን አለፍነው።
ሌላ እውነት ደግሞ ልንገራችሁ። እዚህ ሲዊዘርላንድ
የ193 አገሮች ገጽ በሚመለከት አንድ ጥናት ነበር። እኔ ለካስቲንግ ተጋብዤ ተሳታፊ ነበርኩኝ። ካስቲንግ ከመሄዴ በፊት ለብሼው
የምሄደውን መምረጥ ፈልግኩኝ። ጉትቻው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ተገዝቷል። ልብስ ግን ከምገዛ በቤት ውስጥ ባለው ልጠቀም ብዬ የቤቱ ሁሉ
ልብስ ወጣ። መዘነጥ ዋናው ሆቢዬ ነው ከምል መደበኛ ተግባሬ ነው ከልጅነት እስከ እውቀት።
እርግጥ ነው ፎቶው ከአንገት በላይ ነበር - ገጽ
ብቻ ነበር የሚፈለገው። ነገር ግን ከወገብ በላይ ያለው የፊትን ገጽ የማድመቅ ድርሻ የሚኖረው ልብስ አስፈልጎኝ ነበር። የቤቱ ሁሉ
ልብስ ተዘርግፎ ተሞከረ፤ ሁሉም ሊያደምቀኝ አልቻለም። መጨረሻ ላይ ቲ ሸርት ነበርኝ የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ ያን አውጥቼ ስለብሰው
ምኑን እነግራችሁዋለሁኝ ቦግ አደረገኝ። በቃ ደስ አለኝ።
የሚገረመው ክረምት ላያ ስለነበር ስሄድ ደረብረብ
ያለ የሚመጥን አለባባስ ነበረኝ። ስገባ ካስቲንግ ቲሙ ተመልክቶኛል። እንደ ሁሉ የዕለቱ ተረኛ ቀጦረኛ ነበር ያሰተናገዱኝ። ያው ለካስቲንግ ቀደሞ መሄድ
ግድ ነው። ነገር ግን እንደዛ ዘንጬ ከምንም አልቆጠሩኝም። መልበሻ ክፍል ሄጄ ቲ - ሸርቱን ለብሼ ስወጣ ቲሙ ራሱ እንደ ጉድ ነበር
የተመለከተኝ። መደበኛ ፎቶ አንሹ ሳይሆን የፕሮጀክቱ ማናጀር ነበር ያነሳኝ።
ወደ 45 ደቂቃም በግል ከሌሎቹ ለይቶ ካፊተርያ ውስጥ
አወያዬኝ፤ ቃለ ምልልስ አልወድም ግን ያን ቀን እሺ ብዬ ሰጠሁኝ፤ አሁን ፎታችን በመጸሐፍ መልክ ታትሟል። 100.00 የሲዊዝ ፍራንክ
ነው የሚሸጠው። ለ6 ወርም ዙሪክ ባቡር ጣቢያ እና አካባቢው ፎቶዎቹ ነበሩ የ193 አገሮች ዜጎች ገጾች።
ይህ ሰንድቅ በሚስጢሩ ላይ፤ በማድረግ አቅሙ ላይ፤
በሳቢነቱ ላይ አልሠራንበትም። ልብን ወከክ ነው የሚያደርገው። ከጌጥ እንኳን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሳደርግ እና ሌላ ሳደረግ ገጠመኞቼ
የተለያዩ ናቸው።
አሁን በዚህች ቅጽበት ፊታውራሪ ዩቱብ አንድ ነገር
አመጣልኝ። እጅግ ድንቅ ክስተት በእንጅባራ
ሰማይ ላይ የኢትዮጵየ አባንዲራ ታዬ ይላል ዘገባው። እዩት እና ፍረዱት እስኪ። እንጅባራ ራሱ ታሪከኛ ቦታ ለምለም ቦታ
ነው።
እኔ ለጎጃም ያለኝ ፍቅር ለመስቀሌ ካለኝ ፍቅር ጋር
እኩል ነው። ቅንነታቸው እና በቆረጡት ልክ ስለመሆናቸው ዘመን ቅኔነታቸው እዬገለጠው ስለመሆኑ ሁልጊዜ እህቴን ሳገኛት የመጀመሪያ
አጀንዳችን ነገር ጎጃም ነው። ይህ ታምር ቢታይበት ለእኔ ይገባዋል ባይ ነኝ። እኔ በልዑል እግዚአብሄር ጽኑ አማኝ ስለሆነኩኝ የእዮርን
ታምራት አምኘዋለሁኝ። ወቅቱም በተገባው ልክ ነው።
ሰሞኑን 5 ወጣቶች አደባባይ ላይ የተሰዉበት መሰረታዊ
ጉዳይ ይህው ነው። የባህርዳር የ50 ዜጎች በ አማራ ተጋድሎ ወቅትም የነሐሴ 1 ሰምዕትነትም ይህው ነው። በሌላ በኩል ይህን ያህል ሰው የሚፈናቀልበትም ሚስጢር
ይህው ነው። እስራቱም እንዲሁ። በዚህ ሰንደቅ ላይ የሾለከ መንፈስ ይህ ነው አይባልም። የ60ዎቹ ታጋዮች ብዙም ቀረቤታ የላቸውም ከዚህ ሰንደቅ ጋራ።
ሁልጊዜ የሚፈልጉት ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ ነው። ለዚህ ነው እኔ የሰንደቁን ሚስጢር የመሸከም አቅም የላቸውም፤ አታስገደዷቸው የምለው።
የሆነ ሆኖ እኔ አሁንም ቀጣይ ታምራትን እጠብቃለሁኝ። ምክንያቱም
የሁሉም ሴራ ያለው በዚህ ሰንድቅ ጥላቻ ስለሆነ። „አገር በሠራዊት ብዛት አትጠበቅም“ ያለው ንጉሥ ዳዊትም ይህን ለማጠዬቅ ነው።
አገር የምትጠበቀው በእዮራዊ ፈቃድ ነው። ልዑል እግዚአብሄር ቁጣውን የሚገልጽበት
መንገዱ ብዙ ነው። ይህ ግን ከቀስት እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ምልክት ነው። መንፈስን ሰብበሰብ አድርጎ መጸለዬ ዋንኛው መንገዳችን
ሊሆን ይገባል።
በትምህክት የተወጠሩት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር
„ጌታዋን የተማመነች በቅሎ“ እንዲሉ አንድ መልዕከት አሰተላልፈውልናል። „ጠ/ ሚር የመለወጥ መብት እንዳላቸው¡“ እንሱ የጠ/ ሚር
ምርጫ ላይ ሲወራከቡ ትግራይ ላይ አንድ ያልተለመደ ምልክት ተከስቶ ነበር። በወርሃ መጋቢት በአንድ በተባረከ ሰንበት ዋዜማ ላይ
„ምልክት“ በሚል ከታሪክ አጣቅሼ ጽፌ ነበር።
ያ ምልክት መቀሌ አካባቢ የመሬት መራድ ነበር። ከዛ
ቀጥሎ ዴያስፖራ ላይ ሌላ ጸረ ዶር አብይ አህመድ ወጀብ ተነሳ እንዲሁ በጉራጌ ዞን አስደንጋጭ ሦስት ቁጣዎች በተከታታይ ተላኩ።
በዛ ሰሞን የመሬት መንሸራተት ጎጃም ላይ ገጥሞ እንደ ነበር፤ ቀደም ብሎም ደቡብ ላይ ተከስቶ እንደ ነበር አዳምጠናል። ይህ ሁሉ
ምልክት የልብ ንጽህናችን ግልብነት አመሳካሪነት ነው። ለውጥ እንሻለን ደግሞም ለውጥ እንፈራለን። የተጠቀለልነበት ክፋት እና ሸር
ደግሞ አለ። የዛሬው ታምር ለብአዴን/ ለአዴፓ
ይህ የለውጥ ጸጋ ትዕቢታችን ጣሪየ ነካ እንጂ
የሰማይ ስጦታ ነበር። ቀስ አድርገን በሱባኤ ልነቀበለው የሚገባ። ነገር ግን የሚታዬው እና የሚሆነው ነገር ደግሞ እጅግ የሚገርም
ነው። ብቻ እንመራበት ዘንድ እዮራዊ ተቋም ተልኳል።
ልብ ያላቸው ይህን እዮራዊ መልዕክት አስበው ከመታበያቸው
ቢታቀቡ መልካም ነው። ሌላ የማይችሉት ዕዳ ለዛ እንወክለዋለን ለሚሉት ድሃ እንዳይመጣበት። በደም ላይ የተገኘ የምሥራች ፈጣሪን በሚዳፈር መልኩ
እዬተጠቀጠቀ ነው እኔ የማዬው „የፉክክር ቤት ሳይዘጋ አያድርም“ ነው።
ድክመቶቹ፤ ግድፈቶቹ፤ መፈነቃሎች፤ ግድዮዎች፤ ዕንባዎች
ሁሉ ታቅደው ለማሰናከል የተሰሩ የሴራ መዳፍ ውጤቶች ናቸው። ነገር ግን የሰከነ ልቦና ያላቸው ዜጎች በአነሰ ግምት በ50 ዓመት
ልናገኘው የማንችለውን ዕድል ማሽሎክ እንደሌለባቸው ልብ ሊሉት ይገባል።
በተለይ አማራ እንደ አባት አደሩ የለውጡ ዘበኛ የመሆን ግዴታ አለበት። ምልክቱ የተላከለትም የአባቶቹን የተደሞ ሌጋሲ
እንዲያሰከብር ነው።
ይህ መልዕክት በማተቡ እንዲጸና እና እንዲቆርጥ
የተላከለት መልዕክት ነው። በምንም ሁኔታ ከሴራ፤ ከተንኮል፤ ከሸር ጋር ባለመተባበር የሰማዩን ፊደል ማንበብ በዛም መመረቅ ይኖርበታል
- የአማራ ተጋድሎ መንፈስ።
ወደ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር ተረገጥ ስመጣ
ቅብዐ የፈጣሪ እንጂ የሰው አለመሆኑን
አምላክ የላቸውም እንጂ ለአማንያን ያ ነው ለእኛ ማተብ ሃይማኖታችን። በዛ ጉባኤ ላይ ከሳቸው ጀምሮ ማንኛቸውም በእለቱ ስለመገኘታቸው፤
ጉባኤው በታቀደው ሁኔታ ስለመካሄዱ፤ ቢጀመርም ስለመጠናቀቁ እርግጠኛ የሚያደርግ አምላካዊ ሥልጣን ያለው ፍጡር የለም። በሰውኛው
ገበታ ግን ሴራ እንደ ተደራጀ አሳምረን እናውቃልን እኛ። የጎንዮሽን ሹክሽታም እንዲሁ …
አዳማ ላይ ከመቀሌ ባልተናነስ ምን ያህል ጤነኛ እና
ጤነኛ ያልሆነ ሁኔታ እንደ አለ ሌላው ሊያስተውለው አልተቻለው ሊሆን ይችላል። እኔ ከስሜን አሜሪካ መልስ ሳይሆን ከሰኔ 16 የዝግጅት
መሰናዶ ጀምሮ እንኩሮው ይሸተኝ ነበር። ወንበሩም ባዶ ሆኖ በህልሜ አይቸዋለሁኝ። ልቡ በቅናት ያልነደደ ለማግኘት ጋዳ ነው። እንዳንስቅ
የተረገምን ፍጡራን ነን።
በሰው ሰራሽ መከራ ከዓለም ህዝብ ፈቅዶ እና አቅዶ
በማፈናቅል የመጀመሪያ ደረጃ አንደኛ ወጥተናል፤ ይህ የሚያጓጉዘን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የመምራት አቅም አነሰው እንዲያሰኝ ታቅዶ
የተሸረበ ስለመሆኑ አይደለም እኛ ምዕራባውያኑም አሳምረው ያውቃሉ። ዘረፋ እና ሴራ መለያ ስለመሆኑ 27 ዓመት ተኑሮበታል። ወይ
አቅም የለም አቅም ያለው ሲመጣ ደግሞ ትርኪ ምኪ … የሚገርመው መከራው ትግራይ ላይ ድርሽ አይለም። ዕንባው ያለው በተቀረው ህዝብ ላይ ነው።
በዛ ጥንግ ድርብ ተግባር በተገኘበት 100 ቀናት
ወስጥ የ10 ዓመት መልካም ተግባርት ተከውኖበታል። ይህም አለ ለካ፤ በዚህም ፍቅርን ማፈስ ይቻል ነበር ለካ፤ ያላለ የወንበር ሱሰኛ
የለም። ለዛ ነው ያልተኖረበት መመስል ተዘውትሮ እምናስተውለው። ሁሉንም ገጽ፤ ሁኔታዎች፤ ሂደቶች ብዙ ነገር መልዕክት ይልካሉ።
ሥራዬ ብለን ሁለመናውን ለምንክታተል ወገኖች የመረጃ ቋታችን ሙሉ ነው፤ በማዬት ብቻ።
ሌላው ቀርቶ በህዝብ መሃል እዬሄዱ ዶር ደብረጽዮን
ገ/ ሚኬኤል ሳይቀር ሰላም ሲሉ በሸንድዬ ባዕል ተመልከትኩኝ፤ ከውስጥ ቢሆን ምንኛ መልካም በሆነ ነበር --- ከዛ መልስ ነበር
ራያ የአማራ ወጣቶች ላይ ማዕት የፈሰሰው።
ሰው ባለው ሳይሆን እሱ በፈቀደው መልካም ነገር ብቻ
ይሁንልን፤ አሜን።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ