#መንግሥታዊ #አናርኪዝም።
"ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ።"
የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ መተንፈሻ ቧን ከኦሮሞ ሊቃናት ውጪ አይታሰብም። ፈፅሞ። ከሰሞኑም አንድ የኦሮሞ ሊቅ የጽህፈት ኃላፊ አድርገው ሹመዋል። ማንን ፈርተው። ሃግ የሚል የለም።እራስ እግሩ እሱበእሱ። የ
መኖሩም መትነኑም ያልተነገረለት ከ98% በላይ የሆነው የኦህዴድ ኦነግ ፓርላማ ይህን መሰል አናርኪዝም ጉዞ ፀጥ ረጭ ብሎ በዝምታ ሙሉ ድምፁን ይሰጣል። መብቱ ተጥሶ የፈለገ ነገር ተከውኖ አጽድቅ ሲባል በሁካታ እና በጥድፊያ #እያውካካ ያፀድቃል።
"ነገርን ነገር ያነሳዋል" እንዲሉ ጋዜጠኞቻቸውን የሸኙት የኢትዮጵያ ህጋዊ ፕሬዚዳንት ወሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ ግን አሉ? ወይንስ ዶር ሙላቱ ናኙበት። ለመሆኑ ተመለሱ? ለነገሩ ምን አገባን እኛን። ለበይ ተመልካችነት እንኳን ያልተፈቀደልን ዘመናይነታቸውን እንኳን ማዬትም መብት አይደለም ተብሎ ሠርክ በድሮን የሚጨፈጨፍ የአማራ ህዝብ ልጆች #አይደለምን?
ይፋዊ ሥልጣን ከሰጠ ማህበረ ኦነግ ኢትዮጵያን ሃይጃክ ስለአደረገ ኦነግ ሥርዓትም ተፈጥሮውም ሥላልሆን በቀላጤ ቢገልጠው ይሻለው ነበር። እንዲህ የውሽማ ሞት ሆኖ ከሚትበሰበሱ።
የሚገርመኝ ለመብቱ የሚታገል አንድም የኦነግ ሊቅ አለመኖሩ ነው። እንደ ተገዛ በግ መጎተት ብቻ። ለኢትዮጵያም #ጭነት። ፈርዶባት። መጥኔ አንቺ አገር ኢትዮጵያ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ግን እንዴት ናችሁልኝ?
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
10/11/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ