ዝበት ወይንስ ስክነት?
እንኳን ደህና መጡልኝ።
ዝበት?
ስክነት?
„በዓመታት መካከል ትታወቅ፤
በማዓት ጊዜ ምህረትን አስብ“
ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።
· ማነው ጥፈተኛው? ማነውስ ይቅርታ ጠያቄውስ?
ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚነሱ ግጭቶች ላይ የምሁራን አስተያየት
Published on Jan 10, 2019
ጋዜጠኛ አቶ አዳም ታደስ /አወያይ/
· ማካሄጃ።
"ፕ /" አባባው አያሌው በአማራ ቴሌቪዥን አሁን ከሆነ ይቀርባሉ ለቃለ ምልልስ፤ ያው እሳቸው የሚፈለጉት የአማራ ብሄርተኝንት ጎልቶ ሲወጣ ወይንም ዩንቨርስቲዎች ችግር ተከሰተ ሲባል ብቻ ነው። ከዚህ ያለፈ፤ ከዚህ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ተወክለው አይተን አናውቅም።
ሌላው ቀርቶ ከታሪክም ከጥበብም አንጻር ብርቱ ሰው በሚያስፍልጋቸው አገራዊ ጉዳዮችም እንዲሁ ያን የመሰለ በፍጹም ሁኔታ የሚመሰጠው ብቃታቸው እዬባከነ ነው የሚታዬው የተገባውን ቦታ አላገኝም እንደማለት። ውጭ ያሉ ሊቃናት አገር እንዲገቡ ሲፈለግ አገር ውስጥ ላሉት ሊቃነት ያላቸውን አንጡራ ሃብት ጥቅም ላይ ለማዋል ያለው ዕድምታ ፈተናው አይሎ አያለሁኝ።
መሰረታዊ ምክንያቱ ብቃት አቅም እውቅት ሳይሆን መለኪያው የፖለቲካ ድርጅት አባልነት ስለሆነ፤ የኮታ ጉዳይ ስለሆነ፤ ይህ ብቻ ነው እንዳልል ደግሞ ከዚህ የወጡ ሹመቶች እና ዕውቅናዎች ሲሰጡ ደግሞ አያለሁኝ፤ በተጨማሪም በምደባም እንዲሁ የሥራ ድልድል ፈንገጥ ያለ ሁኔታም አልፎ አልፎ አያለሁኝ። ለነገሩ ሰከን ያለ ተግባርም ለመከወን አዬሩ ራሱ የታወከ ነው። ማገዝ ቀርቶ መረዳት አልተቻልም አዲሱን መስመር። ስለዚህ ብዙም አያስፈርድም።
· የጉዳዬ ብልሃት።
የዛሬው ጉዳዬ "ረ/ፕ" አባባው አያሌው ሰሞኑን በፋና ቴሌቪዥን ከዶር ብርሃነመስቀል አበበ ጋር ቀርበው ቃለ ምልልስ አድርገዋል። እኔ ብዙም በፋና ቃለ ምልልስ የአያያዝ ጥበብ እንደ ተቋም ሳስበው አልመሰጠም። እንደ ተቀቋም የፋና አወያዮችን ከሌሎች ጋር ሳነጻጻረው ጸጋው የለም። ለፋና አልተሰጠውም ለአዋይይነት እንደማለት። ለማወያዬት ዋልታ፤ ናሁ የአማራ ቴሌቪዥን የልብ አድርስ ናቸው፤ ጠረኑንም ለማስጠጋት አይቸግሬ ናቸው።
እርግጥ ነው የፋና ቴሌቪዠን የቀረጻ ጥራቱ ቅንበር ስለምወደው ብሄራዊ ጉዳዮችን ቢይዘው ምርጫዬ ቢሆንም፤ ቃለ ምልልስ አወያይነት ግን ደረቅ ነው፤ ማዕዛ ያነሰዋል፤ ጠረኑም አቅራቢ አይደለም አድማጭን …
ይህ እንደ ተጠበቀ ሆኖ በጹሑፍም በጋዜጠኛው በተደጋጋሚም „አቶ አበባው አያሌው“ እዬተባለ ነበር በዚህ ውይይት የሚቀርበው። ሌሎች ሊንክ አድርገውት ቢሆን እንደ ሰው ፍላጎት ስለሆነ እርእስም ዕውቅናም የሚሰጠው ብዙም አይደንቀኝም፤ ባለፈው ዓመትም ይህን መሰል ነገር ስለገጠመኝ "አቶ" አባበው ተብሎ ተጽፎ ማለት ነው። እንደ ተቀሟ በፋና ቴሌቪዥን ዩቱብ ላይ ሲሆን ግን ከቀደመው የዕውቀት ክብር ጋር ሊመጣጠን ስላልቻለ ስህተቱ የት ላይ ነው ብዬ እንድጠይቅ ተገድጃለሁኝ …
አሁን እኔ ግራ የገባኝ ጉዳይ ረ/ፕሮ አባባው አያሌውን የአማራ የብዙሃን መገናኛ ሲያቀርብ "ረ/ፕሮፌሰር" እያለ ነው፤ በውይይትም ሰብሳቢ ሲሆኑ "ረ/ፕ" እዬተባሉ ነው፤ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸውም ቆይታ ይኸው ማዕረጋቸው ተሟልቶ ነው። ፋና ላይ ደግሞ ይህ ተድጦ ወይንም ተስተካክሎ ነው። የት ላይ ነው ስክነቱ ያለው?
የትኛው ነው ትክክል? በውነቱ ፋና ከሆነ ጥፋተኛ ይቅርታ መጠዬቅ ይኖርበታል። በተደጋጋሚ አውያዩ ዶር ብርሃነመስቀል እያለ "ረ/ፕ አባባው አያሌውን" ደግሞ „አቶ“ እያለ ነበር ሲጠራ የነበረው። /እኔ እራሱ አንተ የምለው ጋዜጠኛው የጥበብ ቤተኛ ስለሆነ ነው/
ወደ ቀደመው ምልስት ሳደረግ ይህ ጉዳይ በሚዲያ ህግ እና አሰራር መሰረት በፍጹም ሁኔታ መተላለፍ ስለሆነ በተጨማሪም ህዝቡም ትክክለኛውን የማዕረግ ሥም ማወቅ ስለላለበት ማስተካካያ ሊደረገበት ይገባል ባይ ነኝ። ረ/ፕ ካልሆኑ የአማራ ቴሌቪዥን ይጠዬቅበታል፤ ረ/ፕ ከሆኑ ደግሞ ፋና ይጠይቅበታል፤
ምክንያቱም ታሪክም ትውፊትም በትክለኛው አምክንዮ ላይ መነሳት ስላለበት። የቃል ስህተት ነው እንዳልል በጹሑፍ የተለጠፈውም „አቶ“ ተብሎ ነው። መቼም አንድ ሰው ቃለ ምልልስ የሚያደርግለትን ሰው የህይወት ታሪክ ሳይጠና ዘው ሊል አይችልም። የጋዜጠኝነት ሥነ - ምግባር ኤቲክሱ አይፈቅድምና።
የመጀመሪያው በር አክብሮት እና ትህትና ነው። ሁለቱም በእንኳን ደህና መጡ የፍቅር አቀባባል መስከን ይገባቸዋል። የትምህርት/ የሽልማት/ የሃይማኖት/ የጥበብ ወዘተ የፊት ቅጥሎች አክብሮ መነሳት ግድ ይላል። እርግጥ ነው በማቅረብ የጥበብ ሰው ለሆነ ብዙም ጭንቅ የለበትም … አንተ/ አንቺ ቢባል ከዚያ ባሻገር ከሆነ ግን …
ጋዜጠኝነት ከመሪነት በላይ ተጠያቂነት አለበት። እንዲያውም በዚህ በሰለጠነው ዓለም የህግ ሙሩቃንም የሥራው ባልደረባ ናቸው። በመማር ማስተማሩም የሚዲያ የህግ ባለሙያዎች ራሱን ያቸለ ኮርስ ይሰጣሉ። እንደዚህ ዓይነት ጎድሉ ግደፈቶች እንዴት ሊያዙ እንደሚገባቸው ይህ ክፍል ነው የሚከታተለው።
ይህ እኔ ያዬሁት ግድፈት በአሉታዊም በአዎንታዊ ቢኬድ ማዕረጉ በትክለኛው ሁኔታ ካልተጠቀሰ ያስቀጣል። ወይንም ያልተገባ ማዕረግ ከሰተሰጠም እንዲሁ፤ ይቅርታም ያስጠይቃል። በዘፈቀደ የሚሄድ ማህበረሰብ እንዳይኖርም ልጓሙ እንዚህ መሰል ህግ መተላለፍን የሚገሩ፤ የሚያርቁ፤ የሚያስተካክሉ፤ መልክ የሚአስይዙ ፖሊሲዎች ሲኖሩ ነው። እንግዳ ከዚህ አገር ንጉሥ ነው።
ስለሆነም አክብሮ መነሳት ግድ ይላል። የሆነ ሆኖ ጥፈተኛው ማን ነው? ፋና ወይስ የአማራ ቴሌቪዥን? ያጣፈው አካል ሊወቀስ ሊታረም ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባዋል ነው ጉዳዬ … በጓሮ በር ሳይሆን ባደባባይ። ተበዳዩም ሊካስ ይገባዋል፤ ህዝብም ትክክለኛውን የክብር ሥም ሊያውቅ ይገባል።
ከሁሉ በላይ አዲስ የትወልድ ቀረፃ እዬተጀመረ ስለሆነ ለእነዚህ መሰል ጉዳዮች አትኩሮት መስጠት በክፍል ልጆችን ከማስተማር በላይ የበለጠ ጉልበት አለው። እያንዳዱ ክንውን ልጆችን እያሰቡ ቢሆን … መልካም ነው። አክሰሱ ያላቸው ልጆች ሁሉንም ያደምጣሉና።
· ክወና።
ማነው ጥፋተኛ? ማነውስ ይቅርታ መጠዬቅ ያለበት?
· የቀደሙት።
አቶ አበባው አያሌው (ረዳት ፕሮፌሰር)
ረዳት ፕ/ አበባው አያሌው
የአማራ ምሁራን ውይይት በባሕር ዳር ክፍል ሁለት
የታሪክ ሙሁር ተመራማሪ ናቸው
ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚነሱ ግጭቶች ላይ የምሁራን አስተያየት
· ውዶቼ ይህ ከሥር የለጠፍኩት ደግሞ የበለጠ "ረ/ፕሮፌሰር አበባው አያሌውን" እንድታውቋቸው ነው። የቆዬ ቃለ ምልልስ ነው፤ ታሪክም ስለሆነ ሰሞናቱ ልደት
- አስተርዮ ጥምቀትም ስለሆነ … ይጠቅማል።
ጥምቀት እና ጎንደር - አቶ አበባው አያሌው | Sheger cafe on Sheger FM 102.21 / አሁን ከዚህ አቶ አባባው አያለው ነው የሚለው/
Abebaw Ayalew with Meaza Birru About Were ellu on ShegerCafe አበባው አያሌው ከመዓዛ ብሩ ጋር የወረ ኢሉ ነገር
ላሊበላ እና ገና - አበባው አያሌው | Sheger Cafe on Sheger FM 102.1
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ