ትውልድ እና መንግሥት በምን ይጣመሩ? የህዝብ ውዴታ ወይንም ፈቃድ ሸቀጥ አይደለም። አየሩ #ያቃሰተ #ማቃት ላይ ነው።
ትውልድ እና መንግሥት በምን ይጣመሩ? የህዝብ ውዴታ ወይንም ፈቃድ ሸቀጥ አይደለም። አየሩ #ያቃሰተ #ማቃት ላይ ነው።
የምዕራፍ 13 ማጠናቀቂያ ፁሁፍ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ትውልድ እና መንግሥት በምን ይጣመሩ?? " #ይጣመሩ " ከባድ ኃይለ ቃል ነው። ግን ይደፈር። መድፈር ተስፋን የሚገናኝ ወይንም #የሚያቀራርብ ከሆነ። ትውልድ እና መንግሥት መጣመር ቀርቶ ለመቀራረብ ጋዳ ሆኗል በኢትዮጵያ ፖለቲካ። ምክንያት ……… #የዕውነት፤ #የመርህ፤ #የኃላፊነት፤ #የተጠያቂነት ውህደት አራባ እና ቆቦ ስለሆነ።
#ትዝብቴን በስሱ ……
1) አንድ ሥርዓት በስሜት የሚመራ ከሆነ?
2) አንድ ሥርዓት በቅጽበታዊነት የሚተዳደር ከሆነ?
3) አንድ ሥርዓት ጭካኔን ምራኝ ካለ?
4) አንድ ሥርዓት ለህዝብ ዋስትና ለመስጠት አቅም ካነሰው፦
5) አንድ ሥርዓት በገባው ቃል ልክ መሆን ከተሳነው፦
6) አንድ ሥርዓት በፋንታዚ የሚጋልብ ከሆነ፦
7) አንድ ሥርዓት ምን ግዴ ከሆነ፦
8) አንድ ሥርዓት የሚመራውን ህዝብ አክብር መነሳት ከአቃተው፦
9) አንድ ሥርዓት ከማድመጥ ዲስኩር ካዘወተረ፥
10) አንድ ሥርዓት ለዕውቀት ደንታ ቢስ ከሆነ፦
11) ሰው ወጥቶ በሰላም መግባት አቅቶት ሞት የዕለት ጉርስ ሲሆን፦
12) አንድ ሥርዓት የትውልድን ውስጥ ማወቅ ከቸገረው፦
13) አንድ ሥርዓት ለህዝብ ዕንባ ደንታ ቢስ ከሆነ በትውልዱ እና በእሱ መካከል ያለው የውስጥነት ሃዲድ #እክል ይገጥመዋል። እክሉ #የፖለቲካ #ኢንፍሌንሽን ይገጥመዋል። ይህን ጊዜ አናርኪዝም ያቆጠቁጣል። አሁን በኢትዮጵያ እኔ እማስተውለው ይህን ነው።
በኢትዮጵያ ፖለቲካ የተሻለ ዕድል ያገኘው ክስተት #ጭካኔ እና #አረማዊነት ነው። ሰውኛ እና ተፈጥሯዊነት ተሰደዋል ወይንም ተሰውረዋል። ገዢው ጭካኔ ሆኗል። ለጭካኔ እና ለአረማዊነት መሃንዲሱ ደግሞ #አናርኪዝም ነው። ኢትዮጵያ እንደ እኔ ዕይታ በተፃፈ ህግ እንደሚተዳደሩት አገሮች በተፃፈ ህገ - መንግሥት ስትተዳደር፤ እንዲሁም ባልተፃፈ ህግ እንደሚተዳደሩት አገሮችም ባልተፃፈ ህግ ትተዳደራለች። አሁን በኢትዮጵያ እኔ በምታዘበው ልክ ሁለቱም ሥራ ላይ ለማዋል ጋዳ እየሆነ ነው። #ያቃሰተ !#ማቃት ነው እኔ እማስተውለው።
ይህ ሁኔታ አዲስ የተለዬ ፍፁም ጨዋ በሆነ፦ እራሱን ዝቅ አድርጎ በትሁት መንፈስ የሚተዳደር ሥርዓት ባለው ህግን በሚያከብር ግብረ ኃይል ወይንም ቲም ካልተመራ ከቁጥጥር ውጪ ከሆነ የኢትዮጵያ ህልውናም አደጋ ላይ ይወድቃል። በተለይ ህፃናት፤ አዛውንታት፤ ህሙማን፤ ሴቶች፤ ታዳጊ ወጣቶች እጅግ ይጎዳሉ። አሁን ከምናደምጠው በላይ። ጉዳቱ ዘመን ሊጠግነው የማይችል ይሆናል።
ዛሬ በጎንደር የሚታዬው መራራ ዘመን ትናንት በሻሸመኔ እና በአጣዬ አዬነው። ነገ ደግሞ ተዛምቶ ኢትዮጵያ መዲና ላይ እንደማይከወን ምንም ዋስተና የለም። #ትርፋማ ፕሮጀክት አይደለም። ፈጽሞ። እንደ ፕሮጀክት እንደሚሠራበት ነው የማምነው።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ጂኦ ፖለቲካን ተከትሎ #ትዕግሥት እና #ጥሞና በሚሹ ጉዳዮች ላይ የቸኮለው ውሳኔ ጦስ ሌላ ተከድኖ የሚንተከተክ ብሄራዊ ችግር አለ ቢዳፈንም ከፈነዳ የሁሉንም ትብብር ይጠይቃል የተከፋ ህዝብ መኖሩ መቃብር የሆነ ህዝብ ምላሹን መገመት ይቻላል።
የህዝብ ፈቃድ ወይንም #ውዴታ እኮ #ሸቀጥ አይደለም። የሰው ልጅ ሸቀጥ አይደለም እና በገብያ ህግ ልትመራው አትችልም። ይህንን ጉዳይ ህዝባዊ መከታ ለማግኜት ቢሞከር አናርኪዝም፤ እሱን ተከትሎ ጭካኔው ልብ ስለሚያሸፍት ቫልዩ ያለው የህዝብ ተሳትፎ ለማግኜት ጋዳ ይሆናል። ምክንያቱም የትውልዱን ውስጥ ማድመጥ ሲሳን በህዝብ እና በመንግሥት መካከል ያለው አውንታዊ ድልድይ እክል ስለሚገጥመው። የአመፆች አነሳሽ ገፊ ምክንያት እኮ መከፋት ነው።
ተችሎ፦ ተችሎ የገነፈለ መከፋት የሚጠናቀቀው #በፍቺ ይሆናል። ይህን መልክ ለማስያዝ ከተዝለገለገ የፖለቲካ አሰራር በፍጥነት ወጥቶ አቅምን የመጠነ ጥሞና ይጠይቅ ይመስለኛል። በጥግንግን፦ በማባበል፤ በሌለ በፌክ ብሄራዊ ስሜት ፕሮፖጋንዳ የህዝብን ይሁንታ ማግኘት ጋዳ ነው። ህዝብ ሲፈቅድ እኮ ቅንጣት ድርጊት ሳያይ፦ ለማያውቀው መንፈስ መጋቢት ሰኔ 16/2010 በንግግር ብቻ መታመኑን ከዐፅናፍ አፅናፍ አስረከበ። ገደብ የለሽ ፍቅር አጠገበ።
ሌላው በዚህ ዓመት ጫን ባለው ክረምትም የተፈጥሮ አደጋወችን ለመቋቋም የኢኮኖሚም፦ የሃሳብ አፅናኝነትም መመንመን ብሄራዊ ጉዳይ ባለቤት #አልቦሽ እንዲሆን አድርጎታል። ሰላሙን ያጣ ህዝዝም፥ ራቡን ችሎ መከፋቱን በአደባባይ የማይፈቅድለት ህዝብ ሲከር ይበጠሳል ሲሞላም ይፈሳል ይሆናል -- የብልጽግና መንግሥት መጨረሻ።
ህዝብ ተስፋውን ተቀምቶ ሲበሳጭ መንግሥት #ኮበሌ ሊሆን አይገባም። በተጎዳ ህዝብ ላይ በተደጋጋሚ ባሩድ ማጋጋል በበቀል #መፍላት የለበትም። አልነበረበትም። በቀልን ሰንቆ ከመንቀሳቀስ እራሱን ዝቅ አድርጎ የህዝብን ብሶት ለማዳመጥ ወደ ትሁታዊ መንገድ ማቅናት ይኖርበት ነበር። በየአደባባዩ የሚረሸኑ ንፁኃን ደም ወደ እዮር ይጮኃል። የእዮርን ውሳኔ ደግሞ #ኒኩለር አይገታውም። የበቀል አምላክ ይበቀላል።
የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አገዛዝ በዕድሉ ያልተጠቀመ አልቦሽ ነው። ዕድሉን ፈቅዶ ያፈሰሰ ጉደኛ መንግሥት ነው። በሰላም የተረከባትን አገር ወደ ውስብስብ አገራዊ ቀውስ ያሸጋገረ፤ በአንድም በሌላም ቀጠናውን ጨምሮ ቀውስን ያሸጋገር፦ ሊማር የማይፈቅድ፤ ሊታረም የማይወድ፤ ቢነግሩት የማይሰማ፦ ለመዳን - የማይወድ፤ ደጋግ አማራጮችን ሁሉ ያመከነ፦ ቀውስ በቃኝ የማይል፤ ስልት እና ተመክሮ የሳሳበት፤ ፈጽሞ ለማድመጥ የማይፈልግ፤ በራሱ // እ --- ራሱን ተቃርኖ እራሱን እየሸረሸረ የሚገኝ ሥርዓት ነው። መነሻውም መድረሻውም #ክፋ #ሃሳብን እንደ ስንቁ ያደረገ በመሆኑ ቀጣይ ተስፋው #የበለቀ ይመስለኛል።
በየትኛውም ቦታ፤ በዬትኛውም ሁኔታ ተገዳችሁ እራሳችሁን ስትከላከሉም ይሁን፤ በህገ ወጦች ጭካኔ፤ እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋ እራሳችሁን ላጣችሁ የአገሬ ልጆች ሁሉ ነፍሳችሁን በአፀደ ገነት ያኑርልኝ። አሜን። ለሙንዱቡ ወገኔም መጽናናትን እመኛለሁ። እግዚአብሄር አምላክ በቃችሁ ይበለን አሜን። እኔ ዙሪያ ገባውን ሳዳምጠው መፍትሄው በልብ ንጽህና ወደ እግዚአብሄር ወደ አላህ መቅረብ ይመስለኛል። መፍትሄ ያለው ከእዮር ብቻ ነው። ቢያንስ በእጃችን ባለው ማድመጥ እንጠቀም።
……… ምዕራፍ 13 በአመዛኙ በውስጥ ላይ ያተኮረ ጊዜ ነበረን። ይህ የምዕራፍ 13 የመጨረሻ መጣጥፌ ነው። አንድ ፖስት ይቀረኛል። ከዛ ቀሪው ጊዜ የማድመጥ ይሆናል። ቸር አስበን ቸር እንሁን። ቅን አስበን ቀና እንሁን። ኑሩልኝ ክብሮቼ። እናንተን አያሳጣኝ። ቢስም አይይብኝ። አሜን። ደህና ሰንብቱልኝ። አሜን። ዩቱብ ቻናሌ እና ቲክቶኬ ላይ እኖራለሁ ብቅ እያላችሁ ማድመጥ መብታችሁ ነው።
ከቻላችሁ ብቻ ሳብስክራይብ አድርጉ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
https://www.youtube.com/channel/UCJEQXw86u_NG4A1FVC1j2qg
Sergute©Selassie ሥርጉተ©ሥላሴ Kebebushe L/work Media
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
05/09/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ፍቅር ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።
ትዕግሥትም ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ