እኔ እንጂ ...
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 22.06.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
„እኔ ዛሬ ብቀበል አንተም ነገ እንደምትቀብል
እወቅ።“
(መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፳፪)
ሰማይን
ሳይ …
አሱም እኔን ሲያይ
እንዳልደርስበት - እርቆ
የተፈጠረ - ተመርቆ
ሁሌ ላይ ሆኖ ልቆ።
ታች ሆኖ - መች ደቆ
እንዳይመጣልኝ - መች ሥራ አጠቶ?!
ተግበረ ቢሷ - እኔ እንጂ …..
በሰጠኝ ጸጋ - ዕንባ አውራጂ …
በግፍ ሠራዊት ተነጂ …
ጠላቴን የማልከካ በመጂ …
መከራዬን የማልቀቅል በመገፈጂ።
- ተጣፈ።
ሀምሌ
2 ቀን 2002 ዓ.ም ሻፍሃውዝን ሲዊዘርላንድ 2002
ተስፋ
መጽሐፌ ላይ ገጽ 15። ሆኼሃት ፈቃድ ነው እርሱ። ስለዚህ እንደ ፈቃዳቸው ነፃነታቸውን ሳልጫን ከፈለጉበት ቦታ ጭብጣቸው ይቀመጣል። ትንሽ ፈንገጥም ወጣም ያለ ነው። እያነበብኩኝ ስለምጽፈው ምቱ ዜማ ነው ቦታውን የሚሠጠው ...
ትሁቶቹ ታዳሚዎቼ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ