የጋዜጠኛ መሳይ መኮነን የዱብ ዕዳው ዋጋ አሰጣጥ ፉርሽነት!

የጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ደርሶ ዱብ ያለ ለዶር አብይ አህመድ ዋጋ የመጨመር ዕሴቱ ፉርሽ ነው።
መናጆ መሻት ነው።
ከሥርጉተ ሥላሴ 04.07.2018 
(ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ)

„ጌታ ሆይ አድነን ጠፋን እያሉ አስነሡት። 
እርሱም እናንተ እምነት የጎደላችሁ ስለምን
 ትፈራላችሁ? አላቸው። ከዚህ በኋዋላ ተንሰቶ
 ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።“

(የማቴወስ ወንጌል ምዕራፍ፰ ቁጥር ፳፮ )


  • ·       መነሻዬ ይሄ ነው።

https://www.satenaw.com/amharic/archives/59937 ሰውዬው ተራ ጀብደኛ ነው
(መሳይ መኮነን )

እንዴት አለህ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን? ሰላም ነው? በቅድሚያ እንኳን ለዚህ አበቃህ እላለሁኝ። „እንዳያማም ጥራው እንዳይበላም ግፋው“ በነበረው የህሊና ምርትህ ውስጥ በጠ/ ሚር አብይ ጎን ስለመሰለፍ የሚያመለክት ይመስላል ጡህፍህ። ተቆርቋሪነቱ ለዶር አብይ ነብስ ያደላ ይመስላል። እስኪ ከዘለቀ የሚታይ ይሆናል።
  • የወግ ገበታ።


ውዶቼ። የጋዜጠኛ መሳይ ጹሁፍ ዱራኛ ነው። የጠገነ ስለሚመስለው „ጤና አዳም“ ሁልጊዜ በድምጽ ሽፋን ይሰጠዋል። በዛ ውስጥ ያሉ ጉዳዮች ግን እንዳለ የሚለቀቅ አይደለም፤ አልነበረምም፤ አፍሶ መልቀም፤ ለቅሞ ማፈስስ፤ አፍርሶ መጠገን፤ ጠግኖ ማፍርሰ የተመለደ ጨዋታ ነው በኢትዮጵያ ፖለቲካ። ለዛውም ምን የፖለቲካ አቅም እና ቁመና ሳይኖር፤ የተጀመሩ ጥረቶችን ደግፎ ከመቆም በሰማይ መና መማለል የፖለቲካ አስተሳስብ ድህነት ነው - ለእኔ።

እኔ ሲኖረኝ ብቻ ነው ባለኝ ነገር መመካት የምችለው እናም የተሻለ ቦታም ደረጃም በቀጣይ እምመኛው። አገር ቤትም ውጪም ያሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ይታወቃል አቅማቸው። ከዛ እስር እና አፈናው አቅማቸውን በተረጋጋ ሁኔታ ተከታታይ ማድረግ አላስቻላቸውም። ውጪ ደግሞ በትርፍ ሰዓት የሚሠራ ነው። የፖለቲካ ሥራ በትርፍ ሰዓት ሠርተህ ማሸንፍ አይደለም መወዳደር አያስችልም። ቋሚ ሰዎች ያስፈልጉታል በመደበኛ። እንደ ሚዲያዎች ማለት ነው።

ሚዲያዎች ደግሞ የፖለቲካ ድርጅት ነን ቢሉ ዶግማው ያስራል። የነበረው አማራጭ የለማ፤ የገዱ፤ የአብይ እና የአንባቸውን መንፈስ ሙሉ ለሙሉ ሳይጠራጠሩ አምኖ መንቀሳቀስ፤ በነገሮቻቸው ሁሉ የመንፈስ ድጋፍ መለገስ ሲገባ የጦር ሜዳ ውሎ ነበር። በሁሉም አቅጣጫ። ማዕከላዊ አቋም የነበራቸው የኮሚኒቲ ራዲዮኖች ሳይቀሩ ምን እንደነካቸው ሳይታወቅ ጦር አዋጅ ሆነው አብረው ተሰለፉ።  የተፈለገው የሽግግር መንግሥት ተብሎ የሆነ ትርምስምስ መፍጠር ነበር። ይህ ቁልጭ ያለው ድራማ ነበር። በሌለህ አቅም ተራራ የሚያከል የንግሥና ህልም ማለሙ ህልም ዕልም ነው የሆነው። ኦህዴድ እና ብአዴን ቢያስቡት ተጠዋሪ የሚአደርጋቸው የመዋለ ንዋይ፤ የሃሰባ ነገር የለም እነሱም መንግሥት ናቸው። በዛ ላይ በቅርቡ ለሁለቱም ተጋድሎዎች የ አማራ እና የኦሮሞ ያሉት መሬት ላይ እነሱው ናቸው። በግልጽም እንደረዷቸው ተናግረዋል። 
·       አልተሳክቶም በአልተግባብቶ።
 ወደ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ሃሳብ ስንመጣ ትልሙ አለመሳካቱን እሱ ራሱም ያውቀዋል። ህዝብም በነቂስ ያውቀዋል። „ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም እንዲሉ።“ ባለ በሌለ ሃይሉ ተጉ። ለነገሩ ከእንግዲህ አባት አገርም ስሌለ ብቻ ሳይሆን ሚሊዮን ሞትን ፍዳን፤ አካል ጉዳትን ፈቀደ፤ አብረንህ ልንሞት ተዘጋጀን የሚለው ድምጽም አልፋ ኦሜጋ እዬሆነ ነው። ህዝብ የሚሰጠው ድምጽ ዕምነት የሚጣልበት ነው። ውጊያ ቢገጥመው የአብይ መንፈስን ደግፎ ሚሊዮን ይሰለፋል። ምክንያቱም ሁልጊዜም እንደምለው አማራጫ ስለጠፋ ሳይሆን ከዘመን በላይ የሆነ ዕጹብ ድንቅ ብቃት ስላላው ለዛውም በትህትና። በርህርህና።
·       ህም
ብቻ ብዙም ማለት አልሻልም። ምክንያቱም ስለባጀሁበት። በማገኛቸው መረጃዎች ላይ ለማመሳከሪያነት እጅግ በርካታ ጹ ፎችን በብራና ሳተናው ጽፌያለሁኝ። እሱም በፍጹም ቅንነት እና ቸርነት አስተናግዶኛል። መንገዱ ሁሉ ይባረክለት፤ ልጆች ካሉትም ይባረኩለት። አሁን ማን እንደ እሱ ጌታ። አሸነፈ። አንድ እንደ ወልዴ ድህረ ገጽ ነበር። ሥርጉትሻም አሁን የቤተ መንግሥቱ ጋዜጠኞች በማያስገልሉኙ በማያሳግዱኝ የራሴ ብሎግ ሥራዬን ተያዤዋለሁኝ። እሱም ከወቀሳ እና ከነቀሳ ድኗል። እሱ በሌለበት ሰ ዓት ሙጥጥ አድርገው ጹሁፌን ቆሻሻ ውስጥ የሚዶሉቱም ይስፋቸው።

ዛሬም የማከብረው ጋዜጠኛ መሳዩ አንድ ነጥብ አንስቷል። እንደ ተለመደው ሁሉንም አይደለም የእሱን ጭብጥ ማንሳት የምሻው የተወሰነችውን ብቻ ነው። ዱራኛ ሃሳቡን ነው መፈተሽ የምሻው። „ስለጄኒራል ዶሩ“ ጉዳይም ብዙም ስሜት የሚሰጠኝ ጭብጥ አላገኝበትም። መተርጎሙ ግን መልካም ነው።

በተረፈ ለሌላው አጀንዳ ሊሆን ይችላል ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ይሄን ሃሳብ ሥራዬ ብሎ ያነሳው ብዬ ነው የማምነው እንደ ወትሮው፤ አንዲት ሳር ይመዝ እና ቤንዚን አርከፍክፉ ተጋፈጡት ይላል። „የዶሩ የጄኒራሉ“ አነሳስ ሆነ እርምጃን በሚመለከት ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልግም።  ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በበቂ ሁኔታ ስለሚያወቋቸው ምንም ማብራሪያ አያስፈልጋቸውም፤ አስተርጓሚ አያስፈልጋቸወም። ይተዋወቃሉ።

በዛ ላይ በጭንቁ ጊዜ የተወሰነው የሠራዊቱ አባላት ህውሃት ውስጥም „እንዳትነኩት አብይን“ በሚል አቋም ይዘው ነፍሳቸውን አቆይተውልናል። እኔም በተከታታይ ምስጋና ጽፌላቸዋለሁኝ። ጠቅልሎ አንድን ሃሳብን መጥላት፤ ጠቅልሎ አንድን ሃሳብ መውደድ ከራስ ህሊና ጋር ነው የሚያጣለው። በመጨረሻም እንዲህ ጥግ ያሳጣል። 

አሁን የኢሳት ፍዳ  የሆነው ይሄው ነው። ሌላው ቀርቶ ያሳነሳቸው መስሎት ኢሳት ለጠ/ ሚር ሲወዳደሩ ትልቅ ዕወቅና ያሰጣቸውን ዛሬ ለቱሪስት መስህብነት አንድ ግብዕት የሆነውን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ዘሎ ነበር በሌሎች ነበር ሃላፊነቶች ላይ ያተኮረው። ትዝብት ነው። ዛሬ የ ዓለም ሚዲያ አስኪበቃው ድረስ ሙሉ ክብርና ሞገስ እዬሰጣቸው ነው። ተመስገን! ግቢው እራሱ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተቋም ነው። በታሪኳ ኢትዮጵያ ለጥበብ ቤተኞች አን ያህል ግርማ አላብሳ አታውቅም። ያ ተዘሎ ነበር የተሠራው። ዝርዝር ማለቴ አይደለም ግን የሳይንስ እና ቴክኖጂ ሚ/ር ሆነው አገልግለዋል መባል ነበረበት። የታሪክ ግድፈት ነው።

የሆነ ሆኖ የፖለቲካ ሥልጣን ከእንግዲህ ላብን ጠብ አድርጎ ከገጠር እስከ ከተማ ባትሎ የሚገኝ እንጂ ሞቅ ካለው እዬሄዱ በመቀላለቀል ወይ ተቀላቅሎ በመዋጥ የሚሆን አይሆነም። አሟሙቆ የሚቆይ ብቻ ሳይሆን ቤተኛ የሚያደርግ የነፍስ ለቀማው እንደተጠበቀ ሆኖ ይሄ በጉልህ እዬታዬ ስለሆነ። አቅም መፍጠር ሲሳን አቅም ማደን የተለመደ ትልቁ ስትራቴጅ እና ታክቲክ ነው። እንደ ማንፌስቶ የሚመለክ።  

  • ·       አሁን ወደ ማክበረው ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ሃሳብ
„ሰውዬው እንደሚለው / አብይ ከሱ በታች ያለ የሬዲዮ ኦፕሬተር ነበሩ:: ከስራ ያሰናበተው እሱ መሆኑን በገደምዳሜ ይናገርና ምክንያቱን ሲገልጽእንደ አስተሳሰብ ባህሪይ መጠን የአብይ አስተሳሰብና ባህሪይ ለተቋማችን ሥራዎች የሚጎዳ ስለነበር ከኛ ጋር መቀጠል አልቻለም። ከሥራ ውጣ አልነው ወጣ። ከወጣ በኋላ ድርጅቱ ምንም ዓይነት ሥጋት የለውም ማለት ነው። ከድርጅቱ ጋር ፍቺ ፈፀመ ማለት ነው። ስለዚህ ችግሩ የግል ችግር ሳይሆን አብይ ከድርጅታችን ተልዕኮ ጋር የማይጣጣም ባህሪይ ስለነበረው ነው።

እንግዲህ / አብይ ለረጅም ጊዜ በትግል ውስጥ እንደነበሩ ሰውዬው ምስክርነቱን እየሰጠ ነው። የዶ/ አብይ ተራማጅ አስተሳሰብ፡ በህወሀት ጥብቆ ያልተቀፈደደ አመለካከት የነበረው ከቀድሞ ጀምሮ ለመሆኑ በአስረጂነት የሚቀርብ ነው። ሰውዬው ዋጋ ለማሳጣት የሄደበት መንገድ ለዶ/ አብይ ተጨማሪ ነጥብ እንዲያስቆጥሩ አድርጓቸዋል። ውስጣዊ ትግሉ ትላንት የተጀመረ፡ ሳይሆን የቆየና የከረመ እንደሆነ የሚያረጋግጥ መሆኑን ለመረዳት ይቻላል።“ ዋው¡


  • ·       እንብርቷ!
„ሰውዬው ዋጋ ለማሳጣት የሄደበት መንገድ ለዶ/ አብይ ተጨማሪ ነጥብ እንዲያስቆጥሩ አድርጓቸዋል።“  እንደ አንድ ዓለም ዓቀፍ ጋዜጠኛ፤ እንደ ብሄራዊ ተንታኝ፤ እንደ አንድ ብርቱ አወያይ፤ እንደ ተዋናይ የፖለቲካ አባልነት፤ እንደ ጸሐፊነትም የት ነበር ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን? ተጨማሪ ነጥቡን ማስቆጠር ዛሬ ነው የገባውን። አሁን ነው የታዬውን? በቅድሚያ ጋዜጠኛ ፍቅር ስንታዬሁ ከጻፉት ልነሳ። ከሳተናው የተለጠፈው ትንሽ ዘግዬት ብሎ ነው የካቲት 22 / 2018 ነበር እንደ አውረፓውያኑ አቆጣጠር እንጂ ቀድሞ ሌላ ድህረ ገጽ ተለጥፎ ነበር።

እኔ ያው በሳቸው ጉዳይ መደበኛ ሥራዬ ስለ ነበር አይደለም ጹሑፍ የጉጉልን // የዩቱብን የዕዬለቱን የታዳሚ ቁጥር የታደሚውን ሁሉ በዬንግግራቸው አጠናው ነበር። የሚጻፉ አስተያዬቶችንም በትጋት አነብ ነበር። አንድም የተለዬ ሃሳብ አንብቤ አላውቅም፤ እንደ እሳቸው ንግግርም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ወጥ ንጹህ ሰላሙ የተጠበቀለት ንግግር አልነበረም። እልፎ አልፎ አንግሊዘኛ አትቀላቅል የሚል ነበር። ይህም የእኔ ምርጫ ነው። አዎንታዊም ነው ትችቱ። ተቀባይነቱን ማበልጸግ ብቻ ሳይሆን ሁሉ እኩል ተረድቶ ከተሳፋው ጎን እንዲቆም በቅንነት ከማሰብ የመነጨ ነው። አሁን ወደ ጋዜጠኛ ፍቅር ስንታዬሁ የሃሳብ አንኳር እንግባ። ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን መንጠላጠያ አድርጎ ያሳውን ሃሳብ የሚሞግተውን የቀደመ ሃሳብ ሙሉውን ላቅርበው።

   v   እንዲህ ይለናል ጋዜጠኛ ፍቅር ስንታዬሁ …
  • ·       መስረጃ አንድ።

„የመረጃ ደህንነት ኤጀንሲ
የዶ/ አብይ የከፍተኛ ስልጣን ጉዞ የሚጀምረው ሀዳር 15 ቀን 1999 የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ለመመስረት የወጣ የሚኒስተሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 130/1999 ጋር ነው፡፡ የኤጀንሲው መመስረቻ ደንብ እንደሚያትተው የሀገሪቱን ቁልፍ የመገናኛ አውታሮችን ከአደጋ ለመከላከልና ለማሳደግ እንዲችል ሰፋ ያለ ስልጣን እንዲኖረውና ተቋሙ በኤጀንሲ ደረጃ ይጠራ እንጅ የኤጀንሲው ዳሬክተር ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለጠቅላይ ሚኒስተሩ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
ይህ ኤጀንሲ የሀገሪቱን ሁነኛ ተቋማት ማለትም የደህንነት፤ የፋይናንስ፤ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ተቋማት የሚጠቀሙባቸውን የስልክ፣ የኢንተርኔትና ሌሎች የመገናኛ አውታሮች ለመከላከል ሲባል ያለምንም ገደብ እንዲያስስና እየተነተነ እንዲያቀርብ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ በተፈረመ በዚሁ ደንብ ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡

አቶ አብይ ይህን ኤጀንሲ በበላይነት የመሩ ግለሰብ እንደመሆናቸው በመገናኛ ብዙሀንም ይሁን በሌላ መንገድ ስማቸው ጎልተው የሚታዩ ሰው ግን አልነበሩም፡፡ ስለዚህ በወቅቱ የነበራቸው ሚና በቅርብ ከሚያቋቸው ሰዎች ባገኘሁት መረጃ የተመሰረተ ነው፡፡
·       በደህንነት መስሪ ቤቱ ያሳዩት ለውጥ
"አብይ አህመድ የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተር በነበሩበት ወቅት የሚመሩትን የዚሁን የደህንነት መዋቅር (ኢንሳ) ከፖለቲካ ማለትም ከህወሀት ወገንተኝነት ለማላቀቅ እንደሞከሩ መረጃወች ያሳያሉ፡፡ ለዚህም በመጀመሪያ የሚጠቀሰው የደህንነት መስሪያ ቤቱ የምልመላ ሂደት የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂወችን በውጤታቸውና ለሀገር ባላቸው ቀና አመለካከት ብቻ እንዲሆን ለማድረግ መሞከራቸው ነው።

መስሪያ ቤቱ የተቋቋመበት ዘመን ምርጫ 97 ተከትሎ በመጣው የኢህአዴግ ሁሉን አቀፍ ተቃውሞ የማጥፋት ዘመቻ ላይ እንደመሆኑ ከቀበሌ እስከ ዩኒቨርሲቲ በየትኛውም የመንግስት ቢሮክራሲ ያለምንም ውድድር ሰራተኞች በየዩኒቨርሲቲው በተቋቋሙ የኢህአዲግ የህዋስ አደረጃጀቶች ብቻ የሚመለመሉበት ጊዜ እንደነበር በወቅቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበሩ ሁሉ የሚያስታውሱት ነው፡፡
አብይ የሚመሩት መስሪያ ቤት ግን በተለየ ሁኔታ ይሰራ ነበር፡፡ ለዚህም በጊዜው በዩኒቨርሲቲወችና የትምህርተ ዘርፎች የላቀ ቸሎታ ያላቸውን ተማሪወች እንዲመለመሉ ያደርጉ ነበር፡፡ አቅም አላቸው የተባለ ማንም ሁን ማን በስልክ በመደወል ስራ እንዲያመለክቱ ከመወትወት በተጨማሪ ሰራተኞቻቸው በመሰናዶ ትምህርተ ቤቶች ሳይቀር የላቀ ችሎታ ያላቸውን ሰወች በመሰሪያ ቤቱን እንዲቀላቀሉ እንዲያደርጉ ለሰራተኞቻቸው የቤት ስራ ይሰጡ ነበር፡፡
የደህንነት መስሪያ ቤቱ የሚጠብቀው የኢህአዴግን ስልጣን ወይም የፖለቲካ ቡድኖችን ፍላጎት ሳይሆን የኢትዮጵያን ሀገራዊ ጥቅም ብቻ አስበው አንዲሰሩ በግልፅ እንደሚናገሩ ሰራተኞቻቸው ይመሰክሩላቸዋል። በወቅቱ INSA ውስጥ ኢህአዴግን መቃወም ቀርቶ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል መሆን እንኳን ከምንም እንደማያግድ በቅርብ የሚያውቋቸው ይናገራሉ። በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ አንድነትም ሆነ በዴሞክራሲ እንዲሁም በብቃት ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እንዲኖር ያላቸው እምነት በእጅጉ ቀናና የማያወላዳ እንደነበር ይመሰክሩላቸዋል።
ይህ አመለካከታቸው የኋላ ኋላ በህወሀት የደህንነትና መከላከያ ሰወች ጥርስ እንዲነከስባቸው ማድረጉንና አሁን የኤጀንሲው ዳይሬክተር የሆኑት ሜጀር ጀኔራል ተክለ ብርሀን እንዲተኩ ተደርገው እንደተነሱና አዲሱ የህወሀት ሹመኛም ያደረጉት የመጀመሪያ ርምጃ አብይ በየዪኒቨርሲቲው የመለመላቸውን ሰራተኞች በተለመደው ፖለቲካ እየገመገሙ በጅምላ ማባረር ነበር። በጊዜው ስለመስሪያ ቤቱ አውርተው የማይጠግቡት ሰራተኞችም ብዙወቹ የአብይን መልቀቅ ተከትሎ ሀገር ለቀው በስደት እንደሚኖሩ መረዳት ችያለሁ፡፡
በኢንተርኔት ያገኘሁት የአንድ ፀሐፊ ምልከታም ይህንኑ ያጠናክራል፡፡ እንደተረዳሁት ከሆነ አቶ አብይ ኢንሳ የሚባለውን የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ከምንም ተነስቶ አቋቋመው፡፡ ተቋሙ በደንብ መሰረት እስኪይዝም ጠበቁት፡፡ በኋላም ከሱ በኩል ተቋሙ ጠንካራ የመረጃና የቴክኖሎጂ ስራ የሚሰራ መሆን አለበት በሚል፣ ከህወሓት ሰዎች በኩል ደግሞ የለም የስለላ ተቋም እናድርገው የሚለውን የውዝግብ ነጠብ ተከትሎ ጊዜ ጠብቀው አባረሩትና ህወሐቶች እራሳቸው ለስለላ ሲሉ ተቆጣጠሩት፡፡“

የኦህዴድ ሞተር ~ ዶክተር አቢይ አህመድ ማን ናቸዉ? (ፍቅር ስንታየሁ)

አዲሱ የኦህዴድ የአማራር ብቃት በዚህ የተቀመመ ስለመሆኑ ጋዜጠኛ ፍቅር ስንታዬሁ ነው የገለጸው። ሰብዕናውን ያመጣው ያበቀለው ሌላ ነው እያሉ ሲያብጠለጥሏቸው ለነበሩት ለBBN አወያይ እና ተወያዮችም ይህ መልስ ይሰጣል። ሌላም የዳበረ መረጃ አለ። ዘመኑና ጊዜው ሲፈቅድ ይወጣል።

·       ማስረጃ ሁለት ግጥማቸው። አለቅት እንዴት እንዳስቸገራቸው …
 ይህን ግጥም እርእሱ ቪዲዮው ሲለጠፍ አንባቢው አቶ ውባለም ተስፋዬ እንደጻፉት ተደርጎ ነው የሚገልጸው ነው። ግን አይደለም በዚህ ሰቆቃ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ የተጻፈው ነው አንባቢ አቶ ውብአለም ተስፋዬ በዛ ድንቅ አቀረርብ እና መሳጭ ትንተና ያቀረቡት። ድምጽ ይባርክ ብያለሁኝ። ከዶር አብይ አህመድ ጋርም አብረው የነበሩ ናቸው ብዬ አምናለሁኝ። መከራቸውን የተጋሩ።  አሁን ኢትዮጵያዊነትን ተለጠፈባት፤ ከእኛ አጀንዳውን ወሰደው፤ ከእነ ጠቢቡ ቴወድሮስ ተወሰደ ለሚሉት ጋዜጠኞች ሆኑ ተንታኞች ሁሉ ምላሽ ይሰጣል። ልባቸው ስለሚያውቅ ስም መጥራት አያስፈልግም። በጣምም ልግመኞች ናቸው።

„Ethiopia - የመወድስ ግጥም ለዶ/ አብይ አህመድ“

 

በዚህ ላይ የምታዩት ሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ ለቀደመቱት መስራቾች ያዘጋጁትን ሽልማት ሲሰጡ ራሳቸው ከቦታቸው እዬሄዱ ነው። ለ አገራቸው አገልግሎት ላበረከቱ ኢትዮጵያውያን ማክበር፤ ማመስገን ዛሬ ጠ/ ሚር ስለሆኑ ሳይሆን የቀደመው ባህላቸው ነው። እንዲያውም እሰከ አሁን ከተሠሩት የቪዲዮ ጥራቶች ይሄ ብቁው ነው። አንባቢውም መቼም የተሰጠው ነው። ድንቅ።

የግጥሙ ርዕስ „አንቺ አገር ኢትዮጵያ ነው“ የሚለው። ለመተርጎም ግንቦት 5 ነው የጀመርኩት በሌላ ጉዳዮች በመጠመዴ ብቻ ሳይሆን ማጥናት እማሻቸው ሥንኞች ስላሉበት ነው። በነገራችን ላይ እንደ ጀርመኖቹ አዲስ ቃል የመፍጠር እና ግሶችን በማግሰስ አዲስ የማራባት ጸጋም አላቸው። ወደ ቋንቋ ፈላስፋነት የሚወስዳቸውን መንገድ አይቻለሁኝ። ለነገሩ ፈላስፋ የመሆን አቅጣጫም አይባቸዋለሁኝ።

ለዚህ ነው እኔ በቂ ጊዜ ሰጥቼ እያንዳንዱን ስንኝ በተገባው አቅም ልክ ሙሉ ቁመናውን ለመሥራት የወሰንኩት። በሳምንት አንድ ቀን የተወሰነ ሰዓት እዬሠራሁበት ነው። አንድ የማስተማሪያ ሰነድ ነው። እንዲያውም እጅግ የምሳሳለት ገጣሚ / ጋዜጠኛ/ ፈጣሪ ፍጹሜ አሳፋው በማለዳ ኮከቦች ላይ አንድ ጠንከር ያለ የትውና ሥራ እንዲያስከውነበት በአጋጣሚው በትህትና ላሳስበው እሻለሁኝ።  ሰሞኑን ድምጹ ጠፍቶብኛል። ደህና ይሆን አባ ቅንዬ ፍጹሜ?

    v   ወደ አለቅቶች የመሳደዱ ግጥም ጥቂት ሥንኛት …  
„በቀጠርሽኝ ቦታ ሙሽራዬን አንችን ሰርግ ላገለግል ህልምሽን ልፈታ

           ለዚያ ነው ያለሁት የእኔን ነገር ጥዬ ለቀጠሮሽ ብዬ
           ካዋልሽኝ እዬዋልኩ ካኖርሽኝ እዬኖርኩ ስትጥይኝ ተጥዬ“

ሲጣሉ የኖሩ ናቸው። ሲገፉ የኖሩ ናቸው። ሲገለሉ የኖሩ ናቸው። ከአንድ ግሎባል ሚ/ር ወደ አንድ ክልላዊ  ቦታ መላክ እኮ ዲሞሽን ነው። ኦቦ ለማ መገርሳን የመሰለ ቅን ባይገጥማቸው ተውጠው ቀርተው ነበር። እንዲያውም አንድ ጹሑፍ ላይ ለውጭ ጉዳይ ሚ/ር ሁሉ አቅርበዋቸው እንዳልተሳካላቸው ሁሉ አንብቤያለሁኝ።

የሆነ ሆኖ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን የሚጽፍበት መሰረታዊ ምክንያት እሱም ያውቃዋል እኔም አውቀዋለሁኝ። ገፊው ሃይል ምን እንደሆን እሱም ያውቀዋል እኔም አውቀዋለሁኝ። ለዛ ከብረት ለጸና የሹመት ንግግር እንኳን የጻፈውን ያውቀዋል። በግማሽ ሰዓት ንግግር ውስጥ አቧራ ላይ የወደቀችው ኢትዮጵያ ከፍ ማለቷ አልነበረም ጭንቁ። ጭንቁ ያ ሞገድ እሱ ያጨውን ተስፋ እንደሚቀማው ስላወቀ ነበር … ያን የጻፈው። የህዝብን መንፈስ በትርጣሬ አውሎ መናጥ። ተሳካለት በወቅቱ ሊሆን ይቻላል። ዛሬ ግን እእ ነው። ተግባር የማያሸንፈው ውሽንፍር የለም።

ከዚያ በኋዋላም የተጻፉት በዛው መጠን ልክ ነው … ከራሱ ስሜት እና ፍላጎት ወጥቶ እንደ አንድ ጋዜጠኛ ዕውነትን ያነጠሩ ከምንም ነገሮች ጋር ንክኪ የሌላቸውን ሃሳቦች ቢያንሳ መልካም ነው። ይህ መንገድ 43 ዓመት ተኖረበት እሱ ከመፈጠሩ በፊት ማለት ነው። እርሾ አልባ ትውልድ ባከነ። እሱም ወደ አገሩ ያልተመለሰበት ምክንያት ይሄው ነው። ዕውነትን በጥርጣሬ ከዝኖ ከራስ ስሜት እና ፍላጎት ጋር በማጋባት የሚገኝ ትሩፋት የለም። ነገሮችን ከራስ በላይ፤ ከራስ ማራቅ ያስፈልጋል። ጋዜጠኛ የሚለውም ሆነ ጸሐፊ የሚለው ሥም እንዲጠለጠልልን እንዲዘልቅም  ከፈለግን። ለወደፊትም አይጠቅመውም።

ዛሬ ባለው ዕውቅና መቶ ሺዎች ይደግፉታል ነገ ግን እርሾ አልባ ሆኖ ይወድቃል። ምክንያቱም የፖለቲካ ድርጅቶችን አምልኮ መነሳት ጉም ነው። ለዛውም ሲፈርሱ ሲሰሩ ሲወድቁ  ሲነሱ ውለው ለሚያድሩት የፍርሰት ማህበርተኞች ጋር ቤተኝነት አብሶ ለጸሐፍት እና ለጋዜጠኝነት ሞት ነው።

ያ የተጠለልነበት ጎጆ ሲወድቅ አብሮ መፍረስ ነው። ቅንጀት ጎጆ ሠራ አብሮ ተፈረሰ። በቃ! ሰው ግን ህሊናው ከራሱ መንፈስ ጋር መከተም ይገባዋል። አንድ ጋዜጠኛ የጅብ ችኩል መሆን የለበትም። የማይደራደርባቸው ነገሮች ሊኖሩ ይቻላሉ። ከባህል ያፈነገጡ ጉዳዮች ከገጠሙ።

ከዚያ የተረፈው ግን ወደ ፖለቲካ መድረክ የሚመጡትን በጭልፋ ሳይሆን በሙሉ ሰብዕና ከመሠረቱ ማጥናት እና የግልን ዕይታ በአውንታዊነት መሥራት ይገባል። ያ ብቃትን ጥሰው ሲገኙ ደግሞ ስለምን ብሎ መጠዬቅ የተገባ ነው። አብሶ በነበረው የቀዝቃዘው ጦርነት ወቅት መሪ ተዋናዮችን በተገባው ልክ ማጥናት ያስፈልግ ነበር። ከሊቅ አስከ ደቂቅ በግልብ ተሄደ አሁን ሁሉም ወደቀ። ፖለቲካ ጎርፍ የሚከመረው ድርቆሽ አይደለም። ሳይንስ ነው። ፍልስፍና ነው። የምትማራው፤ የምትሰለጥንበት፤ ሰብዕናህንም የምትመራበት ታላቅ የነፍስ፤ የሙያ፤ ይህይወት ሙያ ነው። ማዕከሉ ሰው ነው። ሰው ደግሞ ዓለምን የሠራ ዕጹብ ድንቅ ፍጡር ነው።

ስለሰው አስተዳደር አመራር ተንታኝ፣ ተቺ፣ መሪ ለመሆን ቢያንስ መስከን ያስፈልጋል። አብሶ እንደ ኢትዮጵያ ባለ በትውልድ እጨዳ ላይ ለኖረ ፖለቲካ ይህን መሰል የጎርፍ ፖለቲካ ኪሳራ ብቻ ነው ትርፉ። አይደለም ዶር አብይ አህመድን የቅርብ ድጋፍ ይሠጣሉ የተባሉትን ነበር እዬተነጠሉ መንፈሳቸው ሲወረወር የተባጀው።
  • ·       መወደድም መተቸትንም መቀበል ግድ ነው።

እርግጥ ነው አወያይነቱን አውድለታለሁኝ። አንዳንድ ጊዜ ባሃሰብ ልዩነት ሲወጣ ሁሉ ተመልክቻለሁኝ። በማያወቃቸው ነገሮች ላይ ሄዶ ጥልቅ አይልም። ይሄ የማከብርለት ጉዳይ ነው የጋዜጠኛ መሳይ መኮነን። ድመጹም ማለፊያ ነው። ጹሁፉ ግን ከፖለቲካ ድርጅቱ ፍላጎት የራቀ አይደለም መድፊያው ያው ማንፌሰቶው ነው። ማዕላዊ ለመሆን የማያስችለው ፍዳም ይሄው ነው። ለኢትዮጵያም አይጠቅምም።

ለባከነው ትውልድም አይረዳም። ተተኪ ጋዜጠኞችን ለማብቀልም መንገዱ ሰባራ ነው። ከሁሉም በላይ ጋዜጠኛ ነገን ማሰብ አለበት። ነገ ደግሞ ሰውን ማዕከል አድርጎ መነሳት ሲቻል ብቻ ነው ታሰበልት የሚባለው። ሁሉም ሰው ዜጋ ነው። ሁሉም ሊሂቅ የአገር ሃብት ነው ብሎ መነሳት ሲቻል ብቻ ነው። የበለጠ ወደ አንዱ ዝንባሌ ሊኖር ይችላል፤ የፖለቲካ ድጋፍም መኖሩ ሰውኛ ነው። ግን በጨለማ ኳስ ሜዳ ገብተህ የፔናሊት ዕድልን ማሰብ የማይሆን ነው።

ከንግግሩ በፊት እና በኋዋላ እንኳን ያለውን ሂደት ሲፈተሽ ያው ከምኞት ያልተወጣ ወጣ ገብ ነው የሚታዬው። ያ ሁሉ መንፈስን የመበተን፤ የተደራጀ እና የተቀነባበረ ሁኔታ ተሠርቶ፤ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የሽገግር መንግሥት የአደራ መንግሥት ተብሎ፤ በዛ ላይ ባልተቋረጠ ሁኔታ ክፉዎች በዬዕለቱ በተደራጀ ሁኔታ ጦርነት ከፍተው በዬቦታው እሳት እያነደዱ፤

ብቻ ተመስገን የሚያሰኘው ጨዋው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን መልሱን ሰጠ። በቃ ያ ሁሉ ውዥንብር ከባህር የወጣ አሳ ሆነ። የውጪው ፖለቲከኝ፤ ሚዲያ ሲትበሰብ የኢትዮጵያ ህዝብ ሞቱን ፈቅዶ ያደረገውን አደረገ። እንግዲህ ከባህር የወጣ አሳ ከመሆን ትርፍ የለውም።
  • ·       የማይደፈረውን መድፈር ከእንደራሴነት መውረድ ነው።

የዶር አብይ አህመድ አቅም ደግሞ የሚደፈር አይደለም። ዘመን አይቶት አይውቅም። አይደለም ኢትዮጵያ ላይ አፍሪካ ላይም። ጥበብ አበት እንደ ቀደምቶች፤ ስልት አለበት እንደ ቀደምቶቹ። አክብሮት አለበት እንደ ቀደምቶቹ። እውነት አለበት እንደ ቀደምቶቹ ። ብልህነት አለበት እንደ ቀደምቶቹ። ሥልጡን ነው። 

https://www.youtube.com/watch?v=riMkG5bt6Ns&t=54s
Ethiopia - Dr Abiy ፈረንጆቹን አሸማቆ መለሳቸዉ!!

የአመራር ብቃቱ ውብ elegant ነው። ጨዋ decent  ነው። ሉላዊም Global ነው፤ ዘማናዊ Modern ነው። ለዲጃታል ዓለም የተስተካካለ የሚመጥን። ያደገ ነው advanced። ርህርህናው ደግሞ ከገዳይነት፤ ሰውን ከማሰቃዬት፤ ከሴራ እና ከተንኮል፤ ከድፍንነት ድንቡልቡልነት ፖለቲካ በፍጹም ሁኔታ የጸዳ ነው። ሃሳብ የማፍለቅ ችግር የለበትም። ሃሳቦቹ ደግሞ ዝልቅ እና ሩቅ ድግግሞሽ የማይታይባቸው ናቸው። ስንክሳር አይደለም። ከቀደሙት ጋር ለማተካከል ይከብዳል። ለዘመኑ የፖለቲካ ይዞታም ማቀራረብ አይቻልም። ዓላማ ያለው ጉዞ ነው … ዶር አብይ አህመድ በ አንድ ወቅት እንዳሉት እንዳሉትን ዘመነ እንደ ገና መወለድ ነው።  Renaissanc.

https://www.youtube.com/watch?v=vu-kkIUohRw&t=28s

Ethiopia - Dr Abiy ኢትዮጵያን ማሸጋገር ይቻላል!


የቀደመውን ስንመለከት ጭካኔን፤ በቀልን፤ ቁርሾን፤ ግድያን፤ ማፈናቀልን፤ ማዋረድን መድፈር ነበረ። አሁን በፍጹም ሁኔታ ሌላ ዓለም ላይ ነው ኢትዮጵያ ያለችው። ከቀደመው መልካም ነገርን፤ ከለንበት ደግሞ በፍጹም ሁኔታ ልዩ እና አዲስ መንገድ ነው የተጀመረው። ከሊቅ እስከ ደቂቅ ይህን ማድመጥ አልቻሉም። ጥቂቶች ከተወሰነ ጊዜ በ ኋዋላ ወደ መንፈሱ እዬተቀራረቡ ነው። አዝማችም ሆናዋል።
  • ·       ክውና።  

ቋሚ የሆነው ነገር ሃይማኖቱ ካለ ፈጣሪን/ አላህን ማመን፤ በሁለተኛ ደረጃ ዕውነትን መጠጋት። ፈጣሪ የመረቀን የምርቃት ዘመን ብሎ መቀበል ያስፈልጋል። አቅሙን ማድመጥም ማጥናትም ስልልተቻለ ነው ወዲህ እና ወዲያ ጅዋጅዊቱ የሚታዬው። ዕድሜውን ሙሉ ኢትዮጵያን አጀንዳው አድርጎ ለኖረ ለዚያም የሚያበቃውን ጥናት እና ምርምር በራሱ የህሊና ውስጥ የምርምር ማዕከል በማብቃት ለሠራ ሰብዕናን በተለመደው መንገድ ልገምግምህ ቢባል የሚሆን አይደለም። 

የኢትዮጵያ ድርጅት በውስጣቸው በመንፈሳቸው አብሮ የበቀለ ነው። ፓርቲያቸው ራይያቸው በውስጣቸው ያበቀሉት ኢትዮጵያን አፍሪካን ተወዳዳሪ አድርጎ የመውጣት፤ ይህዝቦቻቸውን ዕውቅና እና ተቀባይንት በጥራት ማብቀል ነው። 

„ልክን ማወቅ ከልክ ያድርሳል“
የጎንደሮች አባባል ነው።

የኔዎቹ ዝም ብሎ የሚለቀቀውን ቅልቅል ቁጭ አድርጋችሁ ትፈትሹት ዘንድ ይሄን ብያለሁኝ። 

ኑሩልኝ - አክባሪያችሁ።

ማለፊያ ጊዜ እንዲኖራችሁ እመኛለሁኝ!  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።