ተጠዬቂ እስኪ አንቺ መከረኛ!

መርዝ እዬተዘራ መርዝን ማምከን አይቻልም።

„ነገር ግን ወረተኛ ለጥቂት ቀን የሚሆን ወዳጅ አለና በመከራህም 
ጊዜ ካንተ ጋር መከራህን ከአንተ ጋር አይታገሥም እና 
ፈጽመህ አትመነው“ ምዕራፍ ፮ ቁጥር  ፲

ከሥርጉተ© ሥላሴ 15.08.2018 
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

ሰው መሆን ሰው ሆኖ መፈጠር ብቻ አይደለም። ስለ ሰው መፈጠርም ዕውቀት ሊኖር ግድ ይላል። ሰው መሆን ቢያንስ ከእንሰሳ መለዬት ማለት ነው በቀላል ትርጉሙ። ሰውነት ለኢትዮጵውያን ከሁሉም በላይ የላቀ ሃይማኖታዊም ዶግማም ነበር። እግዚአብሄር ሰውን ቤተ መቅደሱ አድርጎ ፈጠረ ከሚል ሃይማኖታዊ ዶግማም ጋር የሚያያዝ „ ሰውን እንደ መልካችን በአምሳላችን አንፍጠር“

አሁን ግን እኔ ሰው አይደለሁም እያልን ነው። ሰው መሆን ስለሰው መጨነቅ መሆን ቀርቶ ስለሰው እንዴት እንደሚገደል፤ እንዴት እንደሚወገድ፤ እንዴት እንደሚገለል፤ እንዴት እንደሚታረድ፤ እንዴት አካሉ እንደሚጎድል፤ እንዴት ሥነ - ልቦናው እንደሚሸነሸን፤ እንዴት የውስጥ ሰላሙ እንደሚታወክ መራቀቅ ሆኗል ጀግንነቱ።

ጀግንነት ሰብዕናን ሰው መሆንን ጥላህ ከወገብ በላይ ሰው ከወገብ በታች ጭካኔ፤ ወይንም ከወገብ በላይ እንሰሳ ከወገብ በታች ሰው ሆነህ በጥምር መንፈስ በደመ ነፍስ መነዳት ሆኗል። ሰው በራሱ ኢጎ ሠረገላ እዬገላበ ብቻ በቻቻታ እና በሁካት፤ በኳኳቴ እና በዲልቃ መንገድ ሆኗል የሰውነት ደረጃው።

በአደባባይ ሰው ሰው መሆን አቅቶት፤ ስለሰው ሰብዕና ማሰብ ተስኖት ጭካኔን ት/ ቤት ከፍታችሁ ልጆቻችሁን አስተምሩ፤ አረመኔነት የልጆቻችሁ መለያ ምልክት የሰብዕናውም መፈጠሪያ አስኳል ይሁን እዬተባለ ነው፤ ለሽብርተኝነት ካሪክለም ይዘጋጅ እዬተባለ ነው፤ ማፍርስ፤ ማቃጠል እንደ ክብር እንደ ሞራል ልእልና ይታይ እዬተባለ ነው። ወይ ነዶ!

ግን ኢትዮጵያ ምን ብትረገም ይሆን እንዲህ የሲኦል ምድር እንድትሆን እዬተዶለተባት ያለው።

ተስፋ በጠፋበት ሰዓት ተስፋ ብቅ ብሎ በቅጽበት ደግሞ በድቅድቅ ጨለማ እንድንናጥ፤ መያዣ መቋጠሪያው ጠፍቶ እንዲህ በረግረግ እንድንጓዝ እና ተስፋ አጥነት እንዲዘፍንብን ስለምን ዓይነት እርግማን እንደተፈጠር እራሱ ይጨንቀኛል።

ሰው ሁነሃል፤ እንደ ሰው አሰብ፤ እንደ ሰው ተራመድ፤ እንደ ሰው ኑር ተብሎ ተፈቅዶል። ግን እኛ ሰውነትን አንፈልግም ጭራቆች መሆን እንሻለን ብለን በጭካኔ እና በአረመኔነት ላይ ሰምጠን መሽቶ ሲነጋ፤ ነግቶ ሲመሽ በድብልቅል -  በዝንቅንቅ - በቅይጥይጥ ዓለም ሰንዳክር ስለምን ፈጠርከን፤ ከፈጠርከንስ ስለምን ወደ ልቦችን አትመልስነም ብዬ አምላኬ ጠዬኩት?

አሁን እንሳሳነት፤ አውሬነት፤ አራዊትነት ምኑ ይናፍቃል? ሰው ሁኖ ተፈጥሮ እንዴት ቀጣዩ ትወልድ በሥርዓት አልበኝነት ይደግ ተብሎ ይፈረድበታል። እንዴት? ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ሰውን ከሁለት ለመግመስ እንዴት ይታለማል?

እውነት ለመናገር ከቶ በቅኝ ግዛት ባለመገዛታችን ይሆን እንዲህ የነፃነት ጣዕምና ለዛ ስንይዘው እንኳን አለምርባችሁ ብሎን ሰላማዊውን ሰው እያስተጓገልን ነግዶ፤ በደክሞ ጥሮ ግሮ ለማደር እንኳን ዜጋው ፈቃጂ ሰጪዎች እና ነሺዎች የምንሆነው በዬአጥቢያው ዳኛ ሁነን ያለነው?
እኔ በባህርዳር ላይ የተፈጸመው ነገር እጅግ አሳዝኖኛል። ያ ሁሉ ምርት መሬት ላይ ተዘርግፎ እንደዛ መሆኑ ያው ሥርዓተ አልበኝነት ነው።

„ሲይዙሽ ጭብጥ ሙሉ፤ ሲልቁሽ ሜዳ ሙሉ“ ማለት ይሄው ነው። ያ መከራ አልፎ ዛሬ በቅጡ መያዝ አቅቶ መርቃታችን ከበላያችን ተነስቶ ይኸው በምጥ እና በዳጥ እንደለመደብን …

ያን ያህል 27 ዓመት የኖረው መከራ ተገፋ ሲባል ያገኘነው የነፃነት ዕድል አፍር ድሜ አስግጠን ወደዬት እያመራን እንደሆን ይታያል? ከቶ  እኛ ክፍላችን መታሰር፤ መገረፍ፤ መሰደድ ይሆን?

በፍጹም አላወቅንበትም። ለዚህ የደከሙ፤ የለፉ፤ የተሰዉ፤ የተጉት ሁሉ መና እና ከንቱ እያደረግናቸው ነው። ስለምን? ያው የወጀብ ቤተኞች ስለሆን። ህሊናችን የነቃው ክፍል ገና ዱድማ ስለሆነ። ለነገሩ ገና ሰው ነኝ ለማለትም መድፈር ይችገራል።

ለሥርዓተ አልበኝነት ት/ ቤት ይከፈት እያልን አይደል። ግን እኛ ምኖች ነን? ሌላው ደግሞ መዳፌ ውስጥ ነው ያለኸው // ያለሽው ብትፈልግ በዚህ ባትፍልግ በዛ እያለ ያን መከረኛ ህዝብ ይሄው ከጋለው ምጣድ ላይ አስቀምጦ በስጋት ይቆላዋል በአዲሶቹ ንጉሦች። ነፃነት ማለት የሄው ነው። ነገ ደግሞ ማተብህን በጥስ ከዳር እስከ ደንበር አይቀሬ ነው። ምስራቅ ላይ የታዬው ይኸው ነው።

የመከራው ቁልል ያው የመርዝ ዝርያ ነው። ያ መርዝ እያለ ሌላ መርዝ ደግሞ በአደባባይ በይፋ ተነጥፎ ተጎዝጉዞው እዬተካሄደ ነው።
ግን ልዑል አስፋወስን አስራተ ካሳ በአዲስ ወንጌል አርባዕቱ የሰየሟቸው ዶር አብይ አህመድ፤ አቶ ደመቀ መኮነን፤ ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር ገዱ አንዳርጋቸው የት ናቸው? ምኑ ዋጣቸው?

 በቃ ይሄው ነው ያን ያህል ለወራት የዘለቀው ድካም  … ለእንደ ገና ሞት እና ተስፋ ቆራጭነት፤ ለእንደ ገና ስደት እና ተስፋ ቢስነት፤  ለእንደ ገና ስጋት እና ሽብርተኝነት?

ግን ማነው አሁን አጤው? በማን ነው እዬተገዛን ያለነው? ጠ/ ሚር አብይ አህመድን ዶር ሙላቱ ተሾመ ተኳቸውን ወይንስ ጃዋርውያን ወይስ ሌላ የውጭ ሃይል? ተጠዬቂ እስኪ አንቺ መከረኛ አላዛሯ እናት አገር ኢትዮጵያ? 

ብፈልግ ኦሮሚያን ከአራት ወር በፊት መገንጠል እችል ነበር” “ዛሬም ብፈልግ ኦሮሚያን እገነጥላለሁጃዋር መሀመድ
ሄኖክ የሺጥላ ለጀዋር ወቅታዊ ንግግሮች የሰጠው መልስ
ዎች ዛሬ በሻሸመኔ የዱር አራዊት ሆነዋል! (ሐይሉ አባይ ተገኝ

የኔዎቹ መተኛት ስላልቻልኩ ይሄው ቁጭ እንዳልኩኝ አነጋሁላችሁ።
ቸር ወሬ ያሰማን። አሜን!




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።