የእቅፋት እንቅፋት፤
በነገ እና በእኛ፤ በዛሬ እና
በእኛ መሃከል ምን ይደረግ? ደግሞስ ከቀናቶቹ ጋር ምን እና ምን ነን?
„አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ
እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።“
መዝመረ ዳዊት ምዕራፍ ፶ ቁጥር
፩
ከሥርጉተ ©ሥላሴ
15.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
- · እፍታ።
መንግሥት ህዝብን ቢጨፈጭፍ ይውርዳል። ህዝብ ህዝብን ቢጨፈጭፍ ግን እንዴት ይኮናል። አሁን ያለው እንዲህ ነው። አንዱ ህዝብ አቅም ካለው ሌላውን መጨፍጨፍ፤ ማፈናቀል። አፈናቃዩ ደጋፊው ክፉ ህሊና ነው።
በልጅነቴ
ዝምተኛው አባቴ አበይ ነፍሱን ይማርልኝ እና ዝምታውን ጥሶ የሚያልፍ እንጉርጉሮ ነበረው „እናት አባት ሲሞት በአገር ይለቀሳል፤
እህት ወንድም ሲሞት በአገር ይለቀሳል፤ አክስት አጎት ሲሞት በአገር ይለቀሳል አገር የሞተ እንደሆ ወዴት ይደረሳል“
አሁን ያለው ጣምራ ዘመቻ የታቀደው የሽግግር መንግሥትን ወይንም የተጽዕኖ ፈጣሪዎች መንግሥት
ስኬታማ የሚያደርግ እድምታ ነው ያለው። ተፎካካሪዎችም መሬት ላይ ሥራ ለመጀመር ያልፍለጉበትም ምክንያት ያ ነው። የሚጠብቁት ህልም
ስላላቸው። በመሃል ግን ስለ እነሱም ህይወት ምን ያህል እርግጠኛ እንደሆኑ አይታወቅም?
- · መህበረ ቤት።
አገር ማለት በሥርጉትሻ
ዕይታ ዓለም
አቀፍ እውቅና ባለው መሬት እና ካለካሰማ በሚኖር ሰማይ ሥር
የሰዎች
ማህበረ - ቤት ማለት ነው።
ማህረ - ቤቱ ውስጥ የሚኖሩ አባልተኞች ከተጨራረሱ አገር የሚባለው ነገር አይኖርም። ችሎ የኖረው ምንጃር ደግሞ አሁን ተነስቷል። ባለለቀው ሳምንትም ስለ ሰላሌም ዜና ነበር።
„ብፈልግ ኦሮሚያን ከአራት ወር በፊት መገንጠል እችል ነበር” “ዛሬም ብፈልግ ኦሮሚያን እገነጥላለሁ” ጃዋር መሀመድ
አንተ እስከትገነጥለን ድርስ
እማ እኛ አንጠብቅ የሚል እድምታ ያለው ይመስላል የምንጃሩ ጉዳይ፤ ምንጀር ደግሞ ይታወቃል ፍቅሩም መከፋቱም።
አሳዛኙ ነገር በዛ ሰቆቃ ውስጥ
አልፈው ስንት መከራ እና መንከራተት አሳልፈው ከኢትዮ ሱማሌ ክልል ወደ አዳማ የተጠለሉት ወገኖቻችን ላይ ነው ይህ ተፈጠረ የሚል
ደግሞ መርዶ የመጣው። ዛሬም የሰው ህይወት መጥፋቱን፤ ዛሬም የሰው አካል መጉዳሉን፤ ዛሬም እናቶች ማልቀሳቸውን ነው እዬተደመጠ
ያለው። ብትን አፈር፤ መቆሚያ አፍር ብርቅ እና ድንቅ የሆነበት ትውልድ። ወይ መረገም።
ድህነቱም ካዝናውም ባዶ መሆኑም፤ በሽታውም፤
የመጠለያ እጦትም ታክሎ ነው አሁን ይህ ሁሉ ሰው ሰራሽ ችግር የሚደመጠው።
- · የሥነ ልቦና ለውጥ እና አያያዙ ከነሳንኩ እቅፋቱ።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን
ቀድሞ ነገር እነዚህ ከኢትዮ ሱማሌ የተፈናቅሉት ወገኖች ለአዋሳኝ አካባቢዎች አዲስ ሥነ - ልባናዊ ሁኔታ ስለሚገጥማቸው መሬት ላይ
መሰራት ያለበት የህሊና ተግባር ሊኖር ይገባ ነበር፤
ምክንያቱም አሁን ግጭቱ ከምንጃር
ጋር ይሁን እንጂ በቀጣዩ ጊዜም ባራሱ አዳማ አካባቢ በቆየው ኦሮሞ እና ከኢትዮ ሱማሌ በመጣው ኦሮሞ መሃከል የሥን - ልቦና ወጥነት
ለማምጣት ጊዜው የህውከት ስለሆነ ሰከን ብሎ የሚያስብ ስሌለ ሌላ ጦርነት አይቀሬ ነው።
ምክንያቱ ተጨማሪ ሰው ሲመጣ
ተጨማሪ አገልግሎት ይፍልጋል። የአገልግሎት ስፋቱ ደግሞ በነበረው መልክ ከሆነ የቀደሙት የትኩረት ማነስ ስለሚገጥማቸው በዚህ ይበሳጩ
እና ከኢትዮ ሱማሌ የመጡትን ኦሮሞወች እንደ መጤ ሊያዮዋቸው ይችላሉ። ይህ ዛሬ አልተከሰተም፤ ነገ ግን አይቀሬ ነው።
ምክንያቱ
የኦሮሞ ሊሂቃንም መሪዎቻቸውም በአንድ ጠረጴዛ ሊግባቡ የሚችሉ ስላልሆኑ፤ አሁን በቀደሙት ሦስት አመታት አባሳውያን፤ ጃዋርውያን፤
ህዝቃያልውያን፤ ዳውድአውያን፤ አራርሳውያን፤ ከማልውያን፤ OMN ጨምሮ አንድ ወጥ የሆነ ኦነግውያን ነበሩ ከመነሻው በሩቅም በቅርብም
እሳቤ ሌንጮውያን ነበሩ። በሌላ በኩል ደግሞ መራራውያን፤
በቀለውያን በሁለተኛው ወገን አሉ።
በሦስተኛ ወግን ደግሞ ለማውያን፤
አብይውያን፤ አዲሱያውያንም፤ ከተወሰነ ጊዜ አባዱላውያን ነበሩ አሁን በሚታዬው ሁኔታ ወጥነቱ ቀጥሏል ለማለት አያስደፍርም።
ከሁሉም ሳይሆኑ በዝምታ ውስጥ
የነበሩም፤ በ =ኢትየጵያንዚም ፍልስፍና ብቻ ሳይሆን ፓን አፍሪካንሲትም በአራተኛ መደብ የነበሩ አሉ። ማዕካላቸው ሰው የሆነ።
በዚህ ቅይጥ እሳቤ እና ነገ
እና ዛሬ፤ ዛሬ እና ከነገ ወዲያ ሲታሰብ ገና ድቅድቅ የሆነ የጨለማ ዘመን የ ኦሮሞ እናት ይጠበቃታል። „ኦሮሞ ነን። ኦሮሞ ፈርስት፤
ኢትዮጵያ ፈርስት፤ ሁለቱንም በጥምረት ፈርስት፤ መካከለኛው ምስራቅ ዜግነት ፈረስት „ የሚሉ ሃሳቦች አሉ።
ሁሎችም ደረጃው ቢለያይም በኦሮሞ
ታላቅነት ያምናሉ። የሚያራምዱት ፖለቲካ ግን እንደዬ-ሰብዕናቸው የተለያዬ ነው።
- · እቅፋት እና እንቅፋቱ።
በዚህ ባሳለፍናቸው ወደ 9
ወራት ውስጥ የለማውያን መንፈስ ህዝብ አሳታፊ እና አቀፊ ስለነበር የ ኦሮሞ ወጣት ሊሂቃኑ በተለይም ዶር ለማ መግርሳ እና ዶር
አብይ አህመድ በአብዛኛው ኢትዮጵውያን ዘንድ በዘመናችን ታይቶ በማይታወቅ
ሁኔታ ተቀባይነት አግኝተው ነበር።
አሁን ያለው መከራም ያን ማስቀጠል
ወይንም መርከቡ ሲደረመስ አብሮ መስመጥ ነው።
አሁን ለጊዜው መድረክ ያገኘው
ጃዋርውያን እና ህዝቃያላውያን ሲሆን እነሱም እስከ ተወሰነ ድርስ ነው አብረው የሚጓዙት የሚሰማማሙት እንጂ ታዋዊነት እነት እና
ተቀባይንት አዕምሮን የሚያጠቃ በሽታ ስለሆነ ይሰናጣጠቃሉ። ጊዜያዊ የጉልቻ ሽግሽግ ከጋብሳውያን ጸጋዬ ነጠል ያሉ ቢመስሉም ግን
ጊዚያው የሆኑት ነገሮች ሁሉ የሳሙና አረፋ ናቸው።
በዚህ ውስጥ ለማውያን በጠነከረ
አንድነት እና በገጠማቸው ፈተና ሳይበገሩ ለድል በቅተው ነው እድሜ ለብአዴን እና ለቅን ኢትዮጵውያን ተጋድሎ አሁን በሚታዬው የሃይል
አሰለላፍ ድልን ሊያስመዝግቡ ችለው የነበረው። ነገር አሁን በሚታዬው ሁኔታ ግን ቅኖች በደንበር እንዲሰለፉ እያደረገ ነው። ቆይቶ ደግሞ ትእግስት ሲያልቅ
እንደተለመደው፤ እንደ ከዚህ ቀደሙ ፍቅር ስደት ይጀመራል … ግን ምን ይደረግ?
በዚህ ማሀል ተጠቃሚው ማንም
ሳይሆን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሴረኛው አንጃ ነው።
እኔ እንዳማስበው የኦሮሞ ሊሂቃን
በተለይ በሦስት ረድፍ ያሉት እያንዳንዱ ረድፍ ከራሱ ጋር ሳይታረቅ፤ ሦስቱም ረድፍ በአንድ ወጥ የሃሳብ የስምምነት ሰነድ ሳይደር
ነው አገራዊ አደራውን ሦስተኛው ረድፍ ከ አረተኛው ረድፍ ጋር ካሉት በመንፈስ ሃዲድ ስምንት ብቻ ማለት ይቻላል የለማውያን ረድፍ
የተረከበው። ግጭቱ የሚነሳው ከዚህ ነው።
አገራዊ አደራውን የተረከበው
ለማውያን የራሱን ማህበረስብ የፖለቲካ ድርጅቶች አክቲቢስቶች እና ሚዲያውን በተለዬ ትኩረት እና አቀባባል የመያዙ፤ የማቅረቡ እና
ልዩ አትኩሮት የመስጡቱ ሚስጢር እና አገር ቤት የቆዬው የመራራውያን ፓርቲ አትኩሮት ማነስም ሌላው የቅራኔው የታፈነ ግን ነገ የሚፈነዳ
ጉዳይ ነው።
እንግዲህ በዚህ ውስጥ ያለው
አገራዊ ራዕይ ፍዳውን የሚከፍለውም መጀመሪያ ያላለቁ ነገሮች በራሳቸው ወስጥ ሳይኖሩ ነው እኛን አቀፉ እና አቅም ፈጥሮ „በኢትዮጵያዊነት
ሱስ ነው“ መርህ አዲሱን የለወጥ ሐዋርያ የሆነው።
ይህን ማድረጋቸው ባልከፋ ዛሬ
ደግሞ ያ ያላለቀ አጀንዳ በህዝብ ፊት እንዲህ አደባባይ ሲወጣ ከቅዳሜ እስከ ቅዳሜ ሌላም የጦርነት አዋጅ አለማምጣቱ በኪነ ጥበቡ
እሱ ረድቶን ነው።
ይህም ብቻ አይደለም መንግሥቱን የሚመራው የለማውያን ቡድን የሰኔ 16 ሆነ የሀምሌ 19 የግፍ ግድያ በሚመለከት
እርምጃ አወሳሰድ ዘገምተኝነት፤ በተከታታይ የሚፊጠሩ የወል መፈናቀል እና እልቂት ዝምታ እና የፍጥነት ማነስ ታክሎ ነገን እጅግ
አስፈሪ አድርጓታል። ለዚህም ነበር እኔ ጭንቁ ሌቦቹ ለምን ተፈቱ ነው ሳይሆን ለውጡ ሊቀለበስም ይችላል ብሎ ማሰብ ይገባል ያልኩት።
የለማውያን ገዱውያን፤ አብያውያን
መንፈስ አሁን ረመጥ ላይ ነው ያለው። ወይ ይፈርሳል ወይ ደግሞ ያፈርሳል።
ጃዋርውያንን፤ ህዝቃያላውያንን፤ በርቀትም ተስፋዬ ገብራውያንን ተሸክሞ መንግሥቴ በአስተማማኝ ሰላሙን ያገኛል ብሎ፤ ሥልጣኔ ይቀጥላል ብሎ አስቦት ከሆነ ግምል
በመርፌ ቀዳዳ ትሾላካለች ማለት ነው።
ምክንያቱም ቀድሞውን የተሰነጣጠቀው
መንፈስ ልቡ የሸፈተ ህዝብ አምኖ የተቀበለው ተስፋ ጽናቱን በቃሉ ያስፈጽማል ብሎ እንጂ እንዲህ መጋረጃ ሲከፈት እና ሲዘጋ በሦስት
አራት ክፍል ትውና ይኖራል ብሎ አይደለም። አልነበረም። ድርጅቶችን የሚያፈርሳቸው ከድርጅቱ ህገ ደንብ ያፈነገጡ ዕይታዎች አደባባይ
ሲወጡ ነው። አገር ለሚያሳጣው ተስፋ ላይ ሆኖ ተስፋን መጠበቅ በውነቱ ታይቶ የማይታወቅ ጨዋነት ነው።
- · በእኔ አቅድም እኔ አቅድም መዥጎድጎድ ዥንጉርጉር፤
ወደ አገር የገቡት የፖለቲካ
ድርጁቶች ከዚህ ቀደም መታገያ መሬት ስላጡ ነበር መረብ ላይ ጦርነት ከፍተው የነበሩት። ከ እነ ሁለመናቸው አሁን ደግሞ እንዳሻችሁ
ሁኑ ተብሎ ለወጬቸው ሳያስቡ እዬተፈላሳሱ ነው። በውስጣቸው ያለውን መርዛቸው ይዘው አድብተው ተቀምጠዋል።
ነገ ምን ሊሆን እንደሚችልም
በዚህ ዘርፍ በራሱ ማንዛርዘሪያ አልተሰራላትም። የአያያዙም ጥበብ እንዲሁ። ባለቤት የለሹ መከራ ደግሞ ይሄው ነው።
አገር ገቡ ነው እንጂ ይህን
ሰሩ ይህን አደረጉ አይደመጥም። አገር ቤት የነበሩትም ተፎካካሪ የሚባለሉት ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠት ውጪ ምንም ላይ አይደሉም።
እስከ አሁን ያልተደመጠው የፖለቲካ ተፎካካሪዎች ድንገቴ አልጎበኛቸው መሆኑ ነው። ነገስ? አይታወቅም።
አንዱ ላይ አንድ ነገር ከተፈጠረ
በማግስቱ ቦሌ ነው … ለዛውም በወረፋ። እራሱ በዝምታ ውስጥ ያለበት ጉዳይም እም ነው። ሁሉ ከገባ በኋዋላ ምን ይመጣል ጭንቀቴ
ነው። ማን ይሆን የሚጠበቀው? ምን? ስለምን ይህን እላለሁኝ?
ኦህዴድም ብአዴንም በቀደመው
አቋሙ ስለመሆኑ ግልጽ አይደለም፤ መቸኮል ባያስፈልገም ጠረኑ ግን ለእኔ ምቹ አይደለም፤ የተማሩት ፈላስፎች በተለያዬ ሥም እንዲህ
ዓይነት ዕይታዎችን እንደ የሌሊት ጉጉት ጎትት አድርገው ሲመከቱት ስለመቻለሁኝ፤ አነባለሁኝ አደምጣለሁኝ፤ ሁሉም እያታውን እና ስጋቱን
መግለጹ አገሬ፤ ወገኔ ቢል እንጂ 27 ዓመት ሙሉ እኮ ፖለቲካ የጥቂት ሰዎች ብቻ ነው የነበረው።
የሆነ ሆነ እኔም ዜጋ ነኝ
እና፤ ኑሮዬን ወጣትነቴን የገበርኩበት ነውና በዘምታ እና በቸልልታ የማልፈው አንዳችም ነገር አይኖርም። በርቀት ሄጄ ጠረኖችን ማሽተት
እና በዛ ላይ ደግሞ አቅሜ መጻፍ እና ጸሎት ስለሆነ መትጋት ሥራዬ ነው፤
በጎ ተመኙ ከሆነ መመኘት ይቻላል፤
ግን በመመኘት ብቻ ሳይሆን ምኞት የሚሳካው፤ ምኞትን እውን ለማድረግ የገጠሙ ችግሮችን፤ ሳንኮችን፤ እንቅፋቶችን በ አንድ ሰው መረጃ
ፍሰት ሳይሆን ወይንም ቢለቃነት ትንተና ብቻ ሳይሆን ለተፈጠርነበት ተልዕኮ በመትጋት የራሳችን ዕይታ ላይ ሉላዊነት በፈቀደለን መጠን
መናገር፤ መጻፍ መብታችን ነው።
- · ሳንክን በችልታ ከማዬት ይልቅ …
ማናቸውንም የችግር ዓይነት
ጊዜ ሰጥቶ አጥንቶ፤ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት የሥነ - ልቦና ስንዱነት፤ የሥነ ልቡና አቅም ትጥቅ ቢያንስ ያስፍልጋል። ለዚህ ነው
አበው „አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን“ እሰቢ የሚሉት።
አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ አማራሩ
ችግር ላይ አይደለም ብሎ ማሰብም /// አለመሳብም መብት ነው። ከልካይ የለበትም። የለበትም የሚለው ወገን ትራሱን ከፍ አድርጎ
ተስፋውን ጎዝጉዞው ይተኛ የችግር ጠረን ይሸተኛል የሚለው ደግሞ ጉዳዩ የቁስ ሳይሆን የሰው ህይወት፤ የትውልድ ብክነት፤ የትሩፋት
ቅጥለት፤ የትውፊት ድርመስት ስለሆነ ከበፊቱ በበለጠ ወገባችን ጠበቅ አድርገን እንሠራለን እንደ ለመደብን።
- · ዕለታቱ እና እኛ ምን እና ምን ነን? ተገናኜን ወይንስ ተለያዬን?
በዚህ ማህል የህዝብ ለህዝብ
ጦርነቱ ቀጥሏል። ነገ እና እኛ ምን እና ምን ነን ተገናኘት ወይነስ ተለያዬን? ሌላው ቀርቶ ኦቦ ዱላ ገመዳ እና ሠራዊታቸው የለማ
ቡድን እና ሠራዊቱ ፍጥጫ ላይ ስለመሆኑ አለማሰብ አይቻልም። በማደራጀት ረገድ የራሳቸውን መረብ በመዘርጋት ይታወቃሉ የሚባሉት ኦቦ
አባ ዱላ ገመዳ በሁሉም ዘርፍ አቅም እንዳላቸው ማስብም ይገባል።
የቅርቡን ሩቅ ሳንሄድ ማለት
ነው … እሳቸውን አግልሎ፤ የሳቸውን መሰል መንፈሶችን አግልሎ ሌሎችን ለማቀፍ መትጋት ሊያመጣው የሚችለው የሞራል ጦርነት ማሰብም
ይገባል። ኦቦ ዳውድ ኢብሳን ለዛውም ትጥቅ ፈተው ለማግኘት ኤርትራ ድረስ ሲኬድ፤ እቅርብ ያሉት የ ኦህዴድ መሥራችን ገፍትህ ከሆነ
ቀይ መብራት አለበት።
ወይንም ከገፋህ የመቆጣጠሪያው
ስልት በመዳፍህ ስለመሆኑ ማረጋገጥ አለብህ። ቀወስ ፈጣሪዎችም እንዳሻችሁ ሁሉ ቀወስ ላይ ያልቆአችሁትም እንደ ፈለጋችሁ ሁኑ ብለህ
ለቹፌያማው የ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ግዙፍ ፈተና ነው። ምክንያቱም የተሠራው የህሊና ሥራ የሚንዱ ሌላ ትዕይንቶች ደግሞ አሉ።
ቀደም
ባለው ጊዜ ሳይበር ላይ ነው። አሁን መሬት ላይ ነው ሥርአት አልበኝነት እና ህገ ወጥነት እዬታዬ ያለው … ምኑ መዳፍ ላይ ስለሆነ
ነው የተረጋጋ ሁኔታ አለ፤ ጸጥ በሉ፤ ጭጭ በሉ የሚያስብለው።
- · ራስን የማጥፋት አባዜ ከኢሠፓም አለመማር ነው።
እውነት ለማናገር ለማውያን
የራሳቸውን መጥፊያ የሠሩት ራሳቸው ናቸው፤ ማንዘርዘሪያ ሳይሰሩ፤ ሥነ - ደንብ ሳያዘጋጁ፤ ገፋ ያደረጉትን ገፋ አደረጉ፤ ሌላውን
ተቀላቀሉን፤ ተዋህዱን አሉ፤ በዛ ላይ የእነሱ ወደ ሥልጣን መምጣት እና የሌጋሲው ዓለምአቀፍ እውቅና ማግኘት ያሰኮረፈው ሁሉ ባገኛው
ነጻ ሚዲያ ላይ የራሱን ረጅም እጅ ሰደድ እያደረገ ቆሰቆሰ የተማገደው ተስፋ እና ተስፋኛው ሆነ።
ይህም የእስከ አሁኑ የተከፈለው
መስዋዕትነት፤ የወደመው ቅርስም በበቃችሁ ቢጠናቀቅ መልካም በሆን ግን ቀጣይነቱ ተቀጣጣይ መረቦች በክብሪት እና በቤንዚን የዋይታ
ዜና አውደኛ መሆናቸው ግን አይቀሬ ነው።
ሚዲያውን እንኳን ፈር ለማስያዝ አልተቻለም። የተፈለገው ዜና ብቻ ነው የሚቀርበው። የባህርዳርን
የንግድ ማህበረሰብ መስተጓጎል ስትዘግም የሻሸመኔውን መዘገብ ግድ ይል ነበር። የትናንትን ከህግ የበላይነት መጫን ስታወግዝ የዛሬውን
ደግሞ እዬሰራህበት መሆን አለበት።
መንታ ልብ ከኖረ ከባድ ነው።
ይህን መሰል አገራዊ አህጉራዊ ሃላፊነት ከተረከቡ በኋዋላ ኦህዴዶች የውስጥን ስውር ሰው ሰራሽ መሻት ሰርዞ አሸናፊ ያደረገውም መንፈስ መከተል ሲገባ በራሱ ውስጥ
የተነሳው የውስጥ ቋያ ተስፋን በሁሉም አቅጣጫ እያጋዬው ነው።
ትናንት የተደመጠው የአዲስ
አባባን ዩንቨርስቲ ዓለም አቀፍ ዕውቅና የገፈፈው የፊንፊኔ ዩንቨርስቲ የመባል ዜና በራሱ
ለማውያን በራሳቸው የመንፈስ ቅርበት አጅበው ያስገቡት፤ አንጥፈው የተቀበሉት OMN የጦርነት አውድ ነው። በለፈለፉ ይጠፉ ነው የሆነው።
በዛ ላይ የእነሱም ምኞት ባይነርበት ይህ የቅርስ ውድመት እንዲህ የአደባባይ ሲሳይ ባልሆነ ነበር። በዚህ ድቅቅ የሚሉት የሥነ
ልቦና ነፍሶችን መገመት ያዳግታል።
ለማውያን ሳይጀመሩት ገና በውጥኑ
ራሳቸውን ግልጠው የሚሹትን የኦሮሞ የበላይነት በይፋ እና በአደባባይ ሲቃኙበት፤ የኦሮሞ የሥነ - ልቦና ወረራ በኢትዮጵያኒዝም ላይ
በይፋ እና በአደባባይ ሲታወጅ የመጋቢት 24 ቀን የ2010 የተስፋ ድምጽ መደርመሱን ያዬ ህዝብ ገና የታመቀ የህሊና ቦንም ታቅፎ
መኖሩን ማወቅ ይገባል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይጠራጠር
የተቀበለውን መንፈስ ያን ተዝቆ የማያልቅ ተቀባይነት ተገን በማድርግ ግን ዘላቂውን ተስፋ በግርድ እና በእንከርዳድ እንዲነቀዝ እዬተደረገ
ስለመሆነ ምንም ማስረጃ፤ ምንም ማመሳከሪያ አያስፍልግም። በዚህ ውስጥ ያለው የሃላፊነት ደረጃ ማን ይውሰድ ቢባል ኦህዴድ ነው።
ኦህዴድ በህዝብ ዘንድ ያገኘውን
ተቀባይነት በራሱ ጊዜ በቦንብ ያቃጠለው እራሱ ኦህዴድ ነው። የራሱ አጥፊ ራሱ ኦህዴድ ነው። ኢሠፓ ለዘር ሳይበቃ የከሰመ ፓርቲ
ነው። የኦህዴድ መንገድ ያን የተከተለ ይመስላል። ተቀናቃኙን መንፈስ ዕድል ሰጥቶ ህጋዊ ዕውቅና ሰጥቶ
የኢትዮጵያን ህዝብ በራሱ ላይ እንዲሸፍት ያደረገው እራሱ ኦህዴድ ነው።
ይህ እንዲሆን ደግሞ ግድ ነው።
ቁጥር ስፍር የሌላቸው የኦነግውያን መንፈሶች ለድል እንዲበቁ በራሱ ጊዜ ሞዘቦልድ አልጋ ሆኖላቸዋል - ኦህዴድ።
ለማውያን የተለያዩ የኦነግውያን
መንፈሶችን በከበከበ ቁጥር የኦሮሞን የበላይነት በአሃቲ መንፈስ በጉልበታም አንድነት እና በደረጀ መንፈስ ማስቀጥል መስሎት ነበር፤
የሆነው ግን „የቆጡን
አውርድ ብላ የብብቷን ጣለች“ ነው የሆነው።
ኦህዴድ ለተሰጠው አክብሮት እና ተዝቆ ላላቀው
የመንፈስ የህዝብ አፍቅሮት ብጣቂ ዋጋ አልሰጠውም። የፊቱን እንጂ መነሻውን ለማስተዋል አልተቻለውም። እጅግ ቸኮለ የባላይ ነኝ ለማለት።
ነገር ግን ሁሉም የሚያምረው የተሰጠውን ቀስ አድርጎ ሲይዙት ነው። በልክ የሆነ ነገር ጣዝማ ነው። ፈዋሽ።
ጥቂት ቀን ይቀራሉ በአብይ
ሌጋሲ ላይ ድንጋይ ለመወርውር … ኦህዴድ ተግቶ እዬሠራበት ያለውም ይኼውን ነው …
አሁንም እጠይቃለሁኝ መብቴ
ነው ዶር ለማ መግርሳ የት ናቸው? ምን ሆነዋል?
ነፃነት ማለት መኖር ሲቻል ብቻ ነው!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
በቃችሁ ይበለን አማኑኤል፤ አሜን!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ