የልጆች የውስጥ ቀለበትነት…እንደአብዩ ተደሞ!

የአብዩ አፍቅሮተ - ልጆች ተደሞ።
„የብልህ ሰው ጥበብ መንገዱን ያስተውል ዘንድ ነው“
 ምሳሌ ፲፫ ቁጥር ፰
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
 22.12.2018
ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።

·       ፍቅራዊነት መንገድ በመሪነት ሲቆምስ።



በቅድሚያ በዶር ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው ሉዑክ ተልኮውን አጣናቆ ኢትዮጵያ በሰላም መግባቱን አዳምጥኵኝ። ትልቅ ነገር ነው። በሰላም መግባት ትልቅ ዋጋ አለው - በእኔ ዘንድ። የሰው መኖር ነው አስፈላጊው ጉዳይ ሌላው ይደረስበታል። ተመስገን!

እንዴት ናችሁ ቅኖቹ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ? እስቲ ዛሬን በአዲስ አጀንዳ አብረን መጭ እንበል በሰላው መንገድ ... እንዲህ ... ዘንከትከት እንበልበት ... 


ወላጆች ወይንም ኣሳዳጊዎች ልጆቻቸውን የሚያከብርላቸውን ይወዳሉ። ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን የሚወድላቸውን ይወዳሉ፤ ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን የሚቀርብላቸውን ይወዳሉ። ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን የሚፈቅርላቸውን ያፈቅራሉ።


በዘመናት ሂደት አንድ ልዩ ክስተት ኢትዮጵያ ተከስቷል።
ኢትዮጵያ ልጆችን የሚወድ፤ ልጆችን የሚያከብር፤
ልጆችን የሚያቀርብ፤ ልጆችን የሚያፈቅር መሪ
 አላዛሯ ኢትዮጵያ አግኝታለች። ተመስገን!

የኦሮሞ ጉዲፌቻ ባህል ትውፊት ነው ማለት የሚያስችል የኦሮሞ የፖለቲካ ሊቀ ሂቃን ቢኖሩ ዶር አብይ አህመድ ናቸው። በዚህ ታላቅ በሆነው የቀደምት የዕውነት ባህል ውስጥ  በአካልም፤ በመንፈስም ተገኝተዋል ጠ/ሚር አብይ አህመድ። 

ዶር ለማ መገርሳም በልጆች ጉዳይ ላይ ባህርዳር ላይ ባደረጉት ንግግር አትኩሮት ሰጥተውት ነበር። እንዲያውም በፖለቲካ ሊቀ - ሊሂቃን ደረጃ እኔ ልጆች አጀንዳ ሆነው አዬሁ ማለት እምችለው በዚህ ዘመን ብቻ ነው።



አዲስነትን ስንቁ ያደረገው የአብዬ ሌጋሲ እሰከ አሁን ባለቤት ያልነበራቸውን ዜጎቹን የመንፈሱ ጽንስ በማድረግ ረገድ ሪከርድ ሰብሯል። ሴቶች፤ ከማንፌስቶ ውጭ ያሉ ዜጎች፤ አዛውንታት፤ አቅመ ደካሞች፤ ታዳጊ ወጣቶች፤ ወጣቶች፤ የአካል ጉዳተኞች ለአብይ ሌጋሲ ህሊና ናቸው። ያልተሸራረፈ ፍቅርንም አግኝተዋል። አስተዋሽም ሰጥቷቸዋል።


ይህን ዘመን የእኔ ሊባልለት የሚገባው ጉዳይ እንዚህን መሰረታዊ ጉዳዮች የእኔ ብሎ፤ ያገባኛል ብሎ፤ በትርፍነት ሳያይ፤ በባለቤትን ውስጣዊነት ፈቅዶ፤ ወዶ አጅንዳው አድርጎ በመረከቡ ነው። 


ዛሬ ዋልታ ላይ እንዳደመጥኩት በዚህ አዲስ የለውጥ ዘመን የረባ መኖሪያ ፈቃድ ያልነበራቸው፤ በስደት ሲከላቱም የነበሩ ወገኖቻችን እነሆ ባለቤት ዛሬ ኑሯቸው ውደ 30 ሺህ ዜጎች ወደ አገር እንደ ገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ቃለ አቀባይ ገልጠዋል።


ጠ/ሚር አብይ አህመድ የሥራቸው መጀመሪያ የነበረው ባለቤት ያጣውን ስደተኛ ሰማዕት ህፃን በሳውዲ ሆስፒታል ተገኝተው ማዬታቸው ብቻ ሳይሆን ተፈላጊው ክፍያ ተጠናቆ ከኢትዮጵያ የህክምና ልዑዕክ ተልኮ፤ የክብር አቀባበል እንዲደረግለት ተደርጓል።
በመቀጠልም በዛ የውጥረት ሁኔታ እያሉ ሆስፒታል ድረስ ተገኝተው ልጃቸውን ጠይቀዋል።





ጠ/ሚር አብይ አህመድ መሪም ብቻ ሳይሆኑ ጥቃትን ያወጡ ወንድም፤ ጥቃትን ያወጡ ወንድም ብቻ ሳይሆኑ አባትም ናቸው። በሌላ በኩል በቤንሻንጉል ክልል ግፍ የተፈጸመበትን ታዳጊ ሰማዕት ወጣትንም ሆስፒታል ድርስ ሄደው ጠይቀው በመንግሥት ወጪ ውጭ ሄዶ የሚታከምበት ሁኔታ እንደሚመቻችም ቃል ገብተዋል።



በኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት ልቤን የነካው መሰረታዊ ጉዳይ ያችን የነገ ቀንበጥ አንዴት እቅፍ አድርገው፤ ፍቅርን እንደቀለቧት ላዬ ሰው እኒህ ሰው ፈጣሪ ሲፈጥራቸው መርቆ ስለመሆኑ ህሊናው ከኖር ማገናዘብ ያስችላል። ኤርትራን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሲቀበሉ ለከንቱ ውዳሴ አልነበረም። ለምድራዊ ጥቅማ ጥቅምም አይደለም። ሰውን ማዕከል ባደረገ ሰብዕዊነት እንጂ። 


ከዚህች እንቡጥ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሰጧት ፍቅር ጠቅላላ ለኤርትራ የነገ ትውልድ ንጹህ ልባቸውን ማስረካባቸውን ያመሳጥራል። ለዚህም ነው በሐምሌው ዝምታ ወቅት የአንች መንፈስ ምንአ? ብዬ የእሷን ፎቶ ስለጥፍ የነበረው።

ለመጀመሪያ ጊዜ ጳጉሜ በኢትዮጵያ የሰብዕዊነት እንቅስቃሴ ታዳሚነት ያሰበለ ወር ነበር። በዚህም ለቀጣይ የትምህርት ዘመን አቅም ላነሳቸው ልጆች የት/ መሳሪያቸውን እንዲሟላ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል። 

ይህም ብቻ አይደለም ባለቤታቸው ደልዳዋ ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በባህርዳር፤ በጎንደር፤ በአዲስ አባባ አትኩሮት ያደረጉባቸው መስኮች ልጆች ተኮር ነበር። እንዲያውም አንድ ልጅም ለማሳደግ እንደወሰኑ አዳምጫለሁኝ። ት/ቤቶችን በመከፈትም የቀዳማዊት እመቤት ቢሮ ዋነኛ ፕሮጀጀክቱ ነው። ማግስት እንዲህ በተቀናጀ፤ በተደራጀ ብልህነት እዬተመራ ነው።


መንፈሱ እራሱ የሚማርክ ብቻ ሳይሆን የሚመስጥ ጤና አዳማዊ ነው። መሪነት እንዲህ ከጓዳ እስከ አደባባይ፤ ከፖለቲካ ዕሳቤ እስከ ኢኮኖሞያዊ ዕሳቤ፤ ከኢኮኖሚ ዕሳቤ እስከ ማህበራዊ ጉዳይ፤ ከማህበራዊ ዕሳቤ እስከ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች፤ ከሃይማኖታዊ ጉዳዮች እስከ ታሪካዊ ጉዳዮች፤ ከታሪካዊ ጉዳዮች እስከ ትውፊታዊ ጉዳዮች ሳይዛባ፤ ሳይበላለጥ፤ ሳይነጣጠል፤ ሳይዛነፍ፤ ቅርብ እና ሩቅ ሁኔታዎች ሳይፈጠሩለት፤ ድንበር እና ክትር ሳይሰራለት፤ ዜግነት እርቦ እና ሲሶ ሳይበጅለት እንዲህ ወጥ በሆነ በተዋጣለት ጨዋነት ዕውነት ሆነ ማዬት የህልም ያህል ነው ለእኔ።

ጠ/ሚር አብይ አህመድ በህጻናት፤ በታዳጊ ወጣቶች፤ በወጣቶች ያላቸውን ተስፋ ለማብቀል የጀመሩት ጉዞ ማግስትን ለማበጀት አንቱ የሆነ የውስጣዊነት ቅኔ ነው። የብሄር ብሄረሶቦች የመጀመሪያ ዓመት ዝግጅት አዲስ አባበ ላይ በ2011 ዓ.ም ሲከበር እሳቸው ያሳለፉት ከታዳጊ ወጣቶች ጋር ነበር።


 የዚህ ዓመት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የውጭ ዕድል ሽኝታ ላይም ጉዳዬቸው ነውና አገራቸውን ውስጣቸው ማድረግ እንዳለባቸው ያስገነዘበ ንግግር በቦታ ተገኝተው ለከፍተኛ የትምህርት ዕድል ላገኙ ልጆቻቸው አድርገዋል። 

ለተጓዦች ብልሃትን መቅሰም ዋንኛ ተልዕኳቸው ስለመሆኑን ተደራቢ ሃላፊነት ሰጥተዋል። አንድ የአገር ብልህ መሪ ይህን ሲያደርግ ለእኛ ትውልድ ጠ/ሚር አብይ አህመድ የመጀመሪያው ናቸው። 

ለዚህ ዓመት የበጎ አደራጎት ወጣቶች ስምሪትም በሚመለከት ወጣቶችን አወያይተው ዕድሜያቸውንም ዕድላቸውንም ማሽሎክ እንደሌባቸው አበክረው አስገንዘበዋቸዋል።

ጊዜው ካለፈ የማያገኙትን ዕድል ዛሬ በጊዜው መፈጸም እንዳለባቸው በአጽህኖት አስተምረዋቸዋል። ይህን የምክር ዕድል ምነው እኔ ልጅ እያለሁኝ አግኝቸው በሆነ ነበር አሰኝቶኛል። ልጅነት ብዙ ነገር ይሰጣል፤ ልጅነትን በተፈቀደለት ተፈጥሮ ማሳለፍ ደግሞ የልጅንት ታሪክ አለኝ ማለት ያስችላል። ቁምነገረኝነት ቆይቶ በሙሉ ዕድሜ ይደረስበታል። 

የሆነ ሆኖ የዛሬ ወጣቶች ዕድላቸው መጠቀም መቻል በጊዜው ስለመሆኑ፤ በኸረ ጉዳይ ስለመሆኑ በአጽህኖት ገልጠውላቸዋል። ወጣቶች ዕድሚያቸው የሚሰጣቸውን ጸጋ እና በረከት እንዳያሾልኩ መከረዋቸዋል። መሪ ማለት እንዲህ ይገለጻል።


መሪ ግንጥል ጌጥ ሊሆን አይገባም - ጉዞው። መሪ ሁልአቀፍ እና ሁለንትና መሆን ይኖርበታል። የልጆችን ሳቅ፤ ደስታ፤ የምር ሀዘን እንዲህ የሚጋራ። መሪ ዝንጥል ዝንባሌ ሊኖረው አይገባም፤ መሪ ቅርንጫፎችን መሸከም የሚያስችል የህሊና ብቃት ሊኖረው ይገባል፤ መሪ ግንድ ነውና። መሪ የዛሬ ሰው መሆን አይገባውም፤ መሪ የዛሬም የነገም የተነገ ወዲያንም አሻግሮ አልሞ የነገ ወዲያዎችንም ጉዳዬ ሊል ይገባዋል። ዛሬ ተመሰገን አይተነው ሰምተነው የማናውቀውን የመንፈስ ክብር እያዬን ነው። አንድ ያገር ጠ/ሚር እንዲህ ሀዘንን ተጋርቶ ልጅን ሲያጽናና ጠ/ሚር አብይ የመጀመሪያው ናቸው። ተመስገን!



መሪ በግርግር ፖለቲካ ወንበር ተመኝ ብቻ መሆን አይኖርበትም፤ መሪ ተተኪውን ለማፍራት ስለ ተተኪው ጊዜ እና አትኩሮት አቅዶ መከወን ይኖርበታል። እሱ የዛሬ ሰው ብቻ አይደለምና። እነ አጤ ፋሲል በዛ ዘመን የሰሩት ነው ዛሬ አለም ቅርስ እና ውርስ የሆነው። እነ አጤ ቴወድሮስ ያለሙት ህልም ነው ኢትዮጵያዊነት የአንድነት መርህ ሆኖ እንዲቀጥል የሆነው፤ …

… እነ አጤ ዮሖንስ የተጉለት ጽናት ነው ዛሬን የሰጠን፤ እነ አጤ ሚኒሊክ እና እነ ብርሃን ዘኢትዮጵያ ጣይቱ ብጡል ያቋዮዋት አገር ናት ዛሬ የጥቁር መመኪያ ዓርማ የሆነችው። በፓን አፍሪካ ምስረታ የታሪክ አውራ ያደረጉን አጤ ሃይለስላሴም የህብረቱ ሐውልት ናቸው፤፡ የታላቋን ሱማሌን ህልም ከንቱ በመስቀረትም ረገድ ኮነሬል መንግሥቱ ሃይለማርያም ጉልህ ተግባር ፈጽመዋል። ቅኝ እንዳንገዛ አደርገዋል በአመራር ጥበባቸው።

በአብይ ሌጋሲም አፍሪካ ቀንድ ላይ ያለው የመተሳሰብ ድባብም ጉልተ - ትውፊት የሚሆን ነው ለነገ። ጅምሩ ውጥኑ አንቱ ነው። ሰሞኑን የጁቡቲው መሪ በአጽህኖት የጠ/ሚር አብይ አህመድን ትጋት፤ የልቅና ድርጊቱን ያከበረ መልዕክት አስተላልፈዋል። ተመስገን!

መሪነት ሩቅነት ማለት ነው። ይህን ሩቅነት እንደጠማን እንዳይቀር እነሆ ዘመኑ አሳምሮ በረከቱን በምርቃት አንቆጥቁጦ ሸልሞናል። ጠ/ሚር አብይ ዛሬ የሁሉም ህሊና ቤተሰብ ናቸው። ቤተኛ ናቸው። 

  • ·       ልጆች የውስጥ ቀለበትነት…

ወላጆች እና አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን የወደደውን፤ ያፈቀረውን፤ ያከበረውን ዝቅ ብሎ ትህትና የቀለበውን ልጃቸውን ታላቅ/ ታናሽ ወንድማቸውን ሙሴያቸውን ጠ/ሚር አብይን ሌጋሲ ሊያከበሩ፤ ሊሳሱላቸው፤ ሊጠነቀቁላቸው፤ የእኔ ሊሏቸው ይገባል። እሳቸውን ፈቅደው በመስጠት እረገድም የዴሞክራሲ ተቋሙን ዶር ለማ መገርሳንም። ምርቃት በወጉ ካልተያዝ ይነሳል። ምርቃታችን እናክብር እንደ ማለት ... 

ወላጆች ሆኑ አሳዳጊዎች መቻልን ማስቻል እያዩት ስለሆነ ልባቸውንም፤ መንፈሳቸውንም፤ ህሊናቸውንም ሆነ ፍቅራቸውን መሸለም ይኖርባቸዋል ለዚህ አብይ ለውጥ። ልጆቻቸውን የውስጥ ቀለበት ያደረገ መሪ እነሆ እዮር ሰጥቷቸዋልና።


ዛሬ የኢትዮጵያ ወላጆች እና አሳዳጊዎች ልጆቻቸው በቤተ መንግሥት ከጠ/ሚሩ ጋር ሲወያዩ… ሲነጋገሩ፤ እሳቸው በተገኙበት ተገኝተው ንግግር ሲያደርጉ ሲዩ ይህ በታሪካችን የመጀመሪያው አዲስ ምዕራፍ መሆኑ አውቀው እና ተረድተው፤ ይህን ዘመን ፈጣሪ እንዲባርከው፤ እንዲቀድሰው ከተቃጣ ማናቸውም ስውር እና ግልጽ ደባ እንዲታደገው አምላካቸውን በርከክ ብለው፤ በፆም በጸሎት፤ በድዋ፤ በሰጊድ መጠዬቅ ይገባቸዋል።

ይህ ዘመን ለኢትዮጵያውያን የተሰጠ የምርቃት ዘመን ነው። ዘመኑ ብዙ እርስ በእርሳቸው በሰብዕዊነት ተፈጥሮ የተጠለፉ የመልካምነት፤ የትህትና አብነት ጎልተው የሚታይበት የሚስጢር ዘመን ነው።

ይህ ዘመን መሪ መሆን ማለትም፤ መሪ ስለምን እንደሚያስፈልግም፤ መሪ ሲኮን ስለሚከውነው ተግባራት፤ መሪ ሲኮን ሊኖረው ስለሚገባ ብቃት እና ክህሎት፤ የመሪ የማስተዋል እና የትግስት መጠኑ እስከ ምን እንደሆነ፤ የብልህ መሪ አቃፊነት እና አቅራቢነት በድርጊት ለምልሞ በውል በዓይናችን ያዬንበት፤ በመንፈሳችን የዳስስንበት አንገታችን ቀን አድርገን መሪ አለን ብለን ደፍረን የምንውቅስበት፤ ሃሳባችን የምንገልጥበት፤ አቤቱታ የምናቀርብበት፤ እንደ ሌሎች አገር ዜጎችም በመሪያችን ዙሪያ ከሌሎች አገር ዜጎች ጋር በአውንታዊነት ሳናፍርበት የምንወያዬበት ወቅት ነው።



ይህን ዘመን እንደሚጣ ያደረገው ከአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎና ከኦሮሞ ንቅናቄ ተገድሎም በላይ በእስልም እና እና በክርስትና ዕምነት የነበረው የጸሎት ትጋት ታክሎበት፤ የራሄልን እንባ የተመለከተ አምላካችን አቤት ብሎ፤ ጆሮውን ወደ እኛ ዕንባ አዘንብሎ አዳምጦን በለመንው ልክ ምንም ሳያጓድል ሙልትልት ትርፍርፍ አደርጎ የሰጠን የምርቃት የሚስጢር ዘመናችን ነው። 

ልባሞቹ የዕድምታ ሊቀ ሊቃውንት አንድ ይሉታል ብዬም አስባለሁኝ። ዘመኑ የሚስጢር ስለሆነ። መስጥረን የነገርነው ነው ልዑል እግዚአብሄር እንደ ቸርነቱ ብዛት ሐሤትን ያሳፈሰን የክህሎት እኩልነት የዕውነት ዘመን ነውና።


እያንዳንዱ ቀን ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ጀምሮ ያለው በሙሉ የትምህርት ወቅት ነበር። ራሳችን እንድንፈትሽ፤ ዙሪያችን እንድንፈትሽ፤ አካባቢያችን እንድንፈትሽ፤ ሰፋ ያለ አመለካከት እና ግንዛቤ እንዲኖረን፤ በአጭሩ ሳይሆን ዘለግ አድርገን እንድናስብ፤ አቋረጭ መንገዶችን ሳይሆን አድካሚ መንገዶችን መርጦ በጥራት እና በብልህነት እንዲት ማደራጀት፤ እንደምን መምራት፤ ...እንደሚቻል አዬን ተመከተን። ተመስገን ... 

ይህ ዘመን አገርን እንደምን ማስተዳደር፤ እንዴትስ መንፈስን ማቀናጀት እንደሚቻል፤ በፈተናዎች ውስጥ ተሁኖ እንዴት በስክነት እና በእርጋታ እንዲሁም በጨዋነት፤ በተጨማሪም ምራቁን በዋጠ ብልህነት አገር እንዴት እንደሚመራ የስብከት ወንጌል የተግባር ጊዜ ነበር ማለት እቻላለሁኝ - ለእኔ። የአራት ኪሎ የሰብል ስብከተ ወንጌል ማለትም ያስችለኛል። ነፍስ ሆኖ፤ ነፍስን ታድጎ፤ ነፍስ የዘራ ፍርያማ ምርጥ ዘር ወራትን ነበር ያሳለፍነው።



ፈተናን በሚመለከት ወያኔ ሃርነት ትግራይ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር በሰማይ እና በምድር ተፈጥሮን እና ሰብዕን እንዲሁም የዱር እንንሳሳን ሆነ የቤት እንሰሳን ሳይለይ እንዴት እንደነደደ በአይኔ በብሌኗ ስለተመለከትኩ፤ አሁን የማያቸው ጉዳዮች ከዛ ከነበረው ጋር ሳንጻጽረው ከቶውንም የሚወዳደር አይደለም።

 የዛን ጊዜ ሥራ ፈት የሆነው ወገን፤ ለስደት የታደረገው ወገን፤ ለማኝ የሆነው ወገን፤ ቤት ንብረቱን የተቀማ ወገን፤ ለራህብ የተዳረገው ወገን፤ በበቀል የተቀጠቀጠው ወገን፤ የፈረሱ ኢትዮጵያዊ ተቋማት በሙሉ ሲታሰብ አገር ፈረሶ ነበር ማለት ያስችለኛል። የባድመ ጦርነትን እራሱ ውድመት ነው የነበረው። 

ያልተነቀለ፤ ያልፈረሰ፤ ያልውደመ፤ ያልተበተነ፤ ያልከሰለ፤ ያልተዘረፈ አንዳችም ነገር አልነበረም። ስለሆነም ስክነትን ምራኝ ብሎ ማፈረስን ተጠይፎ መልካሞቹ እንዲቀጥሉ፤ መልካም ያልሆኑን በበቂ ጥናት እንዲስተካከሉ የሚደረገው ጉዞ እጅግ ሥልጡን ነው በአብይ ሌጋሲ መስመር። ከሁሉ በላይ በቀል፤ ቂም ቁርሾ እንደ መንግሥት የአብይ ሌጋሲ አለመረከቡ፤ አለመፍቀዱም ማግስትን የእኔ ማለቱን ያመሳጥራል። 

ፈተናዎችም ቢሆኑ ያኮረፉ፤ የተቀደሙ፤ ብልሃት ያነሳቸው፤ በፖለቲካ አመራር ጥበብ ያልበሰሉ ጮርቃ ዕሳቤዎች፤ በሰብዕና ልቅና የተበለጡ ምቆኞች ይህን የጥፋት መስክ መምረጣቸው የሚጠበቅም ነው። የሃሳብ አቅም የሌላቸው ስለመሆኑ ድርጊታቸው ገላጭም ነው። ቅንጅት አዲስ አባባን ተረክቦ ቢሆን የታጨለት ጥፋት ነው አሁን እዬተከወነ ያለው ... ዘር ከልጓም ይስባል ሆኖ ... 



ነገን ማጥቆር ስሌታቸው ለሆነ የኢጎ አርበኞች ዛሬ ለእነሱ መራራ ነው። ዛሬ ያላዬነውን ያላሰብነውን ቸርነት እና ደግነት፤ ከቶም እንዲህ እናዬዋለን ብለን ያለሰብነውን ተፈጥራዊነት እና ሰብዕዊነት፤ ብርቅ የሆነውን የሃሳብ ብጡልነት እና ልዩ ክህሎት እንዲህ የእኛ እንዲሆን ያደረገ አምላክ የተመሰገነ ይሁን። መጨረሻውን ያሳምርልን ፈጣሪ አምላካችን። አሜን!


ዓራት ዓይናማው መንገዳችን የአብይ ሌጋሲ ብቻ ነው!
አብይ ኬኛ!

የኔዎቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።














አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።