ልጥፎች

የገቢዎች ቀን አዲስ ጥረት በኢትዮጵያ።

ምስል
የገቢዎች ቀን አዲስ ጥረት በኢትዮጵያ። „ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን ?   እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም፦ የሰረቅንህ በምንድር ነው ? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው። ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ እኔን ሰርቃችኋልና  በእርግማን ርጉሞች  ናችሁ።“ ትንቢተ ሚልክያስ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ዛሬ አንድ ዜና አዳምጥኩኝ የገቢዎች ሚ/ር የዘጋጀው ጉባኤ ነው። በጉባኤው ላይ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ተገኝተዋል። ጉባኤውን ያዘጋጀው የገቢዎች ሚ/ር ነው። ዛሬ በነበረው የጉባኤ ባህሬ ላይ አንድ ያስተዋልኩት ቁምነገር አለ።  ዶር አብይ አህመድ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚ/ በነበሩበት ጊዜ ከእርምጃ ወደ ሩጭ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ የነበረው ሙሉ መንፈሳቸውን አይቻለሁኝ። ዘና ያለ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን እርግጠኛ የመሆን አቅሙም ያን ያህል ጉልበታም ሆኖ ነው ያዬሁት፤ በግራ በቀኝ የሚወራጨውን የማህበረ ደራጎን የተስፋ ንጥቂያ ዘመቻ እና ትብትብ ሴራ ከመጤፍ አልቆጠሩትም። እንደ ዛን ጊዜው ሚ/ር እንደነበሩበት ወቅት ቅልል ብሏቸዋል። https://www.youtube.com/watch?v=vu-kkIUohRw&t=76s Ethiopia - Dr Abiy ኢትዮጵያን ማሸጋገር ይቻላል ! ከራዕያቸው ለመድርስ በሚያደርጉት ጉዞም አሸነፊ ሆኖ የመውጣት መንፈስ ልክ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ በነበረው አቅም ልክ ነው እኔ ያዬሁት -ዛሬ። ሁልጊዜም እኔ እንደምለው ንግግሩን ብቻ ሳይሆን የሰብዕን ውስጣዊ መንፈስ ለማግኘት ወደ ውስጥ ሰርስሬ ማዬትን ነው ምርጫዬ። ዛሬ የሰጠኝ ግብረ ምላሽ በጠ/ሚር አብይ አህመድ በኩል የመንፈስ ሙሉዑነት እና የለውጡ በሁለቱ እግሩ የመ

በተባረከ ማዕልት እልልታ ይድመቅ። ፍንድቅድቅ ፍልቅልቅም ይበል!

ምስል
በተባረከ ማዕልት እልልታ ይድመቅ። ፍንድቅድቅ ፍልቅልቅም ይበል! „ለቤቱ በዓይነ እርግብ የተዘጉ መስኮቶች አደረገ። በቤቱም ግንብ ዙሪያ በመቅደሱና በቅድስተ ቅዱሳኑ ግንብ  ዙሪያ  ደርብ ሠራ፤ በዙሪየውም ጓዳዎች አደረገ፤“ መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ፮ ከቁጠር፭ እስከ ፮  ከሥርጉተ© ሥላሴ Sergute©Selassie  20.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ·         የእልልታ ዕለት መነሻ … https://www.youtube.com/watch?v=lDymVE596Jc ዶ / ር አብይ ወልቃይትን የአማራ የሚያደርገውን አዋጅ አፀደቁ Ethiopia Abiy Ahmed     የህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ረቂቅ ዓዋጅ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ / ዛሬ ። በ33 ተቃውሞ በ4 ድምጽ ተዕቅቦ። በጉባኤው ላይ የተገኙ 350 አባላትም ነበሩ። ረቂቅ ዓዋጁ የጸደቀው በ317 ድምጽ ነው። ተመስገን ከእልልታ ጋር ክብር ለእሱ ለአማኑኤል ይሁን። አሜን! ·        ዛሬ ለታላቋ ትግራይ ህልመኞች ሌላ የመርዶ ቀን ነው።  ለእኛ ግን የኢሰብአዊነት አወራሪሱ የማህበረ ደራጎን ዘመን ግብዕት ስለሆነ እንላልን እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል። ሰው ገድሎ፤ አሰቃይቶም፤ ሰላምንም ነስቶም፤ ዘርፎም፤ ወሮም ለማይደከመው ብቻ ሳይሆን ደልቶት መኖርን ለተመኘው የህውሃት ህልም ዛሬ ደግሞ ሌላው የምሾ ቀኑ ነው። ለእኛ ደግሞ የሐሤት ቀናችን እልልታ ነው! እንግዲህ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የማንፌሰቶ ማህበርተኞች የልሳናቸው መክፈቻ ህገ መንግሥት ተጣሰ ነውና ይህንንም በ317 ድምጽ ያጸደቀውን ፓርላማው የህግ ጥሰት ፈጸ

የግርግር ፖለቲካ ግብዕቱ ተፈጽሟል።

ምስል
የግርግር ፖለቲካ ግብዕቱ ተፈጽሟል። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 20.12.2018  ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ·        መቅድም። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ ቅኖቹ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? አላዛሯ ኢትዮጵያ ከምትታመስበት መከራ አንዱ በግርግር ፖለቲካ ነበር። በግርግር ፖለቲካ አቅም አላግባብ መባከኑ ብቻ ሳይሆን፤ በገፍ ተጨፍለቀው ወይንም ተደፍጥጠው የሚቀሩ ቅኖችን  ዘመን ሲያስተናግድ ኖሯል በድል አጥቢያ አርበኞች።    ·        እፍታ። በአንድ የግርግር ማዕቀፍ የሚነሱ ሃይሎች የሰከኑ ጉዳዮችን በአሉታ እና በማግለል የመንፈስ ጥሪትን መበከላቸው ብቻ ሳይሆን፤ የቅንነት አንበሎችን ጽልመት በማልበስ ከሜዳ ውጭ በደቦ የሚያደርጉበት ዘመን ጠገብ መከራ እንሆ ዘንድሮ አላዛሯ ኢትዮጵያ መገላገሏን መጋቢት 24 ቀን 2010  አብሯል። በጣም የዘለበው የአላዛሯ ኢትዮጵያ አሳር የነበረው፤ አውሎን የተጠለለ ውሃ ያዘለው ተራራ ማለት ያስችለኛል የግርግር ፖለቲካ ነበር። አንድ ህዝባዊ ንቅናቄ በተነሳ ቁጥር በኮፒ ራይት በመታመስ አዳዲስ ድርጅቶችን በመፍጠር፤ መንፈስ በመበተን ሲተራማስ የነበረው፤ ጭራሽ ስክነት የነሳው ወጀብ ከኢትዮጵያ የተነቀለበት አዲስ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን - ዛሬ። ዛሬ የሰከኑ፤ ደርባባ፤ በሳል የፖለቲካ ሊህቆች የግል ኢጎቸውን ሳይሆን ለ50 ዓመት የዘለቀውን የግራ ፖለቲካ የሥልጣን ጥማት ባይረስ በአመራር ብልጫ፤ በጥበብ በተዋደደ ክህሎት ተሟጦ ከኢትዮጵያ እንዲሰደድ አድርገውታል። እራፊ ትራፊ ማሳ ቢኖረው ትግራይ ላይ ብቻ ነው። የግራ ፖለቲካ መርዛማ ጭራ አገር