በተባረከ ማዕልት እልልታ ይድመቅ። ፍንድቅድቅ ፍልቅልቅም ይበል!

በተባረከ ማዕልት እልልታ ይድመቅ።
ፍንድቅድቅ ፍልቅልቅም ይበል!

„ለቤቱ በዓይነ እርግብ የተዘጉ መስኮቶች አደረገ።
በቤቱም ግንብ ዙሪያ በመቅደሱና በቅድስተ ቅዱሳኑ
ግንብ  ዙሪያ  ደርብ ሠራ፤ በዙሪየውም ጓዳዎች አደረገ፤“
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ፮ ከቁጠር፭ እስከ ፮

 ከሥርጉተ© ሥላሴ
Sergute©Selassie
 20.12.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ


  • ·        የእልልታ ዕለት መነሻ …

/ አብይ ወልቃይትን የአማራ የሚያደርገውን አዋጅ አፀደቁ Ethiopia Abiy Ahmed

 

 

የህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ረቂቅ ዓዋጅ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ / ዛሬ። በ33 ተቃውሞ በ4 ድምጽ ተዕቅቦ። በጉባኤው ላይ የተገኙ 350 አባላትም ነበሩ። ረቂቅ ዓዋጁ የጸደቀው በ317 ድምጽ ነው። ተመስገን ከእልልታ ጋር ክብር ለእሱ ለአማኑኤል ይሁን። አሜን!

·       ዛሬ ለታላቋ ትግራይ ህልመኞች ሌላ የመርዶ ቀን ነው።

 ለእኛ ግን የኢሰብአዊነት አወራሪሱ የማህበረ ደራጎን ዘመን ግብዕት ስለሆነ እንላልን እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል።
ሰው ገድሎ፤ አሰቃይቶም፤ ሰላምንም ነስቶም፤ ዘርፎም፤ ወሮም ለማይደከመው ብቻ ሳይሆን ደልቶት መኖርን ለተመኘው የህውሃት ህልም ዛሬ ደግሞ ሌላው የምሾ ቀኑ ነው። ለእኛ ደግሞ የሐሤት ቀናችን እልልታ ነው!

እንግዲህ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የማንፌሰቶ ማህበርተኞች የልሳናቸው መክፈቻ ህገ መንግሥት ተጣሰ ነውና ይህንንም በ317 ድምጽ ያጸደቀውን ፓርላማው የህግ ጥሰት ፈጸመ እንደሚሉት ልብ ልክ ነው። 

ህግ ጥሰው፤ እንደ ለመደባቸው በረት ገልበጥው የግል ነጻነት ተጋፍተው ጎንደርን የኮ/ ደመቀ ዘውዱን መኖሪያ ቤት እና አካባቢውን ቀውጤ ያደረጉትን ሐምሌ 5 ሆነ ከዛም አልፈው ተርፈው ቤንዚን እና ክብሪት አስይዘው ሽፍቶቻቸውን ልከው የጎንደር ከተማ የተፈጠረችበትን ሚስጢር ቅዳሜ ገብያን  ሲያነዱ ይህ የህገመንግሥት ጥሰት አይደለም ለእነሱ። 


ለነገሩ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፈሴቶግር ብረት ነፃ የወጣው የህዝብ ተዋካዮች ጉባኤንም በዚህ አጋጣሚ እንኳን ለዚህ አባቃችሁ እላለሁኝ።

አደብ ለገዛ፤ እዮባዊነትን ለሰነቀ፤ እንደ ጤፍ ጠላ ከላይ ከላይ ለማይፈላ መንፈስ፤ ስከነትን ታቦቱ አድርጎ ለከበከበ ሰብዕና ፈጣሪውን/ አላህን ላከበረ የእግዚአብሄር ፍጥረት  እንዲህ ሰብልን ማዬት ይቻላል። ለዚህም ነበር እኔ ባላፈው ዓመት ወጀብ ሲጠና እዮባዊነት በእጅጉ ያንሰናል ስል የጣፍኩት። ሳተናው ላይ ያለ ይመስለኛል መጣጥፉ።

ወንዞቹ፤ ተራሮቹ፤ ሸንተረሮቹ ሁሉ ትንፋሽ አገኙ። ወረራ፤ ዝርፈያ፤ ቅሚያ፤ ሌብነት ሁሉም „ጊዜ ገብሪ ለእግዚአብሄር“ ነውና እንዲህ እርቃናቸውን ይቀራሉ። ዛሬ ታላቅ የተጋድሎ ቀኑ ነበር ለህዝብ ተወካዮች የኢትዮጵያ ፓርላማ። ተጋድሎውን በድል አጠናቋል - ፓርላማው። ተመስገን። ይህ ልዩ ዕጹብ ድንቅ ታሪካዊ ቀን ነው።

ውይይቱ፤ ፍጭቱ ሙጉቱ ይበል ብለናል። 33 ተቃውሞ መኖሩን እኔ ወድጄዋለሁኝ። 4 ድምጽ ተዕቅቦም እንዲሁ ተምችቶኛል። ዴሞክራሲ እንዲህ ነው የሚወለደው እና። የሚመቸው ሃሳብ ከማይመቸው ሃሳብ ጋር ተሞግቶ አሸናፊው ሃሳብ በተሸናፊው ሃሳብ ላይ አቅም ኖሮት፤ የሃሳብ ልቅናው ጎልቶ የራዕይ ብሰለት እንዲህ ሲረታ የልብ ያደርሳልም። ጀግኗል የኢትዮጵያ ፓርላማ።

እራሱ የተቃውሞው ድምጽ፤ የተዕቅቦ ድምጽ ለእኔ የሐሤቴ ምንጭ ነው። ይህ የረቂቅ አዋጅ ጽድቅነት ላሰተዋለው ሰው የማግሥት የራዕይ ጽጌረዳዊ ኩላሊቱ ነው። የማግሥት የትውልድ ተቻችሎ የመኖር ሥህኑ ነው። የነገ ነፍሱ ነው።

ከሁሉ በላይ ዘረፋን የሚጠይፍ ትውልድ ለመገንባት አብነት ነው። ሂደቱ ራሱ ሙግቱ ጦፎ መከወኑ መምህር ነው። የተቃወሙትም፤ የደገፉትም፤ ድምጽ ያልሰጡትም በራሳቸው ፍላጎት ውስጥ ያላቸውን ጽናት ያሳያል። ይበል ብለናል።

የእኔ የራሴ ሃሳብም ቢሆን ሞጋች ሞግቶኝ የሞገተኝ ሃሳብ እንዲያሽነፈኝ ፈቅጄ ነው ሙግቱን አህዱ የምለው። ስወጥነው ልሸንፍም ላሸንፍም ስለመሆኑ በህሊናዬ ዕውቅና ሰጥቼ ነው።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሊሂቃን ይሁኑ የሚመሯቸው ተቋማት በሙሉ ትልቁ ችግር ይህ ነው። እንሸነፋለን፤ ብንሸነፍ መሸናፋችን በጸጋ እንቀበላለን ብለው አይጀምሩም። ሁልጊዜም እናሸንፋለን፤ ድል እናደርጋለን ብለው ጊዜ፤ ወቅት፤ ማህበራዊ ንቃተ ህሊና
 እንደ ቧንቧ ውሃ የሚከፈት እና የሚዛጋ አድርገው የማሸነፊያ ጊዜያቸውን ሁሉ ወሰነው ትግልም የሚጀመሩ አሉ።

ለማሸነፍ በሚደረግ ጉዞ ብቻ አይደለም መጠበቅ ያለበት፤ መሸነፍም እንዳለ፤ የባሰም ማህል መንገድ ላይ ተቋርጦ መቅረትም እንዳለም አስበውት አያውቁም። ፈጽሞ! ዛሬ ይህ ዘመን ግን ሁሉንም ቁጭ አድርጎ እዬገራ ነው። ተመስገን። ግሪቱ ደግሞ የነቃውን ህሊና ነው።

ይህን አጥተን ነበር የኖርነው፤ የሞገተ እንደ ጠላት ነው የሚታዬው። ተቃውሞ ፊት ለፊት የሚወጣ ነፍስ በረድ ይለቀቅብኝ ሲል ወስኖ ነው። አንድም እኔ ነኝ ያለ ተፎካካሪ/ ተቃዋሚ / ተቀናቃኝ ፓርቲ በዚህ ህይወት ውሰጥ አላለፍም። እራሱ ውጭ አገር።

ከሰማዬ ሰማያት የወረዱ ባለ6 ባለክንፎች በሚቀይሱት መስመር ብቻ እንዳወረዱለት  መጭ ነው። ሞግቶ የሚወጣ የለም። ሲወድቁ አልወደቁም ተብሎ ሙግት አለበት። ባዶ እጃቸውን ሲቀሩ አሸናፊ ናቸው ብሎ ፉከራም አለበት። ስለምን? ዴሞክራሲ በሦስት እጥፍ ካቴና እስር ቤት ስለነበር።

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፍልስፍና ነጻ መንፈስ አለኝ ብሎ የሚናገር አንድም የነፃነት ፈላጊ ቤተኛ ሊኖር አይችልም። ሁሉም ላደረለት ፍላጎት ተጫኝ ሃሳቦችን አጽድቆ፤ አሜን ብሎ፤ እንደ ታቦት ከብክቦ ነው የኖረው። ለዚህ ነው አንድ ጊዜ ራሱን ነፃ ያወጣ ነጻነት ናፈቀኝ ስል የጻፍኩት። ትግሉ ለነጻነት ከግንበር ላለው ነፍስ ግን ነፃነት ተንፍጎ … በውክቢያ።

አሁን ተመስገን ነው። ረቂቁን ያልተቀበሉ አሉ፤ ረቂቁን በመቀበልም ባለመቀበልም ማህል ላይ የቆሙ አሉ፤ የተቀበሉ ደግሞ አሉ። አሁን ፈተናው ብዙሃን ያሳለፈውን ውሳኔ ያልተቀበሉት እና ማህል ላይ የቆሙት አፈጻጸሙ ላይ የመትጋታቸው ልኬታ የእነሱን ሰብዕና ይለካል።

ዴሞክራሲ ማለት የማይመቸውን እንዲመች አድርጎ በአተገባበር ላይ አብሮ እንደ እራስ ውሳኔ አድርጎ መትጋት ነውና። የተቃወሙት እና ድምጸ ተዕቅቦ ያደረጉት የፖለቲካ ፍልስፍና ብቃታቸው የሚለካው በዚህ ላይ ነው። ይህ የመንፈስ አቅምን እራሰን የማሸነፍ ግብግብ የሚፈጥር አመክንዮ ነው።

ሚሊዮኖች የደገፉት የአብይ ሌጋሲ እንደ ህውሃት ተቃውሞ የወጣው የአቶ ዳውድ ኢብሳ ድርጅት ችግሩ ይህ ነው። ግን ለዴሞክራሲ እታገላለሁ የሚል ድርጅት ነው። አይደለም ኢትዮጵያ መላ ዓለም እንደ ዓይኑ ብሌን እያዬው ያለውን ለውጥ ተፃሮ በተሰወረ መንገድ እዬተጓዝ የሚሄደው የአቶ ዳውድ ኢብሳ ድርጅት ችግሩ ዴሞክራሲ ጽንሰ ሃሳቡን ራሱ ስላማያውቀው ነው።

ፈሪ ነው ለዴሞክራሲ ግንባታ። የአቶ ዳውድ ኢብሳ ኦነግ የመንፈስ ሃብታሙን፤ ዴታውን ለውጥ እወጋለሁ ብሎ ተዚህ እና ተዚያ የሚባክነው የዴሞክራሲን ልዕልና መቀበል ስላቃተውም ነው። የፍልስፍና ድህንት አብዝቶ አለበት። እንዲያውም በቢሲ አማርኛ ዜና እንዳደማጥኩት ትናንት ነፃ መሬት አለኝም አለበት።

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ፤ የፓርላማ አባላት የተቃወሙትን እና ድምጽ ያልሰጡት የዴሞክራሲ ፍልስፍና አቅማቸው የሚለካው በዚህ ዓዋጅ ላይ አፈፃፃም ላይ ያላቸው አዎንታዊነት እና የቅንነት የብቃት መጠን መለኪያውይሆናል። ተቃዋሚዎች ሆኑ ባለ ተእቅቦወች ከአኩራፊነት ወጥተው ለተግባራዊነቱ ሲተጉ ብቻ ነው የዴሞክራሲ ፍልስፋና የገባቸው ስለመሆኑ የሚፈረምበት።


ለነገሩ የዚህ ለውጥ አናት እኮ የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ ነው። የኢህአዴግ ፓርላማውን ራሱ በስልጣኑ እንዲቀጥል ተጨማሪ ዕድል የሰጠውም ነፃ ያወጣውም። ፍሬ ነገሩ ይሄው ነው።

ሌላው የዚህ ውሳኔ ብልህነት ወሳኙ ጉዳይ ይህ የፌድሬሽን ምክር ቤት የሚባለው እሾሃማው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌሰቶ የጫጉላ ቤት ጉዳይ ነው። ፈጽሞ የኢትዮጵያ ማዋዕለ ንዋይ ያለ አግባብ የሚባክንበት፤ ሃብትን መጣጭ ያልተጋባ መዋቅር ነው ለእኔ የፌድሬሽን ምክር ቤቱ። አቅሙ እና ሥልጣኑም ፈጽሞ የማይመጣጠን። መፈረስም ያለበት መዋቅር ነው እንደ ሥርጉተ ሥላሴ።

የዛሬው የረቂቅ ዓዋጅ መንፈስ ይህን መዋቀር ፈተና ሰጥቶ እንደሚለካውም እሙን ነው። ሸራርፎልኛል። ኢትዮጵያ ብልህ ሙሴ አግኝታላች የምንለውም ለዚህ ነው።
  
አሁን በቀጣዩ ምርጫ ተፎካካሪዎች/ ተቀናቃኞች/ ተቃዋሚዎች ውድድር አድርገው በፓርላማ የመወከል ዕድል ሊኖራቸው ይችላል፤ በፌድራል ምክር ቤት ግን እንዴት ብለው ሊወከሉ ይሆን? ይህ የፊት ለፊታችን ፍጣጫ ነው። ምክንያቱም የፓርላማ ጭንቅላት ያለው ከዚህ የፌድራል ምክር ቤት ከሚባለው ነውና።

አወካከሉም አደረጃጀቱም የወያኔ ሃርነት ትግራይን ፖለቲካ በበላይንት ለመጠበቅ የተደራጀ የነፃነት ነቀርሳ ነውና። ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ትልቁ እንቅፋት ይኽው መዋቅር ነው። የፌድሬሽን ምክር ቤት ከምለው የፌድሬሽ መርህ መቃብር ቤት ብለው ይሻለኛል። እንቅፋት ነውና።

የሆነ ሆኖ ዛሬ ልክ እንደ መጋቢት 24 ቀን 2010 ቀን የድል እለት ነው። ራሱ ረቂቅ ህጉ መጽደቁ ለውጡን በሁለት እግሩ ያቆመዋል። ሰፊ የመንፈስ ሃብትንም ያጎናጽፋዋል። ማህል ላይ የነበሩ፤ መሬት ላልያዙ ተጠራጠሪ መንፈሶችም ዋስትና ሰጥቶ ከለውጡ ከጎኑ ያቆማቸዋል። ለለውጡም መታመንን አጎናጽፏል። የችግሮች ሁሉ ምንጭ ይህ ነበርና። አዲስ የተስፋ ማህደርም ነው።

ፓርላማው የተከራከረበት በረቂቅ ዓዋጁ ላይ ነው። ራሱ ህገ መንግስቱ እንደ ሽፋን ቀርቧል በተቃዋሚዎች፤ ህዝብ አልፈልግም ካለ እኮ ህገ መንግሥቱ ራሱ ይለወጣል፤ ህገ መንግሥት ሰው ሰራሽ ሰነድ ነው። ይሻራል፤ ይሻሻላልም ወዘተ … ነገ ራሱ በራሱ ጊዜ ይህን ያደርጋል። ይህን ደፈሮ ልብን ሰፋ አድርጎ መጠበቅ ግድ ይላል። ይህም ብቻ አይደለም ውክልናም እንዲህ በግብር ይውጣ ከእንግዲህ አይሆንም በህዝብ ብዛት ነው ውክልና የሚኖረው 5% ይዞ እኩል ፊጢጥ ማለት አይቀጥልም። 27 ዓመት ተቀልዷል።

ይህ ዘመን እኮ ያን የ100 ዓመት ህልም ቅስሙን እንኩት አደርጎ የወያኔ ሃርነት አውራሪሶችን ትግራይ ትግራይ ላይ አስቀምጦ ምሾ ደርደሪ አደረጋቸው እኮ። እዮባዊነትን ለሰነቅ ሁሉንም ልክ ለማስያዝ የማይችልበት ምንም መንገድ የለም። ራሱ ይህ ፓርላም ነገ ለመቀጠል ወሳኙ ህዝብ ነው።

ነገ የኢትዮጵያ ፓርላማ እንዲህ ወጥ በሆነ ሁኔታም መጪነት የለም። ህብረ ቀለማት
 ያለው ይሆናል - ተፎካካሪ/ ተቃናቃኝ/ ተቃዋሚወችም አብረው የሚታደሙበት፤ ጎን ለጎን አብረው እኩል ተቀምጠው የሚወስኑበት፤ የሚመክሩበት፤ የሚዘከሩበት ዘመን አይቀርም። መንገድ ተጀምሯል።  

የነፃነት ታግድሎው ሚስጢረ ክህሎት እና ግቡ ይኸው ነውና። የወያኔ ሃርነት ትግራይ የበላይነትን ማስከተም የህዝቦችን የበላይነት ማስከበር ነበር ጥማታችን። እናም እየሆነ ባለው መልካም ነገር ሁሉ ተመስገን ብለናል።

የአመራር ጥበብ በጉልህ በሚታይበት የአብይ ሌጋሲ አዲስ ቃና በአዲሳዊነት ፋና እያበበ ነው። ተመስገን።

ዓራት ዓይናማው መንገዳችን የአብይ ሌጋሲ ብቻ ነው!
የፌድሬሽ መቃብር ቤት ደግሞ ፈርሶ ያሳዬን። አሜን!

የኔዎቹ ክብረቶቼ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።