#የእምዩ ሲዊዝ ብሄራዊ ቡድን የአልጀርያን ብሄራዊ ቡድን ሁለት #ለምንም ሸኙ። #ሲዊዝ 2: #አልጀሪያ 0

 

#የእምዩ ሲዊዝ ብሄራዊ ቡድን የአልጀርያን ብሄራዊ ቡድን ሁለት #ለምንም ሸኙ።
 
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 May be an image of soccer, football and text
 
የፊፋው ፕሬዚዳንት በተገኙበት በአውሮፓውያኑ ሰዓት አቆጣጠር ከንጋቱ 11.00
ሰዓት በካናዳዋ አንኮበር ከተማ የተካሄደው ጨዋታ በሲዊዝ #አሸናፊነት በመደበኛ
የጨዋታ ጊዜ ውድድሩ ተጠናቋል።
 
የአልጀሪያ ቡድን እንደ ጣሊያን ቡድን #ጉልበት ቀመስ ነበር ማለት ልቻል። ሲዊዛውያኑ
ደግሞ እንደሚታወቀው #ጨመት ያሉ ናቸው። ግፊያውን ችለው ጨዋታውን #በዲስፕሊን ከውነዋል።
ልክ #በ10 ደቂቃው የገባችው ጎል ተጨማሪ ጎል አስከትላ ሲዊዝን ለቀጣዩ የዙር ጨዋታ #አብቅተዋል
በዛሬው ጨዋታ የግል ጥረት እና የወል ጥረት የተዋህዱበት ነበር። አዲስ ተጫዋች ቁጥር 7 በጣም
ቅንነት ያለው ነው። ዕድሎችን በማመቻቸት ረገድ ቅንነቱን አይቻለሁ። ፈጣንም ነው።
 
የሲዊዝ ቡድን ያሳየው #ጥንካሬ ገርሞኛል። በጣም ለውጥ አላቸው። ስጋቴ የነበረው ጎል ጠባቂው ከቦታው
በጣም #ይርቅ ስለነበር ነበር። እንደ ፈረንሳይ፤ እስፔን ያሉ ቡድኖች እንዲህ ዓይነቱን ዕድል በጣም ይጠቀሙበታል።
ስለዚህም የሲዊዝ ብሄራዊ የእግርኳስ ቲም በር ጠባቂ ብዙም ከጎሉ አካባቢ ባይርቅ ለቀጣዩ ጨዋታ ጥሩ ይመስለኛል።
የአልጀሪያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቲም ጥሩ ተጫውተዋል። ብዙ ሞክረዋል። 
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie.
03/07/026.
 
#ኳሲዝም ይለምልም። አሜን!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።