"የደርሶ መልስ ፊልም" በሚመለከት የእኔ ዕይታ።

„የደርሶ መልስ“ ልቅና!
በእኔአቅም ልቅም ቅኝት።
„ጥበብ ቤትዋን ሠራች፣ ሰባቱንም ምሰሶችዋን አቆመች 
 (ምሳሌ ፱ ቊጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23.12.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


                                                                        ቅኔያዊት!


  • ·        ፍታ።

እንዴት ናችሁ ውዶቼ ክብረቶቼ።

„ደርሶ መልስ“ በሚል እርዕስ በሁለት ምዕራፍ ወደ 28 ክፍሎች በፋና ቴሌቪዥን የቀረበ ተከታታይ የቴሌቪዥን ፊልም ነበር። ፊልሙ ከተለመወደው ወጣ ያለ ጭብጥን በምናዊ ርቀት በቅጡ የቃኜ ሆነው አግኝቻለሁኝ እኔ በግሌ።

ሙሉውን ወደ ሦስት ጊዜ በጥሞና አይቸዋለሁኝ። እርግጥ ነው ለመዝንኛ ብቻ ልታይ ከተባለ፤ ወይንም ወጣ ገባ እያሉ ለማዬት ከታሰበ፤ ስለ ነፃነት ህሊናዊነት ካልተሰነቀ ጭብጡ መከበድ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ፊልሙን የማዬት ሃሞትም ፈሰስ ይልና መንፈስ ባክኖ ይቀራል።

እኔ ግን ከዚህኛው ጎራ ስላልሆንኩኝ ለፈረንጆች የልደት ቀን ጸጥታ በርጋታ ስለሚሆን በዬዘመኑ ይህ ቀን ሲመጣ የመጻህፍት እርማት ሰሞናቴን አቅድ ዘንድሮ አስተላልፌ  የ2018 የመሸኛ ሰሞናትን ለ4ኛ ጊዜ እኔ በፈቀድኩት፤ በወደድኩት የሥያሜ ምርጫ „ራስመሳማን“ በተደሞ እዘልቃዋለሁኝ …

ተቀጣጠርን። ቀጠሮም ሰዓትም ለዛውም በፍጽምና አክባሪ ስለሆንኩኝም ዝንፍ፤ ወትልፍ ሳልል እንገናኛለን፤ ደግመን እንተያዬአለን። የነገ ሰው ይበለን አማልካችን እኔና አቤቶ የቤት ውስጥ ዘንከትክት ብሎ ፊት ለፊት ጉብ ያለውን ደመ ግቡ ቴሌቪዥኔ ጋር። አይቀሬ ነው መደገሙ .. ለአርባዕቱነት …
  • ·        ልሰት ስለፍለቁ ቅኝቴ መዋደድ …

እንዲህም ልባል …
ደጋግሜ ለማዬት ያሰገደደኝ መሰረታዊ ምክንያት የዴርቶ ጋዳን መስመር የተከተለ፤ ርቁቅ ምናብ ያለው ልበ ወለድ ስለሆነ ነው። ምናባዊ አቅሙ ልዑቅ ነው። የተዋናዮች አቅምም ጉልበታም ሆነ አግኝቻለሁኝ። መጽሐፍ እያነበብኩኝ የማዬው ያህል ናፍቆኝ፤ ወድጄው እና አክበሬው ነው የተከታተልኩት። በ እጅጉ ሳይገናን የረካሁበትም ፊልም ነው።


እኔ እንዲያውም እርእሱ የተለመደው „ደርሶ መልስ“ አባባል ዘይቤን ከሚከተል ያልተለመደውን ረቀቅ ያለውን  ሥልጡን ትውፊተኛ ጸጥተኛውን አባ ትዕግስትን፤ የጭብጡን የሎጎ ስያሜ „ራሥመሳምን“ ፊደሎቹ ሳይነጣጠሉ በአህትዮሽ እንደ አንድ ቃልም፤ ሥንኝም፤ ሐረግም ወሰዶ ቢሆን ኖሮ እጅግ ጉልበታም የሆነ የማጓጓት አቅም ይኖረው ነበር። ያልተለመደ ርዕስም ይሆን ነበር። ለማለት ሳይሆን ራሱን የሆነ በሆነው ውስጥ ለመኖር የፈቀደ … ስለሆነ ለ እርሱ ጭንቅ ጥብብ ሊባልለት ሰለሚገባም።

„ደርሶ መልስ“ የሚለው ሥያሜ ግን የጭብጡን መጀመሪያም መጨረሻም ፍንጭ ሰጪ ስለሆነ፤ የተለመደም፤ ዘወትራዊ ስንኝ ስለሆነ የፊልሙን ጭብ አቅም ቀንሶታል ብዬ አስባለሁኝ - እኔው። „ራሥመሳም“ ቢባል ግን የበለጠ የጭብጡ አቅም ሥልጣኔ የክብር ዘውድ ይደፋለት ነበር። ለጭብጡ ጉልበታም አቅም ይኸኛው ሥያሜ ይመጥነው ነበር ብዬ አሰብኩኝ።

ሌላው የገረመኝ የፍጼ ልጆች ወደ አራት የሆኑ የምወዳትን ሄርሚላን ጨምሮ፤ የማከበረውን ዳኛ አሌክስን፤ ከተቋም ተዋናይ ጋር ማለትም ትውልድ ከማይተካው ከጋሼ ደቤ ጋር የመሥራት ዕድሉን ማግኘታቸው ብቻ ሳይሆን የዕድሉን አቅሙን ገብይተውታል ብየ አስባለሁኝ።



ማለትም ወጣት ታዳጊ ተዋናዮች እዬተማሩ ነው ፊልሙን የሠሩት ማለት ያስችለኛል። እዚህ በገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ አገር ወጣቶች በዕውቀት፤ በሙያ እዬሰለጡን በመደበኛ ሥራ ተመድበው ደግሞ ይሠራሉ። ቀለማዊ ዕውቀቱን በማሰልጠኛ ተቋማት፤ በሳምንት የተወሰነ ቀን እዬተማሩ፤ በህዝባዊ አገልግሎት ደግሞ አነስ ባለች የድጎማ ወይንም የጉልማ ክፍያ በድርጅት ውስጥ ተቀጥረው ይሰራሉ። ቀለም ከቢሮ ተግባር ጋር ይዋህዳል ማለት ነው። ፕራክቲኩም ይሉታል። 

ስለዚህ „ደርሶ መልስ“ ለወጣት ተዋናዮች የፕራክቲኩም ዕድል በይዘት ደረጃ የሰጠ ነው ማለት ያስችለኛል። እዬተማሩ ነው የተወኑት እንደማለት። ዕድለኞች ናቸው ከጋሼ ደቤ ጋር ለመሥራት በለስ ስለቀናቸው …  


በዚህ የካስቲንግ መረጣ ላይ ያዬሁት ብርቅ እና ድንቅ ነገር ወጣቶች፤ ጎልማሶች እና አዛውንቶች በውህደት ትውፊትን የመሥራት ጥበብ። የሙያዊ አደራ ውርርስ፤ በዕውቅት እና ክህሎት የኪዳን ውርርስ፤ በልምድ እና በአቅም የውል ውርርስ ህሊና ጠገብ ተግባር በንብርብር ተከወኖበታል።ማለትም ልብ ያለው የማመጣጠን ክህሎት ዳብሮ ተገኝቶበታል እንደ ማለት።



ስለሆነም ሦስት ትውልድ አንድ ላይ እንደ አንድ ልብ አሳቢ እንደ አንድ ብልህ የዘመን መካሪ አብረው የሠሩት ስለነበር እጅግ በተደሞ መስጦኛል። እኔ የተተኪ ጉዳይ በሁሉም የሙያ ዘርፍ ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ካለኝ ምኞት ጋር የናፍቆቴን ያህል ፍሬ ነገር አግኝቻለሁ ብዬ አስባለሁኝ „በራስመሳም / ደርሶ መልስ/“ የቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም።
  • ·        ተመስጦዬን ስለግሰው …


ባልተለደመ ሁኔታ የተዋናዮቹ አቅም የተለካው ከቁንጅና ውድድር ወጣ ያለ መሆኑ ሌላው በካስቲንግ ምርጫ ላይ የነበረው ዝበት በእጅጉ የተሻሻለበት፤ እንዲያውም ሥር - ነቀል ለውጥም ክሱት የሆነበት ሁኔታን አይቸበታለሁኝ። አዲስ ተዋናይን ለማፍራት የተደረገው ጥረት በጉልህ መሬት ላይ ተመሳጥሯል። አሁን ያቺ የሻ/ ትጉህ ጸሐፊ ማህል ላይ ያለቸው ናት፤ ሰብዕናውን ስታሰተውሉት በዬቤቱ ያለው አቅም ተዳፍኖ „በደርሶ መልስ“ እግዜሩ ፈቅዶለት ፍትህ አግኝቷል ብዬ አሰብኩኝ።


እርግጥ ነው በዘመን አመጣሹ ቋንቋ ሲኬድ ወደ አንድ ብሄረሰብ ያደለ የተዋናይ ቁጥር ከፍ ብሎ ብመለከትም፤ አቅማቸውን ስመዝነው ግን ለጭብጡ ስልጡን አቅም አብዛኞቹ  መጥነው ስላገኘሁት „አሜን“ አንደሚባለው ከዚህ ቀደም እንደተቸሁት ፊልም የሙያው ሥነ - ምግባር አልመጎዳቱን፤ የተስጥኦ ወጌሻ ማግኘቱን አገናዝቤበታለሁኝ። አቅሙ ሳይኖር በፖለቲካ ውሳኔ ብቻ የጥበብ አምላክን ተፈጥሮ በመጫን፤ ካለ መክሊት ያልተገባውን ደረጃ መሰጠት ወንጀል ስለሆነ።

እንዲያውም የአህድ/የቤዛ/ የክርስቲ ሃይሌ አቅም ከጠበቁትም ካሰብኩትም በላይ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ያው የእሷ አቅም በማለዳ ኮከቦች ለአሸናፊነት ስትመረጥም የተስማማሁበት፤ የዛን ጊዜ ውሳኔውን ሳልተቸው ያለፍኩበት ምክንያት ለካሜራ ቀልብ ሳቢ መሆኗ ሰለመሰጠኝ ነበር። ካሜራ ከሚያድናቸው ፍጥረቶች አንዷ እሷ ናት። ጎረድረድ ብላ ቀልጠፍ ያለች ናት … ለካሜራ ቅኝትም ሥልጡን ናት።

አህድ ለካሜራ ደመግቡነቷ እንጂ አቅምን በሚመለከት ግን ከዛን ጊዜው ይልቅ አሁን አጎልበታለች ብዬ አስባለሁኝ። የተሰጣትን ገጸ ባህሪ በብቃት ተወጥታዋለች ብዬም አስባለሁኝ። የገጸባህሪያቱ የመለዋወጥ ባህሪን በተጨማሪ ተፈጥሯዊ በማድረግ እረገድ በዬአንዳንዱ የእሷ ክፍል ውበቱን አልቃዋለች። አዲስም አትመስልም። መክሊቱ የእውነት አላት።
  • ·        የዲያሎግ ብስለት።


በሙግቱ ሂደት ቅይጥ መጤ የቋንቋ አጠቃቀም አለዬሁም። ከጃን ሥም በስተቀር። ሌላው በዚህ ፊልም ላይ እጅግ የመሰጠኝ የዲያሎጉ ብርታት እና ብሰለት ነው። እውነት ብናገር አይጠገብም። አጠር ብሎ ከሰሞናቱ የተለቀቀ የ50 ደቂቃ ክሊፕ አለ … በምለሰት ጥቂት ዲያሎጎችን በዚህ ማሰተዋል ይቻላል …


https://www.youtube.com/watch?v=WM-T3xUcKIs&t=10s

Derso Mels: አንዳንድ የደርሶ መልስ ተእይንቶች፤


አብሶ መጸሐፍ ማንበብ ለሚወድ ፍጡር ልዩ ሥጦታ ነው ይህ ፊልም። የቋንቋው የሙግት አቅም እና ተዋናዮች ከተሰጣቸው ገጸ ባህሪ ጋር የነበራቸው የመሆን መቻል ውህደት በእጅጉ መስጦኛል። አሁን የሁለቱ አይትሞች የእመቤት መና እና የወ/ሮ አስቱ ጉዳይ ውበቱ ከጠቅላላ ጄስቸር እንቅስቃሴው ጋር ነፍስ የሚገዛ ነበር።

የሁለቱ ክውን ያሉ ጉልበታም የንግግር ጥበብ የምልልስ የሙግት የወግ ጅረቶች እንደ አይጠገቤው የምንጭ ውሃ ሲንፎለፈሎ ወይንም እንደ አባይ ፏፏቴ ሲፍለቀለቅ ቋንቋው ራሱ ሲፍነሸነሽ ይታይበታል። ከአንዱ አምክንዮ ወደ ሌላው ሲሻገጋሩ ሁለቱ አይትሞች ብቻ ሳይሆኑ ባሉበት ጭብጥም ውስጥ ሆነው እርስ በእርሳቸው ሲጠራረቡ፤ የሰውነት ገላጭ ትይንቱ ጋር ስሜታቸውን ሲዋደዱት፤ ሲፈራቀቁት፤ ሲያፋለጡ እና ሲፋሉም በስሜት የሚፈጣሩት የገባሪ ወንዞች ሄደት፤ ከጭብጡ ውቅያኖስ ጋር በመንፈስ ያጋባሉ።

የዲያሎጎች /የብርቱ ሙግቶች ሂደት መነጣጠልን ሳያሳይ ወይንም ትንንሽ ሽርፍራፊ ክፍልልፋዮችን ሳይቀነጣጥብ እንደ ተፈጥሮው እጅ ለእጅ እንደተያያዙ ሲተሙ ከጭብጡ አለማውጣታቸው ዲያሎጉን ሞናትንስ እንዳይሆን ረድቶታል።

የሙግቶች ሂደት ሆነ የታሪኩ አወቃቀር በደራሽ ገጠመኞች የተደረተ ቅጥልጥል አይደለም። ወጥ ነው መንፈሱ። በመንፈስም ተመልካቹን እዚህም አዚያ እዬወሰደ አያበትልም፤ ወይንም አያላጋም ወይንም አይሸጓጉርም። በጸጥታ እንደሚነጉድ ፏፏቴ እያስማማ ነው የሚያዋድደው … የሙግቱ ሽብሽባው ትይንቱ አትልቀቁኝ ባይ ነው - ተወዳጅ።

በንግግር ወራጅ ወንዝ ውስጥ የቃላት፤ የሥንኛት፤ የሐረጋት የጥድፊያ ጉዞ እና የእርጋት ህብረ ቀለማት እንዲሁም የፍጥጫ እና የፍልሚያ ሁነቶችን ከድምጽ ቅላጼ ቃና ጋር የሚፈጥሩት ሁኔታ ከትውናው በላይ ሌላ ተጨማሪ ትውና ተፈጥሮላቸዋል። የቋንቋ ውበት ትውናን። 

የጃን እና የአቶ ዘነበ የሙግት አቅምም የዛኑ ያህል ቀልብን የሚገዛ ነው። እንደዛ የባከነው የአቶ ግርማ ቤተሰብ እጣ ፍንታ እና ያ ያረጋ፤ ሰላም ያጣ ቤተሰብ ሳስብ ከብዙ ነገሮች ጋር ወሰዶ ዶለኝ። ጋብቻን አንሻም ብለው ወይንም ቢጀምሩትም እንዲህ ብኩን ቤተሰብ ፈጥሬ ከምባክን ብለው በጥዋቱ ትዳራቸውን በውጥኑ የፈቱ መከረኛ አንስቶች ወ/ሮም ወ/ሪትም ለመባል በመኖር ውስጥ የሚገጥማቸውን የእሰጣ ገባ ሽሽት ሳስበው ሌላ ዓለም ውስጥ ወሰደኝ።

ማለትም አላገባሁም እንዳይሉ አግብተዋል ወ/ትነት እንደ ነገሩ ተንኮላሽቷል፤ አገባሁም እንዳይሉ ወይዘሮነቱ ሳያምርበት የሎጥ ድንጋይ የሆነ ገጠመኝ ይሆንባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የማህበረሰቡ ጥያቄን ለመሸሽ ትዳር አላት/ አለው ለመባልም ተዳብለው በዬሉም የሚከዘኑ የትዳሮች ዕጣ ከዕውነት ጋር ጭብጡ ስላቆረኘን የጸሐፊዋን የልበ ህሊና ድርጁ አቅም አሳይቶኛል። ርቁቅ የሆኑ ጭብጦች ራሳቸውን ችለው በተናጠል ቢታዩ ሌላ ራሱን የቻለ የፊልም ጭብጥ ሁሉ ይወጣቸዋል ብዬም አሰብኩኝ። ብዙ በሮችን ሲከፍት በጥበብ ሃድራ ነው … ጨረሩ ...




  • ·        ም! እትጌ ነፃነት እና ፍዳዋ የተገለጠበት ጥበብ…


ሌላው የግል ነፃነት፤ የቤተሰብ ነፃነት፤ የቡድን ነፃነት፤ የማህበራዊ ነፃነት፤ የፍላጎት ነፃነት፤ የሙያ ነፃነት፤ የፍቅር ነፃነት፤ የተፈጥሮ ነፃነት በዘመናችን ብቻ ሳይሆን ራቅ ባለ ሁኔታም ያለበትን ግዳጅ እና ሞጋች ገጠሞኞችንም የፊልሙ ጭብጥ በአንድም በሌላም እንደ ኮረሪማ ቅመም የምኞት ፈቃድን መንፈስን በጽኑ ፍላጎት አስተሳስሮታል።


በሌላ በኩል ነፃነት ያለው ነፃነት፤ ነፃነቱን ያለተዘረፈ ነፃነት፤  በቀጣዩ ዘመን በምን ያህል ዕሴት ሊለካ እንደሚችል ብቻ ሳይሆን ነፃ ሳንሆን ነፃ ነን የምንለው እስከምን ድረስ ርቁቅ ስለመሆኑ አጋናዝቤበታለሁኝ።

የነፃነት ቀማኛ የሆኑ የፖለቲካ፤ የማህራበራዊ፤ ባህላዊ፤ ሙያዊ፤ ወጋዊ ወጣ ገብ ጉዞዎች በተለዬ በቤተሰብ ላይ፤ በተማላ ምስኪን ዜጎች ላይ የሚፈጥሩት የመከራ አንቀልባ ውስጡም ስላለሁበት የራሴ ታሪክ እስኪመስለኝ ድረስ በቤተሰባዊነት ነበር ፊልሙን በተደሞ ነበር የተከታተልኩት። እርግጥ ነው በግል ነፃነት ያለው ጫና መቼ ልንገላገል እንደምንችልም የህልም ያህል እርቆኛል …

እኔ ሳልሆን የፊልሙ ወጣት ጸሐፊ ልበ ብርሃኗ ማዕዛ ወርቁ በርቀት ሳይሆን እዚኸው መጥታ፤ ህይወቱን ኑራበት ሲዊዘርላንድ መጥታ የጻፈችው ሁሉ እስኪመሰልኝ ድረስ ልቅናውን ለማዬት አስችሎኛል። ውስጥን ያገኘ ጭብጥ ነው።

ልብ አምላክ የተባለው ንጉሥ ዳዊት እንዲህ የፈጣሪውን ውስጥ በመንፈስ ርቀት ጥበብ መተርጎም ስለመቻሉ ራሱም ምስብእከ ስለሆነ ነው ይህን ታላቅ ጸጋ በአምላኩ የተቸረው። በስደት የምንኖር ባተሌ ዜጎች የበኩላችን ለማድረግ በምናደርገው ጥረት ያሳለፍነውን የመከራ ዘመን፤ የነበረውን ፍትጊያ፤ ዛሬም ያላባራውን የነፃነት ቅሚያ እና የግል ነፃነት መብት ሰረቃ ሁኔታ በስፋት በዚህ የፊልም ጭብጥ አይቸበታለሁኝ። ስለሆነም ልቤ የሚለኝን ያህል መርቄያታለሁኝ ጸሐፊዋን እና ደራሲዋን ብርክተ ማዕዛ ወርቁን።

በጥቅሉ ሳዬው በሳል እና ባለግርማ ሞገስ ፕለይ ነው። በሳል ምልከታ ነው፤ ነገን ያሰብ፤ ያሰተማረ፤ ዛሬንም ያደመጠ። በሳል ምናብ ነው መድፈርን የደፈረ ለራሱም ነፃነት በገፍ የቸረ፤ ለብዕር ነፃነት ሆኖ የተኘ ልባም። ሥልጡንም ጭብጥ ነው የአምሮት የሆነ። ውብ Elegant። 



ከሁሉ በላይ ዝክርክ ያላለ ሽክፍ ያለ ክውን ነው። ተዋናዮችም ቢሆኑ እንደ ሥርጉተ ሥለሴ ዕይታ የተሰጣቸውን ገጸባህሬ አብዛኞቹ በሚገባ ተወጥተውታል ብዬ አስባለሁኝ። የገጸባህሪ አወቃቀሩ እና የታሪኩ ፍሰት ደግሞ ልብ ያንጠለጥላል፤ መንፈስን አትልቀቀኝ ብሎ ጨምድዶ ይይዛል። ከሁሉ በላይ አይረሳም።

የምናቡ ርቀት ዕውነትን የደፈረበት ወይንም ሃቅን የደረበበት አምክንዮ የፊልሙ ህሊና ነው። ይህ ትውልድን በመቅረጽ እረገድ ሰፊ ድርሻ ይኖረዋል። እንዴት?

  • ·        አንደኛው እንዲህ ራቅ ያለ ምናብ ማግስትን ለማደራጀት ፈር ይቀዳል፤

     ሁለተኛው ጸሐፈት ከተለመደው የጭብጥ ድግግሞሽ፤ ከተለመደው አሰልቺ የለብ ለብ ግርድፍ ጭብጥ ወጣ ባለ መልኩ ህይወትን በርቀት የመምራት፤ የማደራጀት፤ የማቀናጀት እና አፈንጋጭ ስሜቶችን የመግራት አቅም ለመፍጠር ናሙና ይሆናቸዋል - ለወጣት ቀጣይ ጸሐፍት።

·        ሦስተኛው የተነሳበትን ጭብጥ አለባከነው ፊልሙ። ይህም ያልተጋባ ጅረት በመፍጠር በአርቲ ቡርቲ አልታጨናነቀም፤ ይህ ምን ማለት ነው። ማንኛውም አካል መንግሥታዊ ሆነ ፖለቲካዊ በሚያደራጀው ዓላማ እና ግብ ውስጥ በዘለቄታ ለመኖር መወሰን ብቻ ሳይሆን ቆርጦ መሆንን አሰተምሯል። ወጀብ በመጣ ቁጥር ተስርቶ መፍረስን የዳጠ ፊልም ነው። 

    ይህ ሂደት ለፖለቲካ ድርጅቶችም በአንክሮ ትልቅ ነገር አሰተምሯል። አንዳንድ ጊዜ ከዋናው ጭብጥ እዬተወጣ ጊዜ ሰጥ ነገሮችን ይታከሉና፤ የግቡን ሚዛን አዛብተው አባክነውት ከንቱንትን የሚመግቡ ሁኔታዎች በተደጋጋሚ በተለያዩ ፊልሞችም አያለሁኝ። አሁን የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ጉዳይ በልተገባው ቦታ ሲዶል አስተውላለሁኝ እንደ ፈረሰኛ የወንዝ ሙለት፤ ይህ ፊልም ግን ከተነሳበት ዓላማ ንቅንቅ ሳይል በጽናቱ ውስጥ ሰክኗል፤ በወጀብ ሳይናጥ፤ ንፋስ አምላኪ ሳይሆን በራሱ ውስጥ መርጋቱ  ለአንድ ሙያ ብቻ ሳይሆን ለመጠነ ሰፊ ተቋማት አደረጃጀት እና የአመራር ጥበብን አሰተምሯል።

  • ·        ውፊትን የመጠበቅ ጽናት።


በዚህ ፊልም ጎልቶ ያዬሁት ወሳኝ ጉዳይ ትውፊታዊ፤ ባህላዊ ተፈጥሯዊ ቁምነገሮችን አትኩሮት ሰጥቷል ፊልሙ። „ራስመሳም“ በኽረ ትውፊት ነው። ሌላው ቀርቶ በተለመደው የፍቅር ጭብጥ እንኳን አቀራረቡ ለዬት ያለ መሆኑ ህይወትን በሁሉም አቅጣጫ ለመተርጎም አዲስ መንገድ ከፍቷል ብዬ አስባለሁኝ።

ከሁሉ በላይ በፍቅር አያያዝ ክህሎት ከኢትዮጵያዊነት ከበቃው እና ካሰበለው ትውፊታችን ለማፈንገጥ አለመፍቀዱ እጅግ አርክቶኛል። ኢትዮጵያዊነት ሚስጢርነቱን በጥንቃቄ በጥበብ ነፍስ ዘርቶበታል ጭብጡ። 

በፍቅር አያያዝ፤ አመራር፤ አስተዳደር ኢትዮጵያዊነት የራሱ ጥበብ እና መንገድ አለው። ኢትዮጵያዊነትን ሚስጢር ከሚያደርጉት በኸረ ጉዳዮች ይህን ተፈጥሯዊ ጸጋ ከደን ብሎ በጥንቃቄ ልቅና የሚራራው ኢትዮጵያዊነት የፍቅር አስተዳደር በተደሞው ልክ፤ ሙሉ ተፈጥሯዊ ሥነ - ምግባሩ ብዙም ሳይጣስ ነው የቀረበው። ይህ መሆኑ ሳይቆራረጥ ፊልሙን ማዬትም አስችሎኛል። ለትውልድም የሚበጅ መንገድ ነው። 

እራስን ሆኖ ለመኖር መፍቀድ ከሁሉም በላይ መርህ ነው የመኖር ብጡልነት። መንፈሴም ዓይኔም የማይፈቅዳቸው ሁኔታዎች አንዳንድ ጊዜ ሲገጥሙኝ አሳልፌ የማዬት ግዴታ ይገጥመኝ እና የሚሾልክ የጭብጥ መንፈስ ይኖር ነበር። በዚህ ዘርፍ እራሱ ተመስገን ብያለሁኝ። ቅጽበታዊ ሁኔታ ከሆነ እንኳን ሰላዬው ባልፍም ጭብጡን ለማያያዝ አልቸገርም፤ ብዙም አያመልጥም ትንሽ አለፍ አድርጌ ስመለከተው … ታሪኩንም ለመከታተል አልቸገረም ...

  • ·        ግነትን ስለመጸዬፍ።

በዚህ ፊልም ያዬሁት መልካም ነገር ግነት የለም፤ የአነጋገር የእንቅስቃሴ የጩኽት ሁከት የለም፤ ሰውኛ ያልሆኑ፤ ቅልቅል ያሉ፤ ወይንም ድንዝዝ ያሉ፤ ወይንም ከተፈጥሮ ውጭ የሆኖ የአካልም የድምጽም አወጣጥ፤ የሰውነት እንቅስቃሴዎች አላዬሁም። በፍጹም ሁኔታ ተፈጥሯዊ ነው።

እራሱ የፊሽ የስካር ሂደት እንደ ሥካር ተፈጥሮ ስለከወነው የዕውነት እንጂ በግነት የዘለበ አይደለም። ከስካር ተፈጥሮ አፈንግጦ እና ተጋኖ የወጣ ነገር ፈጽሞ አላዬሁበትም፤ እንዲያውም በፍቅር እና በታማኝነት መጉደል ማህል የተፈጠረው የታሪክ ግጭት በውን ያዬሁበት አጋጣሚ ነበር። 

ሰው ለህሊናው እንዳይኖር፤ በሌላ አካል ተጽዕኖ ነፃነቱን ሲገፈፍ የህሊናውን ዳኝነት ለመሸሽ በሚያደርገው ግብግብ የተፈጠረው ስብቃ እና ውጤቱ ራስን የፈተነ ስለመሆኑ አሳምሮ አስነብቦኛል፤

በዚህ ሂደት ተጨማሪ መጠጊያ ፍለጋ ሌላ መሸሸጌ ተዳባይ ተቀጥላ ባህሬ እንዲሁም የ አዲስን ፍቅር ልሙድ ለማደረግ የተፈጥሮ የፍቅር ጉዞ ሂደት በራሱ የፈጠረው ፍልሚያ ሌላ የተውኔት ግንባርም አሳይቶኛል፤ ራሱን አስችሎ ሌላ ፊልም ለመስራት የሚያስችል ፍንጭ ወይንም ጭብጥ አመላካች ስበት ነበረው ማለት ያስችለኛል …

  • ·        ካላዊ የብቃት ትይንት አስተምኽሮ፤


በንግግር ጥበብ ሆነ በትውናም ተፈጥሯዊ የሆኑ አካላዊ የስሜት መግለጫ ገፀ ባህርያት ወሳኝ ድርሻ አላቸው። ስሜትን ገርቶ ወደ ተፈለገው አቅጣጫ ለመምራት ሆነ በታሪኩ ውስጥ በተመስጦ ለማቆዬት። ከሁሉ በላይ በዚህ ፊልም የተገነዘብኩት ዋንኛ ጉዳይ የገጽን ድርሻ ራሱ ሙሉ የተውኔቱ ቤተኛ የማድረግ አቅም አንቱ ሆኖ አግኝቻለሁኝ።

ገጽ ብቻ ሳይሆን የአገላለጽ ዘይቤው ራሱ „ነው!“ ያለው የጋሽ ደቤ ቃና ሆስፒታል ላይ ፍጹም ልዩ ተፈጥሯዊ መስህብ ነበረው። እንዴት አድርጎ ጣል አድርጎ ዜማዊ ቅላጼዎችን ክብር እንዳጎናጸፋቸው ከመኖር ጋር በነበረው የቃላት ምልልስ ትወና ላይ ተከስቷል። ልዩ ነበር። የድምጽ ምቱ እና ቃና ከገጽ ጋር የነበረው ውህደት የተውኔት ጽላት የመሆን አቅሙ ጉልማ ሳይሆን ጉልት ነበር ለእኔ። 

በሌላ በኩል የአሌክስ፤ የመኖር፤ የሻ/ ትጉኽ ፤ የግርሜ፤ የሰናይ /መኖር ቆፍጠን ያለ ገጽ እና ድርጊት በራሱ አንድ ድርሳን ነው - ለእኔ። እኔ ይህን ፊልም አያዬሁ ታዋቂዋ ጸሐፊ አጋታ ክርስቲ ነበር ትዝ ያለችኝ። በልጅነት እጅግ አድናቂዋ ነበርኩኝ። እዚህ ሲዊዝ የህፃናት ጋዜጠኛ ጓደኛ አለችኝ፤ እና እሷ ደግሞ ሞጋች ነገሮችን እያነሳች ፍቅሬን በተወሰነ ደረጃ ብትቀንሰውም አጋታ ዋና የጭብጧ ፍሬ ነገር ሴቶችን የማይታመን ተፍሯዊ አቅም የመስጠት ልቅናዋ እኔ እንደ ሴቶች መብት ተቆርቋሪ ተሟጋችም ስለማያት አሁን እማከብራት ብቻ ሳይሆን እምወዳት ጸሐፊ ናት አጋታ ክርስቲ።

በዚህ „የደርሶ መልስ“ ፊልም የምናብ ርቀት ሆነ የታሪክ አወቃቀር፤ እንዲሁም ለሴቶች ጉልበታም አቅም ለመስጠት ጸሐፊዋ ወጣት ማዕዛ ወርቁ የሄደችበት እርቀት የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ጸጋ ሳትለቅ የአጋታን መሰመር የተከተለች ይመሰለኛል።

ደግሞ በቁልፍ ጉልበታም ተውኔት ክርስቲም ሥሟ እና የተሰጣት ገጸ ባህሪ ቅመም ነገር በሆነ ሁኔታ ተዋዷል ከአጋታ አባት ነፍስ ጋር፤ እና እኔ በሁሉገብ ሁኔታ የፊልሙን ነፍስ ሳዬው ህሊናዬን ለመቆጣጠር፤ ፍቅሬን ሆነ አክብሮቴን ለመግለጽ አቅሙ ሙሉ ነበር።
  • ·        ልገባኝ።


ሌላው ሳይገባኝ ያለፈው ነገር የግርምሽ ቤተሰብ ቤት ሲለቅ እዛው ለዛው ስለሆነ ተሎ የሚደረስበት መሆኑ ትንሽ ከዕውነት ጋር አልገናኝልኝ አለ።

ሆቴሉም ሆነ የአባቱ ቤት እመቤት መና የምትኖርበት ከቀደመው መኖሪያ ቤታቸው አልራቀም። ትንሽ ከዚህ ላይ ርቀታዊ ምልከታ በቴክኒክ ቢስተካካል መልካም ነው። አልሸሹም ዞር አሉ ሆነብኝ። ትንሽ የቀደመውን ቤታቸው እና ጎረቤታቸው ጋር የነበረውን ሁኔታ ለማሳዬት ረዘም የለ ጉዞ እንደሚያስፈለገው ቢሆን መልካም ነው።

በተጨማሪም የግርምሽ ባለቤት አስቱ ሥራ እንዳላት ይገልጽና፤ ግን አንድም ቀን ቢሮ ታይታ አትታውቅም። አዬር ላይ ተንሳፈፈበኝ ይህ የጭብጥ ክፈለ አካል። እርግጥ ነው ለእኔ የሰጠኝ ግብረ ምላሽ ደርባባዋ - ንቁዋ - ጠንቃቃዋ ሴት አስቱ በሌላ የደህንነት ተግባር የተሰማራች ስለመሆኑ ጥቂት ቅርጥምጣሜ ዝንባሌ ቢፈጥርብኝም ታሪኩ ግን መደበኛ የሥራ መስኳ ተንሳፋፊ ሆነብኝ። በጭብጡ ላይ የቤት እመቤትነት ገፀ ባህሪዋ ነው የታዬው፤ ለዛውም ጓዳ ጉድጉድ ስትል ደግሞ አትታይም … ታሪኩ ተቀጣሪ ሰረተኛ አድርጎ ግን ጭብጡ የቤት እመቤት ዓይነት ገጸባህሪ ተጫነው  … ይህን ስል ሁሉም ነገር አንድ ባንድ ይቀርብ ማለቴ አይደለም ግን ተቀራራቢ ምክንያታዊ ሰንሰለት ቢፈጠርለት ... 
  • ·        ግጭት መናህሪያ ቃናዊ አንጠልጣይነት ...


በዚህ ታሪክ ውስጥ ታላቅ እህት እናትም ናት የሚለውን በውን እንዲህ ባይም፤ 


እናት እናት የመሆን ተፈጥሮዋን የሚሻሙ ነገሮችም አይቻለሁኝ። ግጭት ልበለው ይሆን?ተፈጥሯዊ እናትነት አዛኝነት እና ልጅን ሽፍን አድርጎ መያዝ አለ፤ ይህን ማዬት ችያለሁኝ። ነገር ግን የግል ተፈጥሯዊ ሰብዕና የአስቱ የአለቅነት የተጫኝነት ስለሆነ እናትነት ተፈጥሮውን ኮርኩሞት አይቻለሁኝ።

በዚህ ውስጥ ሰው ሆነን ተፈጥሮዊውን ሁነት በሰብዕና አገናብብ ላይ በሚገጥሙ የአስተዳደግ፤ የውርስ፤ ወይንም አካባቢያዊ ተጽዕኖ የሚመጡ ተዳራቢ ባህሪዎች በዋናው ተፈጥሮ ላይ ያላቸውን የገዢነት ባህሪ አይቸበታለሁኝ። ስለሆን ግጭቱ ቀላል አልነበረም … እና የእያንዳንዱ ሰብ የግል ተፈጥሮ በሚያስገድገዳቸው ጉዳዮች ላይ የሚገጥሙ  ፍልሚያዎች አዲስ የጦር ግንባር ወይንም ቀጠና በዬጊዜው እዬፈጠሩ አፋትጎናል … ሞግቶናል ተመልካችን …

እንደ እናትም በመሆን ልጆች ባጠፉት ጥፋት ልክ ልጆችን ለህግ ለማቅረብ አለመፈቅድ፤ ህግ ጣሽነትን፤ ህግ ተላላፊነትን፤ በሌላ በኩል ደግሞ የሰብዕና አዎንታዊ ኢጎ ተጫኝነት ተፈጥሮ  በዕውነት መህደር የሚያደርጉት ግብግብ፤ የገጠማቸው ፍጥጫ ሌላው የታሪኩ አጓጊ ገጠመኝ ነው። 

እናት መሆን በመቻል እና እናት ለመሆን ባለመፍቅድ መሃከል ያለው የሃላፊነት ደረጃ ልዩነት እና ውሳኔ በሰብ ሰብዕና ተጽኖዎች ሲያይዙት ምን እንደሚመስል ያዬሁበት እሰጣ ገባ ልብ ቢሸለመው አይበዛበትም።

ፈቅዶ እናትነት በመቀበል ግን እናትነቱም የተገባውን ተልዕኮ ለመወጣት አቅም አንሶት፤ ልጆች ባክነው ሲቀሩ፤ ሚስትነት እና የጉርብትና መሰል የትዳር ኑሮ በቤተሰብ አገነባባብ ብቻ ሳያሆን በትወልድ ቀረጻ ላይ የፈጠረው የተስፋ ድርቀት፤ በሌላ በኩል ይህን ለመሸሽ ሳያገቡ የሚቀሩት አንስቶች የውሳኔ ቁርጠኝነት እና ለእነሱ ወሳኔ ከቤተሰብ ጀምሮ ማህበረሰቡ ያለው ምልከታ ገዳዳነት፤ ተፈጥሮ እንደነፍጋቸው አድርጎ የመመልከት መከራን በጽኑ ሳዬው የሴቶችን ውስጥ የሚቀኙ ንጥረ ነገሮችን ማዬት አስችሎኛል።

 የግጭቶች የፍላጎት የስክነት የውሳኔ ዳገት እና ቁልቁለት፤ የቁርጠኝነት ቀጣይነት እና ግብብግብ ግጭቶች፤ የግብ መዳረሻና የተስፋ ጭንጎላ በእነኝህ  ውስጥ የታዬው ትይንት በራሱ ተርጓሚ የሚሻው ሌላ ቅጽ ነው።

ከዚህ የመውለድ ነፃነት ጋር አብሮ ሊታይ የሚገባው በሰዎች እጅም ይህ የመወለድ ተፈጥሯዊ ነጻነትን የመቀማት የማጣት ጨለማ ገጠመኝ ጋር፤ ፈቅደው አልወልድም ከሚሉት ጋር በመንፈስ ሃዲድ ስንጓጓዝ ሌላ ዓለም ውስጥ ይጨምረናል። እመቤት መና አልፈለገችም መወለድን። ‚ሰናይ/ መኖር ግን/ እስር ቤት የደረሰውን ባይገልጸውም ጭብጡ ወደ ዛ ያመራናል። የሚስጢር ሰውር ፍቅረኛው በተሰወረው መከራው ላይ እሱም ሌላ ፍልሚያ ላይ ነው …

በመጨረሻ የመኖር እስር እና ገጠመኞቹ ጃን እና ሩት ከሙያቸው ውጪ ሰዋዊ ተፈጥሯዊ በሆነ ሁኔታ በትሁት መንፈስ የደረሰበትን ሲጠይቁት እሱን ከመኖር ውጭ ያደረገውን የጭካኔ አብይ ጉዳይ፤ የፍትህ ያለህ እያለ የሚጮኸው ኢ - ተፈጥሯዊ የባጀንበት መከራ እርምጃ ምን ያህል በመኖር ውስጥ እዬሞቱ መኖር ለተፈቀደላቸው ወገኖቻችን መከራውን ሲከፍተው „አፍርሰውኛል“ ነበር ያለው፤ ጃን ሲጠይቀው ምንድቡ መኖር ሲመለሰው።


እራሱ መኖር ሥሙ ወርቅ ነው። እኔ አንድ የግጥም ስብስብ አለኝ በዚህ „መኖር“ በሌላ በኩል አህድ  ከእሥር ከተፈታች በኋላ ራሷን ለሰጠችለት የነፍስ ፍቀረኛዋ አለግባብ አለፍርድ መታሰሩን ከወታደሮቹ ጋር ያደረገችው ሙግት አንዲትም ሰከንድ ባላጠፉት ግዞት ለተፈረደባቸው ወገኖች ማን በምን ያህል ወቄት የህሊና ካሳ ሊከፍላቸው እንደሚችል የነበረው የጭብጥ አቀራረብ ሂደት „ደርሶ መልስ“ የሰብዕዊ መብት ተሟጋች ፊልም ቢባል አያነስውም። በተለያዩ ቋንቋዎች ቢተረጎም ሉላዊ የመሆን አቅሙ ድርጁ ነው። ኮርቸበታለሁ ስል ሐሤቴን በፍቅራዊነት ጠልፌ ነው። 
   
በሌላ በኩል በደህንነት፤ ፍትህን ፍለጋ፤ እውነትን ፍለጋ በሚኳትኑ ነፍሶች ዙሪያ ያለውን የተጋድሎ መስመር ፍንትው ብሎ ማዬት ይቻላል፤ በዚህ ፊልም ውስጥ። በዚህ መስመር የሚሰማሩ ሰብዕናዎች ያለባቸው የህይወት ፈተና ትልቁ የራስን ዓይን፤ ተተኪ ትውልድ የመፍጠር አጋጣሚውም ጠባብ እና በመጠራቅቅ መሆን እንዴት ሊታረቅ እንደሚገባ ምልክት ቢኖርም ገፋ ብሎ ቢኬድበት መልካም ነው። ቢያንስ ማህበረሰቡ ቅኖች ስለሚከፍሉት መልካም ነገር እራስን ረስቶ የመኖር ተጋድሎ እናመሰግናለን ቢቀር ሽሙጡና ወቀሳውን ቢቀር …

(1)             በዚህ የሦስትዮሽ የጭብጥ አሃታዊ አመክንዮዊ ጥምረት፤ ሦስት ሰብዕናዎችን እናገኛለንበገጠማቸው አታካች የህይወት ገጠመኝ መውለድ እየቻሉ መውለድን የማይፈቅዱ፤

(2)             በጨካኞች በሚደርሳባቸው መከራ መወለድ እዬፈለጉ ግን የማይችሉ፤ ማፍቀር አትችሉም፤ ሰው አይደላችሁም፤ ዘር መተካት አትችሉም ተብሎ ሰውነታቸው በግፍ የተሰረቁ በጨካኞች መኖርን የተቀሙ ምንዱቦች፤ አልተወለዳችሁን የተባሉ አሳረኞች፤

(3)            በሌላ በኩልም መውለድም ማፍቀርም እዬፈለጉ በሥራ ባህሪያቸው ምክንያት ሥነ - ተፈጥሮ የተገደበባቸው ነፍሶች ሁሉ አቤት የሚሉት ቁምነገር አለ … የተፈጥሮ ፍትህ ፈላጊነት የትውልድ ውርርስ ወይንም መተካካት … ጉዳይ ይህ ብሄራዊ ብቻ ሳይሆን ሉላዊ ነው። የፊልሙ ጭብጥ ወደ ሰብዕዊነት፤ ለዛም ተሟጋችነት ያደለ ወይንም ያመዘነ ሆኖ ነው ያዬሁት የምለው ይህን ሁሉ ስለሚያመሳጥር ነው። … ‚ደርሶ መልስ‘ ስለትውልዱ ዕጣ ፈንታ አብዝቶ የመጨነቅ፤ አብዝቶ የመጠበብ ቅምረት አለበት።

  • ·        ህበረሰብ እና ዕድምታው።

በዚህ ፊልም የእናት እና የልጅ ግንኙነት በሥራ እና በገጠመኝ አስገዳጅነት ያለበትን ጫና መመልከት ያስችላል። የጃን እና የወላጅ እናቱ ሁኔታ አንዱ ማሳያ ሲሆን፤ በሌላ በኩል በሙያቸው አስገዳጅነት የወላጆችን ልጆቻቸው አግብተው ወልደው የማዬት ተስፋ ጥንዙል የመሆን አጋጣሚ፤ በማህረሰቡ ያለው ግንዛቤ ጋር ያለው ትስስር ለማዬት የጭብጡ ፍሰት ብዙም ወደ ማህበራዊ ህይወት ስለማይዘለቅ ማዬት ባይቻልም ግን በርቀት መዳሰስ ያስችላል … ያልወለደች አንስት፤ ያለገባ ተባዕት፤ ወልደው ግን ያልተባረኩ ልጆች፤ ራሷን ያልቻለች ግን ሰፊ ሃላፊነት ያላት አንስት፤  የባከኑ ዕጣዎች ወዘተ ..

በሌላ በኩል ይህ በወጣትነታቸው በዚህ መሰል የትጋት ተፈጥሮ ዕድል ጀባ ላለቻቸው ነፍስች ብክነት እና ለትወልድ የሚያበርክቱት መስዋዕትነት፤ ራስን ሳይተካ ግብን ማሰብን በማዘውተር የሚያመልጡ ተፈጥሯዊ ግዴታዎች ጋር ሁነኛ ውሳኔ እንደሚያስፈልጋቸው አቅጣጫ ያሳያል።

ነገር ግን ማህበረሰቡ እንደነዚህ ላሉ ነፍሶች ባለመቻል ሰለሆነው ነገር ሊረዳላቸው እንደሚገባ ባሊህ ብሎት የማያውቅ፤ እናመሰግናለንም ተብሎበት የማያውቅ ጉዳይ ስለሆነ ትንሽም ቢሆን ፍንጭ የሰጠ ይመስለኛል ታሪኩ … ይሄ የባተሌዎች መስዋእትነት ጉዳይ ባሊህ ባይ አጥቶ ብክነታቸው እዳሪ አዳሪ የመሆን ጉዳይ ...  ሲያልፍም ደመ ከልበነት ...

  • ·        ንከራ ክርክሮች /ሃርድ ቶክ/ ዘይቤን የመከተል … ዝንባሌ።

በዚህ ፊልም ጠንካራ ሙግቶችን /ሃርድ ቶክ/ ዓይነት ዝንባሌ አይቸበታለሁኝ። ሙግት ስለምወድ ቀልቤን የሳበው አንዱ ምክንያትም ነው። አብሶ የቋንቋ አጠቃቀም ለተፈለገው  ተልእኮ የአገላላጽ ብቃቱ አቅሙ ሙሉ ነው።

ለቋንቋ ዕድገት እንዲህ መሰል የጠነከሩ፤ የነጠሩ ጉልበታም የሙግት /የሃርድ ቶክ ፊልሞች/ ያላቸው ድርሻቸው ጉልህ ነው። ትውልዱን ወደ ምከንያታዊ የህይወት መንገድ ይመራል። ፊልሙ በአልባሌ ቃሎች የተደረተ አይደለም። ፊልሙ በግብር ይወጣም በግርፎሽ የተዋቀረ አይደለም። 

በዚህ ስሌት „የደርሶ መልስ /ራስመሳም ፊልም“ የተውኔት ምናባዊ አቅም የኢትዮጵያን የፈልም አወቃቀር ደረጃ ፈታትሾ ከፍ አድርጎታል። በሌላ በኩልም የአማርኛ ቋንቋ ደረጃን በጥራት ከፍ አደርጎታል ብዬ አስባለሁኝ እኔ በግሌ።

በዚህ ውስጥ ያዬሁት አብይ ጉዳይ የደራሲያዋ የቋንቋ ተሰጥዖ ከተለመደው ውጪ መሆኑ ባለመክሊት መሆኗን ተስጥዖዋን ማነጋገር አስችሎኛል። መጻፍ ብቻ ሳይሆን ወዝ ያለው አቅም አላት ብዕሯ። ጠረኑ፤ ጣዕሙ ልዩ ነው። ቅኔዊ መንገድ የተከተለ ነው ፊልሙ። የዜማዊ ምቱ ብቻ ሳይሆን ቃላትን እንዲህ አደራጅቶ ተዋጊ፤ አጥቂም፤ ተከላካይም፤ ጎል ጠባቂም፤  በማድረግ ሜዳ ላይ እንዳለ የኳስ ተጫዋች ትይዕንት በቅጡ እጬጌውን አማርኛ ቋንቋ መርቶ ተልዕኮውን እንዲወጡ በማድረግ እረገድ „ደርሶ መልስ“ብዙ ርቀት ተጉዟል ብዬም አስባለሁኝ። ለረጅም ጊዜም ሳይበርደውም፤ ሳይቀፈውም የመዝለቅም በህሊና ተደላድሎ የመቀመጥ አቅም አለው። ግን ነፃነትን እሴታዊ ተፈጥሮ ከወስጥ ከኖረ።

አስደሳቹ ነገር የቃላት አመራረጥ ጥንቃቄ ውበቱ ታሪኩ ከተነሳብት ጭብጥ ጋር ተዋህዷል። የፊልሙን ጭብጥን ሥልጣኔ ያህል የቋንቋው አወቃቀር ደረጃው በውል፤ በመስተጋብር በሚገባ ተዋዷል ብዬ አስባለሁኝ። እኔ ቃላትን እንደ ሞድ ነው እማያቸው፤ ግጥሞቼም እንዲሁ በንድፍ በዲዛይን የተሰሩ ናቸው።

https://sergute.blogspot.com/2018/05/blog-post_14.html

  • ·        ውልድ።

ይህን ፊልም „ደርሶ መልስን“ እንዴት ታይዋለሽ ብባል „ትወልድ“ ብዬ ነው እምገልጸው። ትውልዱንም አገናኝቷል። ለትውልዱ አዲስ የርትህ ዘመንም ተመኝቷል። ፊልሙ አቅም ባይኖረው ጋሼ ደቤ አይሳተፍበትም ነበር። ይህን ፊልም እያዬሁ የትወልዱ ነገር ጭንቄ ስለሆነ ትውልዱ መታደሉም እንደ ዜጋ እርፍት ሰጥቶኛል። የጭብጡ ደረጃ ከፍ ያለ ነው።

ልቅም ክውን ያለ ፊልም ነው። ምዕራፎችም ከ60 እንደማያልፉ ስለአደመጥኩኝ ሳይረዝም ሳያጥር እንደ ጣፈጠኝ፤ ልቤም እንደ ተንጠለጠለ ይጠናቀቃል ብዬ አስባለሁኝ። የሁለተኛው ክፍለ አጨራረሱ እራሱ የዓመትባዕል ጉዳይ ዱብ ዕዳ ነው የሆነብኝ።

እንዲህ ዱብ የሚል የጭብጥ አቅም ሲኖር ፊልሙን የበለጠ አጓጊ እና ማራኪ ያደርገዋል … እንደማሰበው በማገኘው አጋጣሚ ሁሉ መልሼ መላልሽ ልክ እንደ ፍቅር እሰከ መቃብር፤ እንደ ምጻዕተ እስራኤል እና እንደ ፊያሜታ እያንዳንዳቸውን ከ15 ጊዜ በላይ እንዳነበብኳቸው ያን ያህል ፍቅር ስላሳደረበኝ ይህ ፊልም ሁልጊዜም እንግዳው እሆናለሁኝ። ለዚህ ነው ሳብስክራይብም ያደረኩት። ሁሌ መንፈሱ እንዲጎበኘኝ መፍቀድ ስለነበረብኝ። ጠረኑ ቤተኛ አድርጎኛል። ለብቁ ምናብ ውብ ፍቀረኛ የሆናችሁ የቀንበጥ ታዳሚዎች ከቁጥር አንድ ጀምሮ በ እርጋታ ብታዩት የውሳጣችን መሻትን ያሳያችኋል። https://www.youtube.com/channel/UC6mAYT-zar6iqcZJHsfgXog
  • ·        ልበ ብርሃኑ ሎጎ።

ራሱ የሎጎው መለያ እና ቀለሙ እኔ ብዙ ነገር ገልጦልኛል። መዳፍ። እጣት። የእጣት አገልግሎት።  የእጣት ሚስጢራት፤ የእጣት አሸራ። የእጣት ምልክትነት፤ የጣት ቀለበት፤ እኔ የብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ድህረ ገጽ ስጀምር መዳፍ ነበር መለያው ሎጎው። በሌላ በኩል እጅ መዳፍ የሆነ ማህበረሰብ ደግሞ ኢትዮጵያ አላት። መዳፍን የሚወክል ማህበረሰብ ለእኔ የጉራጌ ብሄረሰብ ነው። ታታሪዎች ትጉሃን ስለሆኑ። የጉራጌ ማህበረሰብ ሎጎ ቢባል መዳፍ ነው።
  • ·        መገናኛ አለነ።

መናህሪያ አለን። ኢትዮጵያ ከዓለም ተለይታ ብሄራዊ አባባ አላት። አድዮ። የደራሲ ማዕዛ ወርቁ የቀለም ምርጫ ቢጫ ነው። ቢጫ ለእኔ ኢትዮጵያ ናት አድዮ። አድዮ ደግሞ የኢትዮጵያ የአንድነት ሊንካችን ናት። ማያያዣ መክሊተ መገኛችን። አድዮ መገናኛ ናት። አድዮ አሻጋሪ ድልድያችንም ናት። አድዮ መስከረም ላይ በሁሉም ጋራ ሸንተረር፤ ሃብታም የእኔ ቢጤ ሳትለይ እደጃችን ድረስ ከች ትላለች፤ ቦታ ሳታመርጥ እንዴት ባጃችሁ ትለናለች? አላችሁልኝን ስትል ፏ ፍንትው ብላ ነው? ናፍቆቷ በሳቅ ነው። አንኳን ዘመን ከዘመን አሸጋገራችሁ ስትለን በእቅፍ ሙሉ ነው፤ አድዮ በልቧ ውስጥ ሙዳይ አለ።

 በአድዮ የልብ ሙዳይ ውስጥም ልጆች አሉ የነገ ባለ አደራዎች። አድዮ ለልጆች እራሱ የተስፋ ብርሃናቸው ናት። ነፍሷ እሲከጠፋ ትወዳቸዋለች። እነሱም የእሷ ነገር አይሆንላቸውም። አድዮ እና ልጆች ፍቅር በመስተዋድድ የተዋህዱ ናቸው። ሰዋሰው። አድዮ ስዋሰውም ናት። አድዮ መርህ እቅድም ናት፤ አድዮ የምስራች አብሳሪ ጋዜጠኛም ናት። ስለ አዲስ ዓመት አመጣጥ ወሬ ነጋሪ …


አድዮ እትጌ ኤርትራም አኮረፈች ብላ አትተዋትም፤ እዛ ድረስ ሄደ የኔዋ አካል አምሳል እንዴት ባጀሽልኝ ትላታለች። አድዮ መንፈስ ናት ለእኔ። አያት ቅድመ አያቶቻቸን ብሄራዊ የዜግነት ሰንደቅ ዓላማችን ቀለም ሲመርጡ እንደ  ዕማደ ሚሰጥር የፍቅር አገናኝ አድርገዋታል ብዬም አስባለሁኝ - እኔው። አድዮ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የዜግነት መለያችን አረንጓዴ እና ቀዩን የምታገናኝ ባለ ብዙ ፈርጅ ልዩ የብሥራት ተልዕኮኛ ናት። ለእኔ  አድዮ እርብግቤዋ ርህርህት አዛኝም ናት።
  • ·        ውንነት።

"ደርሶ መልስ" ፊልሙ በዬምዕራፉ 30 ደቂቃ ብቻ አይደለም። ከተለመደው ረዘም ያለ ስለሆነ ቅንጭብ አይደለም። አያሯሩጥም። በዚህም የፊልሙን ትልም ስክነቱን እና እርጋታውን ማሰተዋል ይቻላል። ቁርጥ ብሎ ሰለማይቀር መንፈስን አያጣድፍም ፍሰቱ። እያንዳንዱ ምዕራፍም ክውነቱ ጥልቅ ነው። አዲሱ ሊጋባ ምዕራፍን ሂያጁ ሲሰናበተው እራሱ ዜናውን ሠርቶ ነው። አብስሮ። ይህን ይዢ እመጣለሁ፤ አደራ ጠብቁኝ የማለትን፤ አስቀድሞ መረጃ የማቀብልን አዲስ ግልጣዊ ዘይቤም አለው።

በጠቅላላው የጸሐፊዋ መንፈስ በፈለገው ደረጃ ቅንብሩ፤ ቀረፃው፤ የቦታ ምርጫው ጥራቱን የጠበቀ ነው። እኔ በፋና የቪዲዮ ጥራት በጣም ነው እምረካው፤ እንዲያውም ብሄራዊ ጉዳዮች አብሶ የጠ/ሚር አብይ አህመድን ውሎ እነሱ ቢይዙት ሁሉ ምርጫዬ ነው።



የሚዲያ ቀረፃ ጥራት ለጉዳዩ፤ ለጭብጡ የሁለገብ ቪታሚን ነውና። የአንድ ፊልም ቀረፃ አነባቢው ጉዳይ የጥራት ደረጃው ነው። በዚህ የተዋጠላት ተግባር ነው የተከናወነው። አሁን ለክለሳ ከቀረበው መጨረሻ ላይ ድምጽ ግድፈት ከታዬበት በስቀር በዬምዕራፎቹ አንድም ቦታ የድምጽ ውልግድ አልታዬበትም፤ የመብራት አለመመጣን አልታዬበትም፤ የቀለም ውርግርግም አልተከሰተበትም።
  • ·        ም ስለ።

ሌላው በዚህ ካስቲንግ ላይ ለዬት ያሉ ሥሞች አይቻለሁኝ። ይህም የዚህ ፊልምን የቋንቋን ጸጋ ክህሎት እና መክሊት ዕውቅና በመስጠት አረገድ ያዬሁት ልዩ ብልህነት ነው። „መኖር፤ አህድ፤ ዐመትባል፤ ማለዳ፤ ትጉህ“ የወደድኳቸው ሥሞች ናቸው።

በተጨማሪም ለጭብጡ አቅምም አንድ ተጨማሪ ተደማጭነት ፈጥሮለታል ብዬ አስባለሁኝ። በሥም አወጣጥ በብሄራዊ ደረጃ ቅኔው ጎጃም የተለዬ ጸጋ እና ክህሎት ያለው የሚስጢር ዓውደ ምህረት ነው። ፊልሙ የግዮንን መንፈስ አጣጥሙ ያለበትን ሂደት በሥም አወጣጡም ቀኘት አድርጌበታለሁኝ …
  • ·        ደረጃ።

በዚህ ፊልም በጠብኩት ልክ ኢትዮጵያ አፍሪካዊቷ አገር ስለሆነች እንደ የፊልም ኢንደስትሪ ጀማሪነቷ ጥራት ያለው ተግባር በቴክኒክ ቅንበሩ ተከናውኗል ብዬ አስባለሁኝ። ከጭብጡ አቅም ጋር ጥራቱን፤ ደራጃውን ክህሎቱን የጠበቀው ጠቅላል ዝግጅቱ ፊልሙን ሙሉ ካደረጉት ጉልሁ የቴክኒክ ባላሙያዎች ትትርና ጋር መኖርን እጅግ ጥልቅ  አድርጎ ከሽኖታል። ይህ ፊልም የመኖር ታገድሎ ፊልም ነው። ይህ ፊልም በጥቅሉ ለእኔ የሰጠኝ እርካታ ሰውነትም የመሰረቅ ሁኔታን እንዴት ማስቆም እንደሚቻል በዜማዊ ቃናው እያለሰላሰ አዋዝቶ መክሯል።

ያው ነፃነት ከተነጠቀ፤ ወይንም ነፃነት በተጣበቀ ሁኔታ ከተቀፈደደ፤ ነጻነት ነፃነቱን አጥቶ በተጠረቃቀ ሁኔታ መሆን ቻለው ከተባለ፤ ሰውነትን መሰረቅ ስለሆነ፤ ዕውነተኛውን የሰው ልጅ የተፈጠረበትን የነፃነት ሚስጢር ፍለጋ ላይ ያለ ፊልም ነው „ደርሶ መልስ“


ፍለጋ ላይ ነው … ነፃነት እና ራስመሳም እዬተፈላለጉ ነው ይገናኙ ይሆን? … ያገኘው ይሆን? ዕውነትንም ይፈልጋል ፊልሙ ይሳካለት ይሆን? ርትህንም ይፈልጋል ግን ወፍ ያወጣው ይሆን? ግን „ደርሶ መልስ“ ከነፃነትም፤ ከእውነትም ፤ ከርትህም ጋር ቢገናኙ ምን እና ምን ይሆኑ ይሆን?ያያቸው ሰው/ ና - ፈ - ቀ -ኝ ተቃቅፈው ይሳሳሙ ይሆን? ወይንስ በሥርዐተ ተክሊል ተጋብተው ትውልድን ያገዩ?
  • ·        ትህ?

ሌላው ቁም ነገር ከላይም ገልጨዋለሁኝ የህሊና ዳኝነት ከሁሉ የገዘፈ ችሎት መሆኑን ፍሰሃ አጋጣሚ የፈጠረበትን ግድፈት፤ የፍቅር መነጠቅ እና ፍትህን ለመስጠት ራሱ ዳኛ ሆኖ፤ ራሱን በበደሉ ልክ ለመቅጣት ያደረገው ተጋድሎ በስውር ትናንትም ዛሬም የተለመደውን የተለያዬ የወንጀል ዓይነት ተሸክሞ ግን ራስን እያታለሉ መኖር እሰከምን ሊወስድ እንደሚችል ፊልሙ ዘመኑን ቁሞ አስተምሯል። የፍትህ አቦል አሰኝቶኛል ይለናል „ደርሶ መልስ“ 

የማረሳው ደግሞ የሶፈንያስ የቤት ውስጥ ውሎ እና ሰው ጊዜ በኖረው ቁጥር ለማወቅ ያለውን የጉጉት ጣሪያ አይቸበታለሁኝ። ሂደቱ የዘመኑ ሥልጣኔንም የቃኜ ወደ ዲጅታሉ ዓለም አለሁኝ ብሏል፤ 



የሶፊ  ሩጫው ግን ፈጽሞ ከህሊና የማይወጣ ማህተም ነው ማለት ያስቸልኛል። እንዲያውም እኔ እሱን እያየሁኝ ኳስ ሲያገኝ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እንዴት ድድድድ እፍፍፍፍ ክንፍፍፍፍፍፍ እንደሚል አስተዋልኩበት፤ ህይወት ራሷ ሩጫ ናት እና አይደል?



  • ·        ዕይታ መከወኛ።

እማጠቃልለው ተስፋ መጽሐፌ የመጨረሻ ሽፋኑ ላይ … ባለው ጉዳይ ይሆናል ..
  
„ምን ያህል እንደ ተጓዝኩ አላውቀውም።
ምን ያህል እንደሚቀረኝም አላውቀውም።
አለማወቄን ስጠይቀው አለማወቁን ገለጸለኝ።
ተስፋን እጠብቃለሁ“ ይላል …

ማንም ሰው ምን ያህል እንደ ተጓዘ አያውቀውም። ስለምን እሱን እራሱን ዘሩን ወደ ኋዋላ ሄዶ ሲያጠና አባት እና እናቱ በጉዞ ውስጥ ነው የተገናኙት፤ አባት እና እናቱን የተፈጠሩትም በጉዞ ውስጥ ነው የተገናኙት፤ አያት ቅድመ አያቶችም ጉዞ ያገናኛቸው ስለሆነ የጉዞው መነሻ ዲካ የለውም … 

ስለዚህ ሁሉም ሰው የጉዞ መነሻውን ለማወቅ አይችልም መገመት እራሱ … የፍጻሜውንም ጉዞ እንዲሁ … መቼ የሚለውን መተንበይ አይችልም፤ ግን የጉዞ ቅሪት አካል ይኖራል ታሪክ ሥም እና ልጅ ከተካ ሰብዕናው … እራሱ አንድ ጽንስ ከእናቱ ማህጸን ካረፈባት ቅጽበት ጀምሮ ከእናቱ ጋር ጉዞውን ይጀምርና ሲወለድም ጉዞውን ይቀጥላል። እናቱን ወደ ምድር ያመጣትም ያው ጉዞ ነው በእናቷ ውስጥ ተጉዛ፤ ስለዚህ ይህ የጉዞ ዘለበት ኪሎሜትርም አብሮ ይቆጠራል …

 … ህይወት ጉዞም የጉዞ ጓዝም ናት ተስፋም እንዲሁ ተጓዥ ነው። ደስታም ተጓዥ ነው „ደርሶ መልስ“ እራሱ በጉዞ ማዕቀፍ ያለ ነው „ደርሶ መልስ“ ማለት ሄዶ ይመጣል ነው አይደል። መሄድና መምጣት ደግሞ ጉዞ ነው። እና እጬጌው „ደርሶ መልስ“ እዚህ ሲዊዝ በጉዞው ልክ መጥቶ መንፈሴን ፈታተሸኝ፤ ራሴን ፈታተሸኝ፤ ውስጤንም ፈታተሸኝ፤ ብዕሬንም ያለሽን አዋጭ ብሎ ብርብር አደረጋት እና መክረን ይህን ኮለመን።  „ያለውን የሰጠ …“ ምን አይባልም ነው የሚባለው ፈጥሙት … 

ተባሩኩ ሁላችሁም ወርቅ ሥራ ነው ... ቀጣዩም በጉጉት ይጠባቃል ... ጭምቷ ሲውዝሻም ትታደማለች በተደሞ... 

ውዶቼ ከነበረን ሞንሟና ኪናዊ የአብሮነት ጉዞ ደልደል ያለ ውብ ጊዜ ተመኘሁላችሁ። ኑሩልኝ … ሩትን መውደዴን ሳልገልጥ … የሩት ድምቀት … ፏቴ ነው።

ሙሉውን ለማዬት ለምትሹ ውዶቼ አትጎዱም ታታርፋላችሁ አደብ ገዝታችሁ እዩት በትሁት መንፈስ፤ ውስጣችሁን በአንድም በሌላም ታገኙታላችሁ።  


ሴቶች ጥበብ ናቸው!


መሸቢያ ጊዜ፤

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።