የአቶ ልደቱ አያሌው መከራ ሐዋርያችን ሊሆን ይገባል።
እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።
ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል
እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"
(ምሳሌ 16 ቁጥር 9)
• የአቶ ልደቱ አያሌው መከራ ሐዋርያችን ሊሆን ይገባል።
• ሰብዕዊነት ስደት ላይ …
ሰባዕዊነት ሰው መሆንን ብቻ ይጠይቃል። ሰው መሆን ያልቻለው የኦሮሙማ ግብረ ሃይል ሰውነትን ከተፈጠረበት ልክ ዘቅዝቆ እዬደረመሰው ይገኛል። የሰውነት አጥፊ ኦሮሙማ ሰውን እምራለሁ ሲል እያጠፋ ነው።
ህወሃት የራሱ ለራሱ ማላታይን አዘጋጅቶ ከሰመ። ፍዳንም ተቀበለ። ከሁሉ በላይ ከባዱ ነገር መጠላት ነው። ወድቀህ ተነስ የሚለው አንድም ነፍስ የለም። የፈጠራቸው ሳይቀሩ ክደውታል።
ኦሮሙማም የፈጠራቸውም፤ እዬፈጠራቸው ያሉም እንደ ሲዳማ አይነት አዲስ ሁነቶችም ከእሱ ጋር የሚከስሙበት ጊዜ ይመጣል። ጠብቁት። የማናውቀው ጊዜውን ብቻ ነው። ከሁሉ በላይ ግን አሁን እሱን የተሸከመው አልጋው አማራ ነው። አልጋው አማራ ሞቱን ተሸክሞ ለሞቱ ሞትን አጭቶ እዬከበከበ ይገኛል።
በክህደቱ ልክ መንቃት የማይችለው አፈር የለበሰ ብቻ ነው። በቁማቸው አፈር የለበሱ ነፍሶች አሁን ሞታቸውን ደግፈው፤ ለማብቃታቸው ጉዝጓዝ ሆነው እሱን ሆነን „ብልጽግናን ወክለን“ ኮሮጆ እንለቅማለን ይሉናል። እነኝህ ሰወች ቁጥር ናቸው።
ዕውነት ለመናገር በዚህ ዘመን በአቶ ልደቱ አያሌው የሚደረገው የሸፍጥ፤ የቂም፤ የበቀል፤ የጭካኔ፤ የአረመኔነት እንድርቺ እንድርቺ ብቻ ታላቅ ዩንቨርስቲ ነው። ልንማርበት ይገባል። ይህ ሥርዓት ብናኝ ሰውነት የሌለበት፤ ተፈጥሯዊነት ያለተፈጠረበት ስለመሆኑ የአቶ ልደቱ መከራ ያሳያል። ይመሰክራል። ያናግራል።
ሐዋርያ ሆኖ ይሰብካል። ብንማርበት ሁላችንንም ቀጥቶ ወደ ትክክለኛው የጸዳ ጎዳና ሊያስገባን ይችል ነበር። ነገ በኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ህይወት ምን ሊመጣ እንደሚችልም አናውቀውም።
ጭካኔ፤ አውሬነት፤ አረንዛነት፤ ማሽንክነት ነው አሁን ኢትዮጵያን እዬመራ የሚገኜው። ይህን ተጠይፎ ከሰውነት ጋር መቆም ሰው ሆኖ መፈጠረን ማመሳጠር ነው። ግን አልተቻለም። ሰው ለመሆን እራሱ ገና ሌላ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልግ ይመስለኛል።
ኢትዮጵያን በምታክል አገር ውስጥ ተፈጥሮ እንደምን ሰው መሆን ያቅታል? እንደምንስ ተፈጥሯዊነት ይገፋል? ሞት የሚጠበቅባት አገር ሰትሆን ኢትዮጵያ እንደምን አያስቆጣንም? እንዴት? ግን እኛ ማን ነን? እኛስ ምንድን ነን?
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
28.03.2021
ጎዳናዬ ሰብዕዊነት ነው!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ