የነፃነት ዋርካ አቶ እስክንድር ነጋ።

 

እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።

 

ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት

በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና

በቢሆነኝ የተብራራ ብራ

በሰብለ ህይወት አዝመራ

ለራህብ የሚራራ።

 

የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል

እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"

(ምሳሌ 16 ቁጥር 9)

 


የነፃነት ዋርካ አቶ እስክንድር ነጋ።

 

ማዕዶተ ሰባዕዊነት ለዛውም በሰንበት።

 

እንዴት ናችሁ ቅኖቹ? ደህና ናችሁ ወይ?

ቅኑ ጠንካራው፤ ሩህሩሁ አቶ እስክንድር ነጋ ካቴና ላይ፤

የዚህ ሁሉ መከራ አምጪ ፋፍሪካ አቦይ ስብኃት ነጋም ካቴና ላይ?

ይህን ፍርድ ማን ይዳኘው?

ይህን ወልጋዳ ገጠመኝ ማን ይግራው?

ይህን ቅጥ መጠን ያጣ ዝብርቅርቅ ማን መልክ ያስይዘው?

ይህን ፍርክርክ ሁነት ማን ውስጡን ይመርምረው?

ይህን የግፍ ቁልል ማን ይናደው?

 

እኛስ የት ነን?

ዓላማችን የት ነው?

ግባችንስ ምንድን ነው?

ግን ዓላማ አለን? ግባችን እናውቀው ይሆን?

ምንድን ነው የምንፈልገው?

ምን አጣን?

ምን ለማግኔት ይሆን የምንታገለው?

 ምን ጊዜም መቼውንም ቢሆን ሰውነት ላይ ብንሆን አንወዛወዝም። የመጣ ቢመጣ፤ የሄደ ቢሄድ ሰውነት አስቀድመን ታግለን ቢሆን ትናንት የእኛ ያልነው፤ በሥሙ የከበርንበት፤ በሥሙ አንቱ የተባልንበት አቶ አስክንድር ነጋ ካቴና ላይ ሆኖ በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ባለተኮርን ነበር። እሱ የመታገያ አጀንዳችን በሆነ ነበር። የሌት ተቀን ህልማችን እሱን እሰከ ቲሙ ማስፈታት በሆነ ነበር።

 እሱን ለማስፈታት አቅም ሁሉ ፈሰሱ ወደዚህ ያጋድል ነበር። አልፈን ተርፍን ይህን ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ነፍስን ተዳፍረንእብድብለን ባልተዳፈርንም ነበር። በውነቱ ከዓላማችን ጋር አንተዋወቅም።

የአቶ እስክንድር ነጋ የብጽዕና አቋም ነገ ይዳኛዋል። ፈጣሪ መልስ ይሰጥበታል። ልክ እንደ አቶ ልደቱ አያሌው ማለት ነው። ለነገሩ ዛሬም እያዬን ነው። 7 ወር ሙሉ ኦሮሙማ ምን ያህል አዲስ አበባን በቁሙ እንዳራገፈው። ሙት መሬት ላይ ሆኖ ጩኽት ምን ሊያተርፍ? ኪሳራ ካልሆነ፣ ጸጸት ተክሎ እራሳችን ካልሞገተን፤ ንስኃ እንግባ። ብዙ ነገር ተበላሽቷል።

 

·      እኛ የሌለንበት እኛ።

ለዛውም የኢህዴግ ጉራጅ በሚመራት ኢትዮጵያ ውስጥ ያን ወግነን በግልጥም በስውርም፤ ሰባራ እንጠግናለን ተብሎ ስትንት አቅም ፈሰሰ? ለዛ አጥር እና ቅጥር ሆነን የእኛን ስለ እኛ ዘመኑን ሁሉ የተማገደውን አባዋራ የነፃነት ዋርካ ስንዘልፍ፤ ስናቃልል፤ እስሩን "ኢሪሌባንት አንዳርገዋለን" ብለን በድፍረት ስንነሳ፤ አዳዲስ አጀንዳ ቋሚውን አጀንዳ ስንጠቀልል፤ እኛ የሌለንበት እኛ መሆናችን ይገልጠዋል።

እንሆ በስውርም በግልጥም ንደትን፤ ፍርሰትን፤ እርቃን መቅረትን የተመኜ፤ ለዛ ያደረ አብይዝም ቀዳዳ በቀዳዳ እንዲህ ሲብተከተክ ምኑን ይክደነው፤ በምንስ አቅም ወትፎ ይታደገው።

ያው እንደ ሽንብራ ቂጣ እዬተገላበጡ ሦስት ምንትዮሽ መንገድ ላይ ተገትሮ አብሮ የወለሌ ገበታ ሆነ። የሳዝናል። መድከም ካልቀረ ጥርት ባለ ጎዳና ላይ ቆሞ መትጋት ይገባል። አሁንም ወደፊትም ሁሉንም አንሁን፤ ሁሉንም አንድርግ፤ ሁሉም ያቅተን አቋም ግን ይኑረን።

የጠራ፤ የተስረከረከ ያልሆነ። ቢያንስ ሰው ነኝ ብለን እንቀበለው እራሳችን። ሰው በመሆን ውስጥ ሰማያዊ የሚስጥራት ዓምደት አሉ እና።

ያቃተን እራስን ከድቶ ዓላማ እና ግብ አለን ማለቱ ላይ ነው። እራሳችን ከድተነዋል። እራሳችን ዋሽተነዋል። እራሳችን ስተነዋል። እራሳችን ከተፈጥሯዊ መክሊቱ ነቅለነዋል። እራሳችን ሸሽተነዋል። ከዚህ የዳኑ ጥቂቶች አይነሩም እያልኩኝ አይደለም። አሉ።

ከእነዚህ ውስጥ አንዱ አቶ እስክንድር ነጋ እና ቲሙ ነው። ለካቴና በተዳረገው ቲሙ ውስጥ ዕውነትም፤ መርኽም፤ መታመንም ሰክነው አሉበት። በመታመን ውስጥ ተፈጥሯዊነት ቆምሶ አለ። በተፈጥሯዊነት ልክ በተሰጠው ልክ ለመኖር መፍቀድ ጸድቋል። ይህን ጽድቅ ያገኙ ናቸው ካቴና ላይ የሚገኙት።

ለህዝብ መብት መከበር፤ ለዕውነተኛ ዴሞክራሲ እንዲህ ዘመንን ሁሉ መስጠት ያልተለመደ ግብረት ነው። ቢያንስ ዕውቅና እንስጠው ለማገዶነቱ፤ ለግማዱ።ኢሪሊባንትእስሩን ማድረግ ማለት ሲታሰብ ምን ያህል ዕለታዊ እንደሆን ብቻ ሳይሆን ስለምን፤ ስለማን እንደምንታገልም አለማወቅ ነው።

ውጤቱም እዬታዬ ነው። ያን የፋመ የነፃነት ተጋድሎ በረዶ ከልሶ ተስፋ ከሰለ። አቅም ለዘዘ። ሙቀት ወደ ግግር በረዶነት ተቀዬረ። እና ኢትዮጵያ? አፍሪካ? ዓለም በዚህ ድፍርስ የፖለቲካ ዕሳቤ ይጠቀሙ ይሆን? ገዢ መሬትህን ፈቅደህ ሙት መሬት ላይ አስተኝተህ ኤሉሄ? ያስምጣል።

·      ገናናው መንፈስ እስክንድራውያን ነበር።

ግን ከተቀናቃኞቹ በላይ ሆኖ ያን ያህል መታገል አይገባም ነበር። በዚህ ውስጥ ትውልድ የሚወርሰው፤ አብነቴ የሚለው ያጣል። ይህ ማለት ሞራላዊነት ይከስላል። ትውልድ ትውልድን የሚተካው አይከን በሆኑ ሰብዕናዎችም ጭምር ነው። ለተቀቀለ ስብዕና ያን ያህል መፈታትን አይገባም ነበር።

አቶ እስክንድር ነጋ እና ቲሙ በውነቱ ዕውነት ኛቸው። በውነቱ መርኽ ናቸው። ግን እነሱ የተማገዱለት ዓላማ በተገባው ልክ ትጋት አላገኜም። እንደ አዱ ገነት አይነት ሊቀ - ትጉኃን ባይኖሩ ጭራሽም ቲሙ ተረስቶ ነበር፤

የተፈለገውም የአቶ እስክንድር ገናና አንፀባራቂ መንፈስን አደብዝዞ ሌላ መንፈስን መተካት ነበር። የመንፈስ ነቀላ እና ተከላ ትራጅዲ ነበር እኔ ያስተዋልኩት።

እንጠቃማልን? እእ። አሸናፊ መንፈሳችን ሙት መሬት ላይ ተነጠፍ እንለዋለን።፡

ቅብዕ የፈጣሪው ነው። ቅብዕወን የሚጠብቅ አምላክ ደግሞ አለ። ቅብዕ የሰው ስላልሆነ። እኔ እንደማስበው አቶ እስክንድር ነጋ ቅብዕ አለው። ስለዚህም የእግዚአብሔር ጥበቃ አይለዬውም ብዬ አስበላሁኝ። ይህን መፎካካር አይቻለም። ይህን ማጠዬም ወይንም ጥቅርሻ ማልበስ አይቻልም። ፈጽሞ፤

ዕለታዊነት የሳሙና አረፋነት ነው። ትውልድን አያበረክትም። በጸዳ ልብ የጸዳ ጎዳና መከተል እስካልተቻለ ድርስ ትውልዱም ከብክነት ኢትዮጵያም ከውርዴት አትድንም። መዳን የሚቻለው በደነገለ ጎዳና የደነገለ ተግባር ሲከውን ብቻ ነው። በስርንቅ ፍላጎት፤ በቅምጥ ፍላጎት አገርም ትውልድም አይድኑም። አልዳኑም።

አሁንም ፍሬ ነገሩ ላይ አይደለም ያለነው። አስር ውሃው ላይ ነን። የቆረጠ የጠራ መስመር ለመከተል የደነገለ መሪ ያስፈልጋል። የማይዋዥቅ። ሦስት አራት ፍላጎት አዝሎ ብዙኃኑን ሚስሊድ እያደረገ የማያምስ። እሱንም የጠፋውንም ነፍስም የሚያድነው ድንግል ነፍስ ያስፈልጋል።

የጠፋውን ሁሉ፤ ያፈነገጠውን ሁሉ፤ የጠተረውን ሁሉ፤ የሸከረውን ሁሉ ወደ አንድ ማዕከል የሚሰበሰብ ቅን ንጹህ ነፍስ ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል። የለም አልልም። ፈቃደ እግዚአብሔርን የሚጠብቅ የተከደነ ሲሳይ እንዳለ አስተውላለሁኝ።

ትወልድ ጠፍቷል። በዕውነተኛ የትውልዱ ጸሮች ብቻ ሳይሆን በአርቲፊሻል ሰውነት በተሰለቡ ፌክ ሰብዕናወች ጎዳናውን የሚሰተውም እጅግ ብዙ ነው።

ሰውነት አፈጣጠር ላይ ከተተኮረ ግን ዕውነቱን የማግኜት ሚስጢር ጋር መገናኜት ይቻላል። በተደጋጋሚ ጊዜ እጽፈዋለሁ፤ እናገረዋለሁኝ ኢትዮጵያን አናውቃትም። ብናውቃት ኖሮ እሷን መሆን አያቅተንም ነበር። እሷን በመምሰል ሳይሆን በመሆን ውስጥ የሰከኑባት የረጉ ናቸው። ስኩን ናቸው።

 ያስተውላሉ። የጨመቱም ናቸው። ሁሉ እያላቸው እዩኝ መለያቸው አይደለም። አውድሱኝ ጎዳናቸው አያደሉም። ፉክክር ግጥማቸው አያኢደለም። መጠቅለል ጣዕማቸው አይደለም። ዓይን አፋር ናቸው። ዕለታዊ አይደሉም። አይጎርፉም። ከዘለለው ጋር አይዘሉም። ጊዜያዊ እንድርቺ እንድርቺ ጋር ግንኙነት የላቸውም። ለዝና አርኬቡ አያታከክቱም። ዝና ጤዛ ነው። ትውልድ ግን መሠረት የአገር ነው።

አገር የሆነው አቶ እስክንድር ነጋ በቅንነቱ ልክ የፈለገ ቢገለል፤ የፈለገ ዓይነት ምድራዊ ትብትብ ቢሰራበት እሱን ያከበረ፤ ያስከበረ አምላኩ ግን አያንቀላፋም፤ አይተኛም። ጥበቃው አይለዬውም።

የአምላካችን ጥበቃ ለእሱ ብቻ ሳይሆን እሱን ብለው ለሚቀቀሉ፤ ለሚንገረገቡ፤ ቀራንዮ አብረው ለላኩ ሁሉ አምላካቸው ደጀናቸው ናቸው። ክብራቸው ከእሱ ዘንድ አለ። እኛም እኛን ሳናውቀው ኖርን እንደተላለፈንእዚህ ውርዴት ላይ ሆነን ቀን ሌላ ሌሊት ሌላ ነን። ሌላው ይቅር አምላካችን እንፍራ። ንስኃ እንግባ። ትውልድ እና አገር እዬሰመጡ ነው።

በእኛ ውስጥ እኛ ስለመኖራችን እራሳችን አሸንፍን እንገኝ። እርግጥ ይከብዳል። ግን ዛሬም አይመሽም። ዛሬም ጊዜ ነው። ወደ ዕውነት፤ ወደ ጥርት ያለ ጎዳና እንምጣ። መዳን ቅድመ ሁኔታ የለውም። እራስን ማሸነፍ እጅ ያለ ወርቅ ነው። መዳን ከራስ ይጀመር። ስናዳምጥ በዛ ውስጥ እኛ ስለመኖራችን እናረጋግጥ። ኢትዮጵያዊነት እውነት ነው።

ፈጣሪ የሰጠንን ማስተዋል እንኖርበት ዘንድ ይፍቀድልን። አሜን።

ጎዳናቸውን የሳቱትንም ወገኖቻችን የኛው ናቸው እና ፈጣሪ ወደ ዕውነተኛው ድንግሉ የኢትዮጵያዊነት ሚስጢር ይምለስልን። ፈጣሪ አምላክ። አሜን።

ይህን የምለው የጠፋውም፤ የደበዘዘውም ለኢትዮጵያ እንደሚያስለፍግ ሆኖ ዕዝነ - ልቦናው ከተቀረጸ ሁሉም ያስፈልጋታል ኢትዮጵያ። ኢትዮጵያ ክፉ አይደለችም። ክፉዎች ስለሚኖሩ ነው መልካሞችን ይዘው የጠፉት። መልካምነት የነገሠበት ዘመን ይናፍቀኛል።

ወደ መክሊታችን። ወደ ተፈጠርንበት ሚስጢር እንመለስ። ልካችን ነው።

ፈጣሪ ይርዳን። አሜን።

 


ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

27.03.2021

ጎዳናዬ ሰብዕዊነት ነው!

https://scontent.fzrh3-1.fna.fbcdn.net/v/t1.0-0/s600x600/165960971_438362950757965_7451800699160564591_o.jpg?_nc_cat=102&ccb=1-3&_nc_sid=730e14&_nc_ohc=0Mk6TlfxdkoAX-MO8MN&_nc_ht=scontent.fzrh3-1.fna&tp=7&oh=c01062af3e851f84aa0131d9672a419f&oe=6084BD16

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።