1% በኢትዮጵያ የፖለቲካ ውክልና የሌለው የገበሬው ምጣት ዘመን 32 ዓመት አስቆጠረ

 

1% በኢትዮጵያ የፖለቲካ ውክልና የሌለው የገበሬው ምጣት ዘመን 32 ዓመት አስቆጠረ። 
 No photo description available.
No photo description available.
ብዙ በጣም ብዙ ጊዜ ጽፌበታለሁ። ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድም እንደ ሰው ቁጠሩኝ ባሉበት ዘመን ግንቦት 5/2010 መቶ ቀናታቸውን ሳያጠናቅቁ ነበር ወሳኝ ብሄራዊ ጉዳዮችን ነጥብ በነጥብ ዘግቤ ያሳሰብኳቸው። ካሳሰብኳቸው በኽረ ጉዳዮች አንደኛው የገበሬው ጉዳይ ሲሆን ሁለተኛው ደቡብ ሱዳንእና ጋንቤላም ነበሩበት። በጣም በስፋት ነበር የፃፍኩት። የቁቤ ትውል መልሶ በብሄራዊ ስሜት ማነጽም ይገኝበት ነበር።
ኢትዮጵያ ዬገበሬወች አገር ሆና ግን ዬኢትዮጵያ ገበሬ የፖለቲካ ውክልና የለውም ሰፊው ማህበረሰብ። ሁለገብ በሆነው የኦነግ ጆኖሳይድ ተጠቂ ከሆነው የአማራ ማህበረሰብም ገበሬው ግንባር ቀደም ነው። ልጆቹን በማገት፤ በጅምላ በመጨፍጨፍ፤ የቤት እንሰሳቱ ላይ ጆኖሳይድ በመፈጸም ሰፊ የሆነ ፀረ መኖር ዘመቻ ሲካሄድ እንሆ 50 ተቆጥሯል።
አገር ተደፈረች፤ ሉዓላዊነት ተነካ ሲባልም በገፍ የሚያልቀው የአማራ ገበሬ ነው። ያኮረፈ ሁሉ የሚተመው ምሽግ የሚያደርገውም አማራ ገበሬን ነው። የኢሊባቡር፤ የጋሞ፤ የባሌ፤ የጅማ፤ የአርባምንጭ፤ የአሰላ ወዘተ ጫካወች በሰላም ውለው ሲያድሩ የአማራ ቀዬ ግን ዕድሜ ልክ ስቃይ ብቻ።
በዚህ በአምስት አመቱ የሌኮ አብይ አህመድ የቤርሙዳ ትርያንግል ዘመን ጭካኔን፤ አረማዊነትን፤ በዓይነት አይተናል። ዬአማራ ገበሬ ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ፤ ከቀደመው ከዘመነ ህወሃት እንዳይወልዱ እንዳይከብዱ የማምከን ተግባር ተፈጽሞበታል። በዚህ መከራ ውስጥ ያለፈው ትውልድ ነው አሁን ለንብርብር መከራ እዬተዳረገ ዬሚገኜው። ዬአማራ ገበሬ ምርቱን ተዘዋውሮ እንዳይሸጥ ማዕቀብ ተጥሎበታል። ይህን ሁሉ የቻለ የአማራ ገበሬ አሁን ደግሞ #ማዳበሪያ ታግዷል። ዬእምነት ቦታወቹ መጽናኛወቹ ቢሆኑም ጦር ዘምቶበታል። ሙሉ አምስት ዓመት ቀዝቃዛ ጦርነትበአማራ ህዝብላይተካሄዷል።
ግፈኛው የኦነግ አስተዳደር ሙሉ አቅሙን፤ ሙሉ ኃይሉን በአማራ ህዝብ #የመኖር #ጥበብ#የመኖር #ዘዬ#የመኖር #ቃና ላይ ይፋዊ ጦርነት ዓውጇል። ይህ ዝብርቅርቅ እና ዝልግልግ ሥርዓት በስምጠቱ ውስጥ ያለው ፍሬ ነገር ኢትዮጵያን የፍርስራሽ ክምር የማድረግ ነው።
እነኝህ ንፁኃንሁለንዓመትበጦርነት ባጅተው አሁን ደግሞ ቀያቸው የጠኔ እንዲሆን በስልት ተዘምቶበታል። ጠኔ ደንበር አልባ ስለሆነ የቅኔው ጎጃም ገበሬ ተርቦ የሚተርፍ ይኖራል ተብሎ አይታሰብም። ኢትዮጵያዊነት ሱሴ በስል ገብቶ የቀናበትንየመኖር ጥበብ ሁሉ የዶግ አመድ እያደረገው ይገኛል።
በበቀል የዘለበው ዬአብይዝም የመቃብር ሥፍራ ሥርዓት እዬሰመጠም እያሰመጠም ያለው ገደልማ ስልቱን ሁሉም የእኔ ብሎ ከልቡ ከውስጡ በማድረግ ጥበብን ውጦ በስልት ሊታገለው ይገባል።
"ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
01/06/2023
ቅንነትዬድል ቀንን ያቃርባል። ፈጣሪም ይረዳል።
አይዞን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።