በጎርፍ ውኃ ጠጅ አይጣልም።
"ስምምነትን መቃወም ፍትኃዊ አይደለም።" በትውስት አቅም መፍትሄ አይገኝም። በጎርፍ ውኃ ጠጅ አይጣልም።
አዲስ ዋልታ ሊቃናቱን ያወያዬበት ርዕሰ ጉዳይ ነው። ግን ፍትህ ለዶር አብይ መንግሥት ምንድን ነው? ህግ አውጥቶ ከንቲባ መሾም? ወይንስ በህዝብ የተመረጡ የፓርላማ፤ የምክር ቤት አባላትን ተዳፍሮ ከምክር ቤቱ፤ ከፓርላማው ፈቃድ ውጪ ማሰር እና በበቀል መበቀል ነው? ይህ ይሆን ፍትኃዊነት?
እሳቸውን ለስልጣን ያበቃውን የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ መልስ ሳይሰጥ በጭነት 3 አዳዲስ ክልሎችን ፈጥሮ በባጀት እጥረት እያገላበጡ ማሸት? ወይስ ከፋኝ ያለን ማህበረሰብ በማሽን መፍጀት ማሸማቀቅ? ወይንስ አማራ የተባለን ህዝብ አልይህ ብሎ ለብቻው ከልሎ በህግ አውጣ ቀንዳም የበቀል ሾተላይ ሙሉ ዘጠኝ ወር የበቀል ግጥግጠኛ መሆን??? የአማራ እናት እትብትን እና ማህፀንን በጭካኔ መጨፍጨፍ፤ ማሰር ማንገላታት? መቼ ነው የምክክር ኮሚሽኑን እዬነጣጠሉ ጥቃት የሚፈፅሙበት። የሳቸው የጠቅላይ ሚሩ ማለቴ ነው #አስፈንጥሮ መፈጥፈጥ ልማዳቸው ነውና። ከሄሮ ወደ ዜሮ። ግን አዲስ ዋልታ የት ላይ ይሆን ቢሮው??? ጁቢተር ወይንስ ኡራኖስ?
አገራዊ ምክክሩ ምን አስቀረ? እሱ እያለ እኮ ነው ደብረ ኤልያስ፤ መራዌ መአት የሚዘንበው? አቅም አልባ አቅም ነን ፋንታዚ ይመስለኛል። በጎርፍ ውኃ ጠጅ አይጣልም። የገረመኝ የደህንነት ዋስትና እንሰጣችኋለን መባሉ ነው። የእናንተ ደህንነት ዋስትና ካገኜ በቂ ነው። መንግሥታዊው ሥውር አካል ዕውቅና ተሰጥቶት በጠራራ ፀሐይ ያሻውን በሚያደርግባት ኢትዮጵያ? "እኛ ዋስትና እንሰጣለን"??? የቅንጡ ጥያቄ ነው በሞት በዓት ኢትዮጵያ።
ለመሆኑ ሚዛን ካለ መቼ ነው ፋኖ ኦፊሻል ጥያቄ የቀረበለት። "ተራ ሽፍታ ጃውሳ አይደለም ወይ የሚባለው?" ጠቅላይ ሚር አብይ ምናቸው ይታመናል? ለማን ይሆን ታማኝነታቸው? ለኢትዮጵያ ወይንስ ለአርብኢምሬት? ምክክሩን የሚመራው የአረብ ኢምሬት መንፈስ ነው። በጀቱ የሚንዶለዶለው ከዛ ነው። አገር ከሥሯ ታማለች። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
01/06/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ