#ድርድር እና የሰው ልጅ። ሕይወት #አናጋሪም #ተናጋሪም፤ #አናባቢ #ተነባቢም ና

 

#ድርድር እና የሰው ልጅ። ሕይወት #አናጋሪም #ተናጋሪም#አናባቢ #ተነባቢምት።
 May be an image of 6 people and text
(ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)
"የሰው ልጅ መንገድ ያዘጋጃል
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያዘጋጃል።"
እጽዋት ቅኖች ናቸው። ቅን ባይሆኑ ፍሬ ሳይሆን ትል ያፈሩ ነበር። እኛስ????
ድርድር የፈጣሪ ሥጦታ ነው። ፈጣሪ ሠራሽም ነው ለእኔ። የመኖር ጥበብ ነው። ከቀስት እንድን ዘንድ የመዳንም ምልክት ነው ለእኔ።። ህይወት ድርድር ናት። የድርድርም ውጤት ናት።
የሰው ልጅ እና ድርድር አብረው የተፈጠሩ ናቸው። ድርድሩን ስታፈርሰው ቅጣት ይኖራል። አዳም ከፈጣሪ አምላክ ጋር የነበረውን ድርድር አፍርሶ ነው የሃጢያት መርገም የወረደው። አባ አባት ነውና በፍጥሮቹ ስቃይ ደስተኛ አልነበረምና ስቃዩን እንደ ሰው ሆኖ አይቶ ስቅለትን መረጠ። ስቅለቱ የኃጢያትን ግድግዳ ሰብሮ የእርቅ ድልድዩን ትንሳኤን ሰጠን። የዚህ ትርጉም ማመሳጠር የኔ ፀጋ አይደለም። በቁሙ ንባቡ የሰማያዊ ግርማ ሞገስ ድርድር ሂደቱ ከተሰጠን ስጦታወች የመኖር ጥበብ ውስጥ አንዱ ነው። ለድርድር ልኩ ማስተዋል፤ ጥሞና፤ ፀሎት እና ፈቃደኝነት ነው። ሦስተኛው የግጥም መዐሐፌ "ውል" ነው እርዕሱ።
#ውል። የድርድር አስኳል ነው።
ውል ላልቶ ሲነበብ ትዝታ፦ ሽውታ ይሆናል። ሽውታም በራሱ ጠብቆ እና ላልቶ ሲነበብ የራሱ ትርጉም አለው። ሽውታ ቅፅበታዊነትንም ያመለክታል እንደማለት። ውል ዘመኑ በትርፍ ስሌት የተመሰጠረ ነው። ወይንም ሰጥቶ በቀበል የእኩልዮሽ መርህ። እናት እና ልጅ ውል አላቸው። እንቁላሉ ሰው ለመን ጽንሱ ሀሌት ካለበት ጀምሮ። በመኖር ውስጥ ውል - ድርድር - ስምምነት የሌለበት፤ ክርክር - ሙግት የሌለበት የመኖር ዘይቤ አይገኝም። ዕብን የሚባሉት እንሰሳት ውሻ፤ ደሮ፤ ፈረስ ወዘተ ውል አላቸው። ጋብቻ ስትፈፅም፤ እቃ ስትገዛ እና ስትሸጥ፤ ጓደኝነት ስትጀምር እና ስትቀጥል ውል ድርድር አለበት። ውሉ ድርድሩ ሲፈርስ ደግሞ የሚታጣ፤ የሚቀር ነገር ይኖራል።
ለምሳሌ ችግኝ ስትተክል ውል ነው። እምትፈራው ነገር ይኖራል ያን ለመቋቋም ችግኝ ትተክላለህ፤ በመስኖ ማሳህን ታለማለህ። ገብያ ሄደህ እቃ ስታነሳ ልትገዛውም፦ ላትገዛውም ቢሆን ክርክር፤ ድርድር ስምምነት በውስጡ ይዟል። ልጅህ አባቴ እንዲልህ የምታደርግለት ይኖራል። ልጅህም ልጄ ስትለው የሚሰጥህ አለ። ሳቁ ደስታ ይሰጥኃል። በዬለቱ የሚታዬው እድገቱ ተፈጥሮን የምታይበት የድርድር የውል አይነት ነው።
ስትራመድ ከመሬት ጋር ውል ፈጽመህ ነው። ግራቢትህን ሳትስት መራመድ ከቻልክ መኖርን ታሳምረዋለህ። ከመስኮት፤ ከመዝጊያ ጋርም ውል አለ። መስኮትህን ስትከፍተው ንፁህ አዬር ታገኛለህ። ጫጫታ ሲበዛ ስትዘጋው ሰላም ታገኛለህ። ከቅንጣቱ እስከ ገዘፈው ክስተት ውስጥ ውል አለ። ውሉን የሚያፀናም የሚያፈርስ ክስተትም አለ። ተፈጥሮን ዕውቅና መስጠት። በተፈጥሮ ፀጋ ውስጥ እንደምን ስምም ሆኖ መኖር እንደሚቻል ጥበብ ይጠይቃል።
የነቃው የህሊና ክፍል በውል በሚታዬውም በማይታዬውም የመፈጠር፤ የመኖር፤ የማመን፤ የመተዳደር፤ የማስተዳደር #ሰቅ ውስጥ ድርድር አለ። ውል አለ። በዝምታ ያለ ስምምነት አለ። ስደተኛ ሲሰደድ የሚሰደድበትን አገር ህግ፤ ባህል፤ እምነት፤ ትውፊት፦ ታሪክ ውስጥ ከቻለ የራሱን አሻራ ጨምሮ፤ ካልቻለም ያለውን ሥርዓት ሰጥ ጥቅም ዕውቅና ሰጥቶ አክብሮ ይቀበላል፤ ይፈጽማል። ትልልፍ ከመጣ ቅጣት ይከተላል።
ፓለቲካ ሰው ነው በእኔ ትርጉም። በቀላል ፍቺ በመንግሥት አስተዳደር መሳተፍ ነው። ፖለቲካ የሰው ከሆነ፦ ፖለቲካ በመንግሥት አሰተዳደር መሳተፍ ከሆነ ተሳትፎ #ህግ #አልባ አይደለም። #ውል አልባ አይደለም። #ንግግር አልባ አይደለም። #ስምምነት አልባ አይደለም። አንዲት ሴት በእንዝርት ስትፈትል ጥጡ፤ የእንዝርቱ እንጨት ሸንበቆው፤ ቃሪያው በስምምነት ተፈጥሮ አብቅሎ ከሰጠው በተቀረፀ ብልሃት ነው ልብስ በሽመና የሚገኜው። ከሽመና በፊት የገዘፋ ተግባራት ተከውነዋል። ጥጡ እንዴት ተገኜ? በገበሬ እና በተፈጥሮ ስምምነት የመጣ ነው። ሰሊጥ አፋን ከከፈተ ይረግፋል። ስለዚህ የሰሊጥ ገበሬ እናትህ ሞተች ቢባል አይሰማም። ሰሊጥ ተፈጥሮ ጋር የገባው ውል ስለሚፈርስ ተጣድፎ አጨዳ መከወን አለበት። ውሉን ካፈረሰ ሰሊጥዬ ክንብል ብላ የአፈር ሲሳይ ትሆናለች።
ውል፤ ድርድር፤ ንግግር ማቹሪቲ ይጠይቃል። ለድርድር የወቅት፦ የጊዜ የብቃት ልክን ማወቅም ይጠይቃል። ማቹሪቲ ስል የዕዕምሮ ጮርቃ ለማለት አይደለም። ውል ለማድረግ ያለው የአቅም እና የተጨባጭ ሁኔታወች መስተጋብር ማልዷል፤ ረፍዷል ውሏል መሽቷል ይህ ሁሉ ሊታይ ይገባል። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ለሎሪት ሲታጩ ማቹሪቲ ይታይ ብዬ ሞግቻለሁኝ። አይሸለሙ አልነበረም የእኔ ሙግት አራዝሙት እና ለኳቸው አትትጣደፋ፦ ሽልማቱ በሚሰጠው ጉልበት በሰባዕዊነት ላይ ሊደር የሚችለውን መከራ ጊዜ ይገስፀዋል፤ በኢትዮጵያ የተቋማት ችግር ስላለ ጥንቃቄ ይሻል ነበር ያልኩት። አልሆነም።
ቢዘገይ ኖሮ ሎሬትነቱ #ጦርነቱ #ላይኖር ይችል ነበር። የ16 የምስጋና ሰልፍ እራሱ ችኩል ነው ብዬ ሞግቻለሁኝ። ያ ማለት የህሊና ብቃት አንሷል ሳይሆን ጊዜ የሚሰጠን ኢንፎርሜሽን ስላለ ነው። ውል የድርድር፤ የክርክር ውጤት ነው። ውል #ሀ ሲል ስምምነት ተደርሷል ማለት ነው። የድርድሩ ውጤት ስምምነት ነው። ስምምነት የመሻት የመፈለግ ቀለበት ነው።
ስምምነቱ በገቢር ነው የሚታዬው። የመጀመሪያው ቃል ነው። "መጀመሪያ ቃል ነበር፦በእግዚአብሄር ዘንድ ነበር፦ ቃልም በእግዚአብሄር ዘንድ ነበር። ሁሉ በእርሱ ሆነ፦ከሆነውም አንዳችስ እንኳን ካለርሱ የሆነ የለም።" ቅዱስ የኋንስ ምዕራፍ አንድ።
እርግጥ ነው በዓይን በስሜት ህዋሳት የሚፈፀሙ ውሎች አሉ። ንግግር ሳይደረግ።እናታችንበዓይኗ ነበር የምትመራን። በንግግር ከሆነ ግን #ቃል ነው የሚሆነው። ቃሉን ሰጠ ሲባል ምንማለት ነው? ቃሉን ጠበቀ ሲባልስ? ቃሉ ተራዘመ ስንልስ? ቃሉ ተሰረዘ ሲባልስ? ቃሉ ዕውን ሆነ ስንልስ? ቃሉ #አሰበለ ሲባልስ? በህይወታችን አስገብተን እንፈትሸው። ግብረ መልሱን በአኗኗር ዘይቤያችን ላይ የሰጠው ትፍስህት፤ የፈጠረው ተጽዕኖም እንለካው።
ፖለቲካ ፍጥረተ ነገሩ #የንግግር ዓውድ ነው። አንደበቱ ርቱዑ ያልሆነ በፖለቲካ ህይወቱ መሪነትን ከፈቀደ እጅግ ከባድ ይሆናል። የፖለቲካ የሠራ አካላቱ የቀይ ይሁን ነጭ ደም ሴሉ ተቦክቶ እንጀራ መስጠቱ መነሻው መድረሻውም #ንግግር ነው። ለችግርም ለመፍትሄም፦ ለስኬትም ለውድቀትም ሁሉም የሚያልፈው ፦በንግግር ነው።
ምርጫን ብንወስድ #የጨመተ ድርድር ነው። ጉባኤወች፤ ስብሰባወች፤ የበጀት ፍሰት እና ሂደት፤ የሠራተኛ ቅጥር እና ስንብት ድርድር ነው። በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ህዝብ አመነበትም /// አላመነበትም ከህገ - መንግሥቱ ጋር ድርድር አለው። ለውሳኔው ተገዢ ይሆናል። ባይስማማው እንኳን ያ ህግ ሥራ ላይ እስከሆነ ድረስየውዴታ ግዴታ አለበት። ከዛ ህግ በላይ ላለመውጣት። እኔ ኢትዮጵያ በተፃፈ ህግ እንደሚተዳደሩት አገሮች ባልተፃፈ ህግ ትተዳደርአለች። በተጨማሪም ባልተፃፈ ህግ እንደሚተዳደሩ በህገገመንግሥትትተዳደራለች። በጥምር ህግ ነው የምትተዳደረው።
አሁን እኔ ሲዊዝ ነው እምኖረው። ነገር ግን እምሠራው ለህዝቤ እስከሆነ ድረስ ህግ እንዳልተላለፍ፤ በማህበረሰቡ ዘንድ #ጥዩፍ እንዳልሠራ እጠነቀቃለሁ። ለምን? ከህግ በላይ ስላልሆንኩኝ። ማህበረሰቤ የማይፈቅደውም አንዳች ነገር አላደርግም። የሲዊዝ ህግን በመፈፀምም ከሚገባው በላይ ጥንቁቅ ነኝ። ሌላው ቀርቶ ሰንበት ላይ ሚክሰር አልጠቀምም። ከመሽ ከ4 ሰዓት በኋላ ሙቅ ውሃ ስለምጠጣበ ማሽን አላፈላም። በምድጃ አፍልቼ እጠጣለሁ። በር ስዘጋ እና ስከፍት እጠነቀቃለሁ። በሙሉ ሕይወቴ በርም መስኮትንም በኃይል ዘግቼ አላውቅም። ቁሶች ለአገልግሎት እንጂ ለዱላ አልተፈጠሩም የሚልም ፍልስፍና አለኝ። ለምን? ከህግ በላይ መሆን ስለማልፈልግ። በዬለት ኑሮ #ንግግር አለ። ድርድር አለ። ቋሚ ውል አለ። ግን በጋራ ስምምነት ጎረቤቶቼን ሰላም የሚነሳ ነገር በፍፁም አልፈፅምም። ፍፁም ነኝ አይደለም። እጠነቀቃለሁ።
በፖለቲካ፤ በማህበራዊ፤ በኤኮኖሚ፤ በዕምነት፤ በሃይማኖት ዙሪያ ምንጊዜም #ድርድር ይኖራል። ወንጌል እንዴት ተስፋፋ? ቁርዓንስ እንዴት ተስፋፋ፤ በቁርዓን፤ በወንጌል የሚያምኑ እንዴት ተገኙ? በንግግር ነው። በድርድር ነው። በስምምነት ነው። አንስማም የሚሉ አሉ። ሃይማኖት የሌላቸው። ያም የንግግር ውጤት ነው። ምንጊዜም #ንግግር ይኖራል።
#አንደበታችን የተሰራው እኮ #ለመነጋገር ነው። ንግግር አይዘጋም። ንግግር #ኢትዮጵያኒዝም ማዕቀብ አይጣልበትም። ያ ከሆነ ፈጣሪን ማስከፋት ይሆናል። ለምን አንደበት? ስለምን ጉሮሮ፤ ስለምንስ ትናጋ፤ ስለምንስ ላንቃ፤ ስለምንስ አፍንጫ ስለምንስ ደረት፤ በጥቅሉ እናገርዘንድ፤ እሰማ ዘንድም ለምን ፈቀድክ? ዓይነት ነው።ትግሉ ከሰው አልፎ አምላክን የሚሞግት ይሆናል። ግን መሪ ያለ ንግግር ይፈጠራልን? ይኖራል??? እያንዳንዷ የተሰጠን የአካል ክፍል ተመርቆ የተሰጠንነው። ምርቃቱን ሥራ ላይ ማዋል ዬባለቤቱ ነው። ልጁን፤ ሚስቱን፤ ጎረቤቱን፤ ባልደረባውን፤ የበታቾችን ሁሉንም የሚያገኜው በዳሰሳ አይደለም። የሰው ልጅ ፈጣሪውን የሚያገኜው እኮ #በንግግር ነው። እጅ የንግግር አካል ነው። ዓይን የንግግር አካል ነው። ሆድም ቋንቋ አለው። ህፃናት በምድር ሲመጡ ያለቅሳሉ። ንግግር ነው። ጩኽት ንግግር ነው። እልልታ ንግግር ነው። ዋይታም ንግግር ነው። ዕንባ ንግግር ነው። ወዘተ …… #ሳቅም ንግግር ነው።
ረቀቅ ባለው የገኃዳዊ ዓለም እና የመንፈሳዊ ፀጋ የጋራ ድርድር የእንቁላል የዘር እና የፈቃደ እግዚያብሄር የውል ስኬት ነው።
#ርገት ይሁን።
#በንግግር ጥበብ የአካል እንቅስቃሴ የጥበቡ አካል ነው። የንግግር ቁንጮ ጉልላት ግን ኃያሉ አጤ ቅንነት ነው። ቅንነት የሁሉም ችግር መፍቻ ነው። ለፍቅርም ቅንነት ይጠይቃል። እግዚአብሄር እንዳይከፋው፤ ከፍቶትም ምርቃታችን እንዳይነሳ በተፈጥሮ ውስጥ ለመኖር መፍቀድ ይገባል። #መመረቅንም ውጊያ እንግጠምህ ካልተባለ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ክብሮቼ እንዴት ነን? አይዞን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
01/06/2024
ጊዜ ራዲዮ ነው።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።