የሚነግሩን ሳይሆን የማይነግሩንን የሚያደርጉት ጠሚ አብይ አህመድ። ዕውን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ሥልጣናቸውን ለማስከበር ዝግጁ ናቸውን?

 

የሚነግሩን ሳይሆን የማይነግሩንን የሚያደርጉት ጠሚ አብይ አህመድ።
ዕውን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ሥልጣናቸውን ለማስከበር ዝግጁ ናቸውን?May be an image of one or more people and text
 
 May be an image of 3 people, overcoat and the Brandenburg GateMay be an image of 1 personMay be an image of one or more people, crowd and textMay be an image of 1 person
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
እንዴት አደርን? እኔ ረጅም ጊዜዬ ነው በሳቸው ንግግር መነሻነት ሙግት ካቆምኩ። ዋነኛው ምክንያት ተደማሪወቻቸው በጽኑ እዬሞገቷቸው ስለሆነ እረፍት ቢጤ፤ ሁለተኛው ግን ጠሚ አብይ አህመድ አሊ የሚነግሩንን ሳይሆን #የማይነግሩንን ስለሚሠሩ አሳቻነታቸውን ስለማውቅ አዬር ላይ ለሚቀር ንግግር ጊዜም አቅም ማባከን አይገባም በሚል ነው።
#ጦርነት እና አብይዝም።
የሆነ ሆኖ የመተማውን ሰማዕት አጤ የኋንስን ዘለው አጤ ሚኒሊክን እና አጤ ቴወድሮስን አንስተዋል። ያ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ፍቅር ደፍተው እራሳቸው መሬት እዬደበደቡ ጦርነት አምጣልኝ "ጀግና" ተብዬ ልመስገን፤ ልሸለም፤ ልክበር ብለው በልቅ እና ባልተገራ ንግግር ከአለቆቻቸው ጋር እልህ ተጋብተው ነበር ጦርነት የጀመሩት። ከዛም በፊት ኮረና እንደመጣ ያልተመረመረ ወታደር በላስታ እና በጎንደር ልከው ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት የቀደመ ጨካኝ ተግባር ፈጽመዋል። ያስቆመው የአክቲቢስት ሙሉነህ የኋንስ ፒቲሽን የማሰባሰብ የመሞገት ተግባር ነበር። የአቶ ጃዋር ከበባም ሌላው ሳይለንት ጦርነት ነበር፤ የአርቲስት ሃጫሉ ግድያም እንዲሁ፤ የአማራ ክልል ሊቃናትን #መተራም ቀውስን ከመናፈቅ የመጣ ክስተት ነው። በአባይ ግድብ የኮፒ ራይት ሽሚያ መሰናዶም ትጉሁን ኢንጂነር ስመኜውን መበቀል፤ ቀብሩበእገዳ መከወን።
በ100 ቀኑ የትጋት ጉዟቸው እርገት አፋር ክልል ነበር። "ደርግ የወደቀው ሰው ስለፈጀ ነው ብለውን ነበር።" በወቅቱ በፋክትም ሞግቸወትነበር። በርስወ ዘመንስ አንዲት ቅንጣት ማዕልት ካለ ሰኔል እና ቹቻ ሰብር ዜና አልፈን እናውቃለን። ለቀብር የታደሉት የታደሉ ናቸው። ለአራዊት በድናቸው የተሰጡ ወገኖችም አሉን። የተቃጠሉም። በቅርቡም ሻለቃ ናሆሰናይ እና ጓደኛው እሬሳ አንሰጥም ውሳኔም የሥርዓተወትን ሰላማዊነት፤ የምርኮ አያያዝ ጥበብ ሳይሆን ውድቀት ልክ ያሳዬ ዕውነት ነበር። በገዳይም በሟች ማህል የኢትዮጵያ እናቶች አለ። በዝምታ ውዳሴ ከንቱን አሻም ያልን ኢትዮጵውያን በትጋታችን ውስጥ ለድምጽ አልባ የኢትዮጵያ እናቶች ድምጽ በመሆን ተደማጭነት ስላገኜ ነበር እርስወ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የመጡት። ፈፃሚው አካል ሹክ እንደሚለወት አምናለሁ። የመጀመሪያ ካቢኒወት 50% ሴቶች እንዲሆኑ ምላሽ የሰጡት በዛ ምክንያት ነው። ይህ ፋክት ነው።
ሌላው አሁንስ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥም በመላ ኢትዮጵያ በሚገኝ አማራ ላይ ያወጁት ጦርነት በድሮን ተደግፎ የሚካሄደው አብይዝም ሠራሽ ሰው ፈጂ ጭካኔ መሆኑን ዘነጉትን? ወይንስ ጦርነቱን ስውር ኃይሎች በመንፈስ ያሉ ይሆን ዓዋጁን እዬሠሩበት የሚገኜው። መቼ ነው ንግግርወት፤ ቃልወት እና እርስወ እርቀ ሰላም የሚያወርዱት?
"እኛ ዝሆን ነን እንቀረጥፋለን፤ እንሰብራለን #እንበላለን" ባሌ ሶፍ ኡመር ዋሻ ሲሉ ዝም ብሎ የሚበላ ማህበረሰብ መኖር ነበረበትን? የሰሞኑ የወለጋ የትምክህት ንግግርስ የትኛው ባንክ ይቀመጥ የገዳ ኤኮኖሚ ዞን ላይ? ያው በትጋት ለሚሰሩት ፕሮፖጋንዲስቶችወ ስንቅ ማቅረብ ይመስለኛል። ስላለቀበወት። እንጂ ከሚሊዮን በላይ በሰው ሰራሽ ቀውስ የሚያልቀው #ኢንሴክት አይደለም የሰው ልጅ እንጂ። የኢትዮጵያን የህዝብ ቁጥር መቀነስም ስውሩ ፕሮጀክት ስለመሆኑ ዛሬ ሳይሆን የዛሬ ሦስት ዓመት ጽፌበታለሁ።
"#ሥልጣን እንለቃለን በሪፍረደም።" ኦዬ¡¿¿¿ እርስወ???
እርስወ??? "በቀን 100 ሺህ አርዳለሁ "ሥልጣኔ ከተነካ ያሉት? ኮሽ ባለ ቁጥር ፊደል የቆጠረ አማራን ሲገድል፤ ሲያስር፤ ሲያግት፤ ሲያሰድድ ውሎ የሚያድረው ያልተረጋጋው መንፈሰወ ይሆን ሥልጣንን በሪፍረንደም የሚያስረክበው? "ሽግግር" የሚል ቃል የሚያስበረግገወ መሆኑን እኮ ተጀመሮ እስኪጨረስ ከማንም ያልሆን #ለተገፋት ብቻ በራሳችን ወጪ እና ጊዜ የዕንባ ዋናተኞችን ድምጽ ለማሰማት ለምንተጋው እንኳን የሚናገሩትን ሳይሆን #የማይነግሩንን እዬሠሩ መሆኑን እናስተውላለን? ግን ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት በዬትኛው አገር ሥልጣኔ ሥር ቅኝ እዬተገዛች ይሆን? ዕውነቱ እርስወ ፓንአፍሪካኒስት ሳይሆኑ ፓን አረቢክ እንደሆኑ ይሰማኛል። በ2923 ጥምቀት በዓል የሚዲያ ቅንብር በአረብኛም ነበር። ቋንቋ ዕውቀት ነው ብዬ ባምንም እርስወ እና መንፈሰወ አሳቻ ስልሆኑ የአሉታዊ ዴሞግራፊ ስለመሆኑ ይረዳኛል።
አዛን እና ማህሌትን ሲያነሱ ዘመቻው ምቹ እንዲሆን ለዬትኛው ህዝብ እና አገር ሉዑላን የእረፍት ፓራዲዝ ሴሪሞኒ እዬሠሩ እንደሆን አይገባንም፦ አናውቅምን????? አንዲት ሰከንድ ለገደላቸው፤ ላሳደዳቸው፤ ለሚገፋቸው ዜጎቹ #አይዟችሁ ያላለ፤ #ያላጽናና#የሃዘን ቀን ያላወጄ #አለት ልብ ያለው አገዛዝ የህዝብን ድምጽ አክብሮ በህዝብ ድምጽ ሥልጣን ሊያስረክብ???? ኢዮቤል ቤተ - መንግሥት የሚያሠራ? ሰርክ በግብረ ሰላም መላሾ ካድሬን ሲቀልብ ውሎ የሚያድር ሥርዓት በህዝብ ድምጽ ሥልጣን ሊያስረክብ???? ፈቅዶ እና ወዶ ለዛውም።
ማስፈራሪያው ይታወቃል። እኔም እምፈራው እሱን ነው። ኢትዮጵያን ወደ አሰቃቂ የርስበርስ ጭካኔ የሚያስገባ አዘጋጅተው እንዳሉ በሚገባ ይገባኛል። ለዚህ ነው ኃይል አዋጪ መንገድ አይደለም የምለው። ጠሚር አብይ ፈቅደው ወደው ሥልጣናቸውን የሚለቁበት ሥራ ይሠራ የምለውም። ብዙውን ነገር ቲካ ቲካ ሳልልም በተደሞ እመከታተለው። ኢትዮጵያ በዘመኗ ውስጥ እንዲህ ዓይነት #አስፈሪ ዘመን አይጠብቃትም። በእኔ መረዳት።
ትንሽ ስቄያለሁ። ሲዊዝን ልምሰል ሲሉ። የርስወ ሪፍረንድም #ማት እና #ምጥ ይዞ ይመጣል። ብዙ ሰው ያልቃል። ብዙ ሰው ይታሠራል። ብዙ ሰው ለካቴና ይገበራል። ብዙ ሰውም ይሰወራል። ይህን የሚፈቅድ ብቻ የርስወን ሪፍረንድም ይፈቅዳል። #ተመድ #ታዛቢ ሠራዊቱን ከላከ ብቻ ሊሆን ይችል ይሆናል።
ያም ቢሆን የእርስወን ሰብዕና በቅጡ ተረድቶ በቅጡ ቅድመ ዝግጅቱን ማሟላት መቻል ይኖርበታል። በትንሽ መስዋዕትነት ሰፊ ትርፍ። ዘጠና ደቂቃ በኢንተቤ አይነት። ይህ ደግሞ በዲፕሎማሲ አካላት በጥንቃቄ ሊፈፀም የሚችል ከሆነ ብቻ። ዶር አብይ አህመድ በሰብዕና አገነባብ እና ተመክሮ በጥንቃቄ ሊታዩ የሚገቡ መሪ ስለሆኑ ነው እኔ ቤርሙዳ ትርያንግል የምለው። ብስጭት፤ ግልፍተኝነት፤ የድረስ ድረስ ጉዳይ ሁሉም አትራፊ አይመስለኝም። ላቂያ ማስተዋል ይጠይቃል።
ብዙ ጊዜ አዲስ ሥርዓትን ተስፋ የሚያደርጉ ቅንጥብጣቢ ነገሮችን ገጣጥሞ "አለቀለት፦ ባዶ ቀርቷል፥ አይቆይም፥ አፋፍ ላይ ነው" ሲሉ እሰማለሁኝ። አይደለም አብይዝም ሙሉ መሰናዶ ያለው ህወሃትም አለቀቀም፦ በሚባለው፤ ተስፋ በሚደረገው መልኩ በአጭር ፍላጎት እና ትጋት ሊሆን እንደማይችል ይገባኛል። ብርቱ ጥንቃቄ እና ያልተቆራረጠ አቅም እና ብቁ በሳል አስተዋይ አመራር እና አማራጭ ሃሳብን የሚጠይቁ መስኮች አሉ። ዶር አብይም ልባቸውን ሞልተው የሚናገሩት ለዚህ ነው።
ለቀኑ ቀን ሲሰጠው ስኬት ይሆናል። ለእግዚአብሄር የሚሳነው ነገር የለም። ይህ ሁሉ ጭንቀት፤ ይህ ሁሉ መከራ አማኑኤል በቃችሁ ያለን ዕለት ይሆናል። ተስፋችን አምላካችን ነው። ይህንን የምለውም ህወሃት እንዴት ከመንበረ ሥልጣኑ እንደለቀቀ ጠንቅቄ ስለማውቅም ነው። ስለ ሁሉም ነገር ዕንባ መልስ ሰጪ አለው የላይኛው። ሰከንዷ የምትወሰነው በእግዚአብሄር በአላህ ነው።
ግን ሊታመሙ ወይንም የባሰ ነገር በተፈጥሮ ሊመጣም ይችላል? የፈጣሪ ፍርድ ረቂቅ እና ኃያል ነውና። እንደ እኔ በህይወት እያሉ ግድፈቱ ታርሞ " ሽግግርም፤ ጥምርም የሚለው ሃሳብ ነፃነት ተሰጥቶት ቢታይ ባይ ነኝ። እኔ በግሌ ኢትዮጵያ አጽናኝ፤ አይዞሽ ባይ ቲም ያስፈልጋታል። የፖለቲካ ድርጅት ልኳ ስላልሆነ ሰባዕዊና ተፈጥሯዊ የሆነ ቲም ቢመራት የሚል ፕሮፖዛል ያቀረብኩት። ሲዊዝሻ ሪፍረንደም በሁሉም ጉዳይ የሰለጠነባት ቅድስት አገር ናት። አንድ ጠቅላይ ሚር የላትም። ሰባት ናቸው። ታዩ ከሆነ በዬትኛውም ህውከት ጉዳይ ንቁ ተሳታፊ አይደለችም በሰከነ ሰባዕዊና ተፈጥሯዊ ሥርዓት ስለምትመራ። እና ምኞቴ የቅድስቷን ተመክሮ ፈጣሪ ያድርገው ነው። ፖለቲካዊ ፓርቲወች አሉ ግን ሰዋዊ እና ተፈጥሯዊ ናቸው። ሰው ከሰለጠነ ተፈጥሯዊነትይገዛው ላልሰለጠነው ደግሞ አራዊትነት።
#ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ።
የእኔ ዕይታ የትኛውም ሥርዓት የራሱን ዓርማ ሊያደርግ ይቻል። የኢትዮጵ ሰንደቅ ዓላማዋ ግን ንፁሁ #አረንጓዴ ቢጫ ቀይ በቋሚነት ሊሆን ይገባል። በቋሚነት። ይህ ማለት ያለው ሥርዓት የራሱን ይዞ በባዕላት መውጣት ይችላል። ንፁሁን የሚፈልግም ንፁሑን ያለምንም ገደብ ይዞ እንዲወጣ ቢደረግ ሪፈረንደም አያስፈልገውም።
እርስወ የሚፈልጉት የገዳወኦዳን ነው።። ድምጽ ውሳኔ #ላላንቲካ ነው። (ላንቲካ ፍቹን ቀዳማዊቷን ይጠይቁ)። ለዚህ ነው የምክክር ኮሚሽኑ ለመቀበል ያቃተን። ጠቅላይ ሚር አብይ የሚናገሩት #የማያምኑበትን ነው። #ሳይነግሩን የሚያደርጉት ደግሞ ያቀዱትን ነው። ያ ደግሞ #ገዳን በኢትዮጵያ ላይ መጫን። ይህን አይሰቡት። የአብይዝም ገዳ የመቃብር ሥፍራ ስለመሆኑ ዛሬ ዓለማችን አህቲ ድምጽ ላይ ነው። ዕውነቱ ይህ ነው። ገዳ ድሮ እና ዘንድሮ ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገነም። እያዬነው ስለሆነ።
ቀድሞ ነገር አሉታዊ ዴሞግራፊ ቁልጭ ያለው መርሁ #ፋሺዝም ነው። ስድስት ዓመቱ በፋሺዝም ቀመር አዬን። ነገስ? የፈጣሪ ሥራ ይጠበቃል። ፋሺዝም እና ሪፍረንደም??????
ስለ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ከተነሳ የእኔን ተመክሮ ላጋራ። ሲዊዘርላንድ ዙሪክ ከተማ የ193 አገሮች የፊት ገጽ ኤግዚቢሽን ለመሥራት ታቀደ። እኔ በፀጋዬ ራዲዮም፤ ያን ጊዜ ቲያትር ስልጠና ላይ ነበርኩኝ በተቋሙም ሪኮመንድ ተደረኩኝ። የቀጠሮ ቀን ከመድረሱ በፊት ምን ለብሼ የሚለውን መልክ ለማስያዝ ተሰናዳሁ። ገዛሁም። የቤቱን ልብስ የተገዛውን አዲሱንም ሞከርኩት። አልረካሁም።
ከዛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቁን ቲ ሸርት ስለብስ ውበት በብርሃን ሆነ። ከዛ ወሩ የካቲት ስለነበር ለወቅቱ የሚስማማ ልብስ ለብሼተገኜሁ። ያው ለሞድ ከተቀጠረው ቢያንስ 30 ደቂቃ መቅደም ያልተፃፈ ህግ ነው። ከዛ ልብሴን ለብሼ ስገባ የተለመደ ሰላምታ ተሰጠኝ። ገብቼ ክብሬን ለብሼ ስወጣ ግን ሁሉም ተነስተው ተቀበሉኝ። ይህ የሰው አይደለም። የፈጣሪ ነው። እኔ ራሴ ደነገጥኩኝ። ፎቶ ያነሱኝ ባለሙያወች አልነበሩም። #ማናጀሩ እንጂ። ከዛ በኋላ ለ45 ደቂቃ በቡና ግብዣ ሥራ አስኪያጁ ጋር ተጫወትን። በልዩ ሁኔታ መጽሐፋ ላይም የኢትዮጵያ ገበሬ ስሎጋን ነበር።
በመፀሐፍ መልክ ታትሟል። ወደ አራት ኪሎ ይመዝናል። ለወር ያህል ዙሪክ ከተማ ላይ የመንገድ ላይ፤ ዬተቋማት ላይ ኤግዚቢሽን ነበር። ኢትዮጵያ ሚስጢሯ ያለው #በሰንደቋ ውስጥ ነው። ብዙ አፍሪካውያንም የሚስማሙበት ነው።
አይታወቅወትም? የኢትዮጵያን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማን፤ የአማርኛ ቋንቋን፤ የአማራን ሲብላይዜሽን ግዞት ላይ እንዲሆን አድርገውታል እኮ። በዬትኛውም ብሄራዊ ውድድር በውስጣቸው በውጫቸው ብሄራዊ ሰንደቁን የመሰጠሩ በመንግሥት ተቋማት ሚዲያወች ሳይቀር ይለፍ አይሰጣቸውም። ይህ እኔ አበክሬ እምከታተለው ዕውነት ነው። ፋና፤ ኢቲቢ፤ ዋልታ፤ ኤንቢሲ ሁሎችም ወጣቶችን የሚኮተኩቱበት ዓውደ ምህረት መብራቱ ሳይቀር ከአረንጓዴ ቢጫ ጋር የተጣላ ነው።
የአፍሪካ አገሮች የፓን አፍሪካ መሪ ሰንደቅ ያደረጉትን በርሰወ ዘመን ዴሞግራፊ እንዲሰራበት የሚፈቅድ ኢትዮጵያዊ እራሱን ይጠይቅ። ነፃነቱን ለባርነት እንደገበረም ይቁጠረው። እኔ በቤቴ ውስጥ ታቦት እንዳለኝ ነው የሚሰማኝ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማዬ በክብር አለና። አንቲ ዲስክርምኔሽን ቢሮ ስሳተፍ የአለቃዬ ቢሮ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ነበረው። አንባሳደሮች አለንለት። እርስወ ዘቅዝቀው ሲለብሱት አዝንለወታለሁ። ሚስጢሩ እራሱ መንበረ ሥልጣነወት ርጉ ያልሆነ የሚያረገርግ እንዲሆን እንደሚያደርግ አምናለሁ። ያፈሰሱት የህዝብ ፍቅር ወርቅ ነበር። ወርቅ ደግም ቀልጦ ከፈሰሰሰ አይታፈስም።
እመ ቅኒትን ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ፈተኗት። መለያዋን አሰቀዬሯት። #ቀናትን??? ለማስታገሻ ያሰሩት ዓርማ ሥልጣነወትን እያደላደሉ ሲመጡ ይህንንም # በድጋሚ #እንደሚበውዙት እረዳለሁ። መወሰን ያለበት የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ አይደለም። አፍሪካውያን። ጃማይካውያኑም ናቸው። መንፈስ ቅዱስ ነውና። እሱን ተፃረው ቆሞ። ያሉበትን ጊዜ የሚያውቁት እርስወ ነወት።
በመጨረሻ የእርስወ ወንበር ዬለም። ያለወንበሩ ጠሚር ማለት ይቀላል። ይህን 2011 ወንበሩ ባዶ ነው ብዬ ጽፌበት ነበር። ገና በለጋ በሥልጣን ዘመነወት። ወንበረወት መሄድ … መሄድ … መሄድ … መሄድ። ማይክ እና ካሜራ ስለሆነ። ይልቅ የሲዳማ እና የሱማሌ የአፋር ፕሬዚዳንቶችን ለአጀብ ባይጠሩ። ትጉኃኑ ሥራቸውን ይሥሩበት። አያውኳቸው። እባክወት? ቀሪወችን ይዘው መጓዝ ይችላሉ። ሥራ ላይ ያሉትን ግን ሥራ አያስፈቱ። እባክወትን?
ሌላ ያ የሚሊዮኖች ተቀባይነት መንግሥት ሚዲያ ላይ ያለውን አድማጭም ይዩት። ምላሽ ስለሚሰጠወ።
#የዴሞክራሲ ተረብ።
በህዝበ ውሳኔ ለሚፀድቅ ተገዢ ነን። ማን ፈቅዶላችሁ ይሆን ሁለት ጊዜ ጦርነት ያወጃችሁት? ማንፈቅዶላችሁ ይሆን ሸገር ከተማን እንመሠርታለን ብላችሁ ህዝብን የወረወራችሁ? ማንፈቅዶላችሁ ነው ግራ ቀኝ ቤተ መንግሥት ለመሥራት ያቀዳችሁት? ማን ፈቅዶላችሁ ነው የአማርኛ ቋንቋን የሥራዊ ውሳኔን የሻራችሁ? ማን ፈቅዶላችሁ ነው የአጤ ሚኒልክን ቤተመንግሥት የበወዛችሁት? ማን ፈቅዶላችሁ ይሆን ኢንጂነር ታከለ ኡማን ከንቲባ ለአዲስ አበባ ያደረጋችሁት? ማን ፈቅዶላችሁ ይሆን ፒያሳን የናዳችሁት? ማን ፈቅዶላችሁ ይሆን የኮሪደር ልማት ብላችሁ በህዝብ ሰቆቃ ሥልጣኔ አመጣን የምትሎት? ሚሊዮንክስተቶችን ማንሳት ይቻላል።
ለመሆኑ በራሱ የሚተማመን ሰብዕና የአስመራጭ ኮሚቲ ሰብሳቢ ሆኖ ለራሱ እራሱ ሰብሳቢም ድምጽ አሰጭ የሆነው የት አገር? የት ቦታ? የትኛው ድርጅት? ከእርስወ በስተቀር። ደቡብ አፍሪካን እዬተከታተሉ ነው አይደል???
#ይከወን።
ንግግሩ የመጋቢት 16/2010 ዳግም አዝለኝ እዘለኝም ተንሳኤው ይመስላል። #በሌሉበት አመክንዮ ማለት መሆንን አያጎናጽፍም።
ውዶች እንዴት ናችሁ???
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02/06/2024
ፍቅር ሲያልቅ ትዕግሥት ይሰደዳል።
ትዕግሥትም ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።