#እኔን። #የጋሞሞይቱ #ገራገሯ #እንስፍስፏ #እናት እናት ሆይ!

 

 
#የኢትዮጵያ መንግሥት፤
#የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት፤
#የኢትዮጵያ ሴቶች፤ በጋራ እና በወል ብሄራዊ ንቅናቄ ሊያደርጉበት የሚገባ እጅግ አሰቃቂ ክስተት ነው። 
 
 
#የጋሞሞይቱ #ገራገሯ #እንስፍስፏ #እናት እናት ሆይ! እንደምን ውለሽ አደርሽ ወይ?
 
"አቤቱ አምላካችን ሆይ! እንደ ቸርነትህ ብዛት ምህረትን ላክልን።" አሜን።
 
 May be an image of text
 
#የጋምይቱ ደጊቱ እናትዋ ሆይ!
 
ይህን የመሰለ የሰው ልጅ ሊሸከመው #የማችልወን አሳር በየትኛው አቅምሽ ቻልሽው ይሆን - አንቺ የደጋጎች እናት?
ልበ ንጹኋ የጋሞ እናት ሆይ! እንደምንስ #መሽቶ ይነጋልሽ ይሆን? 
 
ሳታስቢው፤ ሳታቅጂው ይህን የመሰለ የዕንባ #ናዳን እንደምን ተሸከምሽው ይሆን?
እንደምንስ? እንዴትስ ባለ ሁኔታ በዚህች ደቂቃ ትሆኚ ይሆን?
 
እናት ሆይ! ማን ካጠገብሽ አለ?
ማንስ በቅርበት #እያጽናናሽ ይሆን?
ማንስ #አይዞሽ እያለሽ ይሆን?
 
በዚህ ሁለመናው በከበደ፤ ሁለመናው በጨለመ #ጨቀጨቅ ማት ውስጥ ሆነሽ ምን ታስቢ ይሆን?
#እኔን! #እኔን! አንቺ ከልተመታሜ፤ አንቺ ባተሌ፤ አንች ትጉህ፤ አንቺ #የገርነት መለኪያ እንዴት እየሆንሽ ይሆን?
ፈጣሪ አምላክ የራሄል #ዕንባ ያዳመጠ አምላክ ለአንቺ ይደርስልሽ ዘንድ እማጸነዋለሁኝ።
 
ዕንባሽ፤ ጭንቀትሽ፤ ስቃይሽ፤ ሃዘንሽ ሁሉ ድቅን ይልብኛል።
አንቺ ብርቱ የጋሞ እናት ሆይ! እግዚአብሄር አምላክ #መጽናናቱን ይስጥሽ። አሜን።
 
አንቺ #ገራገር የጋሞ እናት ይህን መከራ ፈጣሪ አምላክ #የመጨረሻ ያድርግልሽ። አሜን።
አንቺ ደግ #የጋሞዊቱ ሩህሩህ እናት ይህን መከራ የመጨረሻ ያድርግልሽ። አሜን።
 
እናት፤ እምዬዋ የነገ ተስፋሽሽ ምን ይሆን? ያስጨንቃል። ያስጠብባል። ያሰቃያልም። 
 
እንዴት አመሻችሁ ማህበረ - ቅንነት።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን፤ አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
13/03/2026
ጌታ ሆይ! ምህረትህን፤ ይቅርታህን እባክህ ላክ። አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።