ከቶ የአላዛሯ ኢትዮጵያ ባለቤቷ ማን ነበር?
ከቶ የአላዛሯ ኢትዮጵያ ባለቤቷ
ማን ነበር 27 ዓመት ሙሉ?
„እግዚአብሄርም ቃየልን ወንድምህ አቤል ወዴት ነው
አለው፤
ቃዬልም እኔ የወንድሜ የ አቤል ጠባቂ እኔ ነኝን
አለ።“
መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ፳፰ ቁጥር ፬
ከሥርጉተ©ሥላሴ
13.11.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
· መነሻ።
ሰሞኑን በሕግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችን በተመለከተ
የጠቅላይ አቃቤ ሕግ
መግለጫ፣የብረታ
ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን በተመለከተ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ
· መቅደመ ብልሃት።
እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ዶር. አብይ አህመድን እንዴት ትተረጉሜያቸዋለሽ ብባል ብሄራዊ ቀናችን ናቸው ብዬ ነው። ኪንግ ማርቲን ሉተር አሜሪካን የማዳን የመሪነት ብቃታቸው ዛሬ ነው ይበልጥ የታዬ የተገለጠው - በወጉ። አሜሪካ ለራሷ ተርፋ የብዙዎች ተስፋ መሆን መቻሏ የትናንት የኪንግ ማርቲን ሉተር የተጋድሎ ውጤት ነው።
ተስፋ ባጣንበት፤ ጥልፍልፉ ችግራችን መፍትሄ አልቦሽ ሆኖ ከጭቃ ወደ ጭቃ በዙር አዳክሮ በደቆስን ሰዓት፤ ጨንቆን ጥግ አልቦሽ በሆንበት ወቅት ብቅ ያለ የመሪነት ልዩ ድንቅ ክህሎት ነው የዶር. አብይ አህመድ መንገድ። እርግጥ ዛሬ ፍሬውን ልናይ አንችል ይሆናል፤ ብንከተለው ግን ብሄራዊ ቀን የሚያስወስን ቁም ነገር በዚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ህሊና ውስጥ አለ። በተቃርኖ ያልሰመጠ፤ በአድሎ ያልበከተ፤ በግለት ያልጨቀዬ፤ በበደል ያልከተመ በንዑድ መንፈስ ንጥረ ነገር የከበረ እርእሰ ጉዳይ ነው የዶር. አብይ አህመድ ቀናው መንገድ። ከመፍትሄ በላይ …. ውዶቼ ይህን የጻፍኩት ጥር 5 ቀን 2018 ነው።
https://sergute.blogspot.com/2018/05/
· ጊዜ እና ወቄቱ!
የነፃነት ጥማት እና ራህብ የነበረብን ኢትዮጵያዊ ዜጎች በምንችለው ሁሉ ስንታገል
ለቆዬነው ሁሉ ታሪካዊ ድርሻችን እንደ ተወጣን የሚታወቀው አሁን ነው። ስለምን እራሳችን ስንቀቅል እንደኖርን። አብሶ ለባለቤት
አልባዎቹ የነፃነት ታጋዮች ጊዜ ምስክሩ ቀኑን አያጥፍብነም ብለን በህገ ልቦና እዬጠበቅን ነው። ከወላጅ እናት ነፃነትን
አስቀድመን የእናትን ድምጽ ሳይሰሙ ዓመታት ማስቆጠር መራራ ገጠመኝ ነበር።
ወላጆቻችን፤ ቤተሰቦቻችን፤ የቅርብ ይሁን የሩቅ ሰዎቻችን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ
ይፈጥሩብን የነበረው ጫና አሁን ላይ ሆነው ሲዩት ይህን ገመና ተሸከሚ ለተባለችው ኢትዮጵያ ዋቢነት ስለነበር በልባቸው ይመርቁናል
ብዬ አስባለሁኝ።
አብሶ እንደ እኔ በግል ለሚታገል፤ አይዞሽ ባይ የሌለው ሰው፤ ብቻውን ለሚፋለም የዬትኛውም
ድርጅት ማንፌስቶ ማህበርተኛ ላልሆነ ባተሌ ሰው ፈተናው እጅግ ሰፊ እና የገዘፈ ነበር። እራሱም ለነፃነት እታገላለሁ የሚለውም
ድርጅት እስከ ሰራዊቱ ፋታ ስለሚነሳን። ለዚህም ነው እኔ ለማውያን ነኝ ብዬ የወጣሁት፤ ከሻሸመኔው፤ ከቡራዩ እንዲሁም ከአዲስ
አበባ የጭንቅ ገጠመኞች በስተቀር ተስፋውን አላደረቁትም ለማውያን።
ዛሬ ቀኑን እንዲህ በርቶለት ሌብነትን የሚጸዬፍ መንግሥት ሰላማዊ በሆነ የሽግግር
ሁኔታ ሲታይ፤ ሲመጣ በውን ይህ የምናዬው እውነት ነውን ብሎ ለሚያስብ ሰው ረቂቅ ነው። በዚህ አጋጣሚ የቀድሞው ጠ/ሚር አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ
በፈቃዳቸው ስልጣናቸውን መልቀቃቸው በዚህ ድል ውስጥ ሆኖ ሂደቶችን ለሚገመግም ሰው ብሩኽነት አለው። ሰለሆነም ሊመሰገኑም
ሊከበሩም ይገባቸዋል።
·
የወቄቱ ስሌት።
ለመሆኑ ኢትዮጵያ 27 ዓመት ሙሉ ባለቤት ነባራትን ብለን ብንጠይቅ መንግሥት ነበር
ለማለት አይቻልም ነበር። እኔም መንግሥት የለኝም ነበር የምለው። ህግም አለ ለማለት አያቻልም ነበር። ምን አለ የህግ
ፋክልቲውን ብትዘጉትም እል ነበር።
ዝም በሎ ይህን መግለጫ ስታዳምጡት የተወረረች አገር ነው የሆነችው እኮ ኢትዮጵያ። ይህን አስመልክቶ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና አንድ ያደረገው ቃለ ምልልስ ነበር ያ ቃለ ምልልስ ተደራጊ ከፍጠኛ መኮነን የሰጡት ጭብጥ እና አሁን በኢትዮጵያ መንግሥት የተሰጠው መግለጫ ተመሳሳይ ነው።
https://www.youtube.com/watch?v=EyGBId2nyIs
„ESAT Yesamintu Engeda General Melaku Shiferaw July 2018 part 1“
https://www.youtube.com/watch?v=AaIVlfG1dLM
„ESAT Yesamintu Engeda B.General Melaku Shiferaw part 2 August 2018“
ጭብጡ
ኢትዮጵያ ባለቤት የሌላት አገር የነበረች ስለመሆኗ ይነግረናል። ያን ቃለ ምልልስ እኔ በዚህ ወር መጨረሻ እና በሚቀጥለው ፕሮግራሜ በተከታታይ በጸጋዬ ራዲዮ ለማስተላለፍም ቀን ቀጠሮ ከተያዘላቸው
ዋናው ነው።
አሁን ሌብነት ዝርፊያ እና ስርቆት እንዲህ ህጋዊ ሆኖ ተፈቅዶለት በደሃ አገር ላይ ሲዘማነኑ ሚሊዮኖች ደግሞ እሚበሉት እሚጠጡት አጥተው በጠኔ ያንቃላፋሉ። ለነዛ በጠኔ ላለፉ ነፍሶች አሁን ማነው ካሳ የሚከፍለው።
የአቶ አባይ ጠሐዬ ልጅ።
የመከረኛ ልጅ።
ይህ የተዘረፈ የኢትዮጵያ ሃብት እና ንብረት ሥራ ላይ ቢውል ስንት ገቢረ መንፈስ ያድን ነበር። ክሱም መታዬት
ያለበት ከዚህ አንጻር ነው። ባንክ ቢቀመጥ እንኳን ወለዱ አንጡራ ሃብት እዬተዋለደ በቀጠለ ነበር።
እኔን ያበረታታኝ መረጃው መልካም ዜና መሆኑ ነበር፤ ዜናውም መሰረቱ ጭብጡ በጥናት ላይ የተመረኮዘ ስለነበር አርክቶኛል። የክስ ጭብጡን በጥናት ካለቀ በኋዋላ ነው ተጠያቂዎች የታሠሩት።
ለዚህም ነበር እኔ በ7ኛው መጸሐፌ „እርግብ በር“ ላይ የሥርዓት ለውጦች ሲደረጉ የነበሩ ነገሮችን እንዳሉ ማፍረስ ሳይሆን ሊፈርሱ የሚገባቸውን በሚገባ በባለሙያዎች መጠናት አለባችው ብዬ መግቢያ ላይ በአጽህኖት የሰራሁት። ሌላው ቀርቶ ስለ አጋዚ የሥነ ልቦና አጠባ ሁሉ በመጸሀፌ ላይ ገልጨዋለሁኝ። ሁል ጊዜ በማፈረስ ከታቱ መውጣት ስላልተቻለ።
በጹሑፎቼም ላይ አበክሬ ስገልጽ የኖርኩት ይህንኑ ነው። አሁን አስቸጋሪ የሆነው ይህን ሁሉ በደል በተሸከመች አገር ደግመን እንገዛለን በማለት የሴራው መረብ ተጨማሪ የህዝብ መፈናቀል እን የ ዕንባ ጎርፍ መብዛቱ ነው። ሰርቅው፤ ዘርፈው፤ ገድለው፤ አርደው አርፋችሁ ተቀመጡም ቢባሉ እንኳን የማይቻል ሆነ። በዬዕለቱ መርዶ ሲያደራጁ ውለው ያድራሉ። አሁን የቅማንቱ ትዕይንት ይኸው ነበር። ነፍሳቸው አታርፍም በቃ ለክፉ ነገር ጥሪ አለባቸው።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ዛሬ የማይርባ የሚባለው ከ100 ዓመት በኋዋላ የአገር ቅርስ እና
ውርስ ይሆናል። የቱሪስት ገቢም ማስገኛ ይሆናል። ስለዚህ ማስቀረት መወገድ ያለባቸው ሲኖሩም እንዲህ የሚፈለጉትን ከማይፈለጉት በመለዬት እንዲህ ጥናታዊ ከሆነ የልብ ያደርሳል።
ያን ጊዜ ጥገናዊ ለውጡ ሳይሰክን ጫና የበዛበት፤ ግብታዊ እርምጃ እንዲወሰድ ይገፋፉ
የነበሩትም ብዕረኞች ከዚህ እርምጃ መማር አለባቸው። አደብ ይኑራቸው። ሽርሽር አበዛ አብይ እያሉ ሲኮንኑ የነበሩትም ይኸው ሁሉን መልክ ለማስያዝ
ሰፊ ተግባር፤ ለዛውም በንፋስ ባልተመራ ፖለቲካ በጥናት ላይ ተመስርቶ እዬተከወነ ስለመሆኑ እያተደመጠ ነው። ለዚህም ነበር እኔ ኢትዮጵያን ቁምነገር የማድረግ
ዓላማን የጻፍኩት።
https://sergute.blogspot.com/2018/05/blog-post_38.html
ኢትዮጵያዊነትን ቁምነገር የማድረግ ዓላማ፤
· ሰብዕዊነት እና ተፈጥራዊነት።
ምን ዓይነት መከራ የአላዛሯ ኢትዮጵያ እናቶች ተሸክመው እንደ ኖሩ እንሆ ተደመጠ። ከዚህም በላይ
ሌላም እንዳለ አውቃለሁኝ፤ ያልተነገረ፤ ያልተጻፈ ለቀጣዩ ትውልድ አብሮነት ሲባል በዝምታ ያሉም አረመኔዊ ተግባራትም አሉ። እንደ
እነሱ መሆን ያልተገባ ስለሆነ እንጂ እነሱ በእስር ቤት የሚሠሩት በመጻህፍትም በሌላ አገር ታሪኮች እኔ አንብቤ አላውቅም፤ ፊልምም አይቼም አላውቅም።
የወያኔ ሃርነት ሥረ መሰረት የማንፌስቶ መሥራቾች የነፍስ ሪህ ናቸው። ለ ኢትዮጵያ አልዛይመሮች ናቸው። ብቻ መታገስ በአንድም በሌላም ሆኖ ፍትህን ልዕልና ሲሰጥ እሱ
አንድዬ አማኑኤል ፈቅዷል። ለዚህም ነው „ጎንደሬዎች ሲሰጥ አይነገር“ የሚሉት።
መሬት ስንቱን ጉድ እንደ ተሸከመች፤ ምድር ስንቱን
እንደ ቻለችው፤ ይህን ሁሉ ሰቀቀን ተሸክሞ ምንስ ቻይ፤ እንደምንስ ጽኑ እንደ ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚገርም ታሪክ ነው። ለዚህም
ነው ሥርጉተ ሥላሴ ለድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች ሴቶች ድምፆን ከፍ አድርጋ ለዓለም ስታሰማ የኖረችው።
ፍዳው የአላዛሯ ኢትዮጵያ እናት ነው። ማገዶ አቅራቢያዋ
ለዛውም የሰው የኢትዮጵያ እናት ናትና። በዚህ ውስጥ ፍደኛዋ እናቴም አለች። በእኔ ምክንያት እምትንገላታው። እኔስ እላለሁኝ፤ --- ይህን ዘመን አክብሮ መያዝ ይገባልም። ይኸው ለማ እና አብይን ወያኔ
አዛጋጃቸው እያሉ ሲሟገቱ የነበሩት ንፋስ አምላኪዎች እንዲህ መርዶውን ይስሙት። ለእነሱ ይህ የምጥ እና የዳጥ ቀናቸው ነውና።
· ወይ ጉድ?
ሌላው የማህበረ ተጋሩ ጉዳይ ጓደኛ ፍለጋ የጥፋት
ተጨማሪ ማህበርተኞች መፈለጋቸው ነው። እነኝህ የኢሰብዕዊ ድርጊት ማህበርተኞች አሁን ደግሞ እንደ ሥልጣኑ ሁሉ ኮታ ይደረሰው ሁሉ ማለቱን ተያይዘውታል።
እንዲህ እንዲሆን የግድ እኮ ነው ለ100 ዓመት ህልመኞች። ራስ እግሩ እኮ እሱ በእሱ ነው።
ድርጅቱ አውራው ፓርቲ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ነው።
በዚህ ድርጅት ውስጥ አባል የሚሆኑ ትግሬዎች ብቻ ናቸው። የአንድ አካባቢ ሰዎች። ፓለቲካውን፤ ኢኮኖሚውን፤ ማህበራዊውን፤ ደህንነቱን፤
ጸጥታውን የያዙት ደግሞ እነሱ ነበሩ 27 ዓመት ሙሉ። አሁን ያለው የህዝብ መፈናቀል ምክንያቱ እኮ ይህን ለውጥ አከርካሪውን ሰብሮ በዛው ጭካኔያዊ መንገድ ለመዝለቅ ነው።
የሆነ ሆኖ ለጠፋውም ለለማውም ተጠያቂዎች እንሱ እና እነሱን ሲያጅቡ የኖሩት
ማህበርተኞቻቸው ናቸው፤ የዬትኛውም ብሄረሰብ አባል ሆኖ የጥፋት ተባባሪ ከነበረ ከህግ በላይ ማንም የለም እና ህግ ፍርዱን ይሰጣል።
ሁላችንም እንፈርምበታለን።
ሌላ ያልታዬ ሰውም የማያስተውለው ትልቁ ነገር የሰማይ ቁጣውን ነው። እሱስ ቢመጣ በምን
ሊያስቆሙት እንዴትስ ሊታገሉት ይሆን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማህበርተኞች? የኢትዮጵያ ሰማይ እኮ ቁጣውን
አከታትሏል። በጠ/ሚር አብይ ምርጫ ለታመሱ የኢጎ መኳንንቶች ሁሉ መቀሌ አቅራቢያ ምልክት፤ በጉራጌ ዞን ቁጣው በሦስት ሁኔታ ተገልጧል። እረፉ ብሏል አማኑኤል።
እኔ እምፈራው የዚህ ሁሉ ዕንባ ምን ማዕት ያወርድ
እንደ ሆን እዬአልኩኝ ነው። ሰሞኑን በሐረርጌ
እሳት ከሰማይ እዬዘነበ ነው። እንጅባራ ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ወጥቷል።
ልብ ብሎ ላስተዋለው ኢትዮጵያን ያልረሳት አማላክ
ታምሩን መሬት ላይም እዮር ላይም እዬሠራ ነው።
እና ቀጣዩስ ምን ይሆን እያልኩኝ ነው። በምድርም በሰማይም ምን ይመጣ ይሆን እያልኩኝ እጨነቃለሁኝ። መሬቷን ከዷት። መሬቷን አሰቃዮዋት፤ እናም ገና ነው መከራው።
አብሶ ማህበረ ተጋሩ የራሳቸውን ገማና በቃ ብለው፤
አሻም ብለው ደፍረው መውጣት ይኖርባቸዋል እንጂ ሌብነትን፤ አረመኔያዊነትን፤ ጭካኔን እንደ ክብር እንደ ግርማ ሞገስ ይህን ውርዴት አይተው በዚህ የመከራ ሪፖርት ሊዘባነኑ
አይገባም። ሃፍረት እኮ ነው ሌብነት። ውርዴት ነው ማጭበርበር፤ ዜጋ አገሩን መለመላዋን ሲያስቀራት ከዚህ በላይ ውርዴት የለም ለዛውም
ልመና ፖሊሲዋ ላደረገች አገር። እውነት ለመናገር አላዛሯ ኢትዮጵያ በጠላት ነበር ስተመራ የነበረችው። እግዚኦ ነው።
እነ የተጋሩ ማንፌስቶ ማህበርተኞች መሳፍንቱ እና ልዕልተይ ይልቅ ወደ ፈጣሪያቸውም
ዝቅ ብለው ቀጣይ ማዕት ከሰማይ እንዳይዘንብ ድንጋይ ተሸክመው አቤት ማለት አለባቸው። እኔ „ምልክት“ በሚለው ጹሑፌ ላይ አበክሬ
የጻፍኩት ያን ነበር። እትጌ ትግራይ ድንጋይ ተሸክማ ይቅርታ አላዛሯን ኢትዮጵያ መጠዬቅ አለባት። በልጆቿ መሪነት አራጊ ፈጣሪነት
ግፍ እሷ የሰማይን ቁጣ ማስተናገድ አይኖርበትም እና።
አሁን እኔ የድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች ስለሆኑ
ጉዳዬ ከእንግዲህ የኢትዮጵያ እናቶችን ዕንባ ይብቃ ባይ ነኝ። ስለዚህ ተንደላቀው ዘመንው ለኖሩ ከእትብታቸው ለተፈጠሩት የጭካኔ
መኳንንት፤ የሳጥናኤል መሳፍንት እና ልዕልቶች እትጌ ትግራይ ቁርጥ ያለ አቋሟን ማስመስከር ይኖርበታል። ሊሂቃኖቿ ያው ተዛው ናቸው እንደ ተለመደው፤ ከወያኔ
ሃርነት ማንፈሴቶ መንፈስ ንቅንቅ አይሉም። ጭካኔን እንደ ኒሻን የሚዩ ጉዶች። አለመታደል።
· እገዛ።
ልባሙ የአሜኑ መንፈስ የልቡን ብስል ተግባር እዬከወነ ነው።
እኔ በአብይ ኬኛ ክፍል 6 ማጠቃለያዬ ላይ በዚህ ሰው ጭንቅላት ውስጥ ብሄራዊ ቀን የሚያስወስን ቁምነገር አለ ብዬ ነበር። ጨምሬም
አብይ አፍሪካዊ ማርቲን ኪንግ ሉተር ነው ብዬ እንዲሁ ሌላ ጹሑፍ ላይም።
ይህንኑ ቃል ለጀርመኗ መራሂተ መንግሥት ለግሎባል
የመቻቻል እናትም ጽፌላቸው ነበር። ዶር አብይ አህመድ ለጠ/ ሚር እጩነት ሲወዳደሩ ይፈልግ የነበረው አንድ ለፈስፋሳ ተመርጦ፤ በጫና
የሽግግር መንግሥት ምኞት መመሠረት ስለነበረ የተዶለተው እገዛ እንዲደረግላቸው አስቤ ነበር ያን ጠንካራ ጹሑፍ የጻፍኩት።
ስለ አብይ
ብቻም ሳይሆን ሰለ ለማ፤ ስለ ገዱ እና አንቤም አክዬ ነበር የጻፍኩት። ምክንያቱም ቀደም ባለው ጊዜ ከአማራ ተጋድሎ እና ከ ኦሮሞ ፕሮቴስት ጋር ተያይዞ የተነሳው ሞገድ እና ቃጠሎ ፍትህ ይጠይቅ ስለነበር ክብርቷም ኢትዮጵያ ለጉብኝት ይሄዱ ስለነበር ጉልበታም አቤቱታ አቅርቤ ስለነበር፤ እነለማ ሲመጡ ግን አኔም ለማውያን ነኝ ስላልኩ በነበረው ጥቁር ታሪክ መንፈሳቸው እንዳያዬው መረጃ መስጠት ነበረብኝ። ተስፋዬ ልዑቅ ስለነበር የለውጥ መንፈሱ የተስፋ ስለመሆኑ ጻፍኩኝ።
ያ አቅም ተንኮላሽቶ እንዲቀር የተጉ፤ የሠሩ ሁሉ
ዛሬ ላይ ለውጡን ደግፉ እያሉ ሲናገሩ ስሰማ ይገርመኛል። ለውጡን ለመቀልበስ ያልታተረ ማን ነበር እና? ከሳተናው በስተቀር የትኛው
ሚዲያ? „ኢትዮጵያዊነት ሱስን" ደገፈክ ተብሎ ቋጠሮ ተኮንኑ አልበረንም? የአብይ ሰም ገኖ ወጣ ተለጠጠ አልተባለንም? „ከዝንጀሮ
ቀንጆ ምን ይመራርጡ“ አልተባለንም? „ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም“ አለተባለንም? "በኢትዮጵያነት ሥም ወያኔ የላካቸው" አልተባሉንም?
የሚገርመው እንዲያውም ስኬቱን ሰፊ ሽፋን ዓለም የሰጠውን
ያህል እኛ አልሰጠነውም የታምር የሚመስሉ ነገሮች ናቸው ሁሉም ነገር። ኢትዮጵያን ቁምነገር የማድረግ ዓላማ ያለው አንበሳ ገና ያሳያቸዋል።
ማጥናት ነው መንፈሱን የግል ኢጎን ምሶና ቀብሮ። አቅሙ ከኖረ ወኔው ካለ። አሁን የተግባር ሞገዱ ሁሉን እያሰመጠው ሲገኝ አቃቂር
አውጭው ሁሉ ምን ይበጀው? ሥርጉትሻ ደግሞ ተመስገን አለች አንገታችን አላስደፋንም።
አሁንማ አትገዙ፤ አትተባባሩ ቢባልም የማይሆን ነው።
አትደግፉ ቢባልም የማይሆን ነው። በይቅርታ እና በምህረት ተገብቶም እኮ ማንኮር፤ መጎርጎር ተሞክሮ ነበር አልተሳካም እንጂ። ወደፊትም
በተገኘው ቦታ ሁሉ እፉኝቱ አይተኛም።
ሌላው ጥንቃቄ ሊወሰድ የሚገባው ጉዳይ ግን መስከን ያስፈልጋል። ማደማቅ አይገባም። መፎከር አያስፈልግም።
ደስታን በልክ መያዝ። ትውድን መንፈሱን ከሚያብክኑ ጉዳዮች መቆጠብ፤ ፍርሻ የሚሹትን ሃይሎች ጋር አለመተባበር በተግባር
ይጠይቃል። ከሁሉ በላይ ይህ መቅደመ ነገር ስለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባል። ባለፉት 7 ወራት ህውከት ተደራጅቶ ባይታወክ ይህ መንፈስ
ከዚህም በላይ ማዬት በተቻል ነበር።
ብዙ ያልቆረጡ ነፍሶች እንዳሉ ይሰማኛል።
ምክንያቱም
በሚዲያቸው የሚሠሩት እና በጹሑፍ የሚያስተናግዱት የተፋለሰ ስለሆነ። ልክ ቀደም ባለው ጊዜ ለነጮች መንፈስን ሌላ በመመገብ በኢትዮጵያውያን ደግሞ መስሎ መቅረብን ተክነውታል።
እርግጥ ነው ግድፈት ሲኖር፤ ትኩረት የሚያስፈልገው
አንባ ሲኖር ዝም ይባል ማለቴ አይደለም፤ እኔም አልምረውም፤ ነገር ግን ሆን ተብሎ ብሶት እና ምሾ መደርደር ግን ቢበቃ መልካም
ይመስለኛል። ከሁሉ በላይ ዛሬ አላዛሯ ኢትዮጵያ
ሙሴ ማግኘቷን ከልብ መቀበል እጅግ ያስፈልጋል - አብሶ ለቅኖች፤ ለማንፌስቶ ማህበርተኛ ላልሆኑት።
አላዛሯ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን አፍሪካም የዓይን ማረፊያ
የሆነ ዝርፊያን የሚጠዬፍ መሪ ማግኘቷ እማማ አፍሪካንም እንኳን ደስ አለሽ ልላት እፈልጋለሁኝ። ተፈጥሯዊነት እና ሰብዕዊነት አፍሪካ
በመሬቷ ለማስፈን ናሙና አብነት የሆነ መሪ አግኝታለች ብዬም አስባለሁኝ። ይህን የዛሬ ዓመት በጸፍኳቸው ጹሑፎች ሁሉ ማገናዘብ ይቻላል።
· መሳናዶው የልብ ነበር።
ይህ አቅም በዝምብሎ የተገኜ ሳይሆን በቂ መሰናዶ
በመንፈስም በአካልም የተገኜ ነው። ሲፈርስ ሲሰራ የኖረ አቅም አይደለም። ወይንም ሲጣመር ሲበተን የኖር አይደለም፤ ወይንም ሲዋህድ
ሲለያይ የነበረ አይደለም። ብቅ ያለ አቅምን ሲያሳድም ሲያሳድድ የኖረ አይደለም። አቅሙ ኢትዮጵያን ቁምነገሬ ካለ ነፍስ በሙሉ ልቅና፤ በሁለገብ ብልህነት ጥበብን አክሎ በተደሞ ዕድሜ
ልክ የሰበለ የጥናት ውጤት ነው። ስለዚህ ተስፋውም ጥሩ ነው፤ ነገም ተስፋው ይቀጥላል።
ሁሉ ሰው፤ ሁሉ መንፈስ፤ ሁሉ ነፍስ፤ ሁሉ ቅን የእኔ ካለው
ከኖርንባቸው ዘመኖች ሁሉ እንዲህ ያለ የበቀለ አቅም፤ አንገት የማያስደፋ አቅም፤ የማያልቅ፤ የማይሰለች እጅግ አጓጊ ችሎታ እና
ክህሎት ተፈጥሮ አያውቅም በእኛ ዕድሜ ማለት ነው። እርግጥ ነው ዕድሉን አለገኙም ነበር እንጂ ኮ/ ጎሹ ወልዴም ይህን መሰል ፖለቲካዊ አደብ ያለው ክህሎት እንዳላቸው
አስቀድሜ በተለያዬ ጹሑፌ ገልጫለሁኝ።
አሁን ኢትዮጵያን እዬመራ ያለው ይህ አቅም በትውስት ሃሳብ አይደለም፤ እርምጃውን የጀመረው
በራሱ አቅም ውስጥ ነው አህዱ ያለው፤ ብዙ ሰዎች ፍኖተ ካርታ ምንትሶ ቅብጥርሶ ሲሉ አዳምጣለሁኝ፤ ዘመናይነቱ ከእስከ የለውም።
ለአንዲት ቀን አውሎ የሚያሳድር አዲስ ሃሳብ አፍለቂ
እኮ አላዬንም አልሰማነም የኖርነው በኩሬ ውሃ ዘልበን ነው የኖርነው፤ የአብዩ አዲሳዊነት ዋጠን ብል ይሻለኛል። ውጦናል አዲሳዊነት።
ሌላ
ዜና የሚያደምጥ ከስንት አንድ ነው። እኔ የኦስትርያ የሲዊዝ የጀርመን አልፎ አልፎ ሲኤንኤን እከታተል ነበር፤ አሁን እርግፍ አድርጌ
ያን ትቼ የኢትዮጵያን ብቻ ነው የምከታተለው። እምወዳቸውን ሾዎችን ሁሉ ነው ያቆምኩት። የራሴ በጣሜ ልክ ከሆነ ጊዜዬን ለራሴ ጠረን።
ዛሬ እንኳንስ ኢትዮጵያ ሉላዊቱ ሚዲያ ስንት ሽፋን
ይሰጠዋል መዋለ አብይ ዜና። በአብይ ኬኛ ዘመቻ ባለፈው ጊዜ በ6 ክፍል ሳጠቃለልው እንዲህ ብዬ ነበር። እርአሱ አብይ የኢትዮጵያ ፍላጎት ይል ነበር ቀኑ ጥር 5 ቀን 2018 ነበር።
ዛሬን እኔም በዚሁ ላጠቃልል አብይ የኢትዮጵያ
ፍላጎት።
https://sergute.blogspot.com/2018/05/05.html
Ethiopia's Prime Minister Abiy Ahmed DR
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ
ሚስጢር።
መሸቢያ ጊዜ ውዶቼ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ