ልጥፎች

ከግራጫማ ሰብዕና ማናቆር የሚጠበቅ ነው።

ምስል
ከግራጫማ  ሰብዕና ማናቆር የሚጠበቅ ነው። „የሽንገላ ከንፈሮችን ሁሉ  እግዚአብሄር ያጠፋቸዋል“  መዝሙር ፲፩ ቁጥር ፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ  11.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·        መ ቅድመ ዕለት። የአብይ አቅም፤ ክህሎት፤ መክሊት፤ ሰብዕና ስኬታማ ትልም፤ ነጋዊነት፤ አዲስአዊነት፤ እኛዊነት፤ አቃፊነት፤ ሰብዕዊነት፤ ክህሎታዊነት፤ ሰብሳቢነት፤ አቅራቢነት፤ አደራጅነት፤ ታጋሽነት፤ አያያዥነት፤ ቅኔነት፤ አድማጭነት ከሳበረገጋቸው ሰዎች አንዱ አቶ ጃዋር መሃመድ ነው። ትናንትም ዛሬም የሚያብንነው ይኸው ነው። ይህ ባላስበነው ወቅት እና ሁኔታ ከች ያለው ብልህነት የእሱን ደረጃ ቁልቁል ያስገባም ነው። የአሱን ተደማጭነት ወደ አልነበረ ያሸጋገረም ነው። የጠ/ሚር አብይ አቅም ልክ እንደ ፏፏቴ ነው። ሲሰጥ አይነግር የሚባል መክሊት ነው ያላቸው። ይህን ደፍሬ እምናገረው እኔ ከ2016 ጀምሮ ስላጠናኋዋቸው ነው። የግራ ሴራ ፖለቲካ ነው ለማደናቀፍ እዬተፈታተናቸው ያለው እንጂ ሰላም ቢሆን ስንት ታምር ባዬን ነበር ከዚህም በላይ። ግን እንቅፋቱ በዛ።    በተጨማሪም በሁለቱ ሊሂቃን ማህከል በዶር ለማ መገርሳ እና በዶር አብይ አህመድ ያለው የተከደነ የክህሎት ሲሳይ ጃዋርውያን እና መሰሎቻቸውን ቢያሰበረግጋቸው ይገባል። ማወዳደር የሚቻለው ተቀራራቢ ነገር ሲኖር ብቻ ነው። ማነጻጸርም የማይደፈር ነውና።ለዛውም ከእኛ ተፈጥረው እንጂ ስካንዳንቢያ አገሮች ቢፈጠሩ ኖሮ ስንት መጸሐፍ በታተመላቸው ነበር። አብዝቼ ለሁለቱ እምጸልዬው ንፋስ እንዳያስገቡ እንዲህ በቅናዊ አሃታዊነታቸው እንዲቀጥሉ ነው። ይህን ካስቀጠሉ የቆዬ ሰው ይያቸው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ አብነትነቷ ይታደሳል። ልዕል አገርም ት

የጎንደር እናት ደግማ ድንኳን ጥላ እንደትተከዝ ለወያኔ ምርኩዝ መሆን አለመታደል ነው።

ምስል
የጎንደር እናት ደግማ ድንኳን ጥላ እንደትተከዝ ለወያኔ  ምርኩዝ  መሆን አለመታደል  ነው። „ሰነፍ በልቡ አምላክ የለም ይላል።“ መዝሙር ፲፫ ቁጥር ፩“ ከሥርጉተ©ሥላሴ  11.11.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ። የሚገርሙኝ ነገሮች መብዛታቸው በአዎንታዊነት ቢታዩም ዕንባን በማስቀጠል ከሆነ ግን አሉታዊ ነው። አሁን የቅማንት ጉዳይ ይገርመኛል  በአሉታዊነት። የቅማንት እናትም ጎንደሬ ስለሆነች 50 ዓመት ሙሉ ዓውዱ የጦርነት ስለነበረ ያው በሁሉም መስክ ተጠቂ ናት።  ዛሬ የቅማንት እናት ተመስገን ብላ ዎህ በምትልበት ጊዜ ሻማው በማንቀላፋት ላይ ባለው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሹማምንት ጋር በመሆን የእናትን ጡት መውጋት አለመታደል ነው። አያሳፍርም ወይ የጎንደር ልጆች አሁን እርስ በእርሳችሁ ስትዋጉ። ማፈሪያ!ለዛውም የ አብይን ካቤኔ ሰላም ለመንሳት መጣር? ውርዴት ነው።  27 ዓመት ሙሉ አንበርክኮ ሲገዛ- ሲሰነጥቅ፤ ሲተረትር፤ ሲሸነሽን፤ ሲዘርፍ፤ ሲወር፤ ነቅሎ ሲወሰድ፤ አፈር ሲጭን፤ እንጨት ሲጨን፤ የጎንደር ልጅ በግባ ግቢቱ እዬገባ ሲያድን ሲመነጥር ከኖረ አውሬ ጋር አብሮ መሆን ከህፍረቶቹ ሁሉ የላቀው ነው። ለዛውም ጎንደሬ የተባለን ሲያሳድድ ከነበረ ማህበረ ደራጎን ጋር ሆኖ የራሱን ወገን መዋጋት እጅግም አሳፋሪ ድርጊት ነው። ባይገባቸው እንጂ ቅማንቶች በዬሄድንበት ስንሳደድ የምንኖረው ጎንደሬ በመሆናችን ነው። ያ ማንነት የሚሸመትም የሚቀናም አይደለም። ሙዚቀኛው ቃናውን፤ ስንኙን ካልተካነበት አይደምቅለትም። የነፃነት ትግል አደረጋለሁ የሚለው ካለጎንደር ማጣፊያው አጥረዋል። ጎንደር በሰው ሰውኛ ከሆነ የሚተረጎመው ብዙም ልብ ሰቃይ ጉዳይ ላይኖርበት ይችላል። በመንፈሳዊ ህይወት  የዕድምታ ሚስጢር ከሆነ ግን

የኦሮሞ የተዋህዶ ልጆች የፈተና መባቻ።

ምስል
ልባዊነት። „አቤቱ ለምን ርቀህ ቆምህ?“ መዝሙር ፲ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 09.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ቋንቋ ጥበብ ነው። ቋንቋ እውቀት ነው። ቋንቋ ስልጣኔ ነው። ቋንቋ እድገት ነው። ቋንቋ ልሳን ነው። ቋንቋ ሙያ ነው። ቋንቋ ፍልስፍና ነው። ቋንቋን በሚመለከት ያለኝን እይታ በዚህ ፁሑፌ ማገናዘብ ይቻላል። https://sergute.blogspot.com/2018/05/blog-post_6.html ቋንቋ ሊቀ ሊቃውንትነት እን ጂ መወቀሻ ሊሆን አይገባም። ከአምስቱ የኦሮሞ ድርጅቶ የመብረቅ ወሳኔያዊ መግለጫ ማንፌሰቶ ወዲህ አማራ ግዕዝን በሁተኛ ቋንቋነት እንዲያጠና ዘመቻ መጀመሬ ይታወሳል። አሁን ዛሬ ከትኩስ መረጃ ዩቱብ አንድ መረጃ አገኘሁኝ። እኔ ግዕዝን የአማራ ህዝብ ማጥናት አለበት ያልኩት ለእኔ ለራሴ የትንቢት ያህል ነው የዛሬን መረጃ ሳገኝ የተሰማኝ። በወለጋ ብጹዕና አባቶቻችን መሰደዳቸው ብቻ ሳይሆን በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የያሬድ ዜማዊ ቅኝትም፤ በግዕዝ ቅዳሴም እንዲቆም መደረጉን አዳመጥኩኝ። ዝርዝርዝሩን እናንተው ሂዱበት ከሥር ሊንኩን እለጥፋለሁኝ። ዋና ቁም ነገር ግን ዛሬ የተፈቀደው የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የግዕዝ እግዳ ነገ ሃይማኖቱም እንዳይቀጥል የመጀመሪያው የክፉ ቀን ደወል ነው። የግራኝ ዋዜማ። የዳውዳውያን እና የጃውርውያን ፍልስፍና ይሄው ነው። „ቀስ እያለ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል“ የሚበለውን ልብ ትሉ ዘንድ በአክብሮት እግልጻለሁኝ። አሁንም ቅድምም ከኦነጋውያን ጋር ያለው ድርድር ትውፊታችን ላይ የተቃጣ፤ ማተባችን ላይ የተቃጣ፤ በአብሮነታችን የተሳለ ሰይፍ ሊያመጣ ስለመቻሉ የህሊና ዝግጁነት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። ቅኖቹ ዶር ለማ መገርሳ