ከግራጫማ ሰብዕና ማናቆር የሚጠበቅ ነው።




ከግራጫማ 
ሰብዕና ማናቆር የሚጠበቅ ነው።
„የሽንገላ ከንፈሮችን ሁሉ 
እግዚአብሄር ያጠፋቸዋል“
 መዝሙር ፲፩ ቁጥር ፫
ከሥርጉተ©ሥላሴ
 11.11.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

  • ·       ቅድመ ዕለት።

የአብይ አቅም፤ ክህሎት፤ መክሊት፤ ሰብዕና ስኬታማ ትልም፤ ነጋዊነት፤ አዲስአዊነት፤ እኛዊነት፤ አቃፊነት፤ ሰብዕዊነት፤ ክህሎታዊነት፤ ሰብሳቢነት፤ አቅራቢነት፤ አደራጅነት፤ ታጋሽነት፤ አያያዥነት፤ ቅኔነት፤ አድማጭነት ከሳበረገጋቸው ሰዎች አንዱ አቶ ጃዋር መሃመድ ነው።

ትናንትም ዛሬም የሚያብንነው ይኸው ነው። ይህ ባላስበነው ወቅት እና ሁኔታ ከች ያለው ብልህነት የእሱን ደረጃ ቁልቁል ያስገባም ነው። የአሱን ተደማጭነት ወደ አልነበረ ያሸጋገረም ነው። የጠ/ሚር አብይ አቅም ልክ እንደ ፏፏቴ ነው። ሲሰጥ አይነግር የሚባል መክሊት ነው ያላቸው። ይህን ደፍሬ እምናገረው እኔ ከ2016 ጀምሮ ስላጠናኋዋቸው ነው። የግራ ሴራ ፖለቲካ ነው ለማደናቀፍ እዬተፈታተናቸው ያለው እንጂ ሰላም ቢሆን ስንት ታምር ባዬን ነበር ከዚህም በላይ። ግን እንቅፋቱ በዛ።   

በተጨማሪም በሁለቱ ሊሂቃን ማህከል በዶር ለማ መገርሳ እና በዶር አብይ አህመድ ያለው የተከደነ የክህሎት ሲሳይ ጃዋርውያን እና መሰሎቻቸውን ቢያሰበረግጋቸው ይገባል።

ማወዳደር የሚቻለው ተቀራራቢ ነገር ሲኖር ብቻ ነው። ማነጻጸርም የማይደፈር ነውና።ለዛውም ከእኛ ተፈጥረው እንጂ ስካንዳንቢያ አገሮች ቢፈጠሩ ኖሮ ስንት መጸሐፍ በታተመላቸው ነበር።

አብዝቼ ለሁለቱ እምጸልዬው ንፋስ እንዳያስገቡ እንዲህ በቅናዊ አሃታዊነታቸው እንዲቀጥሉ ነው። ይህን ካስቀጠሉ የቆዬ ሰው ይያቸው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ አብነትነቷ ይታደሳል። ልዕል አገርም ትሆናለች። ብቻ እነሱ በአንድነታቸው ላይ ይጠንክሩልን።
  • ·       እለተ የወግ ገባታ።


ጎልጉል ላይ ዛሬ ሰንበትን ልታደም ብዬ ገባሁኝ እና አንድ የፌስ ቡክ ጉዳይ አዬሁኝ። ቀልቤን ሳብ አደረገኝ። እኔ የፌስ ቡክ ታዳሚ አይደለሁም እንዲህ በ አጋጠሚ ድህረ ገጽ ከማገኘው ከማንበብ በስተቀር ማህበርተኛ አይደለሁም።  
ቁምነገሩ፣ --- ስለ አቶ ጃዋር የሰሞናቱ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ የአማራ ክልላዊ ጉብኝት አቁሱሎት፤ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ መሳፍንት ጥብቅና ቆሟል። 

ልክ እንደ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ ማህበርተኞች አንጀቱ እርር ድብን ብሏል እሱም። ለነገሩ ጠ/ሚር አብይ በተንቀሳቀሱ ቁጥር አውሌያው ቆሌው ይነሳበታል።   

ብልሃት የጎደለውና ያለጊዜው የተደረገብሎታል። በሁለቱ ክልሎች (አማራና ትግራይ) መካከል የተፈጠረውን ውጥረት የበለጠ ከማጋጋል በተጨማሪ ጉብኝቱ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል እየቀጠለ ባለው ሰላማዊ ግንኙነት ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ብሏል። (ጃዋር “reproachment” በማለት የጻፈው የተሳሳተ ሲሆን ትክክለኛው “rapprochement” ነው)

አቶ ጃዋር መሃመድ የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ  የአማራ ክልል ጉብኝትን ወቅቱን ያልጠበቀ ብሎታል። ቀድሞ ነገር ከግራጫ ሰብዕና የሚጠበቀው ይኽው ስለሆነ አይደንቅም።

ምን አልባት ለወዳጁ፤ ከፍ እና ዝቅ ለሚሉለት አዲስ አባባ ሄደው ሠርግና ምላሹን ላሰከነዱት ለአቶ ንጉሡ ጥላሁን እንግዳ ነገር እና መርዶ ሊሆን ይችል ይሆናል፤ አጤያቸው ይህን ሲኮልም የእሱ ማህበርተኛ ስለሆኑ ሊሰማቸው የሚችለውን መገመት ቢቸግርም ግራጫነት ግን አስከ ምን ስለመሆኑ ልብ አላቸው እና ይረዱታል ብዬ አስባለሁኝ። እሳቸውም ናቸው የኤርትራን ፕሬዚዳንት ወደ ክልላቸው የጋበዙት። እሳቸውን ነው የተቃወመው በቀጥታ ቋንቋ።


አሁን ይህን ነቅፎ ሊጋባቸው ጽፏልኝ።  መታወቅ ያለበት ነገር የሶሞናቱ ጉዞ ወደ አማራ ክልል ዘርፈ ብዙ ተልዕኮዎች ነበረው። ለቁንጽሎች፤ ስሜት እና ወጀብ ለሚመራቸው ደግሞ እንዲህ ተዘንጥሎ ይታያል። ዕድምታው የአፍሪካ ቀንዳዊ ልባዊነት ሥህን ነበረው። ነገን ደግሞ ተግባር በህብር ያቀለመዋል። የትውልዱ ድርሻ ነው። በቋሚነት ይህን ህልም ዕውን ማድረግ።

  
የሆነ ሆኖ ሱማሌ ላይ ያ ሁሉ ከ700000 ሺህ ህዝብ በላይ ሲፈናቀል አቶ አብዲ ኢሌ ብቻ አለመሆናቸው ይታወቃል። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሙሉ እገዛ እና የዘመቻው ስልት ምህንድስና በወያኔ መኮንኖች ነበር የተከወነው።
የመጀመሪያው የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ  የኢትዮጵያ ጉብኝት ጊዜ ዶር ለማ መገርሳ በማንኛውም ሁኔታ ነበሩ። ሽልማትም ሰጥተዋል። እና ያ ጊዜውን ያልጠበቀና ስልት የጎደለው ነበርን? ይታወቃል ዛሬም ጥገናዊ ለውጡ በኦህዴድ /ኦዴፓ መመራቱ ስላልተመቸው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሙሉ አቅሙን በመፈሰስ ላይ መትጋቱ …


ለነገሩ የአልጀርሱ ስምምነት ተግባራዊነትን በሚመለከትም ወቅቱን ያልጠበቀ ተብሎ ተተችቶ ነበር ዛሬ ዓለም የድንቆች ፍልቅ ሲል እያወደሰው የሚገኘውን ያን ደፋርን እርምጃ። ሥርጉትሻም የባድመ ዕድምታ በሥርጉተ ዕይታ ብላ ሞግታው ነበር። የሞገተቸውም ሃቅ እዬሆነ ነው ያለው።

የሆነ ሆኖ ሌላም ልከል አዲስ አመትን በቡሬ ግንባር የኤርትራው ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ እና ልጃቸው እንዲሁም ዶር አብይ አህመድ፤ አቶ ደመቀ መኮነን፤ ዶር ደብረጽዮን ገ/ሚኬኤል የሁለቱ ህዝቦች በተገኙበት ልዩ የሆነ ደማቅ ዝግጅት ነበር። 


ያስ ምን ሊባል ይሆን? ያም ብልሃት የጎደለው እና ጊዜውን ያልጠበቀ ነበረን? ከትግራይ ጋር ሲሆን ወቅቱን የጠበቀ አማራ ክልል ላይ ሲሆን ወቅቱን ያልጠበቀ ሊሆን ነውን? ከደቡብ ጋር ሲሆን ወቅቱን የጠበቀ ከአማራ ጋር ሲሆን ስልተቢስ እና ወቅቱን ያልጠበቀ ሊባል ነውን?


በዚህ አገላለጽ አቶ ጃዋር መሃመድ በውስጡ አማራ ላይ ያለውን የልቡን ደንብልብልነት ያሳያል። መጥኔ ብያለሁኝ ለማህበርተኛው ለአቶ ንጉሡ ጥላሁን።
ቀድሞ ነገር ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ጋር ማን ቁርሾ የሌለው አለና? በዚህ ሥርዓት ውስጥ በብዛት አማራ እና ኦሮሞ ጥቃት ተኮሩ ይሁን እንጂ እስሩ እንግለቱ ሁሉም እኮ ደርሶታል። የዘር ጭፍጨፋውም ኮንሶም አማራም ኑረውበታል።


የትግራይ ሥርዕው መንግስት ለሚግጣት ለኢትዮጵያም አይሆናት፤ ሌት እና ቀን ህዝቧ ሰላም እንዲያጣ ፕሮግራም ነድፎ እዬሠራ ነው የሚገኘው። ይህ ሁሉ መከራ እኮ የወያኔ ሃርነት የሴራ ቱቦ የፈጠረው የጭካኔ ዓውድ ነው እኮ። እርግጥ ነው አሁን መሬት ላይ ኦነጋውያን ዳውዳውያንም መከራ - ፍዳ - ለቅሶ ያመርታሉ በምድሪቱ ላይ አባሪ ተባባሪ ሆነው።


በሰላማዊ ግንኙነት ላይ ገና ወያኔ ሃርነት ትግራይ ቅስም ይሰበራል ተብሎ፤ ለእሱ ምቾት ተብሎ፤ ለእሱ የሥነ - ልቦና ጥበቃ ተብሎ ማዕካላዊ መንግሥት ከትልሙ ሊተጓጎል አይገባም።

እንዲያውም የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ነው እዛ አማራ ክልል የተመከረው። ለመጀመሪያ ጊዜም ነው ሦስቱ መሪዎች አዲስ በተመረቀው የባህርዳር ጥበብ ግዮን ዩንቨርስቲ ላይ የተገኙት። ልዩ የታሪክ ቃልኪዳንም ነው።

/ / አብይ የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ያስመረቃቸው የህክምና ባለሙያዎች
በኤርትራና ሶማሊያ የነፃ ህክምና እንዲሰጡ ጥሪ አቀረቡ
November 10, 2018

በመንፈስም ደረጃ ስንመለከተው እንዲያውም ዘግይተዋል ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ የአያታቸውን መካነ መቀብር ቦታ ጎንደርን በትኩረት አለማዬታቸው። ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ወደ ጎንደር ሄደው ልጆቻቸው ማሳዬት ሁሉ ይኖርባቸዋል።

ሌላው ሴራን እንጠብቀው አይነት ነው የግራጫማው ሰብዕና ባለቤት አቶ ጃዋር መሃመድ የሚለን። የነፃነት የዴሞክራሲ ተጋድሎ የኩሬ ውሃ አይደለም። እያንዳንዷ ደቂቃ ዋጋ አላት፤ ዕሴት አላት፤ ታሪክ አላት፤ ትውፊት አላት። ታርኪዊም ነው። አሁን የሦስቱ አገር መሪዎች እዛ መገኘታቸው ነገ ላይገኝ ይችላል። ሁሉም ዕድሜውን አያቋጠረውም ወይንም አያሰላውም።

በሌላ በኩል ካል ጎሼ አይጠራም። የትኛው ዓዋድ ነው የወያኔ ሃርነት ትግራይ የማያበሳጨው? የትኛው አውድስ ነው የወያኔ ሃርነት ጥቅም የማይነካበት? ነገ እዬጠራ ስለመሄዱ ዘንድሮ ሳይሆን እኔ በአብይ ኬኛ ሰድስት ክፍል ብቻ ሳይሆን ጹሑፎቼ በሙሉ በዚህ ቅናዊ መንፈስ ላይ ያተኮሩ ነበሩ እናም ብልህነት እና ብልሃተኛው ልብ ለልብ የተገናኙበት ዘመን ነው። 

እኔ ወደ 450 ጹሑፎች ጽፌያለሁኝ በዚህ በጥገናዊ ለወጡ ምክንያት፤ አመዛኙ በአብዩ ቅንነት እና ብቃት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ጊዜውም እዮራዊ ነው መንፈሱም እዬራዊ ነው።

ያን እናስተጓጉላለን ተብሎ የተሞከረው ሁሉ የዶግ አመድ እዬተሆነ አሁን ተስፋ ማጣት የፈጠረው ጫና ነው ወዲህ እና ወዲያ የሚያወራጨው ባለ ግራጫማ ሰብዕናውን።

ትክክል የማይሆን የነበረው ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ብቻቸውን አማራ ክልል ለሥራ ጉብኝት ቢገኙ ነበር። ለእረፍት ይችላሉ፤ ማንስ ከልካይ አለባቸው እና።
መንግሥታዊ ለሆነ ተልዕኮ ግን ማዕከላዊ መንግሥት ባለበት ጠ/ሚር አብይ አህመድ፤ ምክትል ጠ/ሚር አቶ ደመቀ መኮነን፤ የውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ ዶር ወርቅነህ ገበዬሁ፤ የገንዘብ ሚነስተሩ አቶ አህመድ ሽኔ በተሟላ ሁኔታ ነበር አቀባለሉም ተግባሩም የተከወነው። ይህ ውጤት እና መልካም ጅምር የሚያስመሰግን እንጂ የሚያስወቅስ የሚያስነቅስ አይሆንም።

በሌላ በኩል መሪነት ማለት ጊዜን ወቅትን ተቀባይነትን በስልት እና በብልሃት መምራት ነው። ይህን ነው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ያደረጉት። ፍቅር ደግሞ ስለምን ይሆን የሚፈራው። በሌላ በኩል ወያኔ ሃርነት ትግራይ እና ሻብያ ይተዋወቃሉ። „ከወረቱ ስንቁ ልቆ“ ካልሆነ በስተቀር …

በወያኔ ሃርነት ትግራይ እና በአማራ መካከል ያለው የበታችን ስሜት የፈጠረው ነው ይህን ሁሉ መከራ 27 ዓመት ሙሉ አማራ የተጋፈጠው። አሁን ግን አማራ በሙሉ የሥነ ልቦና ዕሴቱ ላይ ነው የሚገኘው። ዕድሉን የሰጠውም እዬር ነው። 

ከሁሉ በላይ ወያኔ ሃርነት ትግራይ መቼውንም አይነቀልም ብሎ ያሰበው መርዝ ወደ መቃብር ስለወረደ ነው። ያም አማራን ጠላት አድርጎ መነሳት እና ማሳደም። አማራን ማገዶ ማድረግ። ቀድሞ ነገር ፍቅር ሲመጣ መቼ ደስ ብሎት አውቆ ነውና አቶ ጀዋር መሃመድ ይሁን ሚዲያው።

ስለ ጣና ኬኛ ምን አለን? ስለ አባይ ኬኛ ምንስ አለን? እንዴትስ ዘገበው ሚዲያው። ለመሆኑ ከእነሱ አርኬቡ ላይ የዶር ለማ መገርሳ እና የዶር አብይ ፎቶ እንኳን ዕወቅና አግኝቶ ያውቃልን? ንገሩኝ ባይ …


እንሱ ግን ትልቅነታቸውን አሳይተዋል። በራሳቸው የሥልጣን ቦታ በልዩ ጥበቃ ሲያንፈላስሱ ባጅተዋል። መጨረሻው ደግሞ ሴራውም ተንኮሉም አልሳካ ሲል ጓዝ ጥቅለላ እና ቁዘማ ሆኗል። መሪም አማካሪም ነኝ ተብለን ነበር እኮ። ብፈልግ ዛሬውኑ ኦሮምያን መገንጠል እንችላልንም ተብሎ ነበር። ምን ያልሰማናው ዲስኩር አለና። 

እኔ እንደማስበው የነበረውን ተቀባይነት መልሶ ለማግኘት ከእንግዲህ አይቻልም። እነ ኮ/ ደመቀ ዘውዱ ጃዋርውያን የመፍትሄ ምንጭ አድርገው ጥያቄ ሲያቀርቡ ሁሉ አዳምጫለሁኝ። እስኪገርመኝ ድረስ። „ሰው በማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ“ እንዲሉ … ያ ሁሉ የባህር ላይ ኩበት ሆኖ የቀረ ትንት ነበር። የሳሙና አረፋ። 

ገራሚው ነገር የዩንቨርስቲ ሊሂቃንም የነፋስ አውሎን ቁጭ ብለው እንዲታደሙ ተደርጎ ነበር … ማዬት መልካም ሆነ እና ባዶ እጅ መልስ ተሆነ - ተዛሬ ላይ።
ፍቅርም ክብርም ዝናም በልክ ተመጥኖ ሲሆን መልካም ነው። „ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላሉ ጎንደሮች ሲተርቱ … ውጪም ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ነው። የፖለቲካ ተንታኝ እዬተባለ ሚዲያው ሁሉ ደጅ ሲጠና እናይ ነበር። አሁን ሁሉም በባዶ ተባዛ።

የመደመሩን ካልኩሌተር የሠራ ሰው እስከ ፍፃሜው እዛ ሆኖ በሪሞት መምራት ነበር አቅሙ፤ ችሎታው፤ ክህሎቱ፤ ትዕግስቱ ቢኖር፤ አዬር ላይ መናገር እና መሬት ላይ መከራ ጋር እዬኖሩ ህዝብን ማገልገል ልዩነታቸው የሰማይ እና የመሬት ያህል ነው። አቅሙ ከሌለ በሌለነት መወራረድ ነው። ዘመነ ጃዋርውያን በማህል መዲና እንዲህ ህልም እልም በሚመሰል መልኩ አከተመ።

ስለ ሰብዕዊነት ቢጨንቀው በመፈናቀል መከራ ካዩት ወገኖቾ ጋር ነበር ጊዜውን ሁሉ ማሳለፍ ነበር የሚገባው። ሚዲያው እኮ ሰው ተገድሎ ተዝቅዝቆ የተሰቀለበትን ናዚያዊ ትዕይንት የመዘገብ አቅም እንኳን አልነበረውም።

የወጣቱ ችግሩ ኳች የለውም። ሁለተኛው አነሳሱ ከህዝብ አገልግሎት አይደለም። ይህ ነው ከባዱ አሳር። ለጋ ነገር ሲወጣ ልባም ኳች ያስፈልገዋል፤ እንደገናም ከህዝብ ጋር መሬት ላይ መሥራት ያስፈልጋል።

አጋጣሚና ሁኔታ ላይ ያንጠራራው ከሆነ አይበረክትም። መሸከም አይችልም ችግርን። እንዲህ ዓይነት ገጠመኝ አቃቂር አውጪ እና ተቺ ብቻ ነው የሚሆነው። በሌላ በኩል ደግሞ አሉታዊ ነው የሚሆነው። 

እሱ የማይችለውን ሌላ ሲሰራው የመንፈስ ቅናቱ ወደዚህ አቅጣጫ ይመራዋል። ያላቸውማ ደልዳሎች ናቸው። ረጋ ብለው፤ ዝቅ ብለው፤ ወጀቡን እያሳለፉ፤ በመከራው ውስጥ እዬኖሩ ያን ተጋፍጠው ከዚህ ደርሰዋል፤ ለሌሎችም እንሆ ተርፈዋል። ሰው ሁሉ ባለ ማዕረግ እና ባለ ወግ እዬሆነ እያዬን ነው።

ለሁሉም ትሩፉት ነው የሆነው ይህ ጥገናዊ ለወጥ ከሴራ ከሸር ከተንኮል መፈታት ቢችሉ ሊሂቃኖቻችን። በተጨማሪም የ እነሱን ያህል ቀርቶ በከፊል አደቡ ቢኖራቸው፤ እዮባዊነትንም ባሊህ ቢሉ። ብቻ አሁን የታወከው አዬር እዬወታለት ነው እንደ አንከሌስ ሽልም ሆኗል። 
  • ·    ክውን ገበታ።  

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አዲስ አበባ ገቡ

Ethiopia:/ አብይ|ኢሳያስ አፈወርቂ| ኃይለማርያም በምስጋና ፕሮግራም ላይ በአርባምንጭ ከተማ

%E1%8A%A0%E1%8D%88%E1%8B%88/ETHIOPIA ||
 / አብይ እና ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ ቁጥር 3 መረቁ።
አዲስ አመትን በቡሬ ግንባር
የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መሪዎች በሁለቱ አገራት ድንበሮች ላይ ተገኝተው አዲሱን አመት በማክበር ድንበሮችን ከፈቱ
| by  | 0 

Ethiopia-Eritrea border set to reopen after 20 years

September 11, 2018

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።

የኔዎቹ ኑሩልኝ መሸቢያ ጊዜ።፡

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።