ልጥፎች

ኦ! አብይ እንኳንም የእኛ ሆንክልን!

ምስል
ለብጹዕን አቨው ይስሃቅን አማኑኤል ሰጣቸው። „ጻድቃን ሆይ በእግዚአብሄር ደስ ይበላችሁ፤           ለቅኖች ምስጋና ይገባል።“    መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፪ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 10.09.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።                                                   ኑሩልን!                                   "በስም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ፤                            አሜን!" ሳይገባኝ እና ሳልመቼው  የደጀሰላሙን  ታምራት እናገር  ዘንድ ተገደድኩኝ። „ያዬነውን እንናገራለን የሰማነው እንመሰክራነን።“ እንዲሉ፡፡ ·          መነሻዬ። https://www.youtube.com/watch?v=_O_sP971z3k ጠ / ሚ ዶ / ር አብይ አህመድ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ የመኖሪያ ቤት ቁልፍ አስረከቡ ይላል ፋና ቴሌቪዥን ያገኘሁት ዘገባ። ትናንት በጨርፍታ ነበር ዛሬ ዘለግ አድርጌ ደጋግሜ አዳመጥኩት። መቼም ዘንድሮ የምሥራች ይሁን መንፈሳችሁ ብሏል መዳህኒተ ዓለም ክርስቶስ። „አቤቱ በፈቃድህ ለሕይወቴ ሃይልን  ሰጠሃት ፊትህን መለስህ፤ እኔም ደነገጥሁ።“ የኔዎቹ ባለፈው የብጹዑ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መርቆርዮስ  30ኛ ዓመት የፕትርክና የሲመት ባዕል ሲከበር ከፍቶኝ ነበር። ደረጃውን የጠበቀ አልነበረም። አያይዤም የብጹዑ ወቅዱስ አባታችን 4ኛ ፓትርያርከ  ዘኢትዮጵያ ቤት እጅግ ጠባብ እና ጥብቆ እንደሆነም ጠ/ ሚር አብይ ሊጎበኟቸው በሄዱ ጊዜ ታዝቤ ስለነበር ቅሬታዬንም አያይዤ ጽፌ ነበር። የልብን መሻት ያዬ ኤ

ለቀንበጥ ብሎግ ውዶቼ እንኳን አደረሳችሁ! መልካም አውድዓመት!

ምስል
ይድረስ ለቀንብጥ ብሎግ ታማኝ ታዳሚዎቼ በሙሉ። ከሥርጉተ ሥላሴ የቀንበጥ ብሎግና የፍቅራዊነት ዩቱብ አዘጋጅ። „ልባችሁ የቀና ሁላችሁም እልል በሉ።“  መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፩ ቁጥር ፲፩ ናፍቆቶቼ ሆይ! በቅድሚያ ዘመኑ ለተለወጠበት ምክንያታዊ መስዋዕትነትን ለከፈሉ ወገኖቻችን የህሊና ጸሎት በዬቤታችን እናደርስ ዘንድ እለምናችሁ አለሁኝ፤ ለሰኔ 16 ሰማዕታትንም አስበን። በዚህ እንስማማ። ቄሮ እና የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ ላደረጉት የሰፋ እና የደረጀ የተጋድሎ አውራነት፤ ለፍሬም መብቃት ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል። ለዚህ ተጋድሎ ግንባራቸውን ለባሩድ ለተሰዉት ነፍሳቸውን አርያም ገነት ያግባልን፤ አካላቸው ለጎደሉትም መጽናናቱን ይስጥልኝ። ቤተሰቦቻቸውንም ይጠብቅልን፤ አሜን! ጤና ይስጥልኝ እጅግ የማከብራችሁ እና ሙሉ መንፈሴን ለምልገሳችሁ የኔዎቹ፤ የብቻዬ የቀንበጥ ብሎግ ታዳሚዎች ሚስጢረኞቼ። እንዴት አላችሁልኝ? እንኳን ለዘመን መለወጫ ለ2011 ለቅዱስ ዮሖንስ ዋዜማ ዕለት አደረሳችሁ አደረስን። እንቡጢጣ መረጃ ስለ ጎንደር አለችኝ። እንዲህ አንድ የተለዬ ባህል አለው - ጎንደር። እርግጥ ከቤተሰብ ቤተሰብ ይለያያል አፈጸጻሙ። ለጎንደር ዋዜማው ፍጹም የተለዬ ግርማ ሞገስ አለው። እንዲያውም ዕለቱ የልጆች ሲሆን ዋዜማው ምሽት ላይ  የአዋቂዎች ነው ብል ያምርብኛል። ዋዜማው ምሽት ላይ ጉዝጓዙ ግጥም ብሎ ይጎዘጎዛል። በጉዝጓዙ ልክ አድዮ አለበት። ከዛ ቤተሰብ ክብ ሠርቶ አዲሱን ልብ ለብሶ፤ ያልገዛውም ጸዳ ያለውን መርጦ በረድፍ በረድፉ እንደ ዕድሜ ደረጃ ይቀመጣል።  ለቤተሰቡ ልዩ ሆና የምትወደድ የቅርብ ሰው ጎረቤት ልትሆን ትችላለች፤ አበልጅ ልትሆን ትችላለች፤ ጓደኛ ልትሆን ትችላለች፤ ምራት

እልልልልል

ምስል
የመልካምነት  ቤተ -ክብረት! „አግዚአብሄር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከአፉም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤  እርሱ ለቅኖች ደህንነትን ያከማቻል፤ ያለነውር ለሚሄዱት ጋሻ ነው፤  የፍርድ  ጎዳና ይጠብቃል፤ የቅዱሳኑንም መንገድ ያጸናል።“  መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፪ ከቁጥር ፮ እስከ፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ 10.09.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።               ሃይማኖቴ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሆይ! ኮራሁብሽ! ተመስገን! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቤተክርስትያን „አገር ናት“ ያሉት ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በ50 ዓመት ታሪኳ ለአንድ የአገር መሪ ጸጋን ስትሸልም፤ ልቅናን ስታከብር የመጀመሪያዋ ነው።  ይህቺ መከራ ፈተና እና ፍዳ ተልይቷት የማታውቀው ቅድስት ቤተክርስትያን ምን ያህል ከውስጧ የዘለቀ የማስተዋል ጸጋ እንደተሰጣት በዚህ ብቻ ማመሳከር ይቻላል።  ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሰላም አብነት ተቋሙነቷን የረጋገጠችበት ማዕልት ነው ማለት እችላለሁኝ - እኔ። ይህ የክብር ዕውቅና ምርቃትም ነው። ምርቃቱ ለትወልዱም፤ ለአገርም፤ ለማህበረ - ምዕምኑም፤ ለአገልጋዩም ለመልካ ምድሩም፤ ለተፈጥረዊ ጸጋውም ጭምር ነው። ይህ ትውልድ ሆነ ማህበረ ምዕመናኑ ለነፃነቱ ተጋድሏል፤ ሙቷል፤ ታሠሯል፤ ተሰዷል፤ አካሉን አጥቷል፤ ክብሩ ተገፏል፤ ባዕቱን ተነጥቋል። ማንነቱን ተቀምቷል። ይህን ሁሉ ችግር ተሸክሞ ደግሞ አገራዊ፤ ብሄራዊ ግዴታውን ሲወጣ በትጋት ቆይቷል። ሃይማኖታዊ ቀኖናው እና ዶግማው የሚፈቀድለትንም አማኙ ሲከውን ኖሯል። በሃይማኖቱም ተሳዷል፤ ተነግላቷል። ሁሉንም እንደ አዬመጣጡ ታግሶ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዛሬዋ እሸት አንበጥ ዘመን ደርሷል። መልካሙ ነ

ሳተናው ድህረገጽ የ2010 ምርጤ ነው።

ምስል
ምርጤ!                               "ጥበብ በቀደሙ ሰዎች ሁሉ ዘንድ ተመረመረች።                                በሃይማኖት ስማቸውን ላስጠሩም ሰዎች ትንቢትን                                  ታስተምራለች፤ ወደ ነብያትም ምሳሌ ታገባለች።                                    የተሠወረውንም ምሳሌ ትመረመራለች፤                                      ንባቡንም ወደ ትርጓሜ ትመልሳለች።“                                  መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፱ ከቁጥር ፩ እስከ ፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 09.09.2010 ከጭምቷ ሲዊዘርላድ።  የሳተናነት ማር ወለላ አዎንታዊነትን ሲያበላ የቅንነት ነፃነት ገላ የቤተ አብርኃም ፍሬ ዘለላ የጥሪት ቅኔ ፈርጣዊ ዛላ። የሁለመና ህብረ ዜማ ረቂቅ የሁለንትና ነባባተ ብርቅ የተግባር አናባቢ ንዑድ ድንቅ ሳተናው አንደስምህ ወርቅ! ሳተናው ድህረ ገጽ ለቀንበጥ ብሎግ የ2010 የዓመቱ ምርጥ ሚዲያ ነው። ምርጥነቱ ቅንነቱ፤ አሳታፊነቱ፤ አቃፊነቱ እና ሚዛናዊነቱ ልዩ ጣዕም ያለው፤ እውነት የፈለቀበት ከመሆኑ ላይ ነው። ሳተናው ድህረገጽ የሃሳብ ሙግቶችን ያለ ተዕቅቦ የሚስተናግድ  ለኢትዮጵያ የሚዲያ ህይወት እና ታሪክ አዲስ በር የከፈተ ልዩ የሚዲያ ነፃነት ምዕራፋችን ነው። ሳተናው ደፋር ነው። ድፍረቱ ሰውነትን በመቀበል እረገድ ነው። እኔ እንደ እሱ ሰውነት የሚቀብል ሚዲያ አይቼም፤ አድምጬም አላውቅም። ሁሉ በተመሠረተብት ማንነቱ ወይንም ዞጉ ላይ የተመሠረተ ነው። ሳተናው ድህረ ገጽ ለጥብብ ያለው ክብር እና