ኦ! አብይ እንኳንም የእኛ ሆንክልን!
ለብጹዕን አቨው ይስሃቅን
አማኑኤል ሰጣቸው።
„ጻድቃን ሆይ በእግዚአብሄር ደስ ይበላችሁ፤
ለቅኖች
ምስጋና ይገባል።“
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፪ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
10.09.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።
ኑሩልን!
"በስም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ፤
አሜን!"
ሳይገባኝ እና ሳልመቼው
የደጀሰላሙን
ታምራት እናገር
ዘንድ ተገደድኩኝ።
„ያዬነውን እንናገራለን የሰማነው እንመሰክራነን።“
እንዲሉ፡፡
- · መነሻዬ።
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ የመኖሪያ ቤት ቁልፍ አስረከቡ ይላል ፋና ቴሌቪዥን ያገኘሁት
ዘገባ። ትናንት በጨርፍታ ነበር ዛሬ ዘለግ አድርጌ ደጋግሜ አዳመጥኩት።
መቼም
ዘንድሮ የምሥራች ይሁን መንፈሳችሁ ብሏል መዳህኒተ ዓለም ክርስቶስ።
„አቤቱ
በፈቃድህ ለሕይወቴ ሃይልን
ሰጠሃት ፊትህን መለስህ፤ እኔም ደነገጥሁ።“
የኔዎቹ
ባለፈው የብጹዑ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መርቆርዮስ 30ኛ ዓመት የፕትርክና የሲመት ባዕል ሲከበር ከፍቶኝ ነበር። ደረጃውን
የጠበቀ አልነበረም።
አያይዤም
የብጹዑ ወቅዱስ አባታችን 4ኛ ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ ቤት እጅግ
ጠባብ እና ጥብቆ እንደሆነም ጠ/ ሚር አብይ ሊጎበኟቸው በሄዱ ጊዜ ታዝቤ ስለነበር ቅሬታዬንም አያይዤ ጽፌ ነበር።
የልብን
መሻት ያዬ ኤልሻዳይ አምላክ የሚሳነው የለም እና ይህን ታላቅ ብሥራት አሰማኝ። ለአዲስ ዓመት ተጨማሪ ሥጦታነቱ ልዩ ሜሮኔ ነው። ቅብዕ ቅዱስ።
የብጹዕነታቸው የመንፈሳዊ ሚስጢር በፍጽምና ልቦናዬን ይገዛዋል። አድህኖ ምስላቸውን
አይቼ አልጠግበውም። እሳሳዋለሁኝ። ተዶሟቸው አንድ ትውልድ ይፈጥራል። ዝማታቸው ጥበብ ቅኔ ነው። ሁለመናቸው የትውፊትም የትሩፋትም ተቋም ነው።
በእኒህ ብጹዑ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መርቅሪዮስ መንፈስ ውስጥ አንድ ያልተገለጠ ልናመሳጥረው ብንል አቅሙ የሌለን ስለሆነ ብቻ እንጂ ሱባኤው ያጎናጸፋቸው በረከት፤ ረድኤት ስበቱ ልዩ የሆነ እዬኦራዊ ትንግርት አለ።
ብቻ ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ለንዑዱ
ሰማዕት አባታችን ለአቡነ መርቆሪዮስ የሚመች የንጽህና ክብራቸውን ልክ የመጠነ፤ ልዩ የመኖሪያ ቤት ቁልፍ ራሳቸው ጠ/ ሚር
አብይ አህመድ በእጃቸው ማስረከባቸውን አዬሁኝ። በሥርዓቱ ላይም ክብርት ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው መገኘታቸው የበለጠውን
ወስጤን ሰላም ሰጠኝ። ሴቶች እርህርህናቸው ጥበብ ነውና።
ልዑል
እግዚአብሄር የዘመን ምስክር የሆነችውን ቅድስት ኦርቶዶክ ተዋህዶን እንዳከበሩልን እነሱንም ልጆቻቸውንም ልዑል እግዚያብሄር ይባርክ
ይቀድስ። አሜን።
ምን
ይባል እንዴትስ ይገለጥ። በውነቱ አቅም አነሰኝ። መጻፍ አልችል አልኩኝ። ቃላቶች የውስጤን ፍስሃ ሊመጥኑልኝ አልችል አሉ።
እና
የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያን ልባችን፤ መንፈሳችን፤ ህሊናች፤ ውስጣችን ለማን መሸለም አለብን? ጥያቄው ይህ ነው።
ከዕምነታችን
ክብር፤ ልዕልና በላይ የሆነ ነገር ከቶ ምን አለና? ጽኑዋ ቅድስት ቤተክርስትያናችን ይህን ያህል ንጹህ ያልባለቀ ድንግል የቤተ መንግሥት ክብር፤ ግርማ፤
ሞገስ፤ ጉልላት፤ መደበኛ ተግባር ስትሆን፤ ይህን የመሰለ ዕንቁ አትኩሮት ከማዬት ወዲያ ምን ሌላ የመንፈስ ጸጋ እና ሀብት
አለን። እኮ ከቶ ምን? እንኳን ደስ አለን።
ይህ
እኮ ለተኖረበት የ27 ዓመት ግፍ እና በደል ልዑል እግዚአበሄር መሬት ላይ ወርዶ እዬፈጸመው ያለው ታዕምር ነው እኮ። ናፍቆታችን ተፈጸመልን ቢአከነ ጥበቡ በሃያሉ አምላካችን። ኦ!
አብዩ እንኳን ተፈጠርክልን! ኦ! አብዩ እንኳንም የእኛ መሪ ሆንክልን። አንተን ሳያገኙ፤ ሳያዩ፤ ቅናዊ ትንፋሽህን ሳያገኙ ያለፉ
ወገኖቼ ምን ያህል ተጎዱ።
ዕጹብ
ድንቅ ነው። ዕጹብ ድንቅ ነው። ገነት ምድር ላይ በሰው እጅ ተበጅታ ሳያት የመጀመሪያ ጊዜዬ ነው። ገነት የመንፈስ፤ ገነት ለሥነ - ልቦና እርካታ የጽድቅ ያህል ነው።
በመደበኛ ትትርና በተከታታይ እኮ ነው የኢትዮጵያ መንግሥት አደራውን እዬተወጣ ያለው። ቃል ኪዳኑን አክብሮ መገኘቱም ካሰብነው፤ ከገመትነው ልክም በላይ ተቋማዊ መተማምንን ከፍቶልናል። ርግብ በር የሆነ የእልልታ ዘመን። መላዕክታን፤ ቅዱሳን፤ ደናግልና እራሱ አማኑኤል
እንዴት ደስ ይለው? ድንግልዬስ ብትሆን ምንኛ ምርቃቷን ትልክ። ብሩክ መንፈስ እንሆ አዬሩን እንዲህ ተናኘ። ተመስገን!
የቅድስት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ይህን ብላቴና ከጎልያድ መንጋጋ አትርፎ የሰጠን አምላክ የተመሰገነ ይሁን ልንል አዘወትርን ይገባል።
አላዛሯ ኢትዮጵያ በመሬቷ ላይ እንዲህ ያለ የቅድስና ብሩክ የሆነ ተግባር በመንግሥት ደረጃ ለማዬት መብቃቷ ራሱ ልታምነው የማትችለው ገድል
ነው። የቤተ መንግሥቱ ቤተሰብ ሆነችልን ቅድስት ሃይማኖታችን። ተመስገን!
ተመስገን! ነው እንጂ ሌላማ ምን ይባላል። ለልዑል እግዚአብሄር ይህን ከማለት ውጪ እና ከዚህ ቅዱስ ሙሴ ጎን በመንፈስ ከመሰለፍ፤ በተጨማሪም ተግቶ ከመጸለይ ውጭ ምን ይደረጋል። ለካንስ ጎንደር ውነቱ ነው ሚዚያ ላይ አሁን የጸሎት ጊዜያችን ነው ያለው። ይገባልም።
ይህን
እዮራዊ ሽልማት፤ ይህን የመሆን ውበት፤ የህን በቃል የመገኘት ቅኔያዊ ሚስጢር፤ ይህን አዳራን የመወጣት ስጦታ ሥም አጣለሁለት። አብይ
ኬኛን ስጽፍ ማንጠግቦህ ብዬ ነበር ዛሬም ውስጤን ቢገልጸው ማንጠግቦህ ልበለውን?
አሁን
አብይ መንፈስ እዬሆነ ነው። ሁሉ ቦታ ቤተኛ ለመሆን የቻለ ካለኮረጆ ቁጥር ነፍሳችን የመረጠችው ድንቅዬ።
የቅድስት ተዋህዶ
ልጆች ይህን ቅድስና የውስጥ ታቦት ለማድረግ አይከብደንም። እስቲ ውል እንዋዋል? እስኪ ኪዳን እንሰር? ለሰላም ታላቅ ክብር ያላቸው
የሌላ እምነት አባላትም ተካታዮችም ሆኑ ዕምነት የሌላቸውም ወገኖቻችን ቢሆኑ ይህን ተፈጥሯዊነት ማዬት በመቻል ብቻ መንፈሳቸው እንዴት ደስ ይለው?
የአባታችን
የአቡን መርቀሪዮስ ብቻ ሳይሆን የአባታችን የአቡነ ማትያስም
ቅንነት ቢኖር ነው ሁለቱንም በህይወት አኑሮ ለዚህ ጸጋ እና ለዚህ በረከት ያበቃቸው። ይሳቅን ሰጣቸው አማኑኤል። ተመስገን።
የብጹዕን አባቶቻችን ረድኤትና በረከት አይለዬን። አገራችን ይጠብቅልን አማኑኤል። አሜን!
ወስብሃት
ለእግዚአብሄር።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ