ዕውቅና የሌው ችግር ከመፍትሄ ማን አስደርሶት?!
እንዴት? መቼ? በምን ሁኔታ? ስለምንስ?
ዕውቅና የሌለው ችግር
ከመፍትሄ ማን አስድርሶት?
"ንጉሥ በፍርድ አገሩን ያጸናል፤ መማለጃ የሚወድድ ግን ያፈርሰዋል።"
መጸሐፈ ምሳሌ ፳፱ ቁጥር ፬
- · መራራ መነሻ።
የራያ
አማሮች በትግራይ
ቅኝ ገዢ
ወራሪዎች የሚደርስባቸው
እንግልት ግድያና
የማንንት ነጠቃ።
Ethiopia Special News የወልቃይ ስቃይ እየበረታ መቶዋል October/5/2018
ራያ አላማጣ ከትግራይ ጨፍጫፊ ሰራዊት ጋር ፍጥጫ 7 አማሮች ተገድለዋል
- · እምታን በዕድምታ፤ ኡኡታን ለሰርክ …
አሁንም ጩኸት ሆነ። አሁንም እሪታ አለ። አሁንም ስጋት አለ። አሁንም መከራ አለ። ህፃናት ያለቅሳሉ፤ እናቶች ያነባሉ፤ አዛውንቶች ኡኡ ይላሉ። ማን አላቸው እና ያልቅሱ ... ፈጣሪ ከሰማቸው።
አሁንም የታቀደ
ጥቃት አለ። አሁንም ለቅሶ አለ። አሁንም መሰደድ አለ። አሁንም ተስፋ ማጣት አለ ለአማራ። አሁንም መኖር ተከልክሏል። አሁንም መተንፈስ
አያቻልም - አማራ። አሁንም ችግሮች በአይነት ተደርድረዋል በተለይ ለአማራ። አሁንም አሳሩ ውጧታል አማራን። እንዴት ይፈታ? መቼስ ይፈታ?
በምን ሁኔታስ ይፈታ? ስለምንስ ችግሩ አዬለ?
መቼ ይፈታ ቢባል ችግሮችን ለመፍታት ለችግሩ ዕውቅና መስጠትን ይጠይቃል። የወልቃይት የራያ የጠገዴ
የመተከል ችግር፤ አገራዊ ችግር ነው ተብሎ አይታወቅም። ተጋድሎውም እንዲሁ። ኢትዮጵያ የክት እና የዘወትር ልጆች ነው ያሏት እና።
የአማራ የማንነት ጥያቄ የኢትዮጵያ መንግሥት በብሄራዊ ደረጃ
በተለዬ መልኩ አይታዬም። ከሌሎች ችግሮች ጋር አብሮ ይጠናል የሚል ድንብልብል መልስ ሲሰጥ ይስተዋላል። የሚፈራ ድርጅት የለውማ።
ተቀባይነት ያለው ድርጅት የለውማ። አዴፓ እንደሆን ችግርን ለመሸከም ነው የሚመረጠው። ድልድይነት። ወይንም ግርባነት።
የመተከል፤ የራያ፤ የመተከል፤ የወልቃይት የጠገዴ ከሌላው ችግር የእነዚህ አካባቢዎች የሚለይበት
ዋናው ምክንያት የአማራ የማንነትን ሥነ - ልቦናን በቀጥታ ከመግደል፤ ዘሩን ከመንቀል፤ ትውልዱን ከማቀጫጭ ጋር ጉዳዩ የተያየዘ መሆኑን ካለመቀበለ
የሚመነጭ ነው የሚሆነው። ለዚህም ተባባሪ ከመሆን ሞት በስንት ጣዕሙ።
ሌላው እኮ ኦሮሞ ነኝ አትበል አይደለም ትግሉ፤ ወይንም ጉራጌ ነኝ አትበል አይደለም ችግሩ።
የአማራ ተነጥሎ፤ ተለይቶ፤ ታቅዶ ትናንትም፤ ዛሬም፤ ወደፊትም ሊቀጥል የሚችለው አመክንዮ አማራ „አማራ ነኝ“ አትበል፤ በምስል እኛ
በሰራንልህ ማሳክ ውስጥ ተዳፍነህ ተቀመጥ ነው ጉዳዩ።
ይህ ከሊቅ እሰከ ደቂቅ የሚታመሱበት የፖለቲካ ሊቃኑ ሁሉ የጓዳ ድርድር ነው።
እራሱ በዞግ የተደራጀው የአማራን በብሄሩ መደራጀትን አይፈልግም። እራሱ በዞጉ የተደራጀ ጋዜጠኛ ሲጠይቅ ስለምን ትደራጃለህ ብሎ
ይነሳል። እራሱ የራሱን ዞግ ሲሰበስብ ውሎ የሚያድረው ለምን አማራ ይደራጃል ብሎ አፉን ሞልቶ ይሞግታል።
እንደ ኢትዮጵያ ሊሂቃን ሆነ እንደ ኢህአዴግ እንደ ግንባር አማራ ክልል የሚባለው እራሱ ሙሉውን
ቢደመሰስላቸው ይወዳሉ። ሚደያውም የአማራ ሚዲያ ባይባል። ከኖረም በግርባነት ወይንም በገባርነት፤ ወይንም በተጠማኝነት ወይንም በጭሰኝነት ብቻ ነው።
ሌላ ቦታ ሄደው ትንፍሽ የማይሏትን
ከሌሎች የዞግ ድርጅቶች ጋርም ሆነ ከዞግ ድርጅት ከበቀሉ ሊሂቃን ጋር ሠርግ እና መልስ ሆኖ፤ አሸሼ ገዳሜ ሲሉ የማይጎረብጣቸው
የአማራ ነገር ሲነሳ ግን ሁሉም ያንደፈድፋቸዋል። ሁሉም ቀልባቸውን ያጣሉ።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ ይሁኑ ዶር ለማ መገርሳ የኦዴፓ አባል ናቸው። ኦዴፓ የዞግ ድርጅት ነው።፡ድርጅታቸውን የአፍሪካ መሪ ለማድረግ
ነው በርተትተው የሚሠሩ ናቸው። የወጡም ከዛ የዞግ ድርጅት እንጂ ከህብረ ብሄር ፓርቲ አይደለም። ይህ መሆኑ እየታወቀ ነው አማራ ሊሂቃኑን በድርጅቱ እንዳያወጣ ሰፊ ጫና እዬተደረገ ነው የሚታዬው።
እንገነጠላል አለን የሚሊትን የራሳቸውን ገማና በቪአይፒ ደረጃ እያሽሞነሞኑ አማራ ብሄርተኛነት ገና በጮርቃው በቀለ
ተብሎ የወረደውን መከራ ሙሉ 6 ወር ያለ እረፍት በወረፋ፤ በሽታሽቶ፤ በጫና ብዛት አፍነው ሊያፈንዱት ሲታገሉት መክረማቸውን እያዬን ነው።
አቅም
ያለው ሁሉ አቅሙ ጉልበቱን ጫናው የሚያሳያው በዛች ተቆርምጣ በተሰጠችው፤ ኦነግ እና ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተከፋፍለው ሲያበቁ በቸሩት እራፊ ላይ እንኳን
ተሁኖ አማራ ነኝ የሚል ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንዲኖር አይፈቀድም።
በዛው አማራ ክልል ተብሎ በተሰጠውም ቆራጣ ማሳ ውስጥ የአማራ ዕድል ዕድገትም የሌላ ዞገኞች ሲሳይ ነው።
ይህም ሆኖ፤ ይህም ተችሎ በዛ የሚኖሩ ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች የራሳቸው የአስተዳደር መብት ተደንግጎላቸው፤ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮላቸው
በመብታቸው ይጠቀማሉ። ይህም ሌላው ትዕይንት ነው። ያልተደፈረው አመክንዮ። አማራ ግን በተሰጠችው እራፊ መሬትም ጥገኛ ሆኖ እንዲኖር እንጂ አማራ ነኝ ማለት
ፈጽሞ አይፈቀድለትም፤ እንኳንስ የሥልጣን ባለቤት ሊሆን ቀርቶ። እንኳንስ ኦሮምያ፤ ትግራይ፤ ደቡብ፤ ሱማሌያ፤ አፋር፤ ቤንሻንጉል፤ ሀረሬ
ላይ በራሱ በመረጣቸው በወከላቸው ባቋቋሞው ምክር ቤት ሊተዳደር ቀርቶ።
የጫነው ዓይነት ፋክት ወገናቸው ለሆነው ሁሉ ክፍት አድርጌ የምተወው ይሆናል። ፋክተኞችም በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። አማራ ከሌላ አገር
መጥቶ እንደ ሠፈረ መጤ መታዬቱ ግን በዘመቻ ፋታ አልባ በሆነ ጫና መዋከቡን ግን እንናገራለን፤ እንጽፋለን። ትናትን በምን መልኩ እንዳሳለፈ ዛሬም ምን እንደ ታጨለት፤ ነገ ምን እንደሚገጥመው አልተለጎምንም እንናገራለን። ባለቤት የሌለው ህዝብ ነው አማራ ማለት።
የአማራ እናትም ለለቅሶ - ለሐዘን የተፈጠረች ስለሆነች ትናንትም ለቅሶ፤ ዛሬም ለቅሶ ነገም ለቅሶዋ ይቀጥላል።
አማራ ክልል ተመራጮች ተወካዮች የፊት ለፊት አድራጊ ፈጣሪዎች ሌሎች ሆነው ነው የኖሩት። አሁንም
ያ ቀጥሎ እያዬን ነው። እንደገናም በዘረፋ - በወረራ - በስርቆት - በማንአህሎኝነት በተወሰደው የአማራ ህዝብ ባዕት፤ በገፈፋ ለትግራይ
እና ለቤንሻንጉል ተሸልሟል። ከዛም ሆነው ተዘግታችሁ ተቀመጡ ነው ብይኑ። በሌላ ክልል የሚኖሩ አማሮች አንድም ልዩ ክልል ተስጥቷቸው አንድ ውክል የአማራ ነፍስ የለበትም። እስቲ ይነገረን የትኛው ክልል ላይ ነው አማራ ተመራጭ ሆኖ ወንበር የተሰጠው፤ ለፌድራል የሚ/ሚር መ/ቤትስ የተወከለው? እራሱ ስለመኖራቸውም
ከቁጥር አይገባም።
እንደገና ደግሞ የኢትዮጵያ ገመና ከታች ሁን እንደ ተለመደው ተብሎ፤ ሙጌራ ዳቦ ሆናል። በዚህ ሁሉ ሰቆቃው ማህል ደግሞ በአዲሱ
የጥገና ለውጥ ጫን ተደል በዬዕለቱ ባላበራ ሁኔታ ተጭኗለኝ። ይህ ሁኔታ በምን አኳኋን እንደሚታረቅ አንድዬ ይወቀው? ስለምን ይህ ሆነ ለሚለው አማራነትን
ማራቆት ነው ስልቱ። አማራ ተጉድቷል
የሚል የፖለቲካ ሊሂቅ እኔ ሰምቼ አላውቅም። ደግሞም አልጠብቅም።
ትናንትም የነበረው ዛሬም ያለው አማራን ከምድረ ኢትዮጵያ የመሰረዝ ታክቲካዊ፤ ስልታዊ ስትራቴጅ አልሞ የማጥቃት ትልምን ነው እኔ በግሌ እዮባዊነትን ሰንቄ እያዬሁ ያለሁት።
እንዴት ይፈታል? የሚሉ ብለው የሚጨነቁ ጥቂት የፋክት ወገኖች ሊኖሩ ይችላሉ? ዕውቅና ሳያገኝ የሚፈታ ችግር ፈጽሞ የለም።
ኖሮም አያውቅም። ይህ ችግር በቀጥታ የዘራፋ፤ የወረራ፤ የስርቆት ብሄራዊ ችግር ነው፤ ታቅዶ ተስልቶ የተከወነ በደል ነው ብሎ ለመቀበል
ሙሁርም ሊሂቃኑምም የፖለቲካ መሪውም አልተገኘም - ለምስክርነት። ሊሂቃኑ ከግላዊ የህሊና ምቾታቸው ወጣ ብለው ፋክትን ለመፈለግ በሌላ ጉዳይ እንጂ አማራ
ላይ ሲደርሱ ፈተናውን አያልፉም ይወድቃሉ። ዘላቂ ውስጥነትን ለመቀበል ከውስጥ ያለው የጥላቻ ሃውልት መደርመስ ይኖርበታል። ፈቃዱ ያለው ከባለቤቱ ነው። ለበጣውን ኑረንበታል። አፍንጫህን ላስም ተኑሮበታል።
የወልቃይት፤ የራያ፤ የመተከል፤ የጠገዴ ይህን ጥያቄ የለማ ሌጋሲም እንዲነሳበት የሚፈልግ አይመስልም። የራሱን ቤተሰቦች ግን ሲያስፈልግ
በሹመት፤ ሺያሻው በትእዛዝ የሚያደርገውንም አሁንም እዮባዊነትን ሰንቀን እያዬን ነው። እንታዘባለን። ልብም አለን።
ስለዚህ እንዴት ይፈታ? መቼ ይፈታ? የሚሉት ጥያቄዎች
ራሳቸው ባለቤት አልቦሽ ናቸው ወይንም ከወና ጋር ቀለበት አስረዋል፤ ወይንም እዳሪ አዳሪዎች ናቸው። የአማራ ነገረ ሚስጢር ባለቤት
አልቦሽ አምክንዮዎች ደግሞ በሰውኛ የማይፈቱ መሆኑ መታወቅ አለበት። እህሳ እንዴት? ለሚለው እዬራዊ ይጠዬቅ ነው መልሱ።
የራያ እናት ኢትዮጵያዊ አይደለችምና ታልቅስ፤ የመተከል እናት ኢትዮጵያዊ አይደለችምና ታልቅስ፤
የወልቃይት እናት ኢትዮጵያዊ አይደለችም እና ታልቅስ፤ የጠገዴ እናት ኢትዮጵያዊ አይደለችም እና ታልቅስ።
ሁሎችም ስንቃቸው ለቅሶ ይሁን።
በቃ ምን ሲገድ? የአማራ እናቶች ያልቅሱ እስከ ህልፈታቸው … ኑሮውበት ዬለንም? እዮር ዘራፊን፤ ወራሪን፤ ሌባን በአዬር መቃወሚያ፤ በመድፍ እና በመትረዬስ የማይቆመውን ቁጣውን
እስኪልክ ድርስ በተደሞ ተግቶ መጸለይ ብቻ ነው ለ50 ዓመት የአማራ እናቶች እንባተኞች መፍትሄው። ትናንት በጦርነት ዛሬም በታቀደ መንግሥታዊ ሞት። ባለቤት ለሌለው ህዝብ ኑሮውም ሞት፤ ሞቱም ሞት ነውና።
- · አንድ ለመንገድ እንዲህ …
እንዲህ ዓይነት ጉዳዮችን ለመፍታት የፌድራል ምክር ቤት ምንትሶ ቅብጥርሶ የሚባል አለ እኔ ራሱ
ስለምን ይህ ቅጥል አካል ይህ የሲሶ ምንግሥት ያለው ባለሥልጣን አካል እንደ ተቋቋመ አላውቅም። እሚያስረዳኝም ሰው አለገኘሁም። ለምን ተልዕኮ ነው የተቃቋመው?
በጀት እንቆጥባለን ብሎ መሰለኝ የለማ ሌጋሲ ሚ/ር መስሪያ ቤቶችን ያጠፈው እና ይህስ ምን ይሰራል? የድሪቶ ብዛት ምን ያደርጋል?
በነገራችን ላይ አፈ ጉባኤዋ ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሰው ናቸው ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም።
እና አሁንም የመለስ መንፈስን አዝሎ የወልቃይት፤ የጠገዴ፤ የራያ፤ የመተከል ጥያቄ ይፈታል፤ ትልቁ ጉዳይ ቀርቶበት ዕውቅና ያገኛል
ብሎ ማሰብ ጅልነት ነው። አይሆንም፤
የማይሆንም ነው። ማን አስጠግቶት። በዬትኛውም ሚዲያ ስታዳምጡ በትጥቅ ይሁን በሰላማዊ እታገላለሁ ለሚለው አማራ ሁነኛ የለውም። ይህ እውነት ነው። ለውጡንም ያስገኜ ለውጡንም በቅንነት የሚደግፍ ደግሞ አማራው ነው። ምን ባገኝ ብሎ? አሁንም እዮር ጠዬቅ?
ይህም ማለት ደግሞ በትርጉም ሲቃና የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ ያስገኘው ውጤት ተጠቃሚው
ሌላ እንጂ አማራ እንዳልሆነ ቁልጭ ብሎ ማዬት ይቻላል። ብዙ ሰው በተወሰነ ደረጃ ተስፋማ ሆኗል። ቢያንስ ነኝ ባለው ልክ ተከብሯል ከ አዲስ አባቤዎች ውጭ ያለው።
አማራም ዛሬም ያለቅሳል። ጠ/ሚር አብዩን ለሥልጣን የባቃው
እኮ የቄሮ የሳቢያ ትግል ብቻ አይደለም የአማራ የህልውና የማንነት ምክንያታዊ ተጋድሎ እንጂ። አማራ አሳዛኝ ፍጡር ነው።
እናመሰግንህአለን እንኳን አይባልም። ሞቶ እንኳን ያመጣው ለውጥ ተጠቃሚ ያልሆነ
ፍጥረት ቢኖር አማራ ብቻ እና ብቻ ነው። ለሥነ - ልቦናው እንኳን ቆራጣ ጥንቃቄ የለም። በእነሱም ተጋድሎ የተገኘ ነው የሚል የለም
ከዶር ለማ መገርሳ ጀምሮ። ፍቹ ያለ እዮር ዘንድ ነው።
አብዝቶ መጸለይ። አብዝቶ መስገድ። በንጽህናም የግል ሱባኤ መያዝ በእጅጉ ያስፍልጋል።
አሁን ለፈቃድ ፆመኞች ጽጌ ፆም ነው። የድንግልዬ። የፅጌ ፆም ጉርሻዋ አያሌ ነው። ስደትን ታውቃዋላች እና እመቤታችን። 27 ዓመት ሙሉ በአገሩ
የተሰደደ ህዝብ አማራ ብቻ ስለሆነ በምህረት በማጽናኛ እጇ ትዳብሰው መከረኛውን ማህበረሰብ። ደግሞም ታማልደዋለች። ይህን የእኔ ድንግል ታደርገዋለች።
አሁንም ያው መዘለል፤ መረሳት፤ እንዲህም መዘንጋት ከሆነ ደግሞ ከድጋፍ፤
ከበርቱልንም ወጣ ብሎ አቤቱታን ለምድራዊ ሉላዊ ባለሥልጣናት ማቀረቡ በእጅም ያለ ጉዳይ ነው። ያን እንደ ተፈጸመ ሁሉም ይህንም
ለመፈጸም የሚያዳግት ነገር የለም። የሚፈለገው የህሊና ድንግልና ብቻ ነው። ተደሞው እዮባዊነቱ የሚያፈራው ነገር ካለ ተብሎ በጠፍ
መሬት እዬተጠበቀ ነው ያለው።
እኔ በግንቦት ወር ለጠ/ሚር አብይ አህመድ እና ለዶር ለማ ገርሳ አቤቱታ አቅርቤ ነበር እኔም
ዜጋ ከሆንኩማ አብይ ሆይ ብዬ! በሚል ዘለግ ያለ አቤቱታ ነበር። ቢያንስ በወፍ በረር የራያ፤ የጠገዴ፤ የወልቃይት የመተከል አማሮች ደህንነታቸው ይጠበቅ ዘንድ ሰሚ ግን የለም። እርግጥ የተደራረበ ጫና መኖሩን ባውቅም ጭራሽ እንዲህ አትኩሮት ሲፋድስ ግን አዝናለሁኝ።
ለጥበቃ እንኳን አውላላ ሜዳ ላይ ሆነው ባዶ እጃቸውን እዬተሰው ነው፤ በገፍም እዬታፈሱ እዬታሰሩ ነው። የደረሰላቸውም የለም። አድማጭም
የለም። አቤቱታዬም ቢታዩ ቢታዩ ጭራሽ ትግራይም ኦሮሞዎች አሉ ራያ ላይ ሲሉ ነው ያዳመጥኩት ጠ/ሚር አብይ አህመድ እንኳንስ ሌላ። ከዚህም
ባለፋ ዓለም ያወቃቸውን አገሮች ወሰናቸው የቅኝ ግዛት ነውና ያን እንሰበው አፍረካዊነታችንም አለበት።
ይህ ሁሉ ዳርዳርታ ስለምን? እንዴት? የሚለው የራሱን የገዢዎች ገዢ አድርጎ የተቀመጠውን የትግራይን ምሽግ ላለመንካት
ተብሎ ነው። እነሱንም አይከፉ፤ ኦሮሞም አይከፋ፤ ቤንሻንጉልም አይካፋው፤ አማራ ግን እንደ ከፋህ ኑር እከሰማይ ደጅ ታገኘዋለህ ነው ጨዋታው። ልክ ለአቶ ታከለ ኡማ ትብት እና ከፍ ላላው የዕውቅና የሹመት
መደላድል ሲባል በአደባባይ የተረሸኑ አዲስ አበቤዎች፤ በመኖሪያቸው የተሳደዱት ዜጎች፤ ከዚህም ባለፈ፤ በወሮበላነት፤ በሺሻ ቤተኝነት፤ በጫት አምንዥካነት፤ በቁማር
ደላላነት፤ በደረቅ ወንጀል ማፍያነት ተሰይመው ከእስር ሲለቀቁ ለለውጡ እንደ ሆነ እሰቡት
እንደ ተባለው ማለት ነው።
ብቻ ሞኝ ካመረረ በግ ከበረረ ካልሆነስ ጥሩ ነው … ቀድሞ ነገር ማን ደጋፊ ሆኖ ነውና። ማንስ
መሪዬ ብሎ ነውና። ማንስ ሌት ተቀን ተሞግቶ ነውና ያው ቢነሳ ቢወደቅ በአማራ ትክሻ ላይ ነው፤ አሁንም ያለው የጥገናው ለውጥ መደራደሪያ የህሊና ማሳ ቢባል ያው አማራ ነው። አሁን
ምርጫ የሚባለውም እንዲሁ ነው …
በሃዘን ሰነባብቼ ዛሬ ፈገግ አልኩኝ። የግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕ/ብርሃኑ ነጋ ከግዮን ለቀረበላቸው ጥያቄ እኛ በፓርቲያችን አማራን በስፋት ያሰተፈ ነው
ማለታቸውን ተሰማ። ድሮስ ለአገልጋይነት አማራን ማን ቀድሞት? ሰባራ ወፍ ሳትቀድምህ የተባለ ይመስል ጥድፊያ ነው ራሱን ለመገበር፤ ለአንጋችነት፤ አላዬንም አለስማንም አንድም የአማራ ሊሂቅ ዕውቅና ሲሰጠው መድረክ ላይ የሚታወቅ፤ መስሏቸው የገቡትም የአማራ ልጆች ገና በጥዋቱ
ነው የተሰናበቱት። እኛ ባልገባን ስነወርፋቸው ስንሞግታቸው ነበር።
ቀድሞ ነገር ምክር ቤት ለመግባት እኮ አንድ ሌላ ተጨማሪ ቋንቋ ማወቅን ይጠይቃል ደንቡ? ታዲያ
አማራ ከዬት አምጥቶት፤ ሌላም አለ የትግሬ እና የአማራ ንግሥና አበቅቶ ከእንግዲህ የቤንሻንጉል የደቡብ እና የሌሎች መሆን አለበትም
ዓዋጁስ የት ሄዶ? አሁን አማራ ክልል በሚበላው ነፍስ ያለው አንድ አማራ ሊሂቅ ሰው ጠፍቶ የሆነውን ከትከት ብልን እዬሳቅን አይተናል እኮ? እንኳንስ አሁን
ላለው ዳይናሚክ ትውልድ ለኛውም ዘመንም የማይመጥን ነገር ነው እኔ የተመለከትኩት። የት መጥቶ? እንዴትስ አልፎ? የማይሆን ነው።
ይልቅ በህሊና ያለውን ጣዖት ማፍረሱ ያስማማናል። ይቅርታ መጠዬቅ፤ የብቻም ሱባኤ መዬዝም። ሁልጊዜ
ተገበሩልኝ ከማለት በፊት። ስንሳደድ መኖራችን እኮ ተርጓሚ አያስፈልገውም። እኛው በህይወት ስላለን እንመሰክረዋለን። አልፎ ተርፎ
በሞፈር ዘመት መቀመጫ ያጣን ምንዱባኖች አለን።
ምነው አውሮፓው ህብረት ላይ የአማራ ሊሂቃን ተጋባዥ እንግዶች ሆነው ስለምን አለዬንም ያው ግንቦት 7 አንድ
ድርብ ወንበር አለውና?
ባታናግሩን መልካም ነው። አይደለም ግንቦት 7 ክብርት ወ/ሮ አና ጉምዝ አማራን በምን መልኩ ተቀርፆ እንደተነገራቸው እናውቃለን፤ ብዙ ነገሮች አሉበት። ጀግና ሲጠዬቁ እንኳን ቄሮ ነው ያሉት።
ራሱ መርሁ ንድፉ ከአማራ ጋር ንክኪ እንዳይኖረው ተደርጎ ነው የተቀረጸው። ስታራምዱት
የነበረው እኮ የቋንቋ ፌድራዚምን ነው።
አንድ ጊዜ እንዲያውም አቶ ሃብታሙ አያሌው ገልብጡት ሲል ሁሉ አዳምጫለሁኝ ደንባችሁን።
እንግዲህ እሱ እስር ቤት ኦሮምኛውና ሞካክሮ ከሆነም ትንሽ ክፈትተ ቢጤ … መተንፈሻ ካገኜ። በኢትዮጵያ የፖለቲካ አደረጃጀት እንደ
ግንቦት 7 እኮ ዝግ የሆነ ንቅናቄ አላዬሁኝም። ግጭትም ክፍሉ ነው። ያልተጋጨው የለም። የውጩን ጨርሶ እኮ ኦህዴድ ላይ እኮ ጉብ ብሎ ነበር። ዘመን ጥሩ ሆኖ አሁን ደግሞ ፍቅር በፍቅር እያዬን ነው ከጨረሳላችሁ። ነገም ሌላ ምልምል እጮኛ ይኖራል ...
የሆነ ሆኖ በሥርዓት የተመለመለ እና ህግ ደንቡን ያጠና ስለዚያም የሚሟገት ነፍስ እኔ ተዚህ አላዬሁም።
በሚገባ ነው የማጠናችሁ። ደንብ ስለሚባለውም አያውቁትም አባል ነን የሚሉት። ብቻ ተከድኖ ይብሰል። እድሜ ለኢሳት … ይበል ግንቦት
7።
አማራ ቢረሳ ቢረሳ የ2010 የጥምቀት ባዕል በወልድያ ህማማት እና የግንቦት 7 እና የቲፒዴኤም ጋብቻ ይረሳልን? በደል እንዲያገርሽ ባይፈቀድለትም ግን አይረሳም። ይህ
እንግዲህ በነፍስ ወከፍ ከተዋከነው መከራ በዘለለ እንደ ህዝብ አማርን በምን ያህል ርቀት እንደተቀመጠ ግንቦት 7 ያሳያል። ይህ በቅርብ ጊዜ የሆነውን ነው። የታሪክ ዝርፊያውስ? ማቀለሉስ?
መናቁስ? ብቻ ብዙ ማለት ቢቻልም እንደ ተከደነ ተከዝኖ እንዲቀመጥ ገማናው ቢጣር ምንኛ መልካም በሆነ ነበር?ባትነካኩን?
እንግዲህ ትራንስፎርሜሽኑን ለኮሬጆ ብቅ ታደርጉታላችሁ ተብሎ ይጠበቃል … ስለ አማራም በአዲሱ
የፓርቲ ድርጅታችሁ አንድ ነገር ትሉ ይሆናል። ድንግል ልብ እንጂ ወረቀት ምን ሲፈይድ ለአማራ። ስለ እናንተም ሳስብ ይደክመኛል።
ለዚህም ነው ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል የምለው።
አማራም ሴትም ህጻናትም አማራ ወጣትም ከግንቦት 7 ፍርፋሪ አትኩሮት አያገኘም።
ይህ እውነት ነው። አገኛለሁ የሚል ካለ ግን ከልካይ የለበተም፤ ሊረገም ሊወገዝ አይገባም፤ ይግባ እና ይዬው። ከአግልግሎት በኋዋላ እንደ አካፋ እና
እንደ ዶማ እንደ አርበኛ ማዕዛው ጌጡ እና እንደ ከርታቴ አርበኛ ዘመነ ካሴ ያገኘዋል። ሁሉም ደክሞ አይቶታል።
አሁን ገራሚው ጉዳይ ለጊዜ መፍጃ እና ለመሻገሪያ ደግሞም አማራነቱን ለመጫን እንደ ልዩ መሳሪያ
በተሸበለለ ስምምነት የምናዬውን እያዬን ነው። ተስፋማ ሞተ እኮ ስለአማራ። ዕድሜ ለሐምሌ 5 የአማራ ይህልውና የማንነት አብዮት፤
ዕድሜ ለነገረ ጎጃም እሱ ብቻ ነው የተገኘው ባለማተበኛው ቅኔ በዛ መከራ ዘመን።
አማራ አሟሟቱን ማሳመር አለበት ባይ እኔ በግሌ። የገበጣ ጨዋታውን ተግ አድርጎ አማራ ወይ ቆርጦ በጠራ
መስመር ይታገል ስለቀጣዩ ሁለገብ የአማራ ትውልድ ግዙፍ የጥቃት መርሃ ግብር በርትቶ ይታገል፤ ወይ እንደ ቅዱሳን አባቶቹ ገዳሙን
ገብቶ ብራናውን ፍቆ 21ኛውን ዘመን እንደ ለመደበት በቀለም ህብር ይቃኘው። ይኸው ነው።
አማራ ፍርድ እና ዳኝነቱን ከእዮር ብቻ ነው የሚያገኘው።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ