የኳስ ዊዲንግ ሻውር ምዕራፍ አንድ።

ፈረንሳይን ያዬ ዛሬ ።
1 ለባዶ ቤልጀምን።

„ምሕረት እና ዕውነት ከአንተ አይራቁ በአንገትህ እሰራቸው።“
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፫)
ከሥርጉተ ሥላሴ 10.07.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)


ሜዳው ጭር ብሏል። ትንሽ እንደ ማኩረፍም ድንቡልቡሊት ሆናለች። የሠርጓን፤ ጠመልሱን፤ የቅልቅሉን፤ የማጫውን፤ የዊደንግ ሻወሩን የመረጠቸው ባዕትን ቅዳሜ ምሽት ኮከብህ አልገጠመም ብላ ስለሸኝች።

ዛሬ የድንቡልቡሊት ዊዲንግ ሻውር የመጀመሪያው ዕለት ነበር። ምዕራፍ አንድ እንደማለት።

ስለምን ሜዳው በጭርታ ተማታ? የራሺያ የዋንጫ መንፈስ ስለኮበለለ። የሆነ ሆኖ የዛሬ እግር ኳስ ጨዋታ የመጀመሪያው ፈረቃ ውድድር ካስን ነው የሚባለው።

በዘንድሮው የእግር ኳስ ጨዋታ ራሺያ ጋር የነበሩ ግጥሚያዎች ፉክክራቸው እጅግ ዘመናዊ ነበር። 

ከዚያ ውጪ እኔ በተከታተልኳቸው ጨዋታዎች እልህ አስጨራሽ የሚባሉ ነበሩ ለማለት ብዙም አልደፍርም። ኮሎንብያ እና ጃፓኖች ጥሩ ነበሩ። የግብጽና የራሺያ ግን የፋይናል ይመስል ነበር። 

የኮራዚ እና የራሽያም እንዲሁ። ድንቁ ነገር የግብጽና የራሺያ ጨዋታ ገና የፊፋ የ2018 ጨዋታ አህዱ በተባለበት ሰሞናት ስለነበር ደረጃው ከጠበቅኩት በላይ ከፍ ያለ ነበር።

ግብጽ ሳይቀጥል ቢቀርም እስከ አለፈው ሳምንት ድረስ ራሺያ ባገኘው ልምድ ተበረታቶ በሙሉ ደጋፊዎቹ የጀርባ አጥንትም ተጋዞ በጥንካሬው ቀጥሎ ተወዳዳሪዎቹን በሚያሰድምም ብቃት እያሸነፈ፤ ታዳሚዎችን እያስጨበጨበ ቀጥሎ በኮራዝን እልህ አስጨራሽ እጅግም አስገራሚ ጨዋታ በአገሩ በራሺያ ተስዶ በተመልካችነት እንዲቀመጥ ተገዷል።

እርግጥ ነው ያን የመሰለ ብቃት ከመባቻው የነበረው የእኛው ወዛችን አፍሪካዊ መሃምድ ሳለህ የነበረበት የግብጽ ቡድን በጥዋቱ ነበር የተሸኘው። ቢሆንም ግን በብቃቱ የአፍሪካውያን የነፍስ አባት የሆነ የተከደነ ብቃቱን አሳይቷል። በ2014 ቤልጄሞች ሲወጡ የነበረው ስሜት ያህል ነበር የተሰማኝ።

የቤልጄም ብቃት ፈረንሳይ አገር ተካሂዶ ለነበረው የ2016 የአውሮፓ የፊፋ ጨዋታ ልዩ ጌጥ እና ፈርጥ ነበር፤ ምንም እንኳን ዋንጫውን ፖሩቹጋል ቢወስደውም። የፈረንሳዩ ብቃት በዛው ልክ በባድማው ያሳዬው ልብ አንጠይጣይ ጨዋታ እጅግ ወርቅ ነበር። ያን ጊዜ የቀደሞው የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት በዬአንዳንዱ የጨዋታ ቀን እዬተገኙ ለቡድኑ የሰጡት ድጋፍ ፈጽሞ የማይረሳ የፊፋ ታሪክ አጋጣሚ ነበር።

ምልሰት ወደ ግብጽ ሲሆን ዘንድሮ በታዬው ብቃቱ ወደ 8 ዓመት ወደ ፊት ሳሻግረው 2026 ከዚህ ደረጃ የማይደርስበት መንገድ አይኖርም።

ኢትዮጵያም በአሁኑ የአብይ መንፈስ ሁለገብ አቅም ተበረታታ፤ ኳስ የሥነ ልቦናም ጉዳይ ስለሆነ፤ የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ ድንቅነትን ሰንቃ እንዲያው ለዓለም እግር ኳስ የማጣሪያ ውድድር ዝርዝር ውስጥ ኮተት ለማለት ትችል ይሆናል ቢያንስ በመባቻው ሰሞናት …


የቤልጄም እና የፈረንሳይ ባለፉት 8 ዓመታት ያሳዩት ብቃት አግዟቸው ወይንም እርሾ ሆኗቸው ነው ዘንድሮ ታላላቅ የሚባሉትን ግዙፍ ብሄራዊ ቡድኖች እያንጠባጠቡ እዚህ የደረሱት።

ዛሬ እጅግ ስልጡን፤ እጀግ ዘመናዊ ጨዋታ አስከ እረፍት ጊዜ በጉልህ ታይቷል በሁለቱም ቡድኖች። ከእረፍት መልስ በ50ዎቹ መጀመሪያ ላይ ፈረንሳይ አንድ ግብ ከመረብ ጋር አሳታርቆ የጨዋታውን መንፈስ ወደ ቅዝቃዜ ለወጠው። አዎን! ወደ ቅዝቃዜ።

ከዛ በኋዋላ የበቃ ፉክክር፤ የበቃ ብቃት፤ ደረጃውን የጠበቀ ጨዋታ ነበር ለማለት በፍጹም አልችልም።

ቤልጄሞች ጨዋነታቸው ጎልቶ በሚታይባቸው እንቅስቃሴዎች በዛሬው ጨዋታ እጅግ አግሬስብ ተጋፊም ነበሩ በተለይ ከእረፍት መልስ። እርግጥ ነው ከማህላቸው አንድ ተጫወች አለ ልብስ ጎተትትትት የሚያደርግ አላቸው፤ ይህን በተካሄዱ ጨዋታዎች ሁሉ አስተውያለሁኝ።


እኔ ሳልሻቅል ነበር ጨዋታውን የተከታተልኩት። ምክንያቱም ሁለቱንም እኩል ስለምወዳቸው። ባለፉት ዓመታት የነበረው የህዝቡ የቦንብ ጥቃት እና የእናቶች ስቃይ ከልቤ ስለገባ ማንኛቸውም ወደ ቀጣዩ ቡድን ቢያልፉ እኩል ስሜት ነው የነበረኝ። 

ስለሆነም ዛሬ ቤልጄም ቢወጣብኝም ሉካኩን ደግሜ ላዬው ባልችልም ግን ፈረንሳዮች ስላለፉ መልካም ነው ብያለሁኝ።
           እጅግ የምወደው የቤልጄም ተጫዋች!

ፈረንሳዮች የቡድን ጨዋታ ሥርዓታቸው መልካም ነው። ኮራዝያን ከወጣላቸው ተስፋ ይኖራቸዋል። የሆነ ሆኖ ነገ እንግሊዞች ኮራዝን የማሸነፍ አቅማቸው እንብዛም ነው በእኔ ዕይታ። ሁለቱም ቡድኖች ነገ 20.18 በእኛ የሰዓት አቆጣጠር ስለሚጫወቱ ከአሸናፊው ጋር ጠንከር ያለ ፉክክር ፈረንሳይን ይገጥማቸዋል ሰንበት ላይ የሠርጉ እለት። በተለይ ኮራዝ ነገ ካሸነፈ።

እኔ እንግሊዝን ኮራዝን ኮራ ብሎ ያሸንፋል የሚል ሙሉ ዕምነት ነው ያለኝ። ቢበዛ የጨዋታ ጊዜ ሊራዘም ቢችል እንጂ የኮራ ብቃት የሚደፈር ይሆናል ብዬ አላስብም፤ እንግሊዞች ከሲዊዲን ጋር በነበራቸው ጨዋታ አንድ ክንፍ ክፈተት ነበረው። በዛ ላይ ነጥቡ ራሱ ስስ ነበር። የቡድን ጨዋታ ብቃታቸውም እንደ ፈረንሳዮች አልነበረም። ወደ ግል ጨዋታ ያዘነበለ ሁኔታ ነበር ያዬሁት … እንግዲህ የነገ የአጨዋወት አሰለላፋቸው ዕደሉን ይወስነዋል።

እርግጥ ነው ዛሬ የጨዋታው ክ/ ጊዜ ተራዝሞ እልህ አስጨራሽ ፉክክር እናያለን ብዬ ቁምጥ ብዬ ነበር። የሆነው ግን ወደ አራት ቢጫ ካርድን ያሰተናገደው ወሳኝ ጨዋታ በመደበኛ ጊዜ ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ አብዮትም በመደበኝ የአጨዋወት ድል ሴረኞችን በሙሉ ድል ነስቶ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ማማ ትሆናለች! ኢትዮጵያ በማንኛውም ዘርፍ እናት ትሆናለች ለአፍሪካውያን በሙሉ። 

ስለምን?  የአሮን በትር ሴረኞችን እዬነጠፈ ቅኖችን እያለመለመ እያበራከተ ሚሊዮኖችን እያስለፈ ስለሚሄድ።

ዛሬ ግሪዝማን ሳቀ፤ ሳቁን አዬሁት … አሳዛኙ ግን የፈረንሳይ ልባሙ ኮከብ ተጨዋቻቸው 10 ቁጥሩ ዛሬ የቢጫ ካርድ ታዳሚ መሆን … ጥሩ ዜና አልነበረም … ይሄ ለፈረንሳዮች … ለቀጣዩ ወሳኝ ጨዋታቸውም።
  
የሆነ ሆኖ እንደ ሥርጉትሻ ዕይታ ኮራዝን ነገ እንግሊዝን ረቶ ለዋንጫ ይድረሳል ብዬ አስባለሁኝ። እርግጥ ነው ይህቺ ሽቅርቅር ድንቡልቡሊት ደግሞ ኮከብ መግጠም ቅብጥርሶ ምንትሶ የምተለው ስላላ ግጥሜ እንግሊዝ ነው ካለች ደግሞ ይታያል ….

ነገ የ እንግሊዝ ቡድን ዕድሉን የሙጡኝ ብሎ ካልሆነ በስተቀር፤ ከሆነ ግን አንግሊዝ ወደ ቀጣዩ የዋንጫ ውድድር የሚሻገረው በጫዋታ ኮራዝን በልጦ ይሆናል የሚል እምነት የለኝም። ኮራ ጠንካሮች ናቸው።

ዲስፕሊንም ናቸው። ብቻ ወሰኙን የበለጠውን ማጫ ማን አቅርቦ ለዋንጫ ይበቃ ይሆን? የፈረንሳይ እና የእንግሊዝ ከሆነም … ዕድል እና ዕድል ይሆናል ግጥሚያው … እንግሊዝም ሊወስድ የማይችለበት ምክንያት የለም ብቻ ጠይም ዕንቁዎች … እያበሩ ነው። 

 ዛሬ የሁለቱም አገሮች መሪዎችን በጨረፍታ አይቻለሁኝ። ፓሪስ ዛሬ አዳሯ እልልልልልታ ይሆናል …. እናት ኢትዮጵያም እልልልልታ ላይ ናት። ኤርትራም ተድምራለች ለእልልልልልልታው …. ኒወርክም ተደመርኩኝ ብላለች ለእልልልታው … መሪዋን ኢትዮጵያ ድረስ ልካ የዓለሙ የሰባዕዊ መብት ቁንጪ እናት አናትም መደመር ክፋላች ነው ብሏል።

ታዲዬ ይሄ በዕድል አይደለም፤ ከሞቀው እዬተጣዱ ወይንም እዬተሰኩ ከጥሎም ዋጠውን አሳጅቦ ባበዶ በመኮፈስ አይደለም። በብልህነት፤ በብቃት፤ በአቅም + በሰለሞን ጥበብ ነው።
  
እግር ኳስ የዓለም የፍቅራዊነት መሰረት ነው!
በሥራቸው የከበሩ ብዑዓን ናቸው!
በሰው ሥራ የከበሩ ደግሞ ኑሯቸው ሞት ነው!

የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜም።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።