ልጥፎች

ብሄራዊ የቃለ ህይወት መልዕከት በሀዘን ከተጎዱ እናት ከወ/ሮ ሚልካ ይማም …

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  የመንፈስ  አህቲነት። „ምድርም ቅልጥማችን ጠጣች ጠፋን፤ ደም ግባታችንም በመቃብር ጠፋ ፤ ሥጋችንም በመቃብር ተቀበረ፤ ያመረ ቃላችንም በመሬት ተቀበረ።“ መጽሐፈ መቃብይን ካልዕ ፲፰ ቁጥር ፲ ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።                                                           እኔን!  ነፍስ ይማር! ጽናቱን ይስጥልን ፈጣሪያችን! አሜን! ነፍስ ይምር! አሜን! https://www.youtube.com/watch?v=VDrVgtBUe74 Ethiopia: መረጃ - እናቱ ተናገሩ | በአይሮፕላን አደጋው ሕይወቱን ያጣው   የ 27 ዓመቱ ሲድራክ ጌታቸው | Sidrak Getachew እንደምን አላችሁ ቅኖቹ ደህና ናችሁ ወይ? አላዛሯ ኢትዮጵያስ እንዴት ነሽ?ይህ ጉ ማም ጎ ማማ ድንገቴ እንዴት ይዞሻል? ·        ክብረቶቼ … ትናንት በጥዋቱ „እንዴት አደረክ ጀርመን“  RTL የጥዋት የዜና መሰናዶ ላይ ኖይዝላንድ የክርስትያን ቤተክርስትያን ላይ ወደ 49 የሚጠጉ ወገኖች በአሸባሪዎች ህይወታቸውን እንዳጡ አጭር ዘገባ ቀርቦ ነበር።  ዜናውን ትናንት መስራት ባለመቻል ባልችልም ዓለም እዬታመሰችበት ያለ መሰረታዊ ነገር የፍቅርን ተፈጥሮ እና ህግጋቱን ከልጅነት ጀምሮ ልንማር የምንችልበት ሁኔታ አለመፈጠር ነው። ዓለም ጉም ሆናለች። ታስፈራለች። ዛሬ አሸባሪነት ነው ነገ ደግሞ በሌላ ሥም ሌላ ኢ - ተፈጥሯዊ ድርጅት ብቅ ይላል … እነዚህ እግዚአብሄርን የሚያከብሩ ፈጣሪ አለ ብለው የሚያምኑ ንጹሃን የዓለም ሰማዕት ዜጎች በግፍ በአደባ

የኢትዮጵያ በሽታ (ከጸሐፊ አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ)

 እንኳን ደህና መጡልኝ።  የኢትዮጵያ በሽታ መስፍን ማሞ ተሰማ ሠላም ለናንተ ይሁን! እንግዲህ ምን ይሻላል? ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም አጥሩን /ክልሉን እያጠበቀ አትድረሱብኝ ማለቱ ብቻ ሳይሆን እዛው ተወልደውና ከብደው ቤተሰብና ንብረት አፍርተው ለዘመናት የኖሩትንም ከደርቡሽ ወይም ከጣልያን የመጡ ይመስል - ወራሪ፤ መጤ፤ ሰፋሪ - እየተባሉ ማቄን ጨርቄን ሳይሉ በአንድ ጀንበር ከነ እንቦቃቅላ ህፃናት ጭምር <የመሬት ባለቤት ነን> ባዮች (ክልላዊ መንግሥታትና ራስ ገዝ ቡድኖች) በግፍ ሲያባርሩና ሲገድሉ <ለተፈናቃይ ሀገር በቀል ስደተኞች> በወቅቱና በተገቢው ሁኔታ የሚደርስላቸውም ሆነ በተግባር የሚቆረቆርላቸው <መንግሥት> አለመኖር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መሄዱ እጅግ አስጨናቂ ክስተት ሆኗል። <ባለ መሬት ነን> ባዮቹንም ሃይ የሚል የመንግሥት ሃላፊ የለም። እንደውም በግፍና ያለ ህግ የተፈናቀሉትን <ለኛ ፖለቲካ በሚጠቅም መልኩ አስፍረናቸዋል> ያሉ <እንደ ሃይማኖት እናምናቸው የጀመርናቸው የለውጡ <ፊታውራሪዎች ኢትዮጵያዊ መሪዎች> ሲናገሩ ከመስማትና ከማየት በላይ ለሰማይም ለመሬትም የከበደ በደልና ሀጢያት ከቶ ከወዴት ሀገር አለ? ይህ ሁሉ ሰቆቃ የሚፈፀመው ደግሞ የ<ህገ መንግሥት> ሰነድ አይናችን ላይ እያወዛወዙና <ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው> እያሉን መሆኑ ነው። እንግዲህ <ህገ መንግሥቱ> ለዘረኝነትና ለአፓርታይዳውያን መሳሪያነት የቆመ ጠበቃ ነው ብንል ሀሰት ይሆናልን?!    <ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች> የሚለው ቅጥ አምባሩ የጠፋና ትርጉሙም ፍንትው ብሎ በማይታወቅ <አብዮታዊ ዲሞክራሲ> ንድፈ ሀሳብ አጥር ማጠር/ክልል

ሰብዕዊነት ሲበጠስ ትዕግስትም ይበጠስ ...

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  „በሰዎችና፡ በመላእክት፡ ልሳን፡ ብናገር፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ እንደሚጮኽ፡ ናስ፡   ወይንም፡ እንደሚንሽዋሽ ው ፡ ጽናጽል፡ ሆኜአለሁ። ትንቢትም፡ ቢኖረኝ ፥   ምሥጢርን፡ ሁሉና፡ እውቀትን፡ ሁሉ፡ ባውቅ፡ ተራሮችንም፡ እስካፈልስ፡ ድረስ፡ እምነት፡ ሁሉ፡ ቢኖረኝ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ከንቱ፡ ነኝ። ድሆችንም፡ ልመግብ፡ ያለኝን፡ ሁሉ፡ ባካፍል፥ ሥጋዬንም፡ ለእሳት፡ መቃጠል፡ አሳልፌ፡ ብሰጥ፡ ፍቅር፡ ግን፡ ከሌለኝ፡ ምንም፡ አይጠቅመኝም። „ ( ዬሐዋርያው ዬቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቆረንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፫) ፕ/ለማ መገረሳ ይማሩበት ዘንድ እንደ አዶልፍ ሂተለር በግሎባሉ ከመወገዛቸው በፊት። ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08.03.2019 ከእመ ዝምታ።                                                   ቃል የእምነት ዕዳ ነበር! ·        ቁጥር አንድ ለእኛ በጥቁር። ዛሬ ሦስት የህሊና ዳኝነት የኦሮምያ ፕሬዚዳንት እና የ ኢትዮጵያ ጠ/ሚር ለማ መገርሳ ይሰጡበት ዘንድ ሦስት ጉዳዮችን ነው እማነሳው። ሦስቱም ተወራራሽ ናቸው።  የኢትዮጵያን መንፈስ ሃይልነት እና 21ኛው ምዕተ ዓመትን ጭንቅ ስለሚለው ሰብዕዊነት እና ተፈጥሯዊነት። የመጀመሪያው ዛሬ „የኔ የነፃነት ቀን #MyFreedomDay “ ነው። በዚህ ቀን 40 ሚሊዮን የዓለም ህዝብ በዘመናዊ ባርነት እንደሚገኝ፤ ከከእነዚህ 40 ሚሊዬን ውስጥም አብዛኞቹ ሴቶች እና ህፃናት እንደሆኑ፤ የሴቶች ደግሞ በመቶኛ ደረጃው ሲለካ 71% ስለመሆኑ የሲኤን ኤን ዘገባ ይገልጣል። ኢትዮ