ብሄራዊ የቃለ ህይወት መልዕከት በሀዘን ከተጎዱ እናት ከወ/ሮ ሚልካ ይማም …

እንኳን ደህና መጡልኝ።

የመንፈስ 
አህቲነት።
„ምድርም ቅልጥማችን ጠጣች ጠፋን፤ ደም ግባታችንም በመቃብር ጠፋ
ሥጋችንም በመቃብር ተቀበረ፤ ያመረ ቃላችንም በመሬት ተቀበረ።“
መጽሐፈ መቃብይን ካልዕ ፲፰ ቁጥር ፲
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08.03.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።

                                                          እኔን!  ነፍስ ይማር!

ጽናቱን ይስጥልን ፈጣሪያችን! አሜን!
ነፍስ ይምር! አሜን!



Ethiopia: መረጃ - እናቱ ተናገሩ | በአይሮፕላን አደጋው ሕይወቱን ያጣው

 27 ዓመቱ ሲድራክ ጌታቸው | Sidrak Getachew


እንደምን አላችሁ ቅኖቹ ደህና ናችሁ ወይ? አላዛሯ ኢትዮጵያስ እንዴት ነሽ?ይህ ማም ማማ ድንገቴ እንዴት ይዞሻል?

·       ክብረቶቼ …

ትናንት በጥዋቱ „እንዴት አደረክ ጀርመን“  RTL የጥዋት የዜና መሰናዶ ላይ ኖይዝላንድ የክርስትያን ቤተክርስትያን ላይ ወደ 49 የሚጠጉ ወገኖች በአሸባሪዎች ህይወታቸውን እንዳጡ አጭር ዘገባ ቀርቦ ነበር። 

ዜናውን ትናንት መስራት ባለመቻል ባልችልም ዓለም እዬታመሰችበት ያለ መሰረታዊ ነገር የፍቅርን ተፈጥሮ እና ህግጋቱን ከልጅነት ጀምሮ ልንማር የምንችልበት ሁኔታ አለመፈጠር ነው። ዓለም ጉም ሆናለች። ታስፈራለች። ዛሬ አሸባሪነት ነው ነገ ደግሞ በሌላ ሥም ሌላ ኢ - ተፈጥሯዊ ድርጅት ብቅ ይላል …

እነዚህ እግዚአብሄርን የሚያከብሩ ፈጣሪ አለ ብለው የሚያምኑ ንጹሃን የዓለም ሰማዕት ዜጎች በግፍ በአደባባይ ተጨፍጭፋዋል። ደማቸው የፈሰሰው ይሰቀጥጣል ስታዩት።  ነፍሳቸውን በአርያም ገነት ያኑርልን። አሜን!

ለእኛም ነፍሳችንን ወደ ስክነት ልዑል እግዚአብሄር ይመልስልን። አሜን! እንደ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ የመሰሉትን በናዚያዊ መንፈስ ልባቸው ያደነደኑትን ፈርዖናዊዎችንም ልብ ይስጥልን ፈጣሪ አምላክ። አሜን! ከታበዩበት ተራራም ወረድ ያድርግልን። አሜን! ሁልጊዜም ክርስትና ወዮልህ እያልኩ እጽፋለሁኝ፤ አካሂዱ ወደዛ ነው የሚመስለው … 

አሁን በሱሉሉታም ሌላ የመከራ ዳመና እንዳለ ዜናዎችን እያዳምጥኩኝ። የሱሉሉታ ከንቲባዋም ወ/ሮ ሮዛ ኡመር ቃለ ምልልስ ከሸገር ጋር አድርገዋል። መከረኛ እናቶች ደግሞ ድረሱልን እያሉ የስጋት ድምጽ እያሰሙ ነው። ተለይቶ ስለሆነ ምልክት የተደረገባቸው ቤታቸው።

ይህ ጉዳይ ከዚህ የሰንበት መከራ ቀጥሎ ተግ ይላል የሚል ሃሳብ ነበረኝ። መሪዎችም ቢዘኽው ጉዳይ ላይ አደብ የሚያስገዛ ነገር ይኖራቸዋል ብዬ አስቤ ነበር። ከጉዳይም የጣፉት አይምስልም እኔ እንደታዘብኩት። የአቶ ጃዋር የፕሬስ ሰክሬታርያትም የልቡ እዬደረሰለት ነው።


·       ብሄራዊ የቃለ ህይወት መልዕከት ከወ/ሮ ሚልካ ይማም …

ዛሬ ልዕልት ጽዮን ግርማ ያነጋገራቸውን የተጎጂ እናት ድምጽ ሰማሁኝ ከወደ ኬንያ። የድምጽ አልባዎችን የኢትዮጵያ እናቶች ድምጽ ስላሰማችኝ ከልብ አመሰግናታለሁኝ።
ትባረክ። 

በ27 ዓመቱ የህወሃት ሥርዕዎ መንግሥት የግማድ ዘመን እንዲህ አይነት ጀግና የተጋሩ እናት አልተገኘችም። እኔ ተስፋ አደርጋለሁኝ ከእውነት ጎን የምትቆም እናትን ... 

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ እኔ ከመነሻውም ጀምሬ የፈጣሪ ቁጣ ስለመሆኑ ገልጬ ነበር። እኒህ ሃዘንተኛ እመቤት የሞች አቶ ሲድራክ ጌታቸው እናትም የተናገሩት ይህንኑ ነው። „እንኳን ብሄር ብሄረሰቦች ቀርቶ ሁላችሁም የአለም ህዝቦች ይኸው ናችሁ ካፈር አታልፉም በሚል እግዚአብሄር ሊያስተምረን ነው የሚል ስሜት ነው የተሰማኝ“ ወ/ሮ ሚልካ ይማም ናቸው ይህን ቃለ ህይወት ያሰሙን።

እኔም አደጋው እንደደረስ የጻፍኩት እንዲህ ነው። በርካታ ሚስጢሮች የተካተቱበትም ነው። እያንዳንዱን ነጠላ ነገር ብዙ የ ዕድምታ ሚሲጢራት አሉበት። አስቀድሞም ሰሚ አይገኝም እንጂ ኢትዮጵያ የፈጣራት አምላክ አላት እና የፈጣሪ ቁጣ እንዳይላክ አበክሬ ገልጬ ነበር። እንዲህ …

ለአቶ አዲሱ አረጋ ማስተባበያ ጉልበታም ምላሽ።

መሬት ለመሬት መሄድ የትም አያደርስም እዮር አለና። እዬር ፍርድና ዳኝነቱን ይሰጣል - ለቅኖች። ዕውነት እንዲህ ተከድታ በጠራራ ጸሀይ የተሰቀለችበት ዘመን አሁን ነው የታዬው። ዕውነትን ቅርጥም አድርጋችሁ ነው የባለችሁት። ማተብ የሚባል አልፈጠረላችሁም። ደግሞ ዝም ማንን ገደለ?! ዝም ብትሉ ከነገማናችሁ ምን አለበት?! አሁን ይሄ ምኑ ይሰተባበላል?የሆነ ሆኖ ጥጋብን በልክ መያዝ ይገባል። እናንተ ዘመነኞች ናችሁ። ግን ዘመንተኞችን የሚቀጣ ንጹህ አምላክ ደግሞ እንዳለ አትርሱ፤ በበረድ፤ በተባይ፤ በመሬት መራድ፤ በቃጠሎ፤ በአውሎ በብዙ ነገር የሚቀጣ። ክህደት አያበረክትም። ካዳችሁት 100ሚሊዮን የኢትዮጵያህዝብን። አማራንም ጎንደር ላይ ቀጥታችሁታል።  ሆን ተብሎ ታቅዶ የተከወነ ነው። ንጹህ የኦሮሞ ማህበረሰብን ቅራኔ ውስጥ ሰተት አድርጋችሁ ከተታችሁት።

የሆነ ሆኖ ይህን ቃል ከወ/ሮ ሚልካ ይማም በስተቀር አንደም ሰው ሲናገረው አልሰማሁም። ቃለ ምልልሶችን ሁሉ እከታተላለሁ። የግሎባሉንም ጭምር። ያው  ከአውሮፕላን በረራ ጋር ነፍሴ ቤተኛ ናት እና። እንዲህ መሰል አደጋ ሲኖር እንቅልፍም ስለማይወሰደኝ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን ሁሉ መረጃ ነው ሳልደክም እማዳምጠው ሌሊቱን ሁሉ ነው።

                                     
                                         ልብስ ጌጥ እንዲህ ነው ...     
                                   

የሚገርመኝ እዛ ኢትዮጵያዊ ውስጥ ከአደጋው ማግስት በተለያዬ ሁኔታ ሴሪሞኒያል ጉዳይን የሚከወኑ ነፍሶች አገር ባህል ልብስ ለብሰው ሁሉ አይቻለሁኝ። ገርሞኛል። አዝኛለሁኝም። ከምን ይሆን የተፈጠርነው?

                                     ድንግልዬ ብርታቱን ትስጥልኝ!

አሁን በዚህ ባሳልፍነው ሰሞናት ሽሙንሙን ብለን የፈጣሪ ቁጣ እንዲህ ነው ወይ ልንቀበለው የሚገባ ብያለሁ ሚዲያ ያሉትን ነገሮች በታዘብ? ከዛ በኋዋላ ያሉ ንግግሮችን ሁሉ አዳመጥኩኝ ስብር ማለት አልተቻለም። እንደተገተርን ነን። እናም ሰጋሁኝ። መሰበር ከሌለ ሌላም ቅጣት ሊያስከትል ይችላልና።

                                         ጽናቱን እመቤቴ ትስጥልኝ!

እራሱ ተናጋሪ የሚባለው እንኳን ነፍስ ይማር ለማለት የደፈረ የለም። እርግጥ ብሄራዊ የሀዘን ቀን መታወጁ በብሄራዊ ደረጃ መልካም ቢሆንም ትኩስ ሬሳ ከ35 አገር የመጣ የእኛ መሬት ተሸክማ ግን በግል ልናደርገው የሚገባ፤ በመዳፋችን ያለን ነገር መከወን ተሳነን ለ7 ቀን መታቀብ እንዴት ያቅታል?  
                                                  
እና እኔ ሳስበው አደጋው ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው መሬት ሳይሆን መጥቆ ጁቢተር ወይንም ኡራኖስ ላይ ይሆን ያረፈውን አልኩኝ? አልገባንም? አልተሰማነም? አልጎረበጠንም? የእኛም አላልነውም?

እሳት እኮ ነው ከሰማይ የነደደው? ቀኑ ተቆርጦ ነበር፤ ነገር ግን ደቡብ አፍሪካ መሬት ላይ ሳይሆን በአላዛሯ ኢትዮጵያ ባዕት ላይ ነው የተከወነው፤ በዕለተ ሰንበት በልደታ ዕለት ነው። ልብ እንድንገዛ። ወደ ህሊናችን እንድንመለስ። እራሱ የሃይማኖት አባቶች በወል ያሰሙት ድምጽ የለም። የት ላይ ነው ያለነው?

ለነገሩ እኔ አደጋዎች ስለሚቀጥሉ በአንድ ላይ ሆነው አንድ ራስ አድን ፕሮጀክት እንዲጀምሩ፤ መጠለያ እንዲሠሩ ሁሉ ራሱን አስችዬ ጽፌ ነበር። ቆይቷል ይህን የጻፍኩት።

 አባቶች ለወረት „በመደመር ፍልስፍና“ ሆስፒታል እዬሄዱ የለብ ለብ ሥራ እንደጀመሩ ሰሞናት ነበር። ለነገሩ መጀመር እንጂ መጨረስም ይህም ካልተፈቀደልን አይሆንም።
በውነቱ አደጋውን የእኛ አላደረግነውም። ከውስጣችንም ፈጽሞ አልገባም።  ቢያንስ ሚዲያ ላይ የሚከወኑ ማናቸውም ኢቤንቶች፤ ንግግርም የሚያደርግ ነፍስ እንዴት ሃዘኑ አይሰማውም? ጌጡስ ለ7 ቀናት ቢቀር ምን አለበት፤ ነጭ ልብሱስ?

 በእኛ ዕድሜ በ2014 ውቅያኖስ ከበላው ከዛ አሰቃቂ ከተከሰተው አደጋ እጅግ ፈታኝ ዘግናኝ የወል መከራ ቀጥሎ ያለው ይህ ግዙፍ መከራ በመሬታችን በራሳችን አውሮፕላን የራሳችን ሰማዕት ቀንበጦች እና ሸባላዎችን ጭምር ያጣንበት መከራ ነው።


በሰማይ እንዲበር የተሰራ አውሮፕላን አንተም መሬት ነህንና ወደ መሬት ትመለሳለህ ተብሎ ቆፋሪ ሳያስፈልገው እራሱን እኮ ነው ቆፍሮ የቀበረው።

እንዴት ይህ አይገባንም? ይህ ሃዘን ሳይሰማን የነፃነት ታጋይነት፤ የዴሞክራሲ አማጭነት ለእኔ ድንብልብል ነው። ለነፃነት የሚቆም ሰው አንዲት የጥፍሩ ስንጥር ተሰንጥቃ ስትጠዘጥዘው እንደሚሰማው መሆን እንኳን አልተቻለውም።

በዚህ አለታማ፤ አሸዋማ ልቦና እንዴት አንድዬ ይታደገን? ዘወትር ጥቁር ልንለብስ ግድ አይለንም፤ ነገር ግን ቢያንስ 7 ቀን ቅንጡነታችን ታገስ ብናደርገው ምን አለበት? በጣም ዘመናዮች ነን።

·       እትብት።  

የሆነ ሆኖ እኔ እዚህ ሲዊዘርላንድ የምኖረው ሥርጉተ ሥላሴን ነፍሴ የምትለውን ነው እኒህ ደግ ሴት የታድጓዋት ወ/ሮ ሚልካ ይማም ። እሳቸው በአህጉረ አፍሪካ እኔ ደግሞ በአህጉረ አውሮፓ፤ እሳቸው ኬኒያ እኔ ደግሞ ሲዊዘርላንድ ነው የምንኖረው፤ እሳቸው ኢትዮጵያዊ እኔም ኢትዮጵያዊ፤ እሳቸውም አንስት እኔም አንስት መንፈስ ቅዱስ በጥበቡ ሃዲዱን ሰራ። የሚገርመው ከማናቸውም በላይ የኢትዮጵያ ችግርም ከልባቸው መግባት ብቻ ሳይሆን ግፉን አዝነውበታል። ቁስልም ብለዋል በሚያዩትም በሚሰሙትም ነገር።
  
ያስተለፉትም መልዕከት ልብ ቢኖረን፤ ልባም ነፍስን ወደ ልቦና የሚመልስ አቅም መክሊቱ ቢሰጠን፤ እንደ እንጨት ግትር ብሎ የቆመውን ልባቸውን እንደ ተፈጥሮ ስብር አድርጎ ወደ ቀልባችን እንመለስ ዘንድ፤ እያንዳንዱ ነፍስ የቆመበትን መሬት ይመረምር ዘንድ ነው እኒያ ታላቅ ሰው የሰበኩት። ለእኔ ስብከት ነው።

                   ነ            

አንጀት፤ ልጅን ያህል ነገር እንደዛ ጓጉተው ይመጣል ብለው ተሰናድተው ሰከንዷን እዬቆጠሩ ነው ጥቁር ሀዘን ቤታቸው ዘው ያለው። 

ይህም ሆኖ ለመላ ኢትዮጵያ እናት ለመሆን ነው የፈቀዱት። በተጨማሪም ከደረሰባቸው የማህጸን  ጉዳቱ ይልቅ እሳቸው ለፈጣሪያቸው ለልዑል እግዚአብሄር ክብር ዕውቅና ሰጥተውታል። ለፈጠራቸውም አምላክ ታማኝ ሆነዋል። ይቅር እንዲልንም ተማጽነዋል። „እንማርበት ዘንድ  ነው ይህ የሆነው“ የሚሉት።

ምን ያህል ጥንካሬ እና ብርታት ቢኖራቸው ነው? መከራቸውን ታግሰው በመከራው ውስጥ ሆነው ይህን መሰል ጽናት ልንማርበት የሚገባውን እዮራዊ ቃለ የገለጹት?
                                     ድንግልዬ ጽናቱን ትስጠወት! 
     
መከራቸው አባርቶላቸው የማያውቁት የድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች ልብ ወደ ፈጣሪያቸው ያማትር ዘንድ ነው እኒህን መልካም ሴት ፈጣሪ በጥበቡ ያነገረው።
ቁጣው የሰማይ ነው፤ መከራው የጋራ ነው። 

ስለዚህ በወል አመድ ነስንሶ፤ ትቢያ ተንተርሶ ከታበይንበት ዙፋን ወረድ ብሎ ወደ ልዑል እግዚአብሄር መጮኽ ይገባል። እኔ ለዚህም ነበር ዶር ገመችስ ደስታ ምን እያደረጉ ነው ብዬ ባለፉት ጹሑፎቼ የጻፍኩት?

ኢትዮጵያ የጠላት አገር እስክትመስል ድርስ ነው በበቀል ለማረስ ነው ጥድፊያው? ኢትዮጵውያንም ተጭነው ከሌላ አህጉር የመጡ ያህል ነው መጤ የሚባሉት? መራራ ነው። ልብን እንደ ዱባ ይቀረድዳል። አገር እኮ ጨርቅ አይደለችም … ህዝብም ልኳንዳ ቤት አይደለም …
   
·       መከራችን አዬለ።

በጌዲዮ የተፈጸመው የኦሸቲዝም መከራ ነው ዳግም የተከሰተው፤ በሌላ በኩል የጎዳና ተዳዳሪዎቸን አሰባበሰብን ተብሎ ተዘግተው በራብ እንዲሞቱ መደረጉም ሌላው ሚዲያው በቅጡ ያልጎበኘው ጉዳይ ነው፤ ቆይቶ ደግሞ ጆሮ አልሰማም አይልም ሌላም በእነዚህ ታሽገው እንዲቀመጡ በሚደረጉ ምንዱባን ይሰማል ይታያል … ሁልጊዜም እንደምለው እኔ ኢትዮጵያ ሁልጊዜ እንደ ጥንቸል መሞከሪያ አይደለች? ምን ሲገድ?

ልብ ያላቸው ቅኖች፤ ደጎች ፈጣሪ ፈጥሮናል ብለው የሚያስቡ ወገኖች እስኪ የግል የሱባኤ ጊዜ ይኑራቸው ስል በትህትና አሳስባለሁኝ? ፈጣሪ ለአንድም ነፍስ ሲል ምህረት እና ቸርነት ለማድረግ አይገደውምና።

አስፈሪ ጊዜ ነው … ለመንፈሳዊ ነፍስ። ለሥጋዊው መልካም ነገር ሊሆን ይችላል፤ „የተለዬም ወቅት“ ሊሆን ይችላል፤ የሥነ - ምግባር የቃል ኪዳን ሰነድ በወል መፈራረራም …. ለነፍስ ግን ጉም ነው … ሰው መጀመሪያ መኖር እንዲኖርለት ሊፈቀድለት ይገባል …ቢይንስ አይዞህ አለንልህ ይባል ... እንዲረጋጋ፤ ህዝብ እኮ እዬተሸበረ ነው ያለው... 

ድፍረት የሚጠይቁ ዕውነቶች አሉ። ለራሱ ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚያፋጥጡ በዲስፕሊን ውስጥ ያሉትን ነፍሶች አሁንም ቅድምም ከመቀጥቀጥ፤ እና ጫን ተደል የቤት ሥራ ከማነባበር አጉራ ዘለሉን ፋሽስታዊ ሂደት መቅጣትን ይጠይቃል።

·       ለማንስለማን?

ሰዉ ሙቶ ካለቀ ለማን ይሆን ምርጫው? በሰቀቀን ውስጥ፤ በጭንቅ ውስጥ፤ በፍርሃት ውስጥ፤ በመከራ ውስጥ፤ በራህብ ውስጥ፤ በስጋት ውስጥ ለማንስ ነው ዴሞክራሲው? መፈራረሙስ ለማን ይሆን የሚጠቅመው? ለማንስ ይሆን ነፃነቱ? ከቶ የቃልኪዳን ሰነዱ እራፊ መጠጊያ ያጣውን ዜጋ አይመለከት ይሆን? ያው ሰነዱ ምርጫ ስለሆነ ምርኩዙ …?  

ወደ ልቦናችን አማኑኤል ይመልሰን አሜን!

„እግዚአብሄር በአንደም በሌላም መንገድ ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም“



የኔዎቹ አዱኛዎቼ ቸር ወሬ ያሰማን አሜን!  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።