ውድ የአገሬ ልጆች አትጨነቁ፤ አላዛሯ ኢትዮጵያ አምላክ አላትና፤
እንኳን ደህና መጡልኝ።
ውድ የአገሬ ልጆች አትጨነቁ
አላዛሯ ኢትዮጵያ አምላክ አላትና።
„ወደ ህይወት ዛፍ ለመድረስ
ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆቿዋም
ወደ ከተማይቱ እንዲገቡ፤ ልብሳቸውን
የሚያጥቡ፤ ብፁዕን ናቸው፤
አምስቱ ውሾች ግን ከዚያች አገር
ወጥተው ይሄዳሉ።“
የዮሖንስ ወንጌል ፳፪ ቁጥር
፲፬
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
08.03.2019
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።
አምላክ አለው!
ቅኖቹ የጹሑፌ ታዳሚዎች እንዴት አላችሁልኝ? ደህና
ናችሁ ወይ? ዛሬ እዚህ ደመንመን ብሏለኝ። አላዛሯ ኢትዮጵያስ? ያን ግዙፍ መከራ ካስተናገድን ጉዳያችን ቅርባችን ላደርግን ወገኖች
ዛሬ 8ኛ ቀኑ ነው። የሰውም ግፍ ስላለው ስለገጠመው መከራ ለመርሳት ጊዜው ገና ልጅ ነው። ምልክቱ ግን እዮራዊ ነው።
በአላዛሯ ኢትዮጵያ ብዙ ቃለ ምልልሶችን ሌሉትን ሙሉ አዳመጥኩኝ።
ያው ይህ የበራራ አደጋ በመንፈሴ ውስጥ ትንሽ ተገስ እስኪል ድርስ እንዲህ ነኝ - እንቅልፍ አጣለሁኝ። አንድ ጊዜ አውሮፕላን አደጋ
ከደረሰ በኋዋላም ተከታይ ይኖራል ብዬ ስለማስብ ይጨንቀኛል። ሌላው ደግሞ እዛው ኢትዮጵያ መሬት ላይ ተፈጽሞ እንኳን ምንም አይመስለውም።
ወደ ተነሳሁበት ስመለስ ብዙ ሰው መስጋት ብቻ ሳይሆን
ልክ በቅንጅት ጊዜ የተሰማው ዓይነት በመንፈስ፤ በተስፋ መሟሸሽ አያለሁኝ። አገር እኮ አትሸመትም አትቀናም።
ይህም ምን ማለት ነው? ለመሸመትም ለማቅናትም ፈቃደ
እግዚአብሄር አለበት ማለት ነው።
ብላክ ቦክሱ እኮ አልተነበበም ገና ወደ ሦስት ወር ይጣይቃል ይላሉ ባለሙያዎች፤ የመጀመሪያ ደረጃ
ንባቡ ለማድመጥ ለዛውም ከተፈቀደ ነው። ግን እዮር ፈረደና ያ ሁሉ አገር ቦይንግ 737 ማክስ 8 አስቆመ። እሱን ብቻ ሳይሆን በትንሽ
ወንድሙ ላይ የጥናት ጥንካሬ ብርታት በሚያስፈጥር መልኩ ተጽዕኖ ፈጠረ።
ይህ ማለት ምን ማለት ነው? እኛ እዬመሰለን ነው እንጂ
ዳኛው መዳህኒተ ዓለም ነው። አባታችን መዳህኒታዓለም መልካም ነገር ስናይ ደስ ይለን፤ ተስፋ እናደርግ ዘንድ ሰው መሆናችን ፈተነን። እኛ አሰምረን ፈተናው አለፈን። እንዲያውም ከተሰጠን ፈተና በላይ አልፈንም የጽድቅ መንገድ አድርገን አዬነው የለማወአብይ
ቅዬሳን።
ተፈጥራዊው ነው ሰዋዊ ነው ብለን ውሳጣችን ሳንሳሳ ሸለምነው። የድምጽ እላባዎቹ የኢትዮጵያ ሴተች ዕንባ ሊታገስ ነው
ብለን ያለማቋረጥ ወረብንለት። መንፈሳችን በስጦታ ፈቅደን እና ወደን አብዛኞቻችን አቅረብን። የጸጋ ስግደትም ተደረገለት።
ዘር፤ ቋንቋ፤ ፆታ፤ ዕድሜ፤ መልክዕምድራዊ አቀማመጥ፤ ብሄር፤ ዕምነት፤ ሙያ፤ የተማረ፤
ያልተማረ፤ ሃይሞኖተኛ፤ ሃይማኖት አልባ ሳይባል እራሱን ለጠ/ሚር ያጨው ዜጋ ሁሉ ሳይቀር ቢግደረደርም ጫና እንዲፈጥር ተፈቅዶለት
በሰውኛ ከተሰጠው የቤት ውስጥ
ጉብታ ከጉለሌው ኦነግ በስተቀር ሁሉም በአሃቲ ልቦና እልል ብሎ
እየዘመረ ማህሌት ቆመለት።
ድርሳን አደረሰለት፤ ተቀኘለት፤ ወደቀ ተነሳለት፤ ቅኔው በጉአባኤ ተዘረፈ፤ አብሮ ከፎቶ ጋር ለመቆም፤ አብሮ በጥግ ቆሞ ወይንም ተቀምጦ ለመታዬት ገንዘብ
ሁሉ ተማሰነ … ። ፍቅር ቅዳሴ ተቀሞለት፤ ኢትዮጵያም ከሱባኤዋ ብቅ ብላ በበራ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ መለያዋ ጎልታ ወጣች …
የአፍ መፍቻም ቋንቋም ሆነች።
ከማንም ከምንም በላይ እንኩላሊት እና ልብን ከሚመረምረው
ፈጣሪ በስተቀር እንደፈጠረን አፈጣጠራችን አምላካችን መልካም ለሚመኙ
ሊያደርጉ ለሚፈቅዱ ሁሉ ልባችን ከፍተን በቅንነት ከአንድ ዓመት በላይ ተጋን፤ አብሶ ትቢያ ላይ የምንገኝ ዜጎች፤ ባለቤት ያልነበረን
ዜጎች። እኛም ብቻ አይደለም ሉላዊ ዓለምም የ አፍሪካ መድህን ብሎ ከፍና ዝቅ አለ።
ከእኛም አልፎ ከሉዑል እሰከ ሳይንቲስት ምስክርነቱን በማህተም ክታቡ አደረገ። ሹመቱ እንጂ ወደ 12 ወራት እያስቆጠረ ያለው
ከዚያ በፊት የነበረው የብራና ጉግስ ከዓመት በላይ የዘለቀ ነው። የነበረንን አቅም ለምናውቅ ሰዎች አጋጣሚውን በመጠቀም የዴሞክራሲ ሥርዓት
ዝርጋት ለማድረግ የተገኘውን ዕድል በጥንቃቄ ለመጠቀም አቅም ማሰባሰብ፤ ለዛም መትጋት መደበኛ ሥራችን ሆነ በነፃ አገልግሎት …
የለወጡ ማህንዲሶች ቲም ለማ ከዞግ ድርጅት መጡ፤
ተምረዋል አልተማሩም፤ አጭር ናቸው ረጅም፤ ሃብት አላቸው - የላቸውም፤ አግብተዋል - አላጋቡም፤ ኢህአዴግ ነበሩ ያ ከጥያቄ የገባ አልነበረም፤
እንደ ሰው በንጽህና እናት አገራቸውን የምትሰጣቸውን ብሄራዊ ሃላፊነት በሚዛን በእኩልነት ይወጣሉ ወይንስ አይወጡም በሚለው መስፈርት ብቻ ወደን አክብረን ተቀበልን።
የሰው ልብ፤ የሰው ህሊና፤ የሰው መንፈስ ምን
እንደሚያስብ ዓለም የፈለሰመቸው አንባቢ መሳሪያ የለምና እንደሉን አመናቸው፤ ስናምናቸው ዝቅ ብለን እንጂ ተንጠራርተን አልነበረም።
ከራስ በላይ ታመኑ፤ ቅንነት ተመገቡ፤ ፍቅር በገፍ ተቀለቡ። መነሻ እና
መድረሻው ግን የኢትዮጵያን ታላቅነት የዜግነት ክብሩነት እና ልዕልና ከነበረው ክብሩ ያደርሱታል በሚል መታመንንም፤ ታማኝነትንም ያለ ደንበር እና ወሰን ተቀለቡ። የሃይማኖት አበው እና እመው ሌት እና ቀን ጸለዩ ... እንደ አሁኑ አያያዝ እነሱ ቢሆኑ አያደርጉትም ነበር። ሁሉንም የኦሮሞ ሊሂቃን አክቲቢስት የሚዲያ ሰዎች ሳስተውል ጠፍጣፋ የሆነ ነገር ነው የማገኘው። ካለ አናባቢ ተነባቢ ቃል አለመኖሩን እራሱ አምነው መቀበል አይቻላቸውም።
እኛ ግን ፈተናውን አለፍን በአጥጋቢ ሁኔታ። ልዑል እግዚአብሔርን
አላስከፋነም፤ አልበደልነም፤ ፈጣሪያችን ልዑል እግዚአብሄር በሰጠን ልክ መስጠታችን የተፈጠርንበትን የመክሊት ግዳጅ መፈጻማችን በመሆኑ ኤልሻዳይ አምላክ ቢያከብረን እንጂ ቅጣት የለብንም።
በተነገረን አንደበት ልክ አከበርን፤ አውደስን፤ ተቀበልን፤ ሊሰጥ የሚጋባውን ንጽንሃ ድንግልና
ሁሉ እላፊ ሄደን ሰጠን። ስለዚህ እኛ ክብር እንጂ ከፈጠረን አምላክ የሚነሳብን አንዳችም የምፈርቃት ቅንጣት የለም። የፈጠራችን ሚስጢር ዕዳ የለብንም። የሰጠንን እለሳሳንለትም። ፍቅራችን፤ አክብሮታችን፤ መታመናችን በመቁንን አልነበረም። በገፍ ነው የነበረው።
ልዑል እግዚአብሄር እንደ ሰው አስበን መልካም የሆነን
ነገር መደገፍ፤ በቅንነት ማዬት፤ ተስፋ ማድረግ፤ ተስፋ መጠበቅ፤ በምናዬው መልክም ነገር ልክ መመስከር፤ ከጎን መቆም፤ አዎንታዊ
መሆን ምን አጎደለን? ምንም! ቅንጣት ነገር አላጎደልንም።
ስለዚህ ውስጣችን ደስ ሊለው ይገባል እንጂ ሊጸጸትን ከቶውንም አይገባም። ኢትዮጵያን ወደድን። ሌላ ሃጢያት የለብንም። ኢትዮጵያን
አከበርን አስከበርን።
አልተጸጸትኩም የሚሉ ቢኖሩም አላዘንም ማለት ግን
አይችሉም። አላዛነም ባይሉም አልደነገጠንም አይሉም። የተፈራረቁ ስሜቶች በእያንዳንዱ ውስጥ ተፈጥሯል። ራስን መዳኘት እስከማይችል ድረስ። ለመወሰንም፤ ለመቁረጥም ፈተናው ከኖርንበት ዘመን በላይ ሞጋች ነው።
የተፈራረራቁ ዥንጉርጉር ስሜቶች ሁሉንም በዬቤቱ ፈትኖታል። የሰው ልጅ
በእነዚህ ውሳጣዊ ተፈጥሯዊ ስሜቶች ውስጥ መኖር ግድ ይለዋል። የሰጠውን ፍቅር፤ የሰጠውን ቃልኪዳን ሲያጣ ሰው ቢደነግጥ፤ ቢያዝን አይፈረድም፤ ግን ኢትዮጵያ አምላክ አላት። የፈጠራት አምላክ አይተኛም፤ አያንቀላፋም ... ።
እነዚህ ቅን እግዚአብሄር ወዳጆች ሊያውቁት እና ሊገነዘቡት የሚባው ነገር ቅንነታቸው በፈጣሪ
ዘንድ ምርቃት፤ በረከት የሚያሰጥ
እንጂ እርግማን እንዳልሆነ ከልባቸው ሊቀበሉት ይገባል። ቅንነት እኮ ለህሊና ሰላም ጥሪት ነው። የ እኛ ህሊና ዛሬ ሰላም ነው።
በሌላ በኩል ቀደም ብለው ከመጀመሪያውም የተቃወሙ
ከመሰረቱም ያወገዙ ወገኖች ደግሞ ነበሩ። በዛ አቋማቸው ጸንተው የቆሙ አሁን ደጋፊ አካል የነበረውን በድጋፉ ላይ ማዕቀብ ሲጥል
„እንኳን ደህና መጣችሁ ወደ እኛ ቡድን እያሉ ነው።“ እነሱ እና እኛ በፈጣሪ ዘንድ እንለያያለን።
መልካም ነገርን ሰምቶ፤ አይቶ
አለመቀበል፤ አለማድነቅ፤ አለማክበር ጤነኝነት አለመሆኑ ልብና እኩላሊት የሚመረምረው አምላክ ያውቃል እና። እንፈተንበትም ዘንድ
ነው ይህን ያመጣው ልዑል እግዚአብሔር። በሌላ በኩል ሌላው ሁሉ ቀርቶ እናቶች ሞት የተፈረደባቸውን ልጆአቸው ጋር ለቅጽበት ዓይን ለ ዓይን ማዬት፤ ተሰዶ የኖረ ወገን ባድማውን ለቅጽበት ማዬት ይህ ብቻ በቂ ነው ... ሂሳብ ውስጥ ሳንገባ ...
ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ መንፈሱን ተቀብለው ወዲያዉኑም ተቃውሞ ያደረጉት፤ በፍጥነት
አካሄዱን አይተው መንገዱን የጠረጠሩ ጭራሹን ካልደገፉት መለየታቸው ብቻ ሳይሆን እነዚህ ወገኖች ቀድሞ የማዬት አቅም ያላቸው ብቁ
ወገኖች ናቸው ብዬ በሰውኛው ስተረጎመው በመንፈስ ቅዱስ ረገድም የተለዬ ጸጋ ያላቸው እንደሆኑ አስባለሁኝ። ማለት ቢያንስ ከ6 ወር
በፊት ጉዳዮችን እዬተከታታሉ መተንተን የቻሉት … ነገር የሚመረመረው በሚታይ በሚጨበጥ ነገር እንጂ ገና በይሆናል ስላልሆነ፤ ተማሪ ሲኖር ነው ፈተና የሚኖረው፤ ተማሪ ሲኖር ነው አስተማሪም የሚኖረው ...
ሌላው ሲጀመር በነበረው የፀና የተቃውሞ አቋም የነበሩት፤
· አንደኛው ለእኔ ተጠራጣሪነት፤
· ሁለተኛው ያጣው ነገር ያለበት፤
· ሦስተኛ አቅሙን አሳንሶ የማዬት፤
· አራተኛው አማራጭ እኔ አለኝ የሚል ነገር ግን በተጨባጭ ምንም የሌለው ለዛውም ያልተደራጀ ግን ከሰማይ መና የሚጠበቅ፤
· አምስተኛው ቅናት እና የበታችንት ስሜት፤
· ስድሰተኛው ሲፈጠር ኡለታዊ ከሆነ መንፈስ የሚመነጭ ይመስለኛል።
ምክንያቱም ባሳለፍነው
አንድ ዓመት መልካምም // መልካም ያልሆኑ ገጠመኞች ነበሩና። ትርፍም አለው ኪሳራም አለው።
እነዛ የተፈጠሩት መልካም አጋጣሚዎች ግን ለዬትኛው
ፕሮጀክት ማስፈጸሚያነት የተሰሉ ነበር ብሎ ለመመርምር ጊዜው ልጅም ቢሆን ፍንጩ ግን ከመስከረም ጀምሮ የሆነው ሁሉ ምስክር ይሆናል። ያመጠው ሐምሌ የካቲት ላይ ተገላግሏል። አሁን ግርዶሽ የለበትም። በለዬት መንገድ ባለው ሁኔታ የራስን አቋም መያዝ ይቻላል። ማስተዛዘኛም፤ ማስተዛዘቢያም ሳይሆን የታዛ እና የ እንጥፍጣፊ ጠብታን ማወደድ ብቻን ነው የሚጠይቀው።
አሁንም ቢሆን ተስፋን እንደለመደብን ሙጥጥ አድርገን ቆሻሻ ውስጥ ከመጣል ይልቅ ሰከን ያለ መንገድ ለመከተል አቅሜ የት ላይ ነው?
አማራጩስ? ለዛ አማራጩ ሙት መሬቱን ተቋቁሜ እችለዋለሁ ወይ ማዕበሉን በማለት በስክንት ማህሉን ሳይሆን፤ ወይንም ጠ ርዙን ሳይሆን የ አውነትን አስኳል መድፈር ግድ ይላል። ይህም በራሱ ፈተና ነው። የደገፍነውን መቃወም እንደነውር ይታያል፤ አቅም ጉልበት ባለው ደግሞ እንደ ወንጀል፤ እንደ ተጻራሪ፤ እንደ አናርኪ ስለሚቆጠር እነዚህ ሁሉ ፈተኝ ናቸው …
አንድም ጠንካራ የሚባል ተቋም ውጪ አገር የለም።
ለማስፈራሪየ እንኳን የሚሆን። ሁሉም አቅም ወደ አገር ቤት ገብቷል። ቢያንስ ከኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞት ማግስት ትንሽ አደብ
ገዝቶ ሁኔታን ማጥናት ይጠበቅ ነበር። እኔም ጽፌያለሁኝ። በቁጠባ ይሁን በሚል።
ሌላው ከስሜን አሜሪካ መልስ የጠ/ሚር አብይ አህመድ
ጉዳይ የሐምሌውን ዝምታም በአርምሞ ሳይሟጥጡም ሳያሸነግሉም በቅጡ መከታታል ይገባ ነበር። "አክ ወሬ" ሰው በሩን ዘግቶ እንዲቀመጥ አደረገው።በጣም አዘናጊ ሁኔታዎችን ክትል እንዳይደረግባቸው ያደረገ ቀዝቃ ፍልስፍና ነበር። ምን ጊዜም ይህም ሊኖር ይችላል ብሎ ማሰብ ይገባል። ለወደፊቱም ...
ትልቁ ግድፈት ግን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ያን ያህል ሊሂቅ፤ ያን ያህል
የፖለቲካ ድርጅት ውጭ አገር በነበራቸው ቆይታ ጉልበታም ጥያቄ ለማቅረብ አለመቻሉ፤ አለመሞገቱ „አሻግራችሁአለሁ“ ሲሉ እንኳን
መርህ ከተል መንገድ እንዲሆን አለመፈታተን ዛሬ በረዶ ላይ ለመቀመጥ የነፃነት ተጋድሎ ተገዷል።
ቀድሞ ነገር ትጥቁን የፈታ ምኞት ነው ያለን። ለመደራደር የሚስያስችል የፀና ዓላማ እና
ፍላጎት ያለው አለት የአቅም አቅም ግን ጥግም ምርኩዝም መጠለያም የሚሆን የለንም። ሁልጊዜ ንፋስ አምላኪ ስለሆን የወጀብ ሲሳይ
የሆንበትም ሚስጢርም ለዚህ ነው። ሁሉም ጥግ አልባ በባጣ ቆዬኝ ተጥልሎ ቆዬ ይህን አጋጣሚ ሰያገኝ ያን ተቀላቀለ፤ አውራ የሚባሉት ድርጅቶች ቅምጥ አቅም ኑሯቸው ቢሆን ግን ከ ኢህአዴግ ልመና የሚያስኬድ ምንም ነገር ባልነበረ ነበር። ይህን ለረጅም ጊዜ ስናገረው ኑሪያለሁኝ።
አሁን እውነት ብናገረው የነፃነት ትግሉ ትጥቅ ተፈቷል።
ትጥቅ የምለው የመሳሪያ አይደለም ያ ገናና የነፃነት ተጋድሎ መንፈስ
በግልም በወልም ይደረግ የነበረው ጥረት ድብዛው ጠፍቷል፤ ታክቶታልም እስከ እስክንድር ንቅናቄ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ።
ይህም ራሱ በግራ በቀኝ ወጀብ እዬተለቀቀበት ነው። ያው ብቅ ያለ ነገር መንቀል የለመደብን ነውና።
ሳምንት ሳይሞላ ግንቦት 7 መግለጫ አወጣ፤ የግንቦት 7 ጸሐፊው ጠንካራ ቃለ
ምልልስ፤ የሊቀመንበሩ ተጨማሪ ቃለ ምልልስ፤ የሊቀመንበሩ ንግግር፤ የስልት ለወጥ በሰብዕዊነት ላይ ተኮር እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ አዲስ
መንገድ መጀመር ሁሉም የመጡት ከአንቀላፋው የትጥቅ መፍታት መነቃቃትን ቢታሚን ከመገበው የእስክንድር ንቅናቄ በሆዋላ የመጣ ነው።ልክ እንደ የአማራ የህልውና ተጋድሎ ጊዜ ማለት ነው።
በተጨማሪም ቀደም ብሎ እንቅፋት ለመፍጠር ይሁን አትኩሮት ለማሳሳት የጠ/ሚሩ የፕሬስ ጉባኤ ባልተለመደ ባልተጠና ባልታቀደ
ሁኔታ መታቀድ እና መከወን … የኦሮምያ የአዲስ አባባ የባለቤትነት መግለጫ እና የጠ/ ሚር ቢሮ አንዱን ኦህዴድ ከሁሉት እራሱን
ገምሶ አንዱን ተደራዳሪ አንዱን አደራዳሪ አድርጎ የከፈለው ድንገቴ፤ በዓዋጅ የተቋቋመው የማንነት እና የወሰን ኮሚሽን ሥልጣን ነጥቆ የሰጠ
ሌላ ኮሜቴ መፍጠር … በጥቅሉ ሲታዩ ያው ካለወቅቱ እንደመርጋት ያለ ወትት ሳት ላይ ሲጣድ … ነው የሆነው። በተበጣሰ መንፈስ ነው ሁኔታውን እዬተመራ ያለው ... ይህ እንግዲህ ብዕር ብቻ ያለው ነፍስ ንቅናቄ ያስከተለው ነገር ነው ... ዘላቂው ሲታሰብ አምላክ አላት ኢትዮጵያ።
በዚህ ሁሉ ልናዬው የሚገባው ቁምነገር እግዚአብሄር
በሁሉም መስክ ምልክት እዬሰጠን መሆኑን ነው። የሰማዩ አዬር መንገድ ጉማም መከራ ሉላዊ ሞገዱ እና ዕድምታው እሰተ ቅኔው በአንድ
በኩል፤ በሌላ በኩል የምድሩ የእስክንድር ንቅናቄ የፈጠረው ለሽ ብሎ የባጀወን በሥም ብቻ የተኮፈሰውን ሁለመና ናጠው። ጥሪት አልነበረንም፤ ለክፉ ቀን የተቀመጠ አቅም አልነበረንም። ሁሉመናው ሙት መሬት ላይ ተዘረጋ ...
እኛስ ከዚህ ምን እንማራለን? እኔ ከእዚህ እምንማረው
ኢትዮጵያ አምላክ ያላት ስለመሆኗ ማህተም ማግኘቴ ነው። እውነት እና ቅንነት ከኖረ የእስክንድር ንቅናቄ በፈቃደ እግዚአብሄር የተሰናዳ
እና የጠፋብን መንገድ ደግሞ እንደገና እንሞክው ዘንድ አቅጣጫ ያሳዬ ነው። ብርድ ብርድ ያለውን የለመደበትን ለሽይበሉም ጎስጉሶታል።
ግን ግማዱ ቻለኝ ነው። ለህይወቱ እኔ እሰጋለሁኝ … ሌላው ቀርቶ ኢትዮጵያ ማተቡ
የሆነው መንፈስ እንኳን የእስክንድርን ንቅናቄ እንደባላንጣ ማዬት የመረገማችን ሌላው ምልክት ነው። ምክንት!እኛም ለምደናዋል ...
የቀደመውም በፈጠሪ ፈቃድ የአሁኑም በፈጠሪ ፈቃድ
ነው ብዬ አምናለሁኝ። ይህን ጥምር ጉዞ በጥምር ማስተዋል ሰከን ብሎ በመራመድ መፈተሽ ያስፍልግ ይመስለኛል። ኢትዮጵያ እንደ ጣለባት
አሁን ልጆቿን እዬፈለገች ነው። መፈለግ … መፈለግ እንደ ሥነ - ፈልግ ፍልስፍና።
ሰውና ሰው ሰውና ኢትዮጵያ የሚገናኙበት ቀን ይናፍቀኛል።
ይህ ማለት እውነት ያለበትን መንፈስ ለማበረታት አቅም የሚኖረን ማዕልት ሽው ይለኛል። የምጠብቀውም የፈጣሪ ፈቃድን ነው።
አንድ ጊዜ ደስታን በልክ ስለመያዝ አንድ ጹሑፍ ጽፌ
ነበር። እኔ እራሴንም ወቅሼ። አሁንም እኔ እምለው ከሰው በላይ ፈጣሪ ስላለ በፈጣሪም ማዘን ሳይሆን ወስጡን የእጬጌ ሂደትን ገብተን
በዚህ ውስጥ ምን እንማራለን ማለት ይገባናል። እንደ ፖለቲከኞች ትርፍና ኪሳራ ካወጣን ካወረድን አንማርበትም። የእነሱ ስሌት ከአራት ወንበር እና
ከሥም እና መወድስ ከእውቅና ከተቀባይነት ጋር ስለሚያያዝ።
አብሶ ያለዬላቸው አጓጉል አፍዝ ቀዝቃዛ የወለሌዎች ማህል ሰፋሪነት አደጋ የመቋቋም አቅምን ይበላል። ስለዚህ ቢያንስ ዛሬ ህሊናን ማሰራት ይጠይቃል። ሦስት አራት ምጣድ ጥዶ ለ አንዱም ሳይሆኑ ከመቅረት።
አቅም ከሌለ ትናንትም ትናንት ዛሬም ዛሬም ነው። የህሊና ዕድገት ከተወሰነ
ጊዜ በኋዋላ ቀጥ ነው። በዛ ውስጥ ትውልድ እና ብክነቱን አስልቶ ህሊና፤ ከእጬጌው ሂደት ጋርም ታድሞ ምርጫን ማስተካከል ይገባል። ተተኪንም የሚመጠነውን ማሰናዳትም ይገባል።
ለዚህም ፈጣሪ እንዲረዳ መማጸን የተገባ ይሆናል። ተስፋ አድርገን ተስፋን ባጣን ቁጥር ማስተዛዘኛ የግርሻ ጊዜ እዬዘከሩ አብሮ መጠንዘል የበቃ ይመስለኛል። የተሞከረው ተሞከረ ያ አለፈ፤ አሁን ደግሞ ሞከርነው እሱም እያለፈን ነው … ዕድሉን ላለገኙት አለን ለሚሊ እሸቶች ደግሞ ሰጥቶ ማዬት
ነው ተስፋ አያልቅም እና …
እንደ ሥርጉተ ሥላሴ ፈተና ላይ መሆናችን በተሰነጠቀ መልኩ ሳይሆን ይህን አምኖ መቀበል የሚገባ ይመስለኛል። ይህን ካመን ኢትዮጵያዊነት
ደግሞ ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ስለመሆኑ ይህንንም አምነን እንቀበል ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁኝ።
ያ እንዳለፈው
ሁሉ ይህም ማለፉንም ማመን ይገባል። ይህን ስል በዬዘመኑ ብዙ መንፈሶች፤ ብዙ ድካሞች ባክነው መቅረታቸው ይታወቃል። በሰው ህይወት ሲሰላ ትውልደ ነው መንፈሱም ሁለመናውም ያለቀው። ይህም ነገም ሊኖር
ይችላል። ግን ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደረም።
አንድዬ ከተመነ በፈተና ጀርባ ለጽኑዎች ታላቅ የስኬት ማሳ
አለና። በዚህ ስሌት ከሰው የጠበቅነውን ያህል ቢያንስ ከፈጣሪ
ለመጠበቅም እንሰበው። ጥፋታችንም ባይሆን ዛል ማለታችን ዘመን ሳያስተምረን ይኽው ነው። ቢያንስ አንስበው። ፈጣሪ
ሁሉም ይቻለዋል።
መሬትን ካለ ካስማ፤ ሰማይን ካለባላ ያቆመ አምላክ አለን። አይዞን። ሰውን ያህል ፍጡር የፈጠረ ፈጣሪ አለን።
መቼም ምድር እስካሁን ሰውን መፍጠር አልቻለችም ጭቃ አንቦልቡላ እንደምትሰራው ሸክላ ወይንም ብረት ቀጣቅጣ እንደምትሰራው የቴክኖሎጂ አይነት።
ስለሆነም ረቂቅ ከሆነው አምላክ ረቂቅ የሆነ ሥልጣን
ኪነ - ክህሎት አለና በፈጣሪያችን / በአላህ ተስፋ ማድረግን እንለማመደው፤ ግዴላችሁም እንለማመደው። ያ ኪነ - ክህሎት ደግሞ ሰማይ እና መሬትን
የማስተዳደር ቃልኪዳን አለበት። ኢትዮጵያ ደግሞ የቃልኪዳን አገሩ ናት እና አይረሳትም። ቀድሞ ነገር እኛ ምን አቅም አለን?
ስለሆነም ሁሉም ነገር ለመልካም ነው ብለን በጽናት
ተግተን፤ በንጹህ ልቦና ሆነን ያ እዬሸነሸን እምናይበትን ሽሁራር ቸረቸራ የጠል ጥላሸት ሳባብረን፤ ሰው በሚለው ታላቅ የፈጣሪ አምሳያ ውስጥ መሆን
ለመቻል ከቆረጥን ኢትዮጵያን ፈጣሪ አይረሳትም።
ምንም መረባበሽ ሳይሆን በተረጋጋ መንፈስ በውስጣችን
ያለውን ቆሻሻ የሴራ ቤተኝነታችን አጽድተን ቅንነትን ብንሻ ችግራችን ቀላል ነው። መታመን በቃል ውስጥ ሳይሆን በሴራ ውስጥ እንዲበቅል ስለሚፈቀድለት ከቂም ያለፈ ትጋት ያስፈልገናል። ይህን በማድረጋችን የእሱ እርዳታም አናጣም፤ ምርቃትም ሆነ በረከትም አይነሳም።
እርግጥ ነው አሳሳቢው ጉዳይ አገር ውስጥ ብቻ አይደለም
የውጩ ግንኙነቱም ሙሉ ለሙሉ በአንድ ድርጅት ሥር ብቻ የወደቀ ስለሆነ ከምናስበውም በላይ በቀላሉ ሊፈታቱ የሚችሉ ላይሆኑ ይችላሉ። የውጭ ጉዳይ ለከ8 ወራት በላይ እሰረኛ ነው።
በዛ ላይ አቅማችን ስናስበው ደግሞ በልጦ ለመገኘት፤ ቀድሞ ለመገኘት ሳይሆን አንድ ደመቅ ያለ ነገር በመጠበቅ ላይ የተኮረ ምኞት ስለሆኑ እምንሻው የመንገዶቹ ውስብስነት ከምንጠብቀው በላይ ግዙፍ ነው።
አሁን ከኤርትራ ጋር ያለው ግንኙነት በመንግሥት ደረጃ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አናውቅም? ከአረብ አገሮችም ጋር እንዲሁ
… ሁሎችም የሚከወኑት በኦህዴድ በተከደና እና በተዘጋ አኳኋዋን ነው። የወርቅ የነዳጅ ጉዳይ ሳይሆን የተፋጠጡ ዕውነቶች አሉ ኦሮማዊነት እና ኢትዮጵያዊነት ... ወይንም ኦሮታጋሩነት እና ኢትዮጵያዊነት። ስለዚህ ልብ ገዝቶ ማስተዋልን መሰነቅ ይገባል።
በዚህም ስጋት ውስጥ እንደምናሰበው ሳይሆን የተሻለም ነገር ፈጣሪ አላትና አንድዬ ሊኖር ይችላል። ለአላዛሯ ኢትዮጵያ
የሚል ጽናት ከኖረን ጎርፉን እናልፈዋለን። የተተበተበወን፤ የተቆለፈውን፤ የተከደነውንም ምክንያታዊ የሆኑ ቅዱሳንን እያስነሳ መንገዱን
ይመራናል።
ነገር ግን የልባችን መሻት ከቂም ማጽዳት ይጠበቅብናል።
ይህን ካደረግን ከተወረውረ ቀስት እንድን ዘንድ በሁሉም መስክ ምልክት እናገኛለን። ምልክት ስናገኝ ደግሞ ጠበቅ በርታ አደርገን
መያዝ ያስፈልጋል።
ያ ምልክት ያዝ ለቀቅ በማድረግ ሳይሆን በውስጡ ለመኖር መፍቀድ ይጠይቃል። አሁን ትልቁ ችግር በኢትዮጵያዊነት
ውስጥ ለመኖር ፈቃድ አለመኖር ነው የግጭቱ እና የስበቱ ስብረቃ። ድርጅቶችን ሁሉ ከሙሽርነት ውጪ ልልጅል የማያበቃው፤ ኢትዮጵያ ማሟያ በመሆኗ ብቻ ነው። ከዚህ በመለስ ከዛ በመለስ ዋነኛው መንገዳችን ሆኖ 50 ዓመት ዘልቋል።
እንዲህ ውሉ ጠፍቶ ድብልቅልቅ፤ ወይንም ድንብልብል
ሲልብን ፈጣሪን ብንጠይቀው መንገዱን ያሳዬናል። ማሳዬት ብቻ ሳይሆን መርከቡንም መቅዘፊያውንም ይሸልመናል። ይህን ለማግኘት ተረጋግቶ
ማሰብ ያስፈልጋል።
ራሱ ፈጣሪን ለመጠዬቅ የመንፈስ የአካል የሰብዕና ንጽህና ይጠይቃል። ስላለፈው ነገር ሳይሆን ስለመጪው ማሰብ
እና ስለዛ መተለም ይገባል። ሁሉም የሆነው እንዲሆን በተፈቀደለት ሁነት ነው። እኛም በፈጣሪ ሥር ነን። ከእሱ ፈቃድ ውጪ አንዳችም
የማድረግ አቅም የለንም።
ፈተና ተፈልጎ አይመጣም፤ ነገር ግን ራሱ ፈልጎ ከመጣ
በረከት ነው። በዛ ውስጥ ምህረት እና የምሥራች ስላለ። ግን ለጸኑዎች ብቻ ነው ፈተና አልሚ የሚሆነው። ጽናት ደግሞ የሚገኘው በወጀብ
ውስጥ ያለውን ዕውነት ፈልጎ በማግኘት እና እሱን በመጠለል ነው።
እውነትን እግዚአብሄር የፈጠረው ለራሳችን ፈራጅ ህሊና ችሎት ይሆን
ዘንድም ነውና። እውነትን ደፍሮ ክብርን ተፀይፎ ለመኖር መፍቀድ በራሱ የመኖር ጽድቅ ነው። አንድዬ አማኑኤል ጽናቱን፤ ብርታቱን፤ ይስጠን።
አሜን!
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን
አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ