እመ ቅኒት ልዕልት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዘመቻው እሷንም ያለመ መሆኑን አውቃው ይሆን???
እመ ቅኒት ልዕልት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዘመቻው እሷንም ያለመ መሆኑን አውቃው ይሆን???
#ድምፃችን ይሰማም ተመልሶ አይመጣም የሚል ዕምነት ዬለኝም።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን ሰነፍ አድርጎ የሚያይ ብዙ ሰው አለ። እሳቸው ዕድሜ ዘመናቸውን ሁሉ ፕላን ሠርተው የተሰናዱትን እዬፈፀሙ ነው። ዝልኛቸውን አልወጠኑትም። መቼ ይህን ዕድል እንደሚያገኙ ቀኑን፤ ዘመኑን ባያውቁትም ከንግግራቸው ጀምሮ በስልት፤ በብልጠት፤ በማዘናጋት፤ በማተራመስ እራሳቸውን አሰልጥነው ሙሉ መሰናዶ አድርገውበታል። ደራሽነቱ ለእኛ ብቻ ነው። ለዚህ ነው እኔ ለአፍሪካ፤ ለቀንዱም ለመካከለኛውም ለዓለም እጅግ አስቸጋሪ አሳቻ መሪ ናቸው እምለው።
ይህ የሚሆን የጀርባ አጥንቷ በሆነው ዬአማራ ክልልንም ያካታል። ከ14 ሺህ በላይ ፋኖ ሲታሠር እሧም ታስራለች፤ 18 ወጣቶች ሲታገቱ እሷም ታግታለች። 12983 ተማሪወች ከፈተና ውጪ ሲሆኑ እሷም አለችበት። በፓርላማ፤ በካቢኔ ውስጥ ልጆቿ ሲገለሉ እሷም አቅመ ቢስ እንድትሆን ተበይኖባታል። ዙሪያ ገባው እሷን ሆስቴጅ የማድረግ ተልዕኮ ስለመሆኑ በጥልቀት አስባ ሳትዘናጋ ከዓለም አብያተ ቤተክርስትያናት ጋር በደራሽ ችግሮች ሳይሆን በዘላቂ የህልውና ጉዳይ ልትተጋበት ይገባል።
ይህን ስል ወንዝ ቁልቁል እንጂ ወደ ላይ ስለማይፈስ አሻቅቤ ልናገራት አስቤ አይደለም። ፈፅሞ። የልጅነቴን ግልጽነት ትወቅልኝ ለማለት ነው።
በሌላ በኩል አማራዊ መንፈስ ሆኖ የእስልምእና እምነት ተከታይነትም የጊዜ ካልሆነ በስተቀርቀጣዩ መከራ ነው። ድምፃችን ይሰማ ተመልሶ አይመጣም የሚል እምነት የለኝም። አብሶ ጽንሰቱ ጠረኑ ኢትዮጵያዊ ከሆነ።
ነቀላው ከሥር ነው። እጅግ አስፈሪም ነው። ግሎባል የሆኑ ፍላጎቶችም ተቀይጠውበታል ብዬ አምናለሁኝ። ስለዚህ ተራ የሚጠብቁ ምንጠራወች ቀጣይ ናቸው።
ምን ይደረግ?
ሁለመናችን የህልውና አደጋ ላይ መሆኑን አውቆ ለሥር ነቀል ለውጥ እና ለዘላቂ የሥርዓት ግንባታ መታገል። ሁሉንም መከፋት፤ መገፋት የእኔ ብሎ ከሴራ፤ ከኢንትሪግ፤ ከፋክክር፤፦ከምቀኝነት፤ ከጥላቻ፤ ከቂም በቀል የፀዳ አኃታዊ ርጉ ስኩን ተጋድሎ ማድረግ በመከባበር መሪነት።
ውዶቼ ኑሩልኝ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
11/04/2023
አንተ አለህንአማኑኤል፤ አንተ ሁነን ኤልሻዳይ አምላክ። አሜን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ