ክፍል ሦስት - ርትህ።
ርትህ። ርትክፍል ሦስት።
ከሥርጉተ © ሥላሴ 30.06.2018
(ከመንኩሲያዋ ሲዊዘርላንድ።)
„በመንፈስ ደሃ የሆኑ ሰዎች ብጹዓን ናቸው፤
መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና“
- · የእኔ ክብረቶቼ ውዶቼ …
ቀደም ባለው ጊዜ ቅኑ እና ደጉ ሳተናው ብዙ ደንበኛ ስላለው አበዛበታለሁ በማለት የምዘላቸው
ብዙ ጉዳዮች ነበሩ። አሁን በራሴ ብሎግ ላይ ስለምሰራ አባዛለሁኝ የሚል ሰቀቀን ስለሌበኝ በሙሉ አቅሜ እሰራለሁኝ ብያለሁኝ ከፈጣሪ
ጋር። የምዋሳው ሆነ ከሌላ የምጠብቀው የብዕር የህሊና ምርት የግብይት ሥርዓት ስሌለበኝም እራሴው የሚሰማኝን እንደ ገባኝ እጠፈዋለሁኝ።
ማንዘርዘሪያ ወንፊቱ ደግሞ የእናንተ የመንፈስ አዱኛዎቼ ነው።
ባፈው ሳምንት ለጋዜጠኛ መሳይ መከነን „አንዳንዶቹ ባይደመሩስ“ በሚል መጣጥፍ ላይ ስሞግት እኔ
ስለማጠሪያ፤ ማንዘርዘሪያ ወንፊት ዓይነ ጠባቦች የመደመርን ፍልስፍና ያሰተነጋዱበት ጠንጋር ዕሳቤ፤ መደመርንም እኛ እንምራው
ዓይነት ጉዞ ስጥፍ ተናግሬ ነበር። ዛሬ በሠመራው ጉባኤ ይኸውኑን ጠ/ ሚሩ ሲናገሩት ሰማሁኝ። ቅንነት ካለ ሳትነጋገሩ፤ ሳትተዋወቁ፤ አንዱ አፍሪካ ሌላው አውሮፓ ላይ ሆኖ አንድ በሚያደርገው የሃስብ ሃዲድ ትገናኛለችሁ ካለ
ድርጅታዊ ሥር ማለት ነው። ካለ ካድሬያዊ ፕሮፖጋንዲስት ወይንም የፕሮቶኮል ጣጣ ምንጣጣ ማለት ነው። መደመር አብሮ መደመር ነገር ግን ቅሬት አካሎች ሳንክን ፈጣሪ ከሆኑ በማጣሪያው ተግባር ይጣለላሉ ማለት ነው።
የሆነ ሆኖ አሁን ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን ከሥር ከሥር መሥራት የሚያሳቅቀኝ ነገር ዛሬ ላይ የለበትም።
ስለዚህም የአፋርን ዕድምታ ሠመራን መነሻ በማድረግ ምእራፍ አንድ እና ሁለትን ጽፌያለሁኝ የጉዞ ማሳረጊያ በክልል ደረጃ ስለሆነ። ዛሬ ደግሞ በስብሰባው መንፈስ
ላይ ወስጡን በቅንጫቢ ለማዬት እንሞክራለን።
- ውስጠት።
ይህ ስብሰባ በመልስ አሰጣጡ ላይ በተለያዬ ቦታዎች ከተካሄዱት ህዝባዊ ስብሰባዎች የፖሊሲ አቅጣጫ
አመላካች መንፈሶች ነበሩበት ማለት ያስችላል። ሥራ ላይ ያሉ ተግባራትም ፍንጭ አግኝቼበታለሁኝ።
- ጥያቄው እና መልስ አሰጣጡ የርቀት ዓውድ።
አፋርን የመደመር ፖለቲካ ድርሽ ያለባት አይመስለኝም። የአፋሩ ጉባኤ የቀረቡ ጥያቄዎችን ከተሰጠው
መልስ አንጻር በጣም መለዬት በእጅጉ ያስፈልጋል። የእኔ ተመስጦ በመልሱ ላይ ነበር። ህገ መንግሥቱን የሚነቀንቅም፤ የኢህአድግ ግንባርንም የተመሰረተበትን አምክንዮ
የሚነቀንቅ መሠረታዊ ጉዳዮች ተነተውበታል ብዬ አስባለሁኝ። ስለዚህም ቀልቤን ስቦታል።
ይፋዊ ሚዲያ ያላቸው ቀለብ አድርገው ፍሬ ነገሮችን ሊዘርፉ እንደሚችሉም አስባለሁኝ። የትግራይ
ሥርዕዎ ምንግሥትን የአድዋ ሥርዕዎ መንግሥት በማለት እንደ ተገለባባጠው ማለት ነው። አዲስ የአገላለጽ ዘይቤ እንደተባለው ሁሉ።
የተለመደ ነው ዝርፊያ። ዝርፊያ የቁስ ሲሆን ምንም አይደለም፤ የመንፈስ ሲሆን የህሊና ቁርጥማት ነው የማይድን በሽታም። የሆነ
ሆኖ „ህልም ተፈርቶ እንቅልፍ ሳይተኛ ስለማይታደር እንሆ …
- · ጥያቄዎቹ እና መንፈሳቸው።
የሠመራ ጥያቄዎቹ አዲሱን የአብይን ካቢኔ ሊያፈነዳ የሚቃረብ ነበር የጭነቱ ክምር። የ43 ዓመት መከራ
ተሸከም ዓይነት ነበር። መንፈሳቸው ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የሴራ ጉንግን በግልጸት ነበርው። በጣም ያዘንኩት ውጪ የሚኖሩ
የአፋር የፖለቲካ ድርጅቶች በመንፈስ ደረጃ ህዝባቸው ጋር ምን ያህል የተራራቀ ሁኔታ እንዳለ ተመልክቻለሁኝ።
አሁንም አፋር በወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ አምላኪነቱ ሙሉ ለሙሉ እንደ አለ፤ እንደ ተፈጠረ
ነው ያለው። አንዲትም ቦታ አፋር ገዢውን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ጭቆና ሊያነሳ አልፈቀደም። የግድ ጥላቻ ሳይሆን በደሉን ከሌላ
ላይ ከመቆል እንቅጩን ፍርጥ አድርጎ መናገር ሲገባ ግን ወልደ ግራ የሆነ ነገር ነው ያዳመጥኩት።
በዚያ ላይ ታረቁልንም ተማህጽኖም አለበት። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ የገዳይነት፤ የዘራፊነት፤
የሶቃቃ አምራችንት ዘመን አልበቃውም ቀሪ ዘመኖች ተደምረዎለት ለ100 ዓመት በመሪነት ይሸጋገር፤ ለውጡ ይቀልበስ፤ የዛኔ ኢትዮጵያዊነት ምድማዱ ጠፍቶ ትግራዊነት
እጬጌ ሲሆን ህልማችን ነው ዓይነት ነው። ይህ መቼም ለድንቅነሽ ብርቅነት ያመረቀዘ ዕሳቤ ነው። አልተበደለም አፋር ማለት ነውን? ተጠቃሚ
ነበር አፋር ማለት ነበርን? ስለምን አፋር ፍቅርን ጉዞ እንዲህ አስፈራው?
በተጨማሪም የኢህአድግን ድል አምጪ ሃይልም ወያኔ ሃርነት ትግራይ አድርጎ የመለጠጥም ወረርሽኝ
ከመላ ተሳታፊዎች ከተነሱት ጥያቄ ጋር በተወራራሽኝ ለማወቅ ችያለሁኝ። አንዲት ጠዬም ያሉ ደማም አንስት ግን በሁሉም ሚዛን በሳል ዕይታ አቅርበዋል።
በሳቸው ኮርቻለሁኝ።
ከዚህ ባሻገር የነበረው ግን የካድሬ የሚባለው ዓይነት መንፈስ የነበረበት፤ ዕውነትን ለመድፈር የተሳነው፤ አፋር
የተፈጠረበትን፤ የተመሰጠረበትን የእውነት መሰረት ኢትዮጵያዊነት ላይ አጽህኖት ያልተሰጠበት ለዛዛ ስበስባ ነበር። ሚዚናዊም አልነበረም
የቀረበው ጥያቄ ሁሉ። መቀሌ ላይ ስበሰባው የተካሄደ እስኪመስለኝ ድረስ የደብረታቦር አንበሶች እንደ ገለጹት የስልክ ቀፎ በእውነት
ገሃድ የወጣበት ስብሰባ ነበር። አፋር ሴሚ ካርዱ ልክ እንደ ብአዴን ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ በፈቃዱ የገበረ ክልል ሆኖ
አግኝቻዋለሁኝ። ደካማ ተስትፎ፤ የከሳ የአመክንዮ አቅም ነው የታዬው።
- · ጠብታ።
አፋር ላይ የጠበቅኩት በሳል የተደሞ ቅኔ ቀርቶ ግርድፍ የሆነ ሃስብ ለማድመጥ ባለመቻሌ ደንግጫለሁኝ።
ሰሞኑን ሰላማያዊ ስልፍ ነበራቸው። ግመሏ የምታውቀውን ብሄራዊ ሰንደቅ ለምልክት የያዘ ወጣት አልነበረበትም። እኔ ደግሞ ጥሎብኝ
ሰፍ ብዬ ነው የምወዳቸው። አፋር ላይ ገና ሰፊ የሆነ የህሊና መሰናዶ ይጠብቃል። ደግሞ ለእነሱ ስለ ኢትዮጵያዊነት የፊደል ገባታ
ይገዛላቸውን? ታሪክ ብቻ ሆኖ ነው የቀረው የግመሏ እና የሰንደቋ ጉዳይ።
በኢትዮጵያዊነት ጉዳይ የታዬው
ቸለልተኝነት፤ የታዬው የስንጥቅ ዕድምታ ቁመና አፋር ያመለጠን ክልል ስለመሆኑ ማስረጃ አያስፈልገውም። የስብስባው ተሳተፊዎች ሆኖ ቀደም ብሎ የተካሄደው ሰላማዊ ስልፍ መንፈሳቸው
አፋር ሆኖ ለመቆም አቅም ያነሰው ኮስማና ነበር።
የካሳኝ የጠ/ ሚር አሜኑ አብይ አህመድ የመክፈቻ ንግግር እና የመልስ አቀራረብ ብቻ ነው። ሁሉም
ቦታ መልሶች ተወራራሽ ቢሆኑም አፋር ላይ ግን ፓርላማው እና ኢህዴግ በወል በጥምረት ባካሄዱት ጉባዔ ላይ ሊደመጥ የሚችል በሳል
አምክንዮ አዳምጫለሁኝ። ስለዚህም ነው ጊዜ ሰጥቼ በተወሰኑትን ነጥቦች ላይ የበኩሌን እይታ ላቀርብበት የወደድኩት። ሌላው ትልቁ የዚህን
ስብሰባ እድለኝነቱ መግለጽም የተገባ ነው። ይህም እንዲህ በፍጥነት የልብ ለልብ መንገድ በንጽህና ከኤርትራ ጋር ይኖራል የሚል ሃሳብ አልነበረም።
- · ወፊቱ በብሥራት ዜና እጀባ።
የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ግንኙነቱ ፈጣሪ ያለበት መሆኑ የሚታወቀው የሰኔ 16ቱ የ2010 የመቀሌው
መንግሥት ➳ የአዲስ
አባባውን ለመፈንቀል ባደረገው የቦንብ ጥቃት የኤርትራ ምንግሥት ቀድሞ ይሁንታዊ መልስ ባይሰጥ ኖሮ ጉዳዩ ከዛ ጋር ይያያዝ ነበር። ግንኙነቱንም በጥርጣሬ እና
በጥያቄ ያወክበው ነበር። ነግር ግን ሁለቱም ቅን ህዝቦች፤ የኢትዮጵያ መንግሥትም ለኤርትራ መንግሥት ያቀረበው የፍቅር
ጥሪን የኤርትራ መንግሥት በፍጹም ሁኔታ ባለመጠራጠር ቅንነት ያለው መልስ ስለመስጠቱ ከዚህ በላይ እዮራዊ ምስክር ሊሆን የሚችል
ተደሞ የለም።
እኔ ቀደም ባለው ጊዜ ከኤርትራ መንግሥት ድፍን ካለው የዝምታው ውስጥ ባሉ ነገሮች ላይ የማያያሳስቡኝ
ጉዳዮች አልነበሩም። በታሪኩም በውስጡም ስለኖርኩኝ ብዙውን ነገር እንዳለ ለመቀበል የሚያዳግቱኝ ጉዳዮች ነበሩብኝ። አሁን የወያኔ
ሃርነት ትግራይ የፈለገውን የሴራ ዓይነት ዲሪቶ ቢደረድር ከእንግዲህ የሞተ ውሻ ህልም ነው የሚሆነው።
እርግጥ የሚያደርጉ ቅንነቶችን፤ ንጽህናዎችን ከእሽታው በኋዋላ ነው የቦንብ ጥቃቱ የተፈጸመው።
ስለዚህ ከዚህ በላይ ጤፍ እንጀራ በእርጎ የሆነ የድል ርብራብ በፍጹም የለም። አይኖርም። እኔ በመንፈሳዊ ህይወት ስለማምን በዚህ
የጥርጣሬ ወለል የኤርትራ እጅ አለበት ከሚያስብል ፈጣሪ ከጥርጣሬ የጸዳ ሰማያዊ ታምር እንደሰራበት ስለማምን ግንኙነቱ ዘላቂ ስለመሆኑ፤
ልብ ለልብ ስለመሆኑ አንዳችም ጥርጣሬ የለኝም። ልቤን ከፍቼ ነው የምቀበለው። ለዚህ ነው በተደጋጋሚ እግዚአብሄር በቃሽ ብሏት አላዛሯን
ኢትዮጵያ የምለው።
ሌላው ቀርቶ ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ የልቤ የሚሉት የአንድ አገር መሪ ኣላቸው ብዬ አለምንም።
ተዚህ ቀደም ከሄሮድስ መለስ ዜናው ጋር የጫጉላ ጊዜ ፍርሻ በኋዋላ፤ አሁን ግን ንጹህ፤ ቅን፤ መልካምነት የወሰጠ፤ ፍቅርን አንጎሉ
ያደረገ፤ ሰላምን የተመሰጠበት - የሰለጠነበት - የኖረበት የሰላም ፈላስፋ ታናሽ ወንድም፤ ጓደኛም ሰጥቷቸዋል ብዬ አምናለሁኝ።
ዕድለኛም ናቸው እንደ ፈረስ የቀረ ነገር ሳይሆን ከተኖረበት የልዩነት የመቃቃር መንፈስ አሁን በተሻለ ሁኔታ በእዮራዊ ቋንቋ አዲስ ሃዲድ ተዘርግቷል ብዬ አምናለሁኝ። የጸዳ ነገር ይታዬኛል።
ይህ ለትውልድ ጥላቻን፤ መጠራጠረን ነቅሎ ፍቅርን የሚያጠግብ ዘመነ የናፍቆት መባቻ ደብረብርሃን ነው። ስለሆነም በቀጣይነት የፕ/
ኢሳያስ አፈወርቂ ዘመን የውስጥ ሰላም የሰፈነበት፤ የሳቅ እና የተስፋ ዘመን ይሆንላቸዋል ብዬ አምናለሁኝ። በአጋጣሚወም እንኳን
ደስ አለዎት ልላቸው እፈቅዳለሁኝ።
ስለሆነም የሠመራው ጉባኤ በልዑል እግዚአብሄር ረቂቅ ታምር ጥበብ፤ ባለሰብነው እና ባለቀድነው ሁኔታ ለዚህ የምሥራች ቀን ተሰንቆበት የተካሄደ በመሆኑ ልዩ ታሪካዊ ቀን ነው። በዛ ላይ አፋር የኤርትራ
ተዋሳኝ መሆኑም ሌላው ብልህ ጉዳይ ስለሆነ አፋር ወሳኝ የዕድል፤ የምሥራች በር፤ ብሩህ ዜና ተከፍቶለታል። እኔ እንደማስበው ከኤርትራ
ወደ ኢትዮጵያ የባቡር ሃዲድ የዝርገታው ስምምነት በአፋር አድርጎ እንዲመሆን ይሰማኛል። አሰብም የ ኢትዮጵያ የመሆኗ ህልም በ እልህ ሳይሆን በፍቅር፤ በ አሸናፊ እና በተሸናፊነት ሳይሆን በፍቅር ድል አድራጊነት ወደ ባዕቱ ይመለሳል ብዬ አስባለሁኝ። ከዚህ ባለፈም የኮንፈደሬሽን ዕድገት ሊያሳዩ የሚችሉ የወረቀት ሳይሆን የመንፈስ፤ የሥነ -ልቦና፤ የነፍስ ሥርዓት ጋብቻዎች ይፈጸማሉ ብዬ አልማለሆኝ። እኔ ስለ ፍቅር ተፈጥሮ እና መርሆዎቹ ህልመኛ ነኝ።
ያ ደግሞ ኤርትራንም ሆነ የሰው ዘር መገኛ
የሆነችውን ኢትዮጵያ ለማዬት ለሚፈቅዱ የዓለም ዜጎች ሁሉ ታላቅ የምሥራች ቀን ነው። እኛ በሆዳችን እምናብሰለስላቸው የቅራኔ፤ የቂም፤
የቁርሾ መከራዎች ሁሉ የፍቅርን ተፈጥሯዊ ህግጋት ለተቀኘ መፍቻው ቁልፍ ተገኝቷል ብዬ አስባለሁኝ።
ይህም ለፍቅር ተፈጥሯዊ ህግጋት አፈጻጸም ወሰን፤ ደንበር፤ የክት እና የዘወትር አለመለዬት ብሂል
ነው። ለዓይነ ጠበቦች ዘመኑ አልቆባቸዋል። ለሴራም ፖለቲካ ዘመኑ የተቃጠለ ካርቦን አድርጓቸዋል። የፍቅር ተፈጥሮ የዓለም መድህን ስለመሆኑ ለሚያመልኩት ደግሞ ታላቅ የምሥራች የመባቻ ቀናቸው
ነው።
- ክስ።
አፋር ላይ በነበረው ጉባኤ ዋንኛ ተከሳሹ የአማራ ክልል ነበር። ክልሉ የጥርስ መፋቂያ ነበር
ልክ እንደ ቤንሻጉል ጉሙዙ ስብሰባ ማለት ነው። ይህ በቀጥታ የሚሳዬው ሁለቱ ክልሎች የወያኔ ሃርነት ትግራይ የሴራ አሸከርነቱ አለበቃንም፤
ሎሌነቱ አልጠገብነውም ባዮች መሆናቸውን ነው። አማራ መሬት ላይ ቅማንት እንደ እሳት መጫሪያ ገል አድርጎ እንደ ተጠቀመበት ወያኔ፤ አፋር ላይ ደግሞ አርጎባን ነው። ቀድሞ ነገር አማራ መሬት ላይ እኮ መጠዬቅ ካለበት ብአዴን ሳይሆን የወያኔ ሃርነት ትግራይ
ነው። መሪው እሱ ነው። በትግራይ ትግርኝ መንፈስ። አህያውን ሲፈሩ መደላድሉን አሉ።
ምክንያቱም አማራ ድርጅት አልነበረውም። መሪዎቹ፤ ወሳኞቹ ፤ አራጊ ፈጣሪዎቹ እነሱው ናቸው። ብአዴን ሲያስገድለው ኖረ እንጂ ምን ሲፈይድለት ነውና። ወያኔ
ሃርነት ትግራይ የአርጎባ እና የቅማንት ጠበቃ መሆን ካሳኘው ስለምን በወረራ፤ በዘረፋ የሰረቃቸውን መንፈሶች የወልቃይት፤ የጠገዴ፤
የራያ አማራዎች ጉዳይ ስለምን አጀንዳው ሆኖ አያውቅም። እዛው ትግራይ ላይ የተጨፈለቁ አናሳ ብሄረሰቦችም አሉ። ስለ እነሱ መብት
ስለምን አይጨንቅውም፤ አይጠበውም። ዛሬ እንኳን በባህርዳሩ ጉባኤ ብዙ ቅኔዎች የተከደኑበት፤ ዘመን በሚገባ ሊፈትሸው የሚጋባ እውነቶች
ተመስጥረው ተከወነውበታል። ርትህ እንግዲህ ተጠዬቅ ይባል … ረቂቅ አመክንዮዎች። ግን ልብ ያላቸው ልብ ማለታቸው ግን አይቀሬ ነው።
አርጎባዎች ስለ እስልምና ጉዳይ አንስተዋል። እስልምናን ቀድሞ ነገር ወያኔ ሃርነት ትግራይ አይደለም
እኩል ደረጃውን ያስጠበቀው። ደርግ ነው። አፋር ራሱ በደርግ የፌድራሊዝም አደረጃጃት ራስ ገዝ ነው የነበረው። በኢትዮጵያ የመጀመሪያ
የፓርቲ አካላት ከተመሰረተብ ቦታ አፋር ግንባር ቀደሙ ነበር። እኔ በየካቲት 66 የፖለቲካ ኢንስቲቲዩት የኢትዮጵያ የታሪክ መምህሬ
ጋሼ አብዲ የአፋር ልጅ ነበር።
- እስልምእና እና አማራ።
ድምፃችን ይሰማ ብሎ የተነሳው የትኛው ክልል ነው? አማራ አይደለምን? መድፍ እዬረገጠ ራሱን
የማገደው የጎንደር እና የጎጃም አማራ አይደለምን? በአማራ ማህበረሰብ እጅግ በፍቅር የሚከወነው የጋብቻ ዓይነት ከእስልምና ጋር ያለው ነው።
እኔ እራሴ ሁለት አክስቶቼ ዳባት ከሚባል ከተማ ይኖራሉ። በቀደመው ጊዜ የወገራ አውራጃ ዋና ከተማ ነው። አንዷ የአስልምና ሃይማኖት
እምነት ተከታይ ተብዕት አግብታ፤ ሌላዋ ተዋህዶ አግብታ ወልደው ከብደው አብረው በፍቅር ይኖራሉ። አብረው አንድ ቤት ነው ያደጉት።
በመላ የአማራ ማህብረሰብ ሠርግም ሁለት ድንኳን ነው የሚጣለው። ፍሬዳም እንዲሁ። እኔን 50 ሺህ ብር አስይዘው ከእስር ያስፈቱኝ
ሸህ ሲራጅ አህመድ ወልቃይቴው ናቸው። ያን ጊዜ 50 ሺህ ብር የዛሬ ሚሊዮን ብር ምስጋን ይንሳው። በነገሬ ሁሉ የዘወትር ድዋ ይደረግልኝ
ነበር። አማራ ክልል እኮ ነው ለኦሮሞ ማህበረሰብ የተለዬ ልዩ እንክብካቤ እና የተለዬ አያያዝ ያለው ሌላ ቦታ የሚኖረው ሰፊው አማራማ
ሞት እና እንግልት፤ መፈናቀል፤ እስራት ነው ትርፉ። መጤ ነው ነው የሚባለው። በቀዬዩ እንኳን በሞት ነው ኑሮው ጠቀራ ለብሶ የሚገኘው አሁንም።
የትናንቱ ላይበቃ ዛሬ አማራን በጥርስ ይዞ መንገዳገድ ለዛውም አፋር ላይ መልካም አይሆንም። ጥያቄው የተነሳው ከ አርጎባዎች ቢሆን አፋር አስተዳደሩ ድርጅታዊ ሥራ እንደሠራበት እኔ ቅንጣት ታክል አልጠራጠርም።
በኢትዮጵያዊነት መስመር የተለዩ የሚስጢረኝነት ጸጋቸውን ተላልፈውታል። አንድ ቤተ መጸህፍት
ውስጥ ለልምምድ ገብቼ እሰራ ነበር። ከመጸሐፍ ጋር እንደ እናት ጡት አብሬ ስላደግኩኝ። እና አለቃዬ ጋር ውይይት ስናደርግ ስለ አፋር
ብዙ ጊዜ አጫውተዋለሁኝ። እና አንድ ዓመት እሄደለሁኝ ብሎኝ ያን ጊዜ የ97 ሁኔታ ስለነበር ከልክዬ አስቀርቸዋለሁኝ።
ነፍሱ እስኪጠፋ
ስለሚወደው እኔ የኢትዮጵያ ደም ዘር አለብኝ አስከ ማለት ደርሶ ስለነበር የኢትዮጵያ መጸሐፍት ከመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ ጋር ተዳብሎ አንድ
ላይ ስለነበረ ታዲያ ስለምን ራሱን የቻለ አታደረገውም ኢትዮጵያዊ ከሆንክ ብዬው በዛ ላይ ሁሉ እርምጃ ወስዷለኝ። ቤተ መጸሐፍቱ መጸሐፍቶቼን 6 ጊዜ ለሲዊዝ ብሄራዊ የኢንተግሬሽን
ጉባኤ አቅረበው መግለጫ ሰጥተው እዛው ላይ ሸጠው ገንዘቡን ሰጥተውኛል። ምን ማለት ነው ይሄ?
አፋር ላይ ያልተነሳ ፖለቲካ ማደሪያ
የለሽ ወይንም መንገድ ላይ ተቋርጦ ቀሪ ነው የሚሆነው … አፋር ውስጥ መንፈሱ የተለዬ ነው። ዛሬ ግን ያዬሁት የናፈቀኝን አፋር
አልነበረም። አፋርን አላገኘሁትም... አፋርን ሰረቄ ነው የምወደው።
- አርጎባ እና እስልምና።
„አርጎባ“ ዕምነት በሚመለከት በጣም ልክ አጥቶ ከመንጠራራት በልክ ለመራመድ ማሰብ ይገባልዋል
ባይ ነኝ። በእምነት ዘርፍም ቢሆነ የፓርላማውን ወንበር ሲታይ እኮ ምስክር ነው። የፌድሬሹንም የፓርላማውም አፈ ጉባኤ እስልማና
ሃይማኖት ተከታዮች ናቸው። ለዛውም ሁለቱም ሴቶች። እንግዲህ በ27 አመት ውስጥ አንዲት የተዋህዶ አማራ ወጣት ሴት እዛ ደረጃ የመድረስ
አቅም አልነበራትም ማለት ነው ይሄ አምክንዮ የሚነግረን።
ለምን? ወደፊትስ በማን ላይ ነው እንዲሰራ የሚፈልገው። እኔ የዶር አንባቸውንም
የአቶ ገዱ አንዳርጋቸውን መንፈስ አጥንቼዋለሁኝ። አሁንም በዛው በነበረው ይቀጥል ባዮች ናቸው። የእኔን ያህል ውስጣቸው ዘልቆ ህመሙ
አልገባቸወም። ወይንም ከጉዳዩ ጋር ተላልፈዋል። ለአማራ የፖለቲካ መሪ እንጂ የሞራል መሪነት ብቻውን ከዘር ንቀለቱ ሊያተርፈውም ሊታደገውም
አይችልም። ዛሬም አማራ ይከሰሳል? ዛሬም አማራ እንዲበቅል በተገቢው አያ ያዝ እና ጥንቃቄ ክትትል ሊደረግለት ሲገባ አንተ መኖርህን፤ ንፈስህን ለሌላው ሸልም ነው የሚደመጠው።
43 ዓመት ሙሉ በነበረው መከራ
ወሎ እና ጎንደር ነው ድቅቅ ያሉት። ደሴ ላይ እኮ ጉባኤው ዋርካ ላይ ነው የነበረው። ይሄ ሊያሳፍር የሚገባው ነገር ለጅሉ ብአዴን። ከንፍሮ ያወጣቸው የአማራ ልጆች ደግሞ ለእስር እና ለስደት ነው የተዳረጉት። በ27 ዓመቱ ደግሞ ሸዋም ጎጃም ታክለዋል በግለቱ የፖለቲካ
ፖሊሲ። ሌላው አሁን የአርጎባዋ እናት እንደሚነግሩን የእስልምና ክብር ልብስ የመልበስም የአለመልበስም ጉዳይ የባለቤቱ ጉዳይ ነው።
አማራ መሬት ላይ አልነበረም።
እኔ አይቼ አላውቅም። በሌላ በኩል አርሲ ጢቾ አውራጃ ስለሰራሁኝ ግን እዛ ነበር። ሃይማኖቱ ግን ጎንደርም እስልምና ተከታዮች አሉ፤
የራሴም ቤተሰቦችን ጨምሮ። ግን ሃደሬ ብቻ እንጂ ፊት መሸፈን አይቼ አላውቅም። ጓደኛዬም ሞሚና መሃመድ ትባል ነበር። እሷም ጭራሹን
ሃደሬም አትለብስም፤ እናቷ እኛ ከትክሻችን ላይ ነጠላ እጥፍ አድርገን አንደምንጥለው ያደርጉ ነበር። ከዚህ በተረፈ አይቼ አላውቅም።
እንግዲህ የዛሬውን አላውቅም።
አካባቢም ይወስነዋል።
ባህሉ፤ አስተዳደጉ፤ ሥነ - ልቦናው ሁሉ ይወስናዋል። አድርጉ አዳርጉ ተብሎ
አዋጅ አይወጣለትም። ሃይማኖት የስሜት፤ የመቀበል ጉዳይ ነው። አሁን አማራ ላይ ያለ አርጎባ፤ አፋር ላይ እንዳለህ ሁን ቢባል አይሆንም።
አይችለውም። ስለዚህ እንዲህ ዓይነት ዝበት ያዘበጠው ብዬና ለአስተያዬት አቅርቢያዋ ከድርጅታዊ ሥራ እና ከካድሬነት፤ ግዳጅን ከመወጣት
ውጪ ሌላ ተልዕኮ አለው። ፍሬ ያለው ነው ተብሎ ሊወስድም አይችልም። በተመሳሳይ ሁኑቴ ቤንሻንጉል ላይ የነበረው ፉክክር ከአማራ
ጋር ነበር፤ ለዛውም በተለዬ ሁኔቴ ከጎንደር ጋር ነበር ፉክክሩ። ጠላ ቤት ተክፈቶለታል ይበቃዋል ነበር። ስካርን ከፈለጉት እዛው ተነቅሎ ይተከልላቸው።
በዬአካባቢው ያሉትን ተወላጆቹን በጋብቻም ባለው ክር ተጠቅሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የሚሰራው
ቲያትር ነበር አፋር ላይ ቁልጭ ብሎ የታዬው። አርጎባዎች የተለዬ ጭቆና ደርሶብናል ከሆነ ሳጅን በረከት ስምዖንን፤ ሳጅን አዲሱ
ለገሰን፤ ኢንስፔክተር አለምንህ መኮነን እነሱን ይጠይቁ። አማራ እራሱ በራሱ መሪዎች ሳይሆን በአራጆቹ ነው 27 ዓመት የተመራው።
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መጠዬቅ የሚችሉት ከእንግዲህ በኋዋላ ስላለው ነገር ብቻ እና ብቻ ነው። ይህም ብአዴን በአዲስ መልክ የመዋቀር
ዕድል ከኖረው በስተቀር ግን ያው በተቀበረው መቃብር መኖር ነው ተያይዞ …
ለነገሩ መቃብሩ ላይ ለቆመ ሬሳ ሃሳብ ብዙም ጉዳይ ባይሆንም ምንጩ እና ተልኮው ግን ተፈልፍሎ
መቅረብ አለበት። ምክንያቱም አሁን ቀንበር ተሸክመህ ዝለቅ ስለሆነ የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና የዶር አንባቸው መኮነን የወል ዕድምታ
ሳዳምጠውም ሆነ ስመረምረውም።
ክልሉ በክልሉ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ይሁን ሲባል መዥገሮች ይፈንጩበት ከሆነ አይችሉትም ብአዴኖች። አሁን ያለውን
የአማራ የውስጥ ነበልባል እና ቁጣ። አቅሙም መንፈሱም ለቀረበው አዳልቶ አማራ መሬት ላይ ኢህአዴግ ባዶ ጆንያ እንዳሉት የደብረታቦር
ተሳታፊዎች ቀፎውን ይቀራል። የአብይን መንፈስ ለማስቀጠል በተለመደው የጅምላ ጉዞ አይሆንም። ስለምን? አማራን አማራ መምራት ስላለበት።
እዛው የሚኖሩትን ሌሎች ብሄረሰቦችንም አቅማቸውን የወከለ ቦታ ሚዛናዊነቱ ሳይዛባ።
- ኦቦ ለማ መግርሳ በተስተካካለ የ አመራር ብቃት ላይ ናቸው።
ኦህዴድ እንደ ሆነ ጥድፊያ ላይ ነው። ኦሮሞን ተጠቃሚ ለማድረግ ተግቶ እዬሰራ ነው። እነ ኦቦ
ለማ መግርሳ፤ እነ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከሰውነት ተራ ነው የወጡት። እዬባከኑ ነው። ሌት ተቀን እዬተጉ ነው። ሙሽራ ወይንም ጫጉላ ሽርሽር የቆዩ አይመስሉም። ስለዚህም ተፎካካሪዎችን
አሸንፎ ለመውጣት የሚያስችለውን አቅም ኦህዴድ ከሥር ጀምሮ የህዝብን ጥያቄ ባዳመጠ አኳያ እዬገነባ ነው። ብአዴን ግን አሁንም እነ እንቶኔ ይፈንጩብህ ከሆነ ያገኛታል። ለነገሩ
አብን እራሱ መንፈሱ ገና አልተፈተሸም። ምን ያህል ህብረ ብሄር ከሚባሉት የመሰሪ ጉዝጓዝ እንደወጣም እንደ ዳነም ገና መጠናት ያለበት
ድርጅት ነው። እራሱ ጉባኤው ስለምን የሰማያዊ ልብስ ሰለባ ለመሆን የወሰነበት መንገዱ አልገባኝም። ምክንያቱም ሰማያዊ ቀለም የሰማያዊ ፓርቲ የቀደመ መለያው ነው የኮፒ ራይትም ጉዳይ አለበት። በዛ
መንገድ በለበጣ እጀምረዋለሁ ቢል የሚሆን አይሆን።
- · የሹልከት ስለት።
አድብተው የሚጠብቁ ጮሌዎች ደግሞ አሉ። ሲገላበጡ የኖሩ። እኔ መንፈሴ የሚነግረኝ አሁን አማራ
ባለቤት አለው ብሎ ልብ ጥሎ የሚያስተኛ ጉዳይ ያለ አይመስለኝም። እንደ አልጋ ብቻ ሆኖ ጥቅጠቃው ሲበዛበት ዘብጦ የሚቀር፤ ወልቆ
የሚቀር ይመስለኛል የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው መንፈስ። አሁን ዕውቅናው ሆነ ክብክባካቤው በተጠበቀው ደረጃ ነው ለማለት አልደፍርም።
የአብይን መንፈስ ለማስቀጠል የአማራ ጉዳይ በአግባቡ መያዝ ካልተቻለ አሁንም ዳገት ነው … እራሱ
ኢህዴግ ስለመሰንበቱ እርግጠኛ የሚያደርግ ነገር የለም። ምክንያቱም አማራ ሙያ በልብን የኖረበት ነው። አሁን ጎንደር እንደ ተገለለ
ነው። የዛሬው የባህርዳር ህዝባዊ ድጋፍም በመንፈስ ልዕልና ሊፈተሹ የሚገቡ አመክንዮዎች አሉበት። ይህ ሁሉ ህዝብ ተገኝቶበት፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ በነጻነት ተገኝቶበት ምን ያህል የውስጥ መንፈስን ገዝቷል? እያንዳንዱ ስሜቱን ይጠይቅ እኔ ብርድ ብርድ ነው
ያለኝ።
ከዚህ ይልቅ እኔ የደብረታቦሩ፤ የደሴ ስብሰባ ቀልቤን መስጦታል። አንዳንድ ጊዜ ሚሊዮን ዶላር ያወጣ ልብስ እኔ መንገድ ላይ
ወድቆ ባገኘው አላነሳውም። ሰውም ቢሰጠኝ አይደንቀኝም። ብዙ ውድ የሆኑ ዕቃዎች አይማርኩኝም። ለእኔ ስሜት የቀረቡ ርካሽ ቢሆኑም እሸምታቸዋለሁኝ።
- ብአዴን እና ተስፋው።
የሠማራን ዕድምታ እያሰብኩኝ ብአዴንንም አስባለሁኝ። የአማራ መሪዎቹ ከአማራዊ መንፈስ በጣም የራቁ ስለሆኑ። የአስታራቂ፤ የሽማግሌነት ተግባርነት እንጂ
እንደ ኦቦ ለማ መግርሳ የመሪነት ሚናቸው ላይ አይደሉም። አማራውን ውስጡን ማደመጥ ሳይሆን እነሱ የያዙት በቅይጥ እና በዝንቅ ማንነት
አማራ ላይ ቀንበር ጭነው ጎብጦ እንዲቀር ነው ትልሙ። ፍላጎታቸውን አማራው ተሸክሞ ሊያሻግራቸው ይችላል ቢባል መልሱ አይችሉም ነው። ጠንከረው ለመገኘት እንዲህ ቡቃያ አልባ እሸት ቅመሱ በማይባልበት የ ኢትዮጵያ ፖለቲካ አማራ መሆንን ይጠይቃል።
የብአዴን መሪዎች የያዙት አቋም እና የሚከተሉት መሥመር ለሰማዩ ጽድቅ ቢበጃቸው እንጂ ተገፍቶ ተገፍትሮ ተገሎ ተነጥሎ መሬት አልባ ሆኖ አሁንም
በድርብ እና በረቂቅ ሴራ ታስሮ ለሚኖረው አማራ የሚሆነው አይደለም።
በዬቦታው ላለው ጥያቄ መልስ ለመሰጠት የሚደረገው ጥረት እና አማራ መሬት ላይ ያለውን የታገሱን
የፋታ ጥያቄ እና አቦ ለማ መግርሳ ተሻግረው ከሄዱበት ምጥቀት ጋር ማወዳደር ቀርቶ ጥግ ለጥግ ማስቀመጥ አይቻልም። ቤንሻንጉል፤
አፋር ደግሞ የወያኔ ዕድሜ እንዲረዝም ሱባኤ ላይ ናቸው።
አማራም በዚህ የሽግግር ወቅት በወጀብ እና በብዙ ቅራኔዎች በተዋጡ ንጠቶች ማህል አሻጋሪ ድልድይ
መሆን ሳይሆን የሚገባው የራሱን የመብት ጥያቄ አጉልቶ በፖለቲካ የእኩል
ተሳታፊነቱን ማረጋገጥ አለበት። ብቃት፤ አቅም፤ አማራ የለውም እንዴ? ይሄማ ውጪ አገር እንደሚገኙት ሚዲያዎች ተሆነ። አማራ ያዋጣል
የኦሮሞ የትግራይ ድምጽ ተከፍቶ ሥነ - ልቦናው ይጠበቅለታል። የእነሱም
መኖረ መልካም ነው። ነገር ግን ፍዳውን የከፈለው አማራ ድምጽ አልባ ነው። አማራ ይሞታል ሌሎች ይደራደሩበታል። ይህ ቀልድ መቆም
አለበት። የአፋሩ ጉባኤም የሚነግረን ይሄውን ነው።
እምነት በሚመለከት ተዋህዶ በልሙጥነት ደረጃ ነው ያለው። ተዋህዶስ እስከ መቼ ነው አፈር ገፊ
ሆኖ የሚቀጥለው? ሚዛኑን የጠበቀ ሁኔታ አይደለም የማዬው። ይህ ዛሬ በአብይ ካቢኔ የመጣ አይደለም። 27 ዓመት በፖለሲ ደረጃ የተሰራው
አሁን ሰው አምጡ ሲባል አማራም ኦርቶዶክስ ተዋህዶም ብቁ ሰው ማግኘት አልተቻለም። አልተሠራበትማ። ለቦታው ለሃላፊነት የሚመጥን ብቃት በአንድ ቀን ተውልዶ
አያፈራም። ጥቂት አማራዎች በህብረ ብሄር ፓርቲዎች ገቡ፤ እነሱም በሌሎች ከመጨፍለቅ አልዳኑም። ውጩ አገርም እንደዚህው ነው። እነሱም ቢሆኑም አሁን ጨፍልቁን ባዬች ናቸው። ጋና ከእንቅልፋቸው አልነቁም። እኔ እችላለሁ፤ አደርገዋለሁ የለም። የሌላ ታሪክ ዝና እና አቅም ገንቢነት ብቻ ነው የሚደላቸው።
አቅም
ያላቸው ወጥተው ራሳቸውንም ማህበረሰባቸውን እንዳያድኑ አሁንም አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሆነ ዶር አንባቸው መኮነን የሞራል መምህር ከመሆን በዘለለ
አማራ ሆነው ስለ አማራ መብቅል እና ተፎካካሪ ሆኖ መወጣት ሳይሆን ከዚህ ዘር ከዚህ ዘር መጣ አትበሉ እያሉ ነው የሚያሰተምሩት።
ይህን ያመጣው የሚመሩበት የቋንቋ ፌድራለዚም እንጂ የአማራ ተጋድሎ አይደለም። "የፈሩት ይደርሳል
የናቁት ይወርሳል" እንዳይሆን ወደ ራሳቸው የመመለስ የአቅም ምጣኔ በተፈለገው ሁኔታ አይደለም። ልሙጥ ነው። ለውጥ ለማምጣት መታገል እና በለውጡ
የወከላቸውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድርግ በጣም የተራራቁ ፋክቶች ናቸው። ይሄ ጉዳይ ኦቦ ለማ መግርሳንም ይመለከታል የቀረበ አማራር
እና እግዛ እንዲያደርጉበት።
የብአዴን ዕጣ ፈንታ ከተሰበረ ኦህዴድም በቻውን መውጣት አይችልም። አሁን የቄሮ ተጋድሎ ታቅፏል። ምን
እናድርግልህ፤ ምን እንሁንልህ እዬተባለ ነው። የአማራ ተጋድሎ ሞት እስራት እንግልት ደግሞ የውሽማ ሞት ሆኗል። ስለዚህ ይህን
የቤት ሥራ ኦቦ ለማ መግርሳ መሥራት ግድ ይላቸዋል። በውጭም የደገፋቸው በሚታየውም ሆነ በማይታዬውም ለሎቢ ሥራ የተጋው የማንፌስቶ ማህብርተኛ ያልሆነው አማራ እንጂ
የራሳቸው ሰዎች እንኳን እንዳልሆኑ ልባቸው ያውቀዋል።
እኔ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የፈለጉትን ቢናገሩ ይገባቸዋል። እሳቸው ፓን አፍሪካኒስትም ናቸው።
የአገር ብሄራዊ መሪ ናቸው። አኩል የሆነ አማራር መስጠት ይገባቸዋል። እነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ግን የአማራ መሪ ሆነው ሌላ ቢመራህ
ለጥ ሰጥ ብለህ ተገዛ ከሆነ አያስኬድም፤ ያበጠውን፤ ተዳፍኖ ያለውን
እሳተ ጎመራ ከመፈንዳት አያድነውም። አባ ዝምታ ከመናገር በላይ ነው። ይህን ልብ ያለው የለም። ለዚህ ለኢህአድግ መቀጠል
የአማራ ተጋድሎ መሠረት ሆኖ ግን እስከዚች ደቂቃ ድርስ ተገላይ ነው። ጀግኖቻችንም እንዲሁ።
ሰማዕታቱም እንዲሁ። ይህ እሰከ ምን
ያዘልቃል? ዛሬም ሸዋም ዝምታውን ሰብሯል። የደብርብርሃኑ ሰልፍ የዋዛ አልነበረም። የአማራ ሊሂቃን በፍጥነት ወደ ራሳቸው መመለስ
አለባቸው። አማራ ለሌላው መኖር አለበት ነው ትልሙ። ይህ ግን ጅልነት ነው። አማራ መጀመሪያ ራሱን ማኖሩን ማረጋገጥ አለበት። ከአረገረገ አፋፍ ላይ ተንጠልጥሎ ለሌለው እኔን እግብራለሁ ማለት ጅልነት ነው። ማን የሚያደርገውን? ሁሉም የራሱን ጓዳ ነው እያጸዳ
ያለው። ሁሉም ክልል ከአማራ በስተቀር የራሱን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ነው እዬተጋ ያለው። ያለፈው ላይበቃ አሁን ደግሞ እንዲህ እና እንዲያ … ርትህ?
- የሠመራ ዕድምታ።
በጥያቄ አቀራረብ ከሁሉም ክልሎች ጋንቤላ ላይ ድርጁ፤ ሥልጡን፤ ሁለገብ፤ ሁልቀፍ፤ ዓለም ዐቀፍ
ጥያቄዎች የቀረቡበት ነበር። አማራ ክልል ላይ ትግራይ ላይ ከተሳታፊዎች በተነሳው የጥያቄ እና በተሰጠው መልስ ሁኔታ ባልበረደ ንዴት
የተከወነ ስለነበረ ብዙ መጠበቅ ግብዝነት ይሆንብኛል። የማህበራዊ ድህረ ገጹ ወጀብ እራሱ አስፈሪ ነበር። ማህበራዊ ሚዲያ ቀውጢጦርነት ላይ ነው የነበረው። በሌላ ቦታ የተካሄዱት ህዝባዊ የአዳራሽ ጉባኤዎች ግን በረጋ እና በሰከነ ወቅት ስለሆነ ትንሽ በሰል ያለ፤ ከግብታዊነት
የጸዳ መሰረታዊ ነገሮችን ጠብቄ ነበር። ግን የልቤ የምለው ክልል ጋንቤላ ብቻ ነው። በሥርዓት እና በንግግር ጥበብ ደረጃውን የጠበቀው
የአዋሳው የአቀባባል ተደሞ ጥሩ ነበር።
በመልስ ደረጃ አቅጣጫ በማመላከት፤ የፖለሲ ሃሳቦች ፍንጭ በመስጠት ደግሞ አፋር ላይ ነው በጣም
የረቀቁ አመክንዮዎች እርስ በርሳቸው ተዋደው አይቻለሁኝ። ስለዚህም ነው አፈርን እንደ ማዕከል አድርጌ አቅጣዎችን ደረጃ በደረጃ
ማንሳት የምሻው ….
- ውዶቼ
የኔዎቹ ይቀጥላል … ተከታታይ እንዲሆንላችሁ አብረን አበረን ብያለሁኝ።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
እልፍ ነን እና እልፍነታችነን እልፍ እናድርገው!
ኑረሉልኝ መልካሞቹ። መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ