እግዚአብሄር ደስ አለው። ሐሤትም አደረገ። ተስፋን አፋፋ። አዲስ #የሰላም #ግሎባል #ካሪክለም ተነደፈ!
"የሰው ልጅ መንገድን ያዘጋጃል
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"
(ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)

#ቀን ሲመረቅ ………
አዲስ #ቅን ምዕራፍ -- ይታወጃል!
አዲስ ብሩህ #ዘመን --- ያጫል!
አዲስ #ቀና ጎዳና ---ይቀይሳል!
አዲስ የህይወት በር ከፋች #ድንቅነትን ያጎናጽፋል። ተመስገን። አሜን ተመስገን።
የተከበሩ ፕሬዚዳንት ዶናል ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዕፁብ የሆነ ንድፋቸው በግራ ቀኙ ተደራዳሪወች የመጀመሪያው ምዕራፍ ይሁንታን ተቀዳጄ። ተመስገን። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በሰላም ዙሪያ ሊቀ - ትጉኃን ተግባር ተባረኩ። ተመረቁ! የጋዛ እና የእስራኤል ውጊያ ፍጥጫን መልክ ሊያስዝ የሚችል የመጀመሪያ ምዕራፍ ስምምነት በሁለቱ ተደራዳሪወች ዘንድ ተፈረመ። እግዚአብሄርም #ደስ አለው። እኛም ሐሤት አደረግን። ለሰው ልጅ ሰላም ኦክስጅኑ ነው። ሰላም ትንፋሽ ነው። ሰላም ትርታ ነው። ሰላም ለሰው ልጅ ለተፈጥሮ የመኖራቸው ሚስጢር ነው።
አይደለም አንድ ድርብርብ #ኖቤል ቢሸለሙ የተከበሩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ፕሬዚዳንት ትራንፕ #ይገባቸዋል! ፕሬዚዳንቱ #ከተደጋጋሚ ሞት የተረፋበት #ሚስጢር #አዲስ #መጸሐፍ ነው ይህ ድንቅ፥ ፍጹም ድንቅ #የምሥራች #ቀን።
ዕንባ ይቆማል!
የሰው ልጅ ደም መፍሰስ ይቆማል!
የፍርኃት ዘመን ያከትማል!
ልጆች ያለ ሥጋት እየሳቁ ያድጋሉ።
መፈናቀል ቀጥ ይላል።
ልጆች በሳቅ በቀያቸው ይቧርቃሉ።
ራህብ፤ ቸነፈር፤ መሰደድ፤ አገር አልባነት፤ መከላተም ይቀንሳል።
አትኩሮት ወደ ቀደመ ክብሩ ይመለሳል።
ዜጋ የእኔ የሚለው ብትን አፈር ይኖረዋል። #ማንነትም ይደላዋል!
ይህ የምሥራች ለመላ ዓለም ጭምር ነው። እንኳን ደስ አላችሁ የእስራኤል እና የጋዛ ሕዝቦች። ስለ ሰላም ግድ የሚላችሁ የቤተ - ተፈጥሮ ቤተሰቦች ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ። መጨረሻውን ልዑል እግዚአብሄር // አላህ ያሳምረው። አሜን። የተከበሩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናል ትራንፕም ጥረተወት በመሳካቱ እንኳን ደስ አለወት። በዚህ መስመር የራሺያ እና የዩክሬን ጦርነት ያከትም ዘንድ ፈጣሪ ይርዳzወት አሜን። ይህ ዕድል ለኢትዮጵያችንም ይሁንልን። አሜን። የሱዳን ህዝብንም በቃችሁ ይበላቸው አምላካችን /// አላኃችን። አሜን። ለቀጣይ ትውልድ ሰላም ውርሱ ይሁን። አሜን። ሥልጣኔ በሰላም ወደ ፊት ይገስግስ።
ይህ ቀን #የጸደቀ ነው።
ይህ ቀን የተባረከ ቀን ነው።
ይህ ቀን ዕንባ #አባሽ ቀን ነው።
ይህ ቀን የአይዟችሁም ቀን ነው።
ይህ ልዩ ቀን #አጽናኝም ነው።
ይህ ቀን መኖርን ለማስቀጠል የተመረጠ ቀን ነው።
የስንት ዓመት ውጭ ነፍስ፤ ግቢ ነፍስ መከራ እንዲህ በአለ …… በብሥራት ዜና ……
ተስፋን - በሚያፋፋ፤
ተስፋን - በሚያስፈነድቅ፤
ተስፋን - በሚያስከብር ባለግርማ ሞገስ ዕለት በይሁንታ ታተመ። ተመስገን። ይህ ከደስታ በላይ #ሐሤት ነው። ይህ ቀን ልዩ ሥልጣኔን ለማስቀጠል የሚችል #የሽልማት ቀን። ይህ ቀን የሰውን ልጅ በህይወት መኖር ያከበረ፤ #ያስከበረ ቀን ነው። መሪ ማለት ለሰላም የሚተጋ የህዝብ ጠበቃ ማለት ነው። እንሆ በዘመናችን ተፈጽሞ አየነው። የመጀመሪያው መቅድሙ አምሯል። ፍፃሜውም #ይሰምራል። እግዚአብሄር ለሰላም ለሚተጉት አይለያቸውምና።
"የሚያጽናኑ ብጹዓን ናቸው።"
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/10/2025
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ