#ሰላም #ይመረቅልን። አሜን። #ይቅናን። አሜን።
የዛሬ ሁለት ዓመት ለእኛ የፆመ ጽጌ በር ዕለት መስከረም 26፣ በአውሮፓውያኑ #ጥቅምት ፯ ቀን ማት እስራኤል ላይ በጋዛ አጥቂወች ተፈጸመ።
ያን ዕለት ተከትሎ በግራ ቀኙ ስንት ህይወት፣ ስንት መኖር፣ ስንት ተስፋ #አረረ? መፈጠር ተኮማተረ። ደም ፈሰሰ። ዕንባ ፈሰሰ።
ዛሬ በዚህች #ቅጽበት ሁለቱ በአገረ ግብጽ በተከበሩ ፕሬዚዳንት ትራፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት አነሳሽነት ድርድር ላይ ናቸው። ይቅናቸው። አሜን።
የእስራኤልን አገርነትንም ፍልስጤማውያን እና አጋሮቻቸው #ሊቀበሉት ይገባል።
በመጨረሻም፣ ስምምነቱ ያለ #እንከን ይፈጸም ዘንድ ምኞቴ ነው።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፈጠርልኝ።" አሜን።
ይህ የጭስ ፎቶ አንድ ልጅ ሰላምን እየለመነ ይመስለኛል። በወቅቱ ዜና እያዳመጥኩ የቀረጽኩት ነው። እግዚአብሄር አምላክ፣ አላህ ለዓለማችን #ሰላም #ይመርቅልን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/10/2025
በቃ ጦርነት።
በቃ መገዳደል።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ