"ከችግር ማትረፍ" ከልቤ የገባ አገላለጽ።

እንኳን ደህና መጡልኝ።

„ከችግር ማትረፍ“

„ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሳ ነው፤
ርህራኄው አያልቅምና።“ ሰቆቃው ኤርምያስ ፫ ቁጥር ፳፪
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
 01.02.2019

ከእመ ዝምታ ኪሲዊዝሻ።

 


ቅኖቹ አዱኛዎቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ የኢትዮጵያ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠ/ሚር አብይ አህመድ ላቀረቡት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ አዳመጥኩኝ። በዚህ ዙሪያ በቻልኩት መጠን ነጠል አድርጌ የማያቸው ቁም ነገሮች ይኖሩኛል። እርዕሱን ሐረግ አጥቼለት የነበረው ያስቸገረኝ አመክንዮ ስለነበር በዚህ አጋጣሚ ስላገኘሁ ደስ እያለኝ መንበሩ ላይ ጉብ አድርጌዋለሁኝ። አገላለጹ ዩሳቸው ነው። ውስጤን ስላገኙልኝም አመሰግናቸዋለሁኝ።

„ከችግር ማትረፍ“ ወርቅ አገላለጽ ነው። በዚህ ጫናው ባዬለበት ሁሉም መዋቅራዊ ጠገግ ሳይንድ፤ የነበረው መዋቀር ባለመፈረሱ የሚመጣውን ቀውስ ለመሸከም በወሰነ አቅም፤  ሳቦታጅ እና የሴራው መረብ እንዳለ ግን በስልት እና በጥበብ አዲስ ሥርዓት ለማዋለድ በሚካሄደው ግብግብ ውስጥ ጫና ሊፈጥሩ ይችላሉ የሚባሉ ችግሮችን በመጎርጎር በግነትም ይሁን ነገሮችን በማጣደፍ የሚታዩ የትርምስ ዓውዶችን በመፍጠር እረገድ ያለውን ማነኮር የገለጹበት መንገድ እኔ ወድጀዋለሁኝ። „ከችግር ማትረፍ“

በምልሰት የ50 ዓመት የኢትዮጵያ የፖለተካ ጉዞ ስንገመግመው ችግር አምራች፤ ትውልድ አባካኝ፤ መዋዕለ መንፈስ አባካኝ ነበር። በቅሎ ተሳክቶ ጸድቆ አቅም ማዬት ሃራም ነበር። ይህም ብቻ አይደለም የሂደቱ ተዋናይ ካፒቴኑ ራሱ ሁለንትናዊ አቅሙም ድርጁ አልነበረም። ዘመን የሚሰጠውም የሚነሳውም ነገር እንደ ተጠበቀ ሆኖ። ዛሬ ዲጂታል ዓለም ላይ ነው ያለነው። በፊት ይህ አልነበረም። የየዘመኑ ባህሪ ተለዋዋጭ ነውም። በዛው ልክ ዘመኑን መጥኖ መገኘት ደግሞ የልባሞች አብይ ጉዳይ ነው። 

ብቻ መያዣ፤ ማመካኛ፤ ሳቢያ መፍጠሪያ ያው መፈለግ ብቻ ሳይሆን መመኘት እንደ አንድ የትግል ስልት የተያዘ ነው። የነፃነት እርበኞች መታፈን፤ መታሰር ዛሬ ላይ የለም። ስለዚህ ስስ ቦታዎችን እዬፈለጉ የመንፈስ ሰላምን ለማፈራቀቅ የሚደረገው ስልታዊ ጉዞ ቃላት አጥቼለት ነበር። ዛሬ አገላገሉኝ ጠ/ሚር አብይ አህመድ። „ከችግር ማትረፍ“ አሁን ያለው ሥርዓት መምራት፤ ማስተዳደር፤ ማቀናጀት አልታቸለውም በማለት የዓለምን ቀልብ ፊቱን እንዲያዞር ይፈለጋል። 

ችግርን እንደ ዳንቴል በእጅ ከመሥራት ጀምሮ ቁስል እዬቀራረፉ የበለጠ በማድማት አቅልን ለመቀማት መሟሟት። ይህን ነው ዛሬ ፍርጥ አድርገው የተናገሩት።

ልጽፋውም ቢባል፤ ልተቸውም ቢባል፤ ልገምግመውም ቢባል ብዙ አዎንታዊ ነገር ነው በዚህ በ9 ወራት ውስጥ የተከወነው። ከአቅም በላይ ነው ሁሉ ነገር የሆነው። ዕለት ዕለትም ቢሠራ አንዱን ነገር ነጥሎ ለማንሳት ካልሆነ በሰተቀር ራሱ በአንዱ ነገር ላይ ያለውን ጅረት ይሁን ዘርፈ፤ ዘርፍ ይሁን ቅርንጫፍ ፈጽሞ ውስጡን ገብቼ ልበልትው ቢባል 24 ሰዓት ቀን እና ሌት ቢሰራ አይቻልም።

ምክንያቱም ተያያዥ፤ ተወራራሽ የሆኑ ነገሮች ብቻ ሳይሆን ተነጠላዊ የሆኑ፤ ፈጽሞ ያልተለመዱ ተግባራት ሁሉ በዬሰዓቱ፤ በዬሰከንዱ ይከወናሉ። እነዛን እንደ ሰው ሆነን መፈተሽ አልቻልነም ከብረት አልተሰራነም እና። ሠሪው አድራጊው ግን ያደርገዋል። በቃሉ ልክ 7 ቀን እሠራለሁ አለ እሱ 7 ቀን ይሰራል። 7ሲባዛ በ20 ሰዓት እኛ 7 ሰዓት ሰርተን 8 ሰ ዓት ተኝተን የሚሆን አልሆነም። ሁልጊዜም እንደምናገረው የትጋቱ ልክ ስላልተመጣጠን ውጦናል። አንዲት ሥንኝ 10 /15 ዓመታት እንደብርቅ፤  እንደ ጉድ ስንደግማት ስንሰልሳት ኑረን ዛሬ በዬእለቱ እሸት በጓሮ ሲሆን መቀናጣት አልፎ አልፎም ቅልጣንም ያሰኘናል። 

በዚህ ማህል ነው እንግዲህ ጉድፍ እዬተፈለገ ሌላ የሃሳብ ብነት፤ ሌላ ሃሳብ ወጥ አቅጣጫ እንዳይዝ የተለመደው የማሻከር ተግባርን፤ የማራወጥ ተግባር የሚከወነው። በዛ ላይ መሪው ሰው መሆኑንም ሁሉ ይዘነጋል። ይህ ብቻ ሳይሆን ተግባሩ ባለደገች አገር ኢትዮጵያ ላይ መሆኑ ይረሳል። ይህም ብቻ አይደለም በሴራ ፖለቲካ 50 ዓመት፤ በአድማ ፖለቲካ ከራስ ተሰማ ናደው ጀምሮ ሲቆጠር ምን ያህል ካሬሜትር በምን ያህል ርዝምት ብሎ ማሰቡም ለስሌት ይቸግራል።

የሆነ ሆኖ ተቺው እስኪ እንይህ ቢባል እራሱን መስታውት አስቀምጦ ቢመረምረው ሆነ ቢፈትሸው የማይችለውን ተችሎ ሲታይ ግን ማጣጣያ ማቀናነሻ እየፈለጉ የተማከለ ሃሳብን ብርበራ የተገባ አለመሆኑን ነው በዚህ ገለጣቸው እኔ የተረዳሁት። 

የሚገርመው ነገር ግን ሰው ልብ ገዝቶ የእጬጌው ሂደትን ሲሳይ ጠንቅቆ አውቆ አሁንም መንፈሱን ከመንፈሱ ጋር አዋዶ መገኘቱ በራሱ አንድ ድል ነው ለእኔ። ማለት ለውጡን ለማድመጥ ሁሉም አደቡ ሙሉ ሆኖ ነው እኔ የማዬው።

ስለዚህ የግርግር የሥራ ማስኬጃ ተብሎ በስልት የተያዘው „ከችግር በማትረፍ ዕቅድ“ ለማሳካት በተሟላ መልኩ አልተቻለም። በለፈው በብሄራዊ ቲያትር ከማህበረ ጥበብ ቤተኞች ጋር ለመታደም በድንገት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሲገኙ የነበረው ፍቅር አሁንም እንዳለ መሆኑን ለመገንዘብ ችያለሁኝ። ይህ ማለት ማህበራዊ ንቃተ ህሊና የህዝቡ ከሚታሰበው በላይ ብስለት እንዳለው መረዳት ይቻላል። ህዝብ ሚዛኑን የጠበቀ የማስተዋል አቅም እንዳለው ማስተዋል ይችላል። አዲስ የሁሉም መንፈስ አድባር ናት እና። አዲስ ላይ ሁሉም በ ዓይነት ስለሚገኝ ሬሽውን ስናወጣው ደልደል ያለ ግብረ ምላሽ  ይሰጠናል።

ለዚህ ነው እኔ በ2008 እ.ኢ.አ ቁሞ የሚጠብቅ ስታግናት የሆነ ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ወይንም አመክንዮ የለም ብዬ የጻፍኩት። መሆን ያለበት፤ መደረግ ያለበት ግን ሲሆን ሲሆን ከህዝብ ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ቀደም ብሎ መገኘት ይገባ ነበር። በስተቀር አብሮ ለመራመድ ካልተቻለ ወደፊትም መንጠባጠብ አይቀሬ ይሆናል።

ይህም ስለመሆኑ ነው በዚህ ሁሉ ፈተና እና ችግር ማህልም የችግሩም የፈተናውም አፈጣጠር እና የመፍትሄ ምንጩን ህዝብ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ የመሪነት ጥበቡን ለማድመጥ ሆነ እውቅና ለመስጠት አቅሙ ሙሉ ሆኖ የሚገኘው። እውነት ለመናገር የብዙሃኑ ማህበራዊ ንቃተ ህሊናው የጉዞውን አቅጣጫ ሚዛን ላይ ለማስቀመጥ አልተቸገረም። ይህም የሆነው የአማራር ክህሎት ልቅና እና ጥበብ በልጦ ስለተገኜ ነው። ህዝብ ሚዛኑ ያለው ከህሊናው ነው። ማንዘርዘሪያውም ከልቡ።

/ / አብይ አህመድ በብሄራዊ ትያትር በተዘጋጀው የኪነጥበብና ምሽት መድረክ ላይ የታደሙ ሰዎች አስተያየት

የሁሉም መንፈስ ማረፊያ በሆነችው አዲስዬ ለዛውም የሥነ - ጥበብ ቤተኞች ያን ያህል ፍቅርን በገፍ ለመሪያቸው ለአቋጣሪያቸው የለገሡት ድንቅ ነገር የሚነግረን ህዝብ በረጋ መንፈስ ላይ ስለመሆኑ ከችግር ለማትረፍ“ ለሚሹት ደግሞ ኪሳራ ላይ ስክነት አልቦሽ መረብ ላይ መቆማቸውን ነው የሚያመለክተው። 

የዶር አብይ አህመድ የሥነ - ጥበብ አቋጣሪነቱ ቢሆንም የዛሬ አይደለም። እኔ በ20.12.2017  ጊዜ ጽፌው ነበር። መንፈሱ እራሱም ቅኔኛ ቤተኛ ስለሆነ።

የእኛ አብይ የሥነ ጥበባት ጧፍ - ክፍል 5

በመጨረሻ የምለው እኔ ግድፈት መኖሩ፤ ችግር መኖሩ በአዲሱ የተስፋ አመራር ውስጥ ሰውኛ ነው። አመራሩ ሮበትኛ ስላልሆነ። ነገር ግን ከኖርንበት ዘመን ጋር ብቻ ሳይሆን አለን ከምንለው የፖለቲካ ሊሂቃን አቅም ጋር ሆነ ከአለምነው ስኬት ጋር ሲነፃፀር ለእኔ ከአቻነት ከጠበቅነው በላይ ሆኖ ነው የማዬው።

ዛሬ ከአንዲት ጋዜጠኛ ጋር ጥዋት ሳወራ ነበር በስልክ። እናም በዚህ ዘመን ቁልፍ ቦታ የያዙት ሴቶች ብዛት ስነግራት "እንዴት" ብሎ አለችኝ። ምክንያቱም እሷ የምታውቀው እኔ የኢትዮጵያን መንግሥት አብዝቸ ስተች ስወቅስ ነው። ጸጋዬ ራዲዮኔም ለዛ የተፈጠረ መሆኑን ታውቃለች። አንድም የተሠረ ጋዜጠኛ የለም፤ አንድም በፖለቲካ አስተሳሰቡ የታሠረ የለም በማለት የሴቶችን የፖለቲካ አቅም ዕውቅና  መታወጁን ስነግራት ግርም ነው ያላት።

እናም ፎቷቸውን እና ጥቂት መረጃዎችን አብሬ ጨምሬ ላኩለት ለ2019 የማርች 8ቀን ምን አለሽ ከእጅሽ ልትለኝ ስትደውል ስለ ኢትዮጵያ ሴቶች አዲስ ዘመን ብሥራት ነገርኳት። በአጀንዳ እንወያይበታለን ብላኛለች እኔ ባለመቻል ባልገኝም እነሱ ግን ሥራዬ ብለው ይወያዩበታል በቀጣዩ ሳምንት። 

የኢትዮጵያ ሴቶች ጉዳይ በራሱ የኮፐን ሀገን ተጋድሎ ወደ ድል የቀዬረ እንደገና የመወለድ ያህል ነው እንኳንስ ሌላው። ስንቱ ይዘርዘር … ? ክስተት ነው። ለዛውም አንድ ጊዜ ብቻ የሚከሰት።

/ / አብይ ከህዝብ ተወካዮች ምክ ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ- ክፍል 1

/ / አብይ ከህዝብ ተወካዮች ምክ ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ- ክፍል 2

ጠቅላይ ሚኒስትር / አብይ አህመድ በፀጥታ ጉዳይ ላይ የሰጡት ማብራሪያ

ጠቅላይ ሚኒስትር / አብይ አህመድ በኢኮኖሚ ጉዳይ ላይ የሰጡት ማብራሪያ


https://www.youtube.com/watch?v=USuXhJjPlL8


/ / አብይ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ- ክፍል 1

 

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

 


የኔወቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።