የአካዳሚ ነፃነት የትውልድ አውንታዊ ብቅል ነው!

እንኳን ደህና መጡልኝ

ረት።
„የፃድቃን መንገድ ቅን ናት፤
አንተ ቅን የሆንህ የፃድቅናንን መንገድ ታቃናለህ።“
ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፭ ቁጥር ፯
ከሥርጉተ© ሥላሴ
Seregute©Selassie
14.01.2019
ከእመ ዝምታ - ከሲዊዘርላንድ።


·       ፍታ።

እንዴት አመሻችሁ ውዶቼ ደህና ናችሁ ወይ? ይህቺ እንደነፍሴ የምወዳት አገር እምዝምታ ሲዊዝሻ ጸጥታውን እዬመገበችኝ ነፍሴን ታፍነሽንሸኛለች። እኔ ግርግር ጩኽት - ሁካታ-  የአገር ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አልፈቅደውም /ሰላማዊ ስልፉ/። ድምጽ የባዘበት ቦታ ይጨንቀኛል።

አንድም ከቤቴ ድምጹ ከፍ ብሎ የሚሰማ ነገር የለም። እቃ ሲታጠብ በጸጥታ፤ በር ሲከፈትም ሲዘጋም በዝግታ ነው። ራሱ ጎረቤቶቼ ስለመኖሬ ወይንም ስላለመኖሬ የሚያውቁት ምንም ነገር የለም። ጸጥ ረጭ። እናላችሁ ሲዊዚሻን ሳስባት ለእኔ ተብላ የተፈጠረች ይመስለኛል። አብሶ እኔ ያለሁበት ቪኒቲ። ቪንቲ የቁልምጥ ስሙ ነው። ከዚህ ከተማ የተፈጠሩትም የገጠሙኝ ሁሉ ቤተሰብዐው ስብዕና ያላቸው ናቸው። ይህችን እንደ ወግ ቢጤ ካደርኩኝ ስለዛሬው ቁም ነገር ልንገራችሁ … ትውልድ።

·       ትውልድ።

ትንተና የለውም እንዲሁ በመደዴው ስሄድበት ግን ትውልድ በመኖር ውስጥ ያለ የአገር መኖር ማለት ነው። አገር ለማኖር ደግሞ የትውልድ መኖር ብቻውን በቂ ነው ሲባል ጥማድ በሬ ገዝቶ ማሳ የሌለው ገበሬ ይሆናል።

እና የትውልዱ መኖር መበራከት ብቻውን አገርን የማስቀጥል አቅም ሊኖረው አይችለም። ማሳው በበጎ በፈቃደኝነት፤ በባለቤትንት፤ በታማኝነት፤ በምክንያታዊነት መታነጽ ካልቻለ።
ለዚህ ደግሞ አራት ተቋማት ወሳኝ ናቸው።

 አንደኛው ቤተሰብ ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች ናቸው + ሁለተኛው የዕምነት ተቋማት + ሦስተኛ ት/ቤቶች + አራተኛ ደግሞ ማህበረሰቡ ነው= አገር።

ባለፈው አንድ ጉዳይ አንስቼ ነበር ስለመምህራን ማህበር በነፃነት መደራጀት እና መንቀሳቀስ መቻል በርካታ ጠቀሜታዎችን የተብራራ ጹሑፍ ጽፌ ነበር። አብሶ ከማውዕለ ህፃናት ጀምሮ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ መምህራን መሠረት ስለመሆናቸውም አያይዤ ወፍ አውጥቶት በቅርቡ ጠ/ሚር አብይ አህመደም ልዩ ትኩረት ሰጥተውበት አይቻለሁኝ። ደስም ብሎኛልም።

 በቅንነት ውስጥ ያለው ሐዴድ ልብ አምላክ ንጉሥ ዳዊትን ያሰኘው ይኸው ነውና። ቅኖች በምንም በምንም ሁኔታ የሚያገናኘቸው መስመር ይኖራል። "ቸር ተመኝ ቸር" እንድታገኝም ከዚኸው ብሂል የተቀዳ ይመስለኛል። ቸር ተመኘሁ በቂ አትኩሮትን አዬሁኝ። በሌላም አጅንዳ ይህንኑ ሃሳቤን የገቢዎችን የማሰባሰብ ብሄራዊ ዘመቻን አስመልክቶም በነበረው አገራዊ ጉባኤ ላይ ነጥቡን አጠናክሬ አንስቼ ነበር።

·       ሃ ያልነካው ነጥቤ።

ዛሬ ተነስቶ የማያውቅ ነገር ነው ማንሳት የምሻው። መቼም አገር መሪም መንግሥትም አላት ብለው ከሚያምኑት ወገኖች እንዷ ስለሆንኩኝ ያዳምጠኛል አሁን ያለው  የኢትዮጵያ መንግሥት ብዬ ስላማምንም ዛሬን በአንድ ቁምነገር ላስብው ብዬ አሰብኩኝ።
የትውልዱ መባከን በፖለቲካ ንድፈሃሳባዊ መከራ መሆኑን ስንለው፤ ስንለው፤ ስንለው ባጅተንበታል። ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለይ በግራ ፖለቲካ ፍልስፍና መከራ ሌላም ፍዳ አለ ትውልድን በቅጡ ለመግራት ሃላፊነት እና ተጠያቂነትን አጉልቶ እንዳይቀጥል የሚያደርግ ኩፍኝ።

ምን? የአካዳሚ ነፃነት መፈግፈግ። የአካዳሚ ነፃነት መታጣት ትውልዱን በመገንባት፤ በማነጽ፤ በመምራት እረገድ ረግረግ መተንፈሻ ቧንቧው እንዲሆን አድርጎታል። የአገርም ዕድገት ዶክኮበታል። በሶሻሊዝም ፍልስፍና አንድ አውራ ፓርቲ ብቻ ይኖራል። የዛ አውራ ፓርቲ ፕሮግራም ተፈፃሚ የሚሆነው በጨለማው ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ነው። ከላይ ወደ ታች በሚለቀቅ የሚግ ቦንብ።

ከታች ወደላይ የሚመጣ አካል የሚባለው ቧልት ነው። ከላይ ወደታች የሚመጣው በድርጅታዊ ሥራ ነው። እክሌን ምረጥ ተብሎ ይነገራል፤ በሙሉ ድምጽ አጽድቅ ተብሎ መመሪያ ይሰጣል፤ አንተ በዚህ ጉዳይ አንቺ በዚህ ጉዳይ አስተያዬት ስጡ ተብሎ ይነገራል። ስብበሳባ ሲገባ ባለቀ ጉዳይ ላይ ወንበር አሙቆ የተባለውን ተናግሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቆ መለያዬት ነው።

ካለተርጓሚ አሁን ባለው መንገድ ከቀጠለ ለውጡ የተገላገልንበት መንገድ ፍንትው ብሎ ይታዬኛል። ከ7 ሚሊዮን ውስጥም ነፍስ ያላቸው የኢህዴግ አባላትም እንደገና ተወልደዋል። በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ጣልቃ ገብነት እንደ ቀረ አዳምጫለሁኝ፤ ይህን መረጃ ይዢ የእስልምና ስሄድም እንዲሁ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁኝ።

አሁን አዲስ የስቢክስ የግብረ ሰናይ ድርጅቶችን የማደራጃ ረቂቅ ዓዋጅም ላይ ገፋ ያለ ተግባር እዬተከወነ ነው፤ ይህም በትልቁ ከዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ማነቆ፤ አፋኝነት፤ እስረኝነት የሚያወጣ ነው፤ የተቋማት ግንባታ በዚህ መንፈስ ከተቃኝ ምድራዊ ገነት ነው። ዴሞክራሲን በዚህ ውስጥ ማሰብ እንችላላን። በምርጫ ቦርድም ሰብሰባቢም የተወሰደው እርምጃም ይህም በዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የታሠረው ሁሉም መንፈስ ፍታት የተሰጠው ነው። የያዙት ወርቅ ከመዳብ ቁጥር ነው ሆኖ ነው እንጂ ደፋር እርምጃ ነው። 

 ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ማነቆ የአህአዴግ ብቻ የሚመስለው የዋህ ሊኖር ይችላል፤ አይደለም በፍጹም አይደለም። በተቃዋሚ/ በተፎካካሪ/ በተቀናቃኝ ፓርቲዎችም ውስጥ የነበረ የወል ገመና ነው። አንደበትም የላቸውም ገፋ አድርገው ህውሃትን የመሞገት እነሱም የዛ ረግግረግ ቤተኞች ናቸው እና።

በዚህ ውስጥ በነፃ ተፈጥሮ፤ በነፃ የማስብ ፈቀድ ምን ያህል ተኮድኩዶ 50 ዓመት እንደተቆጠረ ሲታስብ ሚዛን የለውም ጉዳቱን ለመግለጽ። ተቀብሮ የቀረውን የማድረግ የመፍጠር አቅም፤ አፍሮ ቅስሙ ተሰብሮ የቀረው ሲሰላ አገር ደሃ መባሏ ሲያንስ ነው፤ ድህንት የኢኮኖም ብቻ አይደለም የአስተሳብም ነውና።

ውጪ ወጥቶ እንኳን በፖለቲካ ድርጅት የማንፌስቶ አባልተኝነት ፈቅዶ ከተጠረነፉ መሰሉ መከራ አይቀሬ ነው። ስለሆነም ኢትዮጵውያን በተቀጠሩበት ድርጅት የሚያሳዩትን ትጋት እና የሚያስገኙትን ውጤት ያህል በፖለቲካ ድርጅት አማራር አካልነት ወይንም ውክል አካል ሆነው የዚያን ያህል ተራምደው የበቃ ተግባር በሙሉ አቅም ፈጽመው ድርጅታቸውን ከሞት ማዳን የማይችሉበት ምክንያት ይኸው ነው። ድርጅቱ ሲፈርስ ያፈሰሱት መዋለ ሃብታት ሁሉ አብሮ ጥሪት አልባ መራራ ሰንብት ያደርጋል። ስለምን ሙሉ አቅማቸውን አውለው ድርጅቱን ለማዳን ፈቃድ ስለማያገኙ። 

ነፃነቱ ቢኖር ግን ከ10 በላይ አመራር ውስጥ አንድ አዳኝ መንፈስ ስለማይጠፋ እንደ የለውጥ ፈርጦች ጥሶ ወጥቶ ከመፍረስም የሚያድን፤ ለውጤትም የሚያበቃ አቅም ይኖር ነበር። ግን ያለው የሚኖረው የአንድ ሰው ፈራጭ ቆራጭነት ዘይቤ ነው። 

ያ ሰው የራሱን ልብ፤ የራሱን ህሊና፤ የራሱን ቁመና ፈጣሪ ሰጥቶት የሌላውንም ዘርፎ ኮርኩዶ በሥሩ ረግጦ ያስተዳደራል ይመራል ስለዚህ ከውደቅት ለማምለጥ አይቻለም ተያይዞ ሲዘሙ መዝምም ሲወድቁም እብሮ ለሽ ነው። እንቅልፋሙ ዘመን የጨፈረብን በዚህ መሰል አዚም ነው። 

ጭብጥ አድርጎ ነው የሚይዘው ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት፤ ጭቆናው ወንዝ እያሳሳቀ ይወስዳል እንደሚበላው ነው። የተገባው ንጹህ አዬር ሆነ ለአመክንዮው የሚያስፍለገው ንጥረ ነገር በሚያስፍለገው ልክ ወይንም ባለው ልክ እንዲያገኝ አይደርግም። 

በልጦ መውጣትም የለም። አይፈቀድም መብለጥ። በፅኑ የተከለከለ አምክንዮ ወይንም መንገድ ነው። ለዚህ ነው ዶር ለማ መገርሳ የዴሞክራሲ አባት የምዕት ቅኔ እኔ የምላቸው። በዘመን መካካል የተፈጠረ አንድ ሰው ብቻ። እርግጥ ነው ኮ/ጎሹ ወልዴም መድህን ፈጥረው በፈቃዳቸው ለወጣት ፕሮፌሰሮች እንዳሰረከቡ አጋጣሚ ሰጥቶኝ አረጋግጫለሁኝ። በ አካልም አውቃቸዋለሁኝ። 

የገደል ያህል ነው እንዲህ ቦታን ለቆ ሌላው ማስረከብ። ለቅድስት ኦርቶዶክስ አማንያን እምቤታቸን ቅድስት ድንግል ማርያም በአካል የመታዬት ያህል ነው ለእኔ ዶር ለማ መገርሳን ሳስብ። አሁን የ እርቅ የሰላም ኮሚሽን የሚባለው ሰብሳቢው ኮ/ ጎሹ ወልዴ ከሆኑ የሆንቱን ያህል በመቁንን ሳይሆን በገፍ ነፃነት በመስጠት አባሎቻቸውን ያሰተምሩልኛል። 

በዛ ውስጥ ማንህሎኝነት ቀስ እያለ እዬተቦረቦረ እዬተሸረሸረ ሰዋዊ መንፈስ ድል እያደረገ ወደ ትክክለኛው ጸጋ የመምጣት አጋጣሚ ይኖራል። ከመስማት ማዬት ተቋም ስለሆነ። ሰብዕናቸው እራሱ የኮ/ ጎሹ ወልዴ ትሁት ነው። የታማኝነቱን ብትህና  የዕድምታ ባላሙያዎች ይሂዱበት። 

በዚህ ሂደት ውስጥ የተኖረውን ኑሮ ከትውልዱ ብክነት አንጻር ስታስቡት ኩርኩም ስለሚባዘበት ኩድኩድ ነው። ሰው ነፃነት ካጣ እንደ ሮል ሞዴል ሊሆኑ የሚገባቸው ስብር ስለሚሉ ወጀቡን ለማሳለፍ ኩርኩም ስለሚበዛባቸው አቅም ያላቸው ስብዕናዎችም በተከታይ እነሱን አይቶ የሚብቀል ትውልድ ለመፍጠር ዕድሉም ይቀጫል ወይንም ይቀጭጫል።

በሶሻሊዝም የአካዳሚ ነፃነት፤ የመፍጠር ነፃነት፤ የማሰብ ነፃነት የለም። እነዚህ ሁሉ በሳንሱርድ፤ በዴሞክራሲ ማዕከላዊነት፤ በእዝ ሰንሰለት የተቀፈደዱ ናቸው። እስር እኮ የሚተካው እስረኛ ህሊናን ነው። 

በርካታ ዩንቨርስቲዎች እንደተገነቡ አዳምጣለሁኝ። የአካዳሚ ነጻነት ከሌለ ድንጋይ ቆጠራ ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያ ዩንቨርስቲዎች አፍ ባለው መቃብር ነው የሚኖሩት። ዩንቨርስቲዎች የሰው ልጅ ጭንቅላት በልኩ በልጽጎ አዲስ የሆነ ግኝት እንዲፈጥር ምቹ መደላድል ሊኖረው ይገባል።

መስኮቱ ከተዘጋ መከፍት፤ በሩ ከተከረቸመ መከፈት ይገባዋል አዬር እንዲገባ፤ ያ በሌለበት በተዘጋ በር እና በተዘጋ መስኮት በታፈነ አየር ፈጠራ አይታሰብም። ፈጠራ ከሌለ የኩሬ ውሃ ነው ሰብሉ። 

በሌላ በኩል ዩንቨርስቲዎች ሉላዊ ናቸው። ሉላዊነታቸው የሚረጋገጠው የአካዳሚ ነፃነታቸው ተጠብቆ በምርምር ተግባራት ላይ አንቱ የሆኑ ተግባራትን ሲከውኑ ብቻ ነው። ይህን የሉላዊነት አቅም ለማምጣት ደግሞ ነፃ ህሊና በነፃነት መንቀሳቀስ የመቻል ነገርን ይጠይቃል … 

እኔ ቤት ውስጥ በህይወቴ ሙሉ ወገቤን የሚይዝ ልብስ ለብሼ አላውቅም። ይጨንቀኛል። መታሠሩን ልብ ወይንስ መጻፉን?ህሊና እንደልብ እንዲወላዳ ካቴና አያስፈልገውም።

·       ስረኛ ትውልድ አማራችነት።

በዴሞክራሲ ማዕከላዊነት መርህ ልቅ የሆነ ያለተጠበቀ መኖር አይታሰብም። እንደ ተፈጥሮ መኖር አይፈቀደም። ወደ ዩንቨርስቲዎች ሲመጣ ፈጽሞ የባሰ ጨለማ ነው።  

ነፃነት በሙሉ አቅም መንቀሳቀስ ይህ አይታሰበም፤ ካልታሰብ የሚያመርቱት ዩንቨርስቲዎች እስረኛ ትውልድ ነው ማለት ነው። ወይንም ስደተኛ ትውልድ። የ አካዳሚ ነፃነት ተነፍጎ፤ በዛ ላይ ደግሞ የፓርቲ መዋቅሮች ተዝርግቶ የማይመረቁ የካድሬ ሰብዕናዎች የፖሊስ ቤት ምስጋን ይንሳው። መመህሩም፤ ተማሪውም፤ ሠራተኛውም፤ ህንፃውም፤ ቤተመጻህፍቱ ካቴና። 

በዚህ ውስጥ በቁሙም በህልሙም ሸሽቶ ለመሄድ ተንቆራጦ የተቀመጠ … ትውልድ ይፈጠራል። ፈሪ የሆነ።  በዚህ ባረጋ መንፈስ ማሰብም መኖርም መበልጸግም መፍጠርም የለም። መኖር አልታቀደም እና። ለመኖር ሰከን ያለ መንፈስ ይጠይቃል፤ 

አሁን እኔ ብትህትና የምጠይቀው ትሁቱን የአብይን መንግሥት ስለ አካዳሚ ነፃነት ሊጨንቀው የሚገባ መሆኑን ነው። ዲስ ሃላፊነት የሚሰማው ነፃ የሆነ የትውልድ ጽንሰት ላይ አትኩሮት ስላለው … መሠረቱ ት/ቤቶች ከሆኑ የአካዳሚ ነፃነት  መታወጅ አለበት።

ከዛ ይታያል ቁጥራቸው የበረከቱት የኢትዮጵያ ዩንቨርስቲዎች እርስ በእርሳቸው በሚኖራቸው ፉክክር ዓለም አቀፍ ዕውቅና በማግኘት ሌላም ዕድል ይኖራቸዋል … ግሎባል ዕውቅና ለማግኘት። በዚህ ቀጥተኛ ምህንድስናም ብዙ የመንፈስ ጥሪቶች ኢንተግሬት እንዲያደርጉ ይረዳል፤ ያግዛል … 

በዚህ ውስጥ ማግስትን ለማደረጀትም ረቂቅ የእኛነት መንፈስ አቅምም ይገኛል። ነፃ የሆነ ዩንቨርስቲ ነፃ የሆነ ልጆችን ያፈራል። ነፃ የሆነ ልጅ ደግሞ ነፃ የሆነ ቤተሰብ ይመስርታል፤ ነፃ የሆነ ቤተሰብ ደግሞ ነፃ የሆነ ማህበረስብ ይፈጠራል፤ ነፃ የሆነ ማህበረሰብ ደግሞ ነፃ የሆነ አደራ የረካከባል። 

ሰው ነፃ በሆነ ቁጥር በሁሉም ነገር ሳንክ ፈላጊነቱ ሁሉ ይቀራል። በታፈነ ነገር ውስጥ ግን አዬር ፍለጋ ቀውስ ቅረበኝ ምራኝ ግራኝ ይላል … አቅም በመፍጠር እረገድ ነፃ የሆነ የማሰብ ልቅና ፏፏቴ ነው አዎንታዊ ትውልድን፤ በራሱ የተማመነ ብቁ ዜጋን በመፍጠር እረገድ …

·       ቅም።

አቅም እንደ አባይ ሲባክንባት የኖረች አገር ብትኖር ኢትዮጵያ ሪከርድ በጣሽ ትሆናለች። ራሱ አቅም ያለንን አናውቀውም። አቅም ውጭ አገር ቢያንስ አይቶ መማር እንኳን አልተቻለም። ውጭ አገር እንግዳ ንጉሥ ነው። አይደለም አዎንታዊ ሃሳቡ ተቃውሟዊ ሃሳቡ አቅም ነው። የጎደለን ስለሚሞላ፤ ግድፈትን ለማረም ስለሚረዳ፤ ተቋሙን ከውድቀት ስለሚታደግም የሚመሰገን የሚበረታታ ነው። 

ይህን በእኛ የፖለቲካ ዘርፍ በተቃዋሚ ይባሉ በነበሩት አይ የነበረው ግድፈት ይህ ነው አይባልም። አያከብሩትም አቅም የአዋጣላቸውን ከፋይዳ ውጭ ነው።  በእቅዳቸውም ውስጥ አይገባም። ምስጋና ቀርቶ ፈታ ያለ አቀባበል አልፈጠረላቸውም። እነሱን ብለህ ሄደህ ተገርፈህ በመንፈስ ትመለሳለህ። እድገታቸው ቁልቁል የሚሆንበት መንገድም ይኽው ነው። ሌላው አገር ቤት እንደሚታሠረው ውጭ አገርም እንዲሁ ነው።

አሁን ባለው የፍትሃት ዘመንኛ ቅኝት እዬተግደረደሩም፤ እዬተሽኮረመሙ የአብይ መንግሥትን ዜማ እና ቃና ለመከተል እየተውተረተሩ ስለሆነ በአገር ደረጃ በብሄራዊ ደረጃ የአካዳሚ ነፃነት ከታወጀ በእነሱ ውስጥ ያሉ ብቁ ሊሂቃንም ጸሐይ ይወጣላቸዋል። እፎይ ብለው በአቅማቸው ልክ የመንቀሳቀስ ባለሙሉ መብት ያደርጋቸዋል።

ለነገሩ በማይታይ በማይጨበጥ ደረጃ በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ማንፌሰቶ እስረኛ የነበረው ሁሉ ይህም አለ ለካ እያለ አዲሱን ሰውኛ፤ ተፈጥሮኛ ቅኔ እያጣጣመው ነው የሚገኘው፤ ለነገሩ እነሱም መሪዎች የሚባሉት እሰረኛ ስለነበሩ እነሱም ከእስር ተገላግለዋል ማለት ያስችለኛል። ስለምን? ትችት አይፈቀደም ነበር። 

ትችት ከሌላ ደግሞ ራስን እንደ ካቦ አንጠራርቶ አቅምን እያንጠባጠቡ ማለቅ ወይንም መንጠፍ ነው። በ2008 እ.ኢ.አ ማለቃቸውን የሚያውቁት ከፈረሱ በኋዋላ ነው ብዬ ሁሉ ጽፌ ነበር። ያሉ የሚስላቸው ደፍሮ የሚናገራቸው ስለማይኖር ነው - ማለቃቸውን።

ስለዚህ የዚህ ዘመን ነፃነት አያያዝ እና ጥበብ የብዙውን የተጠበቀ የታመቀ የተጨባበጠ አስተሳሰብ እያፍታታው ነው፤  እኔ የፍትሃት ዘመን እለዋለሁኝያለ አስተማሪ ኦን ላይን ላይ ክላስ ተከፍቶላቸዋል። በዬቀኑ በአንዷ የጠ/ሚር አብይ አህመድ ንግግር ውስጥ ራስን ለመግራት እና ተስተካክሎ በሚሉት ውስጥ ለመገኘት ሥልጠና አለ፤ በነጣ። እኛ ከዚህ እነሱ ከዚያ።  

በዚህ ላይ የአካዳሚ ነፃነት ከታከለበት ጉዳይ እንደ ሌላው ጉዳይ ትኩረት ተሰቶት ራሱን የቻለ አዋጅም ተቋምም የሚፈጠረበት ሁኔታ ቢፈጠር የህሊና መስኖ ይሆናል።
የአካዳሚ ነፃነት ንፁህ አዬር ገብ፤ ንጹህ ውሃ ገብ መስኖ ነው። 

የሰው ልጅ በምግብ እና በእህል ብቻ አይኖርም። የመንፈስ መስኖ ያስፈልጋዋል። መስኖ ደግሞ የአካዳሚ ነፃነት ነው። የሥነ - ጥበብም ሰው ነፃነት በሌለበት የሚሠራ ከሆነ ያለውን ሙሉ ለሙሉ አውጥቶ አይጠቀምበትም። መምህርነቱ ይነጥፋል። 

ይህ ማለት ተቀብሮ የሚኖር አቅም አለ ማለት ነው። እየቆጠበ ነው ሰው የሚያወጣው፤ ወይንም አጋጣሚ እዬጠበቀ … በነፃነት ውስጥ ሰላም ከተገኘ በራሱ መዋለ ንዋይ ነው። ነፃነት ያለው ሰው ጤነኛም ነው። ጤነኛ ዜጋ ደግሞ የትውልድ አንጓ ነው።

በዚህ ስሌት 50 ዓመት ሲታሰብ በአካዳሚ ነፃነት ብቻ ስንት ቪላርድ አቅም ኢትዮጵያ አጥታ ይሆን? የቁጥር ተማሪ አይደለሁም፤ በዛ ላይ በሳል ጥናት መሰራት ይኖርበታል ብቻ ከቁጥር በላይ እንደሚሆን አስባለሁኝ። አሁን እኔ ነፃነት ስላለኝ በፈግኩት ሰ ዓት የፈልግኩትን ያህል የመጻፍ ፖስት የማድረግ መብት አለኝ።

ስለዚህ ሃሳቤን የሚሸምቱ ወገኖቼም ያለ ተዕቅቦ ነፍሳቸውን ከነፍሴ ጋር ያገናኙታል። ከሰው ጋር ብሠራ ግን ይህን ያህል መራመድ አልችልም እገታለሁኝ … ቀይ መብራት አለ። ከግንቦት አንድ ጀምሮ ወደ 400 የሚጠጉ አዳዲስ ጹሑፎችን ጽፌያለሁኝ። 

ነፃነት ስላገኘሁኝ። ሃሳቤን ምኞቴን የሚገድብ … ስጋትም ሰቀቀንም ብቻ ሳይሆን ለሚፈቅዱልኝ ፖስት ለማድረግ አበዛሁ የማለትም ሌላ በውስጤ የሚፈጠር ስሜትም ይኖራል። ስለዚህ በመቅኑን ይሆናል ፍሰቱ፤ ተልኮ ካለወጣም፤ ከተነሳም ሌላ ለመጸፍ ጫና ትፈጥራል። ደፍሮ በድጋሚ ለመላከም ጫና ይኖራል አበራከትኩባቸው የማለት … ሌላ ካቴናም ያጠልቃል መንፈስ በራሱ እጅ። አሁን ግን ነፍሴ ያለችኝን እላለሁኝ … ጤንነቴም ተመለሰ … ። 

ሰው ነፃነቱን ሲያገኝ ጤናውም ይመለሳል፤ በሥጋ ቢያልፍ እንኳን እረፍቱ የሰላም ይሆናል። ነፃነት በሥጋም ተለይቶ ያለውን ሁሉ ሰጥቶ ስለሚሆን እረፍቱ ተናፋቂ ነው ... 

ከተገታ ያመግላል። ያ ረቂቅ ስለሆነ መንፈስን ስለሚጫን ከሚታዬው ካቴና በላይ ነው። ለጉልበተኞች የሚያገኙት ሰናይ በራሱ ያልተገባ ዋጋ ስለሆነ ድርብ ቁስለት ያመጣል፤ በዛው ልክ ሃቅ ስትቀበር የትወልድ ህሊና መታነጽ ባለው ልክ አለመሆኑ በራሱ ብክነትም ነው።

በቤታቸው የታፈነው አልበቃ ብሎ በሞፈር ዘመት ሲሆን ደግሞ ጨለማ ተደገም ይላል። አሁን ግን ያ ለእነሱ የደላው መስመር ቡድስድስ ብሎ በነፃነት ወክ እና እንዲህ ተሆነ … እላችሁ አለሁኝ። ነፃነት እንዲህ ነው መሆን የሚገባው የተፈጠርኩት በነፃነት ለነፃነት ነውና።  

·       ጥን እና ተስፋው …

ትውድል ተኮር የሆኑ ተግባሮች አገር ቤት ተጀምረዋል። አንድ ሁለት ብለን እምንቆጥራቸው። አሁን የመምህራን ስብሰባ በቤተ መንግሥት ለሙያው ብቻ አልነበረም፤ ገበሬዎች ስለሆኑ ምርጥ ዘር እንዲያምርቱ አዲስ ንድፍ ነበር። የበለጠ ወሳኙ ደግሞ ለእኔ የታሰረው የአካዳሚ ነፃነት ከእስር መላቀቅ ሲችል ነው። ዕወቀት ማደግ፤ መበልጸግ፤ መስፋፋት፤ መንሰራፋት፤ ግኝት ተኮር ትክ መፍጠር የሚችለው ነፃ ሲሆን ነው።

ይህ ነጻ የሆነ የማሰብ አቅም ደግሞ ነፃ የሆነ ማህበረሰብን ይፈጥራል፤ ነፃ የሆነ ማህብረሰብ ደግሞ አደራ ለመቀበል ብቻ ሳይሆን አደራውን አስብሎ ለማስረከብ ብቁ ነው። 

ሰው እና እንጨት ተሰባሪ ነውና በሥጋ የማረፍ ዕድላችንም ሰላማዊ ያደርገዋል።
ተስፋ የምናደርገው ትውልድ ከኖረ ነገም ከነገ ወዲያም አያሰጋንም ፤ የቅኔው ልዑል ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን እንደ ሰጋ ነው ያለፈው „ፈራን…“ እያለ … እሱ እንደሰጋ አለፈ እኛስ?

„የተመሸገቸው ከተማ ብቻዋን ሆነች፤ እንደ ምድረ በዳ ሆና
 የተፈታችና የተተወች መኖሪያ ናት፤ በዚያ ጥጃ ይሠማራል፤
በዚያም ይተኛል፤ ቅርንጫፏንም ይበላል።“

ትንቢተ ኢሳያስ ፳፯ ከቁጥር ፲- ፲፩

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

የኔዎቹ ክብረቶቼ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለአላዛሯ ኢትዮጵያም ኑሩላት - ኑሩልን።
መሸቢያ ጊዜ!


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።