የአማራ እረቀ ሰላማ እንዴት? ከእነማንስ ጋር??? #ሚስጢረኛችን ኢትዮጵያ ብቻ ናት!

 

የአማራ እረቀ ሰላማ እንዴት? ከእነማንስ ጋር???
እንዴት አደርን? የቅኔ አድባራት እንዴት ውለው አደሩ ይሆን? እነ ማህበረ ቅንነትስ እንዴት አላችሁልኝ???
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
 May be an image of 1 person and textMay be an image of 1 personMay be an image of 1 person and textMay be an image of textMay be an image of text that says 'አንድ ዐማራ One Amhara'
 
ይህ ጥያቄ ከ32 ዓመት በላይ ተቀንቅኗል። አማራ እንደ አማራ የጠላውም፤፦የሚጠላውም፤፦የሚያሳድደውም፤፦የሚያወግዘውም፤ ያፈናቀለውም፤፦ያሳደደውም፤ መኖሩን የቀማውም፤ ጋብቻ የከለከለውም፤ በጉርብትና ፊት የነሳውም፤ በግብይት ያገለለውም አይደለም ማህበረሰብ፤፥ተቋም ቀርቶ ግለሰብም የለም። ልብ እና ኩላሊት የሚመረምረው አምላክ አላህ ያውቀዋል። የእኛን ቅንነት እና ገራገርነት።
ስለዚህም አማራ ሊታረቅም ብሎ አቤቱታ የሚቀርብለት ግለሰብ፤፥ተቋም ማህበረሰብ የለውም። ይልቁንም ከሙሉ የህሊና ካሳ ጋር ሊካስ የሚገባው የአማራ ህዝብ ነው። በዳዮቹ መበደላቸውን አቁመው ይቅርታ ጠይቀው ሊክሱት ይገባል። የመንፈስ ካሳ። ውሃ በቀጠነ ማቱ የሚወርደው በአማራ ላይ ነው። ነፃ አውጪወች ሲደራጁ የማኒፌስቷቸው ጭብጥ ፀረ አማራነት ነው። ስለዚህ ይህን ጭብጥ ቢተውት ተቋማቸው የሁሉም ይፈርሳል። እርቀ ሰላሙ ይህ እና ይህ ብቻ ይሆናል።
 
ህወሃት ሙሉ 47 ዓመት ሚዲያው ሊቃውንቱ ዛሬም ፀረ አማራ ዲስኩር ነው። ጦርነት የከፈተው የ፬ኪሎው ኦነግ ሆኖ ዛሬም ናዳ የሚለቀቀው በአማራ ላይ ነው። ኦነግ ፬ ኪሎ የንጉሦችን ንጉሥ የአጤ ሚኒሊክን ቤተመንግሥት በአማራ ትጋት እና ሙሉ ድምጽ አግኝቶ ዛሬም አማራ ላይ ዛሩ እንደተደረረ ነው። የከተማ ተቋማቱ፤ የጫንካ ክንፋ ውግዘቱም ምንጠራውም አማራ እና ጠረነ አማራ ብቻ ነው።
የኦነግ ሊቃውንት የላንቃቸው ጠበለ ጣዲቅ ይህው ፀረ አማራነት ነው። ተማሩ አልተማሩ አንድ አይነት ማት ይፈሳል። እዬረሸኑም፤ እያፈናቀሉም፤ እያገቱም እያሰሩም የሚያባትታቸው ይህው ፀረ አማራነት ዛር ነው።
ከህወሃት ውጪ ያሉ የተጋሩ ድርጅቶችም መሳ ለመሳ ናቸው። እሱ በእሱ።
 
እና ……… እናማ እርቁ በማን እና በማን ቢሆን ያምራል?
1) ህወሃት እና እሱ የፈለፈላቸው ድርጅቶች እና ተቋማት ጋር።
2) ፈለገ ኦነግ እና ፈለገ ህወሃት።
3) ፈለገ ኦነግ እና አምሳያወቹ ማህበረ ኦነግ እና ኦነግ።
5) ፈለገ ህወሃት እና እሱ ያደራጃቸው ህወሃት ሠራሽ የተጋሩ ድርጅቶች።
6) ህወሃት በመንፈስ የወለዳቸው ማህበረ ኢህአዴግ።
እነኝህ እርስ በእርሳቸው አማራን ለመንጠር መታረቅ፤ ስልጣንን በኮታ ለመከፋፈል ኢትዮጵያን ለመቀራመት ይደራደሩ እርቀ ሰላምም ማውረድ ይቻሉ። ከቻሉ። ምክንያት ጠላቶቻቸው ኢትዮጵያ፤ አማራ፤ የአማራ ጠረን፤ የአማራ ወዳጆች፤ የአማራ ትሩፋት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ናቸውና።
 
አባ ገራገሩ አማራዬ ግን ……
 
የሰላም ንግግር፤ የሰላምድርድር አይመለከተውም። የድርድሩ መከወኛ ፀረ አማራ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ፀረ አማራ ተቋማት ህልውና ማጣት መፍረስ ከቻሉ ጠረጴዛ እና ወንበር፤ አስታራቂ እና አደራዳሪ፤ የከረባት እና የገበርዲን ሰልፍ፤ የወረቀት እና የመዋለ ንዋይ ፍሰትም አያስፈልግም።
 
ሁሉም የፖለቲካ ድርጅት ተጨቁነናል፤ የጨቆነን ደግሞ አማራ ነው የተኖረበት ዕውነት ነው። በህሊና የታነፀውም ይህው ነው። ህገ መንግሥቱ፤ ማኒፌስቶው፤ መመሪያ ሰነዶች ሁሉ ምንጫቸው፤ ራዕያቸው እና ግባቸው አማራን ማክሰም፤ አማራነትን መመንጠር ነው። እና ከዚህ ዲል ካለ ገሃነምሁነት ጋር ገራገሩ አማራ ከገደሉ፤ ከጉድጓዱ ከሞቱ ጋር ቁጭ ብሎ እንደምን መፍትሄ ማፍለቅ ይችላል። ሎጅኩም ፋክቱም አያስኬድም።
 
ለዚህ ነው እኔ የአማራን የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ጥያቄ የሃገራዊ ምክክሩም ሆነ፤ የሽግግር የፍትህ ጥንስስ እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስተሩ እና ካቢኔያቸው፤ ፓርቲያቸው እና ጄኒራሎቻቸው ከአቅማቸው በላይ ነው የምለው።
 
ለአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ፖለቲካዊ መፍቴሄ፤ ሉላዊ መፍትሄ ነው የሚያስፈልጉት እምለው። በአማራ ጥላቻ የተፈጠሩ ድርጅቶች ሁሉ ሲፈርሱ ብቻ አማራ እና በጠላትነት የፈረጁት የፖለቲካ ተቋማት ማህል እርቅም፤ ሰላምም ይፈጠራል።
 
#ይቅርታ እና ምህረት።
 
የቃላት ጨዋት አይደለም። በዜግነት ፖለቲካ የነበሩት የአማራ ችግር ከሌላው የተለዬ አይደለም ባዮች ናቸው። መደራጀቱንም አያምኑበትም። በውስጣቸው ጽንሱ አማራን የጠላ ነው። ተመስጥሮ። ጊዜ ራዲዮሎጂ ነውና በግለሰብም፤፦በተቋምም ይህን ዘመን ሰጥቶን አስተውለናል። የሰባዕዊ መብት ድርጅቶች አይደለንም፤ ወይንም በአገኜነው ወንበር ልክ እንጠዬቃለን ማለታቸው ፍቹ ይኽው ነው።
ሲጠቃለል እርሾው፤ ዱቄቱ፤ ዘሃው፤ ፈትሉ ሁሉም ድር እና ማጉም በፀረ አማራነት ላይ የተጠነሰሰ ስለሆነ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የምህረት እና የይቅርታ መንገድ አዲስ ተፈጥሯዊ ሥርዓት መገንባት ብቻ ነው። በአብዛኛው ፖለቲከኛ ህሊና ውስጥ የጥላቻ ዕጢ ተጋግሯል። ያ ደግሞ ሥራን በትጋት ይጠይቃል። እርድ ላይ ቁጭ ብሎ፤ ፍጅት ተሞሽሮ ይቅርታ እና ምህረት እንደ ሰው ገራገሩ አማራ ቢፈቅድም እግዚአብሄር አላህ በእጅ አይልም። "አለባብሰው ቢያርሱት ባረም ይመለሱ እንዲሉ" ነውና።
ጭቃ ውስጥ ሆኖ ፀዓዳ ለብሶ መሞሸር አይቻልም። ፈጽሞ።
 
ለጨዋታ ማሟያ ይሁንላችሁ እንጂ የፈጠጠው ፋክት ግን በጠላትነት የተቋቋሙ ተቋማት ፈርሰው ነው እርቅ ሰላም ሊታሰብ ዬሚገባው። ያደፈ፤ የጎረፈ፤ የጎሸ፤ ያጎፈረም መከራው ከትናት እስከ ዛሬ ዘውድ ደፍቶ እንሆ በፀረ አማራ ዘመቻጦርነቱ ቀጥሏል።
ይህ ዕውነት የበቀልም የቂም ጉዳይ አይደለም። ቂም እና በቀል አመድ የሚታፈስባቸው ናቸው። ይህን ደግሞ አባ ቅንዬ አማራዬ ያውቀዋል። ምርቃቱም እንዳይነሳይም እነኝህ ክሉ ማለት ይጠበቅበታል። ነገር ግን ሞት እና ገዳይ አስታራቂም፤ አደራዳሪም፤ መሪም ሊሆኑ አቅሙም ክህሎቱም የላቸውም። 
 
ፈላስፊት ኢትዮጵያ፤ ሳይንቲስቱ ኢትዮጵያዊነት ከአማራ ጋር አይገዳደሩም። የአማራ መንፈስም መነሻውን መድረሻውን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ የህግ አምላክ ሊጋባም ስለሆነ አያስበውም። ቅኔውም ድጓውም፤ ማህሌቱም ዜማውም፤ ማንዙማውም ድዋውም፤ ሱባኤውም ምህላውም፤ ፆም ፀሎት ሰጊዱም የደጉ አማራ ውስጥ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ብቻ ናቸው። ተፈጥሯዊነቱ ያላበል፤ መንፈሱን ያልተላለፈ፤ ምንም ዓይነት የበታችነት የማይስማው በራሱ የቆመ ማህበረሰብ ነው አማራው። በዚህ ሁሉ የሞት፤ የእልቂት ዓዋጅ ላይ ሆኖም ህግ ሲተላለፍ፤ ተንጠራርቶ ፈጣሪውን ሲያጣውር አይገኝም። ምርቃቱ ሰፊ መቻል የሰጠው ታጋሽ እና ሥህን ነው የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ። 
 
ከዚህ ህዝብ ጋር የተጣለውም ሲበተን፤ ሲፈርስ ሲሰነጣጠቅ እንጂ ለበኽረነት ሲበቃ አልታዬም። የአማራ ተስፋው ፈጣሪው እና አላህ ብቻ ነው። ሙሉ 33 ዓመት ካለ መንግሥት እራሱን ጠብቆ የቆዬ ጽኑ የላስታ አለት።
የእኔ ክብረቶች ኑሩልኝ። ቸር ሁኑልኝ። ቸር እደሩልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/11/2023
#ሚስጢረኛችን ኢትዮጵያ ብቻ ናት!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።