ልጥፎች

19.11.2019 የሞት ጠረን ለሴራ ፖለቲካ ቀመር በኦዳ ኢንፓዬር።

ምስል
  የሞት ጠረን ለሴራ ፖለቲካ ቀመር በኦዳ ኢንፓዬር።     እንዴት ናችሁ ጤና አዳሞቼ? ደህና ናችሁ ወይ? ኦዳና ጃራ ግብግባቸው በጉልህ እስኪወጣ ቀዳሚው የአህድዮሽ ጉዞ በፀረ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ይቀጥላል።    ከዚህ መከራ የሚድነው አሁን ባለው ሁኔታ የአድዋ ሥርዕዎ መንግሥት ብቻ ይሆናል። 18 ወራት የኢትዮጵያን መከራ ያልወቀጠው እሱ ብቻ ነው ማለት ይቻላል። የቀረበት የማህል አገር ዘመናይነት ብቻ ነው። እርግጥ ነው በራሱ መስመር አገርን አምሷል። ሰፊ ስለሆነ እሱን አቁሜ ወደ ዋናው እርእሴ ልሂድ።   በዚህ 18 ወራት የበቀል ማወራረጃ፣ የጭካኔ የመሞከሪያ ጣቢያ የነፍስ ይማር ባዕት ያልሆነ አዬር ባዕት አልነበረም። ቁንጥንጡ፣ ዝርክርኩ፣ መሰሪው፣ ሸፍጠኛው የአብይወለማ ሌጋሲ ተጭኖ በያዘው የአማራ ህዝብ እና መንግሥት ከቀደሙው ዘመን ባላነሰ ፍላጎቱን ለማስፈፀም የመሞከሪያ ጥንቸል አድርጎት ባጅቷል።   አሁን ግዙፋን ኦፕሬሽን በእንደልቡ አቶ ዮኋንስ ቧያለው እና በአቶ መላኩ ፈንታ የስሜን አሜሪካ እና የለንደን ጉዞ ሀ ብሎ ይጀምራል። ሲመለሱ የእራሱ እግር የእግሩ ራስ ሆኖ ይጠበቃቸዋል።   በዚህ ማህል ሁለት አውራ ጉዳዮችን እንይ። ሃሳብን የማስተናገድ አቅም። ጥያቄ መጠዬቅ በህግ ያስቀጣል በዴሞክራሲ አሻጋሪው ጠቅላይ ሚኒስተር የህሊና አቅም። ሽብሽብ። የተገደሉት ሊሂቃን በሙሉ የሞገቱ ስለመሆናቸው እኔ በግሌ አልጠራጠርም። የታሠሩትም ቂሙ የሚመነጨው ሞገታችሁኝ ነው። ጠቅሚሩ ቶለራንሳቸው ዜሮ ነው። ፈሪም ናቸው።   መናገር መናገር መናገር ጥሪያቸው ይህ ነው። ማድመጥ አቻችሎ መጓዝ አልተፈጠረባቸውም። ስለዚህ ዴሞክራሲ ሞቶ የተቀበረው እሳቸው በህይወት የተፈጠሩበት ዕለት ነበር። እኔ ዴሞክራሲን በሳቸው ዘመን አልጠብቅም እንደ ማለት። እሱ ቀርቶ ተጨቁኖ መኖርን ለሚ

19.11.2019 የድንጋይ ጫጉላዊ ሽርሽር።

ምስል
  የድንጋይ ጫጉላዊ ሽርሽር።       ብር ትር የድንጋይ ሽርሽር። ስንድድ ተሰራለት ጨሌ ዘነበለት በጭካኔ ዜማ ጫጉላው ከበረለት። ሸማ ቀረበለት ገዳ ሰገደለት በዕንባ ቅልቅል ሜጫ ፈነጨበት። ድንጋይ እና ሜጫ ውሉ የእርግጫ ህሊናው ግራጫ ዘመኑን ገደሉት እንዲህ በፍጥጫ። ቀርቶ እንደ ዋዛ፣ የጥንት የጥዋቱ ሰውነት ማጣቱ እርስቱ ሆነለት መታበይ ስባቱ። ያ የድንጋይ ዘመን ተመልሶ መቶ፣ እንዲህ ዘመነበት በድንጋይ ሽርሽር፣ መኖርን ፈጨበት። ህይወት ቀጠፈበት ቤት ንብረት ጠፋበት ስጋት ሰፈነበት ዋይታ ነገሠበት።

19.11.2019 ድንጋይ ቀን ወጥቶለት።

ምስል
  ድንጋይ ቀን ወጥቶለት።      ድንጋይ ቀን ወጥቶለት ቄሮ ተፈጥሮለት የጭካኔ ሃውልት በሥምረት ቆመለት የአረማዊ ድርሳን ዘሞ ቀረበለት። ድንጋይ ቀን ወጥቶለት ድንኳን ተጥሎለት የሰው እርድ ቀርቦለት ዕንባ ጎረፈለት። ድንጋይ ቀን ወጥቶለት መንገድም አልፎለት እርፍት አግኝቶበት ሃኒ ሙን ሁኖለት ተጓዥ አልቅሶበት ቄሮን አንግሦለት ማህፀን መክኖበት። ድንጋይ ቀን ወጥቶለት መውገሪያ ሰምሮለት ኦዳ ተቀብሎት በጥቁራማ ዘመን ይሁንታ ቅብነት። የትውልዱ ሞራል ዝቅዝቅ ተጉዞበት የማረጉ ኩራት በኵረት በቅሎበት በስጋት ዳመና አገር ታመሰበት በሰቆቃ ስቃይ ፍጥረት አረረበት ድንጋይ ቀን ወጥቶለት።

ካቴና ያሉት ሳይደክሙ፤ ጫካ ያሉት ሳይዝሉ እኛ ግን ተዳከምን። ምን ነካን?

ምስል
እንዴት ናችሁ? ካቴና ያሉት ሳይደክሙ፤ ጫካ ያሉት ሳይዝሉ እኛ ግን ተዳከምን። ምን ነካን? የእኛ ቤትማ በረድ መሆን ከጀመረ ቆያዬ። በቃ ሁሉም ነገር ተረሳሳ። አባት ታዲወስም ተዘነጉ፤ መስኪም ተረሳች፤ ጎበዙ ጎበዜም ተረሳ፤ ሁሉንም እርግፍ አድርገን ትውት።    አሁን አሁንማ ሳስበው እኔ ስለጥፋቸው ሁሉ አሰልቺ እንደምትሉኝ እያሰብኩኝ ነው። የሆነ ሆኖ ነፃነት በአፍላ፤ በወረት በወፍ አወጣኝ አይገኝም። የቆረጡ፤ የፀኑ የትውልድ ፈርጦች በትጋታቸው በትትርናቸው የሚያስገኙት ሰማያዊ ፀጋ ነው። መኖራቸውን፤ ቤተሰባቸውን፤ ተስፋቸውን እራሳቸውንም ገብረው።   ማገልገልን የመሰል የጽድቅ ጎዳና የለም። በተለይ በነጣ ሲሆን። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 21/11/2023 #ክብር በብላሽ አይገኝም።  

#የቁልል #ዕፍረት ማጣት በበርሊን።

ምስል
#የቁልል #ዕፍረት ማጣት በበርሊን።     ማንበቡም፤ ማድመጡም የተፈራ ትግሉማ እንዴት ይደፈር???? ትናንትና በቅኔው ጎጃም በወበራ አዝመራ በመከወን ላይ የሚገኙ ትንታጎቹ የኢትዮጵያ ጉሮሮወች የጎጃም አርሶ አደሮች በፋሽስት አነጋዊ ኦህዴድ መንግሥት ሠራዊት በግፍ በባዕታቸው መረሸናቸውን ኢኤምኤስ ዘግቧል።   ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አለማፈራቸው ይገርመኛል። ሰሞኑን በርሊን ጀርመን ነበሩ አሉ። የገረመኝ ከውጭ ጉዳይ ሚር አንሰው ኢትዮጵያ ምድር ላይ አቀባበል የተደረገለት የጀርመን መንግሥት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን የጀርመን ካንስለር በክብር አቀባበል እንዳደረጉላቸው፤ እንደተቀበሉ አዳምጫለሁኝ። ቅጣቱ የህሊና ይመስለኛል ለጎግ ማንጉጉ የኢትዮጵያ የፕሮቶኮል አልቦሽነት።   የሆነ ሆኖ ህዝቡን በድሮን የሚጨፈጭፍ ፍፁም ጨካኝ፤ ገበሬው እርሻ እንዳይሠራ ማዳበሪያ የከለከለ፤ በእርሻ ወቅት በባዕቱ ሄዶ ጦርነት የገጠመ፤ ልጆቹ ከ12993 በላይ ለ12ኛ ክፍል ፈተና አትቀርብም ብሎ የቀጣ፤ ስንት አሳር አይተው ተምረው ዩንቨርስቲ የገቡ የአማራ ልጆችን ድብዛ ያጠፋ፤ ያሠረ፤ ያገተ፤ ያንገላታ፤ በመድፍ የፈጄ፤ በራህብ የሚቀጣ፤ በማደህዬት የሚበቀል፤ መጽናኛ የዕምነት ቦታወቹን ያረከሰ፤ ህዝብ ወቶ ለመግባት ዋስትና መስጠት የተሳነው #ቁልል በበርሊን መገኜት ዓይን በጥረጨው ማሸት ብሂሉ በውን የተገለጠበት ሂደት ነበር።    በጣም የሚገርመኝ አቶ ቀን፤ ባላንባራስ ሳምንት፤ ደጃዝማች ወራት እንዲህ አረመኔን ከረባት እና ገበርዲን አጎናጽፈው አደባባይ ማዋላቸው ብቻ ነው። ለዚህ የሰገዱ ኑዛዜወች ደግሞ አደግድገው አገልጋይ ሆነው ማይክ ጨብጠው መገኜታቸው ነው። 1) የተመረተ የእግዚአብሄር አዝመራ የሚያነድ፤ 2) ያለን የሚያራቁት በቅናትም የሚዘርፍ፤ 3) ቅርስን በበቀል የሚያወ

የዴሞክራሲ ሎተሪ ቢደርስ እንደምን በኢትዮጵያ ምድር ይስተናገድ ይሆን? ጓዘ ቀላል ጥያቄ።

ምስል
  የዴሞክራሲ ሎተሪ ቢደርስ እንደምን በኢትዮጵያ ምድር ይስተናገድ ይሆን? ጓዘ ቀላል ጥያቄ። ከአንቀጸ ብርኃን የኢትዮጵያ ሊቀ ቅዱስ ያሬድ የተወሰደ እንዲህም ይላል ……… "የአምላክ እናት ምስጋና፤ በዕውነተኛ ፈራጅ በአምላክ እናት ምስጋናና ይገባታል።" የእኛን ነገር እሷ እምዬ ዋ ድንግልዬ ታሰናዳው እንጂ እኛስ አላወቅንበትም።      ይጨንቃል። የመብት እና የግዴታ ጣሪያ እና ግድግዳ ያለማወቅ። ይቸግራል። "" "" "" "" " ይጠባል። " "" "" "" " ብፁዑ አባታችን እንደ ሰው፤ እንደ ብሄራዊ ዜጋስ አስተያዬት የመስጠት መብታቸው የማን ይሆን? እንደ ተሰጣቸው ሰማያዊ ቅብዓስ በክህነታቸው፤ በሥልጣነ ጵጵስናቸው ልጆቻቸውን የመገሰጽ መብት ማን ይሆን የሚመድብላቸው? ይህም ብቻ አይደለም የሚያጽናኑ ብፁዓን ናቸው መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ ያለው ቅዱስ ቃሉ ህይወት ዘርቶ ትንፋሽ የሆነበት ዘመንንስ አዳራሻውን የማሳጣት ሥልጣነ ክህሎቱ የማን ይሆን? እኔማ ሁሉንም አዳመጥኩት። ምንም ሳልጨምር ቃልም ሳልተነፍስ ከእኔ የቀደሙትን፤ የእኔን ዘመን፤ እኔን ተከትሎ የመጣው ትውልድን ገፀ ባህሬ በውን ስላዬሁበት ቀድቸዋለሁኝ። ለታሪክም አስቀምጠዋለሁኝ። ከእኛ ቤት እንኳንስ ጵጵስና የእኔ ቢጤ ባተሌም ዘቅዝቆ፤ ኤክስ አድርጎ ማቅረብ ስለማይፈቀድ መራራ ስንብት ሆኗል። እርግጥ ነው አክብረው ያዘኑበትን የገለፁ እህት እና ወንድሞቼ ግን መብታቸው ስለሆነ አክብ

#የድል አጥቢያ አርበኞች ወጋወግ። አቶ ጣሂር መሃመድ ተስፋ ከተጣለባቸው የአብን መሪወች አንዱ ...

ምስል
  #የድል አጥቢያ አርበኞች ወጋወግ።     አቶ ጣሂር መሃመድ ተስፋ ከተጣለባቸው የአብን መሪወች አንዱ .... ዬት እንደነበሩ አላውቅም። ግን ወደ ፊት ሲመጡ ተቃውሞ አልነበረኝም። እርግጥ ነው በአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ውስጠት ያልነበሩ ሰብዕናወች ይሁን በሌላውም የትግል ዘርፍ አብረው ያልተነሱ ሰብዕናወች በኋላ ሲዶሉ ፋክቱም ሳይንሱም ችግር ፈጣሪ አንጃ ዓዋላጅ እንደሚሆኑ እሙን ነው። የአብን ጉባኤ ሲካሄድም ባልደራስ ሲመሰረትም ዘለግ ባሉ ሙያዊ የአደረጃጀት ዕይታወቼን አጋርቻለሁኝ። ይህ አደጋ በአቶ ጣሂር መሐመድ ብቻ ሳይሆን በዬትኛውም ሁኔታ በሚመሀረቱ ተቋማት አዲስ ገቦች የችግር መፍቻ ከመሆን ይልቅ የችግር ጦስ ይሆናሉ። የሆነ ሆኖ አቶ ጣሂር በመጀመሪያው ጉባኤ አልነበሩም። እሳቸው በሁለተኛው ጉባኤ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ለመፈንቅለ አብን ከአደራጇቸው ወጣቶች አንዱ ሁነውህዝብ ግንኙነትን ይመሩ ዘንድ ተመረጡ ሳይሆን ተመደቡ ብል ይሻለኛል። በፖለቲካ ውሳኔ። አብን መራራ ስንብቱ ከዓላማው ጋር የተከወነውም ያን ጊዜ ነበር። አቶ ክርስቲያን ታደለ ታስሮ ነበር። ጉባኤው በዋዜማው አቅል አጥቶ ተካሄደ። በማግሥቱ አቶ ክርስቲያን እና ሌሎች የአብን አካላት ከእስር ተፈቱ። በዚህ ጉባኤ ዶር ደሳለኝ ጫኔ በፈቃዱ ለቀቀ አቶ በለጠ ሞላ ፕሬዚዳንት ሆኑ። ይስጥ የነበረው ቃለ ምልልስም የተነፋፋ እና በመታበይ የተባ ነበር። በምክትል እያሉ ያላሳዩት መንጠራራት ሊቀንበር ሲሆኑ መታበያቸው ይፋ ሆነ። አንድ ጊዜ የአብን አባል ያልሆነ ስለኛ አስተያዬት የመስጠት ድርሻ ሊኖረው አይገባም የሚል የተንጠራራ፤ የተወጣጠረ ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ሁሉ ነበር። የሆነ ሆኖ ከኦነጋዊው ኦህዴድ የምርጫ ዕውቅና በኋላ አቶ ጣሂር የአማራ ክልል የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆኑ። ለምን ከዛ

ነብዬ መህመድ ከሞት በስተቀር ይላሉ። የሳይንስ ተመራማሪወች መውለድ ለሚፈልጉ አንስቶች ጥቱ ብቻ እንዲጠቀሙ ይመክራሉ፠ የጥቁር አዝሙድ የጤና ጥቅሞች

  ነብዬ መህመድ ከሞት በስተቀር ይላሉ። የሳይንስ ተመራማሪወች መውለድ ለሚፈልጉ አንስቶች ጥቱ ብቻ እንዲጠቀሙ ይመክራሉ፠ የጥቁር አዝሙድ የጤና ጥቅሞች "1ኛ. ለእርጋታ አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መውሰድ ቀኑን ሙሉ መረጋጋትና ንቃት ያጎናጽፋል፡፡ እንዲሁም ከራት በኋላ ወደ መኝታ ከማምራት በፊት አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድ ዘይት መውሰድ ለሊቱን ሙሉ የተረጋጋና ደስ የሚያሰኝ እንቅልፍ ያስገኛል፡፡ አንድ ትልቅ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሲኒ ቡና ውስጥ ጨምሮ መጠጣት፡፡ የአእምሮ ጭንቀትን አስወግዶ መረጋጋትን ያስገኛል፡፡ 2ኛ. ለሳልና ለአስም በዘይቱ ደረትንና ጀርባን ማሸት በቀን ሦስት የሾርባ ማንኪያ መጠጣት፣ ሁለት ማንኪያ በሙቅ ውኃ ውስጥ ጨምሮ እንፋሎቱን መሳብ ይረዳል፡፡ 3ኛ. የመጫጫንና ስንፍናን ለማስወገድ አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት በአንድ ብርጭቆ ብርቱካን ጭማቂ ውስጥ ጨምሮ ጧት ጧት ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ ልዩነቱን ያገኙታል፡፡ 4ኛ. የማስታወስ ችሎታንና ፈጣን የግንዛቤ አቅምን ለማጎልበት አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት፣ 100 ሚሊ ሊትር የፈላ ናእናእ (Nena) ተክል ጋር ተቀላቅሎ ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ፡፡ 5ኛ. ለኩላሊት ጠጠር (የስኳር ሕመም ያለባቸው ማርን መተው ነው) ሩብ ኪሎ ጥሬ ጥቁር አዝሙድ፣ ሩብ ኪሎ ንጹሕ ማር ማዘጋጀት፡፡ ጥቁር አዝሙድን በሚገባ መፍጨትና ከማር ጋር ቀይጦ በሚገባ ማዋሀድ፡፡ ከዚያም ሁለት ማንኪያ ከቅይጡ ቀንሶ በአንድ ብርጭቆ የሞቀ ውኃ ውስጥ ጨምሮ በጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሻይ ማንኪያ በማከል በባዶ ሆድ መጠጣት፡፡ 6ኛ. ለብሩሕ ገጽና ለውበት አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ማንኪያ የወይራ

የአማራው ፋኖ ሌሎች የተጠየፉትን ኢትዮጵያዊነት አንግቦ መነሳቱ ኢትዮጵያን እንዲታደግ ያስችለዋል--እውቁ የፖለቲካ ...

ምስል

“ድሃውን በማፈናቀል ላይ የሚገነባ ከተማ ‘ስማርት’ ሳይሆን የሰይጣን ከተማ ነው።” ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ [ኤኮኖሚስት]

ምስል

ከዶር ለገሰ ቱሉ ዘለፋ፤ የአቀራረብ ዝበት፤ የኃላፊነት ዝንፈት፥ ዬችሎታ ኩስመት ፥ የሰብዕና ክሳት ሌላው ከዚህ ...

ምስል

SAVE LALIBELA .

ምስል
 

"እሱበእሱ ድርድር ለክፋ ቀን የተቀመጠው የጫካው ኦነግ የኢትዮጵያመሪ ሆኖ ሊመጣ? አይሰማ ጉድ የለም ።

ምስል
  እሱበእሱ ድርድር ለክፋ ቀን የተቀመጠው የጫካው ኦነግ የኢትዮጵያመሪ ሆኖ ሊመጣ? አይሰማ ጉድ የለም ። "የመከራን ቀን ዝም ብዬእጠብቃለሁ።" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍም፫ ቁ ፲፯) አንድ አብይዝም ከራሱ ጋር ሽብሩን ይደራደራል። "ከንቱ የከንቱ ከንቱ።" ጠቅላይ ሚር አብይአህመድ በርከትከት ያሉ ሥውር ታጣቂወች፤ አፋኞች አላቸው። አዲስ አበባም አፓርታማ አላቸው ይህን መሰል ጉዳይ የሚያስፈፅሙበት። #ህገ ወጡ 1) ቄሮ ለማፍያ ተግባር የተመረጡትን ብቻ ይመለከታል። 2) ፎሌ 3) አባቶርቤ 4) "ሸኔ" የጫካው የኦነግ ክንፍ በሙሉ መረጃ እና ሎጅስቲክ ኢትዮጵያን ዘነዘናዋን ያስቀረው። ይህ ህገ ወጡ አደረጃጀት ነው። #ህጋዊው 1) ልዩ ኮማንዶ 2) ሪፓብሊካን ጋር ከአሜሪካ የተወረሰ፤ 3) ልዩ ኮማንዶ ከራሺያ የተቀሰመ ይመስለኛል፥ 4) ኢሊት ሠራዊት ከእስራኤል በቀጥታ የተቀዳ፤ የተኮረጄ፦ 5) የኦሮምያልዩ ኃይል፤ አሁን አሁን ደግሞ ከአማራ ፋኖ መግነን ጋር የኦሮምያ ሚሊሻም አይቅርብን ብለዋል፦ ቅናቱም ያብተከትካቸዋል። 6) መደበኛው ዬኢትዮጵያ የፖሊስ ኃይል የቀደመው ባህር፤ ምድር እና አዬር ኃይል አላቸው። 7) በደህንነቱ ዘርፍ ኢንሳን ጨምሮ በሲቢሉ፤ በወታደራዊው በሙሉ አቅሙ አለ። የህገ ወጡም፤ የህጋዊውም ጠቅላይ አዛዡ ሌኮ/ አብይ አህመድ ናቸው። ሁሉንም አቅደው ለተፈለገው የሽብር ተግባር ያሰማራሉ። የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ትናንት የተፈጠረችው ደቡብ ሱዳን ሳትቀር ክንድ እንለካካ እያለች ነው። በባዕታችን ወረዳም ሰይማለች።ስሜን ሱዳንም ጦርነቱ ገታት እንጂ አና ብላ ገብታ ለም መሬታችን አፈራጣ ይዛለች። እንዲያውም ሱዳን እርስበርስ ጦርነት ባይኖርባት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ቅጣቱን በጎንደር በኩል ያንዶለ

#መንግሥታዊ #አናርኪዝም።

ምስል
#መንግሥታዊ #አናርኪዝም ። "ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ።"   የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ መተንፈሻ ቧን ከኦሮሞ ሊቃናት ውጪ አይታሰብም። ፈፅሞ። ከሰሞኑም አንድ የኦሮሞ ሊቅ የጽህፈት ኃላፊ አድርገው ሹመዋል። ማንን ፈርተው። ሃግ የሚል የለም።እራስ እግሩ እሱበእሱ። የ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶር ሙላቱ ተሾመ በምንም አግባብ እና በምን ውክልና እንደሆን አይታወቅም በዬቦታው ተኮፈውሰው አያለሁኝ። የኢትዮጵያን መንግሥት ወክለው በሁሉም መስክ አራጊ ፈጣሪ ናቸው። በዘመነ ህወሃት ስለመኖራቸው ቱክም ሹክም ሳይሉ የኖሩት ዶር ሙላቱ ተሾመ በተመሰጠረ ሥልጣን አክቲብሊ እዬተሳተፋ ነው። ማን ተፈርቶ? ማንስ አለና። ሞቅ ሞቅ ሲላቸው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ለሚያለዙት፤ ለሚያደነዙዙት ተከታዮቻቸው " #ኦሮሞ እና አማራ ቁጥሩን ለውጊያ ያውለው" እያሉ ያባጭላሉ። እሳቸው እራስ እግሩን የራሳቸውን ወገኖች ሃብት ማማ፤ ፖለቲካ ማማ፤ አህጉራዊ እና ሉላዊ ዕውቅና መንበር ላይ አስቀምጠው። የማይቀረው ነገር ግን ይህ ዘመናይነት ይቀደዳል። እሱ ባለው ዕለት። #ያለለት ። መኖሩም መትነኑም ያልተነገረለት ከ98% በላይ የሆነው የኦህዴድ ኦነግ ፓርላማ ይህን መሰል አናርኪዝም ጉዞ ፀጥ ረጭ ብሎ በዝምታ ሙሉ ድምፁን ይሰጣል። መብቱ ተጥሶ የፈለገ ነገር ተከውኖ አጽድቅ ሲባል በሁካታ እና በጥድፊያ #እያውካካ ያፀድቃል። "ነገርን ነገር ያነሳዋል" እንዲሉ ጋዜጠኞቻቸውን የሸኙት የኢትዮጵያ ህጋዊ ፕሬዚዳንት ወሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ ግን አሉ? ወይንስ ዶር ሙላቱ ናኙበት። ለመሆኑ ተመለሱ? ለነገሩ ምን አገባን እኛን። ለበይ ተመልካችነት እንኳን ያልተፈቀደልን ዘመናይነታቸውን እንኳን ማዬትም መብት አይደለም ተብሎ ሠርክ በድ