ልጥፎች

"የደርሶ መልስ ፊልም" በሚመለከት የእኔ ዕይታ።

ምስል
„የደርሶ መልስ“ ልቅና! በእኔአቅም ልቅም ቅኝት። „ጥበብ   ቤትዋን ሠራች፣ ሰባቱንም ምሰሶችዋን አቆመች   ”   ( ምሳሌ ፱ ቊጥር ፩ )  ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 23.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                                                                           ቅኔያዊት! ·          እ ፍታ። እንዴት ናችሁ ውዶቼ ክብረቶቼ። „ደርሶ መልስ“ በሚል እርዕስ በሁለት ምዕራፍ ወደ 28 ክፍሎች በፋና ቴሌቪዥን የቀረበ ተከታታይ የቴሌቪዥን ፊልም ነበር። ፊልሙ ከተለመወደው ወጣ ያለ ጭብጥን በምናዊ ርቀት በቅጡ የቃኜ ሆነው አግኝቻለሁኝ እኔ በግሌ። ሙሉውን ወደ ሦስት ጊዜ በጥሞና አይቸዋለሁኝ። እርግጥ ነው ለመዝንኛ ብቻ ልታይ ከተባለ፤ ወይንም ወጣ ገባ እያሉ ለማዬት ከታሰበ፤ ስለ ነፃነት ህሊናዊነት ካልተሰነቀ ጭብጡ መከበድ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ፊልሙን የማዬት ሃሞትም ፈሰስ ይልና መንፈስ ባክኖ ይቀራል። እኔ ግን ከዚህኛው ጎራ ስላልሆንኩኝ ለፈረንጆች የልደት ቀን ጸጥታ በርጋታ ስለሚሆን በዬዘመኑ ይህ ቀን ሲመጣ የመጻህፍት እርማት ሰሞናቴን አቅድ ዘንድሮ አስተላልፌ  የ2018 የመሸኛ ሰሞናትን ለ4ኛ ጊዜ እኔ በፈቀድኩት፤ በወደድኩት የሥያሜ ምርጫ „ራስመሳማን“ በተደሞ እዘልቃዋለሁኝ … ተቀጣጠርን። ቀጠሮም ሰዓትም ለዛውም በፍጽምና አክባሪ ስለሆንኩኝም ዝንፍ፤ ወትልፍ ሳልል እንገናኛለን፤ ደግመን እንተያዬአለን። የነገ ሰው ይበለን አማልካችን እኔና አቤቶ የቤት ውስጥ ዘንከትክት ብሎ ፊት ለፊት ጉብ ያለውን ደመ ግቡ ቴሌቪዥኔ ጋር። አይቀሬ ነው መደገሙ .. ለአርባዕቱነት … ·         ም

ነፍስ ይማር ሁላችንም ጠበቂዎች ነን ... መሰሉን ...

ምስል
ዴሞክራሲን ሊኖሩት የፈቀዱት ብቻ ብፁዕን ናቸው። „እንደ ጠቢብ የሆነ ሰው ማን ነው? ነገርንስ መተርጎም የሚያውቅ ማን ነው?“ መጽሐፈ መክብብ ፰ ቁጥር፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute© Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ለሌላው የተፈቀደ የተስፋ ዘመን ለሌላው ደግሞ የተቀፈደደ የጨለማ ዘመን ነው። አንዱ ያገኘው ያገኘውን ንጹህ አየር ሌላው ሲያገኝ ይቀናበታል። አዬሩን ሰጪ እኮ የነፃነት አዳዩ እኮ እሱ አይደለም። አለመታደል። ዛሬ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች የናፈቃቻቸውን አገራቸው እና ህዝባቸውን ማግኘት እኩል መብት ሆኖ ሳለ ግን ገደብ መጣል ወንጀል ነው። ጥፋት ከኖረም ካለም ቁጭ ብሎ መነጋገር ይቻል ነበር። እንዲህ ከሚሆን?   ·        ው ዶቼ እንዴት ናችሁ ይህን ስጽፍ ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ተስፋ እያለቀስኩኝ ነው … የአላዛሯ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ህልም ፈተና የጣለ አዲስ ክስተት ትንሽ ቀደም ባሉ ሰዓታት አነብኵኝ። ማመን ለመቻል ራሴን ከሁኔታው ጋራ ለማዋህድ ጊዜ አስፈለገኝ እና አንድ ሦስት ሰዓት ዘገዬሁኝ። ኢትዮ ሪጅስተር አልከፍትልኝ ካለ ሁለት ሳምንት አልፎታል። ለማረጋገጥ ፈልጌ አልቻልኩኝም። ዘሃበሻን ሰንበት እንዴት ይዟሃል ልል ስገባ፤ ሻማ የበራበት ፎቶ አዬሁኝ። ጹሑፍ እንዲሁ፤ ሥሙን እና ፎቶው አልመጣልሽ አለኝ። እኔ በአካልም በፎቶም አላውቀውም። እማውቀው ብራና ላይ  የብዕሩን ጠብታ ብቻ ነው። እርግጥ ነው እሱም እኔን ያውቃል በዜና፤ እኔም አሱን በዜና አውቀዋለሁኝ። እንድ - ደወልልት ስልክ ተሰጥቶኝ ትደውልልኝ ብሎ አልደወልኩለትም በ2013/2014  ይመስለኛል። እኔ በመደወል፤ በመተዋወቅ ዝንቅ ዝንቅ በማለት ባህል እጅግ ደካማ ነኝ ከምል አልተፈጠርኩበትም። ሰው ደውሎም ራሱ አላነሳም