ኢትዮጵያ የመልካምነት ህሊና እንጂ፤ ኢትዮጵያ የንግድ ሸቀጥ አይደለችም!

 

ኢትዮጵያ የመልካምነት ህሊና እንጂ፤ ኢትዮጵያ የንግድ ሸቀጥ አይደለችም!
"አቤቱ ጌታ ሆይ! ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
 
 
 May be an image of 1 person and smiling
 
ምዕራፍ ፲፮
 
ኢትዮጵያ የጅምላ እና የችርቻሮ #ሸቀጥ አይደለችም። እንዳሻህ በአሻህ ሰዓት እንዳወጣች የምትቸበችባት #ቁስም አይደለችም። ኢትዮጵያ ተፈጥሯዋ #ኦርጋኒክ ነው። እምየ ኢትዮጵያን #የተለበጠ ወይንም የተዳበለ አንዳች ባዕድ ኩነት አላበጃትም። ወይንም አልፈጠራትም።
ነብየ መሐመድ "ሂዱ ወደ ኢትዮጵያ" ሲሉ እሳቸው ስለፈቀዱ ሳይሆን አላህ የሰጣቸውን ነው መልሰው ለእስልምና ሃይማኖት አማንያን የሰጡት። ኢትዮጵያ አካል በሌለው የእግዚአብሄር አገልጋይ በቅዱስ ወንጌል ብዙ ጊዜ ተጠቅሳለች ከምል የዶግማው #ልዕለ መሠረት እሷው ናት ብል ይሻለኛል። 
 
ጥሞና ላይ እያለሁኝ እኔ አንድ ጀግና ጋዜጠኛ ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ሊካተት ይገባ ነበር ብሎ ሲሞግት፤ መላሹ ከሌላው ዓለም የተለየ #የቀደመ ነገር አልቦሽ እንደሆነች በልሙጡ ሲገልጹ ሰማሁኝ። ይህም ማለት ኢትዮጵያዊነት ወና መሆኑን ያጠየቀ ምላሽ ነው የተሰጠ። 
 
የአገላለጹ ኢሞሽኑ፦ ገፊ ኃይሉን ስበቱ እና ስበቃው ስታስተውሉት #የእርግማን መሆኑን ትረዳላችሁ። በጣም ኮሰኮሳቸው። ከስሜን ኢትዮጵያ ጋር መስተጋብር ያላቸው ዕውነቶች እንዲነሱ አይፈለግም።
 
ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ጆግራፊያዊ ክልል ሳይሆን ንጥረ ነገሩ ነው መታየት ያለበት። እኔ እምኖረው ሲዊዘርላንድ ነው። ኢትዮጵያዊ ተግባራትን በቋሚነት እሰራለሁኝ። የኢትዮጵያ ራዲዮ በሎሬት ፀጋየ መታሰቢያ እዚህ ሲሰራ ሞገሱ ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ነው።
መፃህፍቶቼ ለስድስት ጊዜ ያህል በሲዊዘርላንድ በብሄራዊ ኢንተግሬሽን የቤተ - መፃህፍት ጉባኤ ላይ ሲቀርብ ያው የኢትዮጵያ መንፈስ ይጎለብታል።
 
ጥብቆ ከሆነ የማንነት ቀውስ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኢሊት ሊወጣ ይገባል። ምርቃት የሚነሳውም ከዚህ መሰል የውስጥነት መሸፈት ይሆናል። ተወደደም - ተጠላም። በዚህ ውስጥ የኢትዮጵያን የመሪነት ንጥረ ነገር ስታስቡት መጠጊያ አልቦሽ ሲንከራተት በገኃድ ታዩታላችሁኝ። ኢትዮጵያ የምትመራው ደግሞ በኢሊት ነው።
 
አንድ ጊዜ ከአንከር ሚዲያ ጋር አውሮፓ ላይ ትልቅ ሥም ያላቸው ኢትዮጵያዊ እንዲህም አሉ…… "ኢትዮጵያ የሚለውን ሥም #መቀየር እንችላለን" ሲሉ ምንም ሳይላቸው አወያዩ አለፈ። እኔ እንዲያውም እኛ ሙተን ወይንስ ቁመን እየሄድን ብየ ጽፌ ነበር። እውነቴንም ነው።
መሳሬያ ጠበንጃ፤ ኮልት ያልታጠቅን፤ የብዕር ወታደሮቿን ቢንቁን፤ ቢያጣጥሉን፤ ቢያገሉን #ቢያስገልሉን፦ እንዳለንም ባይቆጥሩንም፦ አቅማችን የሰጠን ፈጣሪያችን ቲፍ አድርጎ በባረከልን ቅብዓዊ ስጦታ ስንኩሉን ሃሳብ #የማንበርከክ ክህሎቱ እንዳለን ሌላ ሳይሆን እኛው እናውቀዋለን። በዓዋጅ ይነገርልን፤ ይነጠፍልን ይጎዝጉዝልን የማንል አለንበት። ኢትዮጵያን ንቆ ኢትዮጵያን አድናለሁ የማለትን ዳጥ እና ገደላ ገደል #አይሰቡት
 
እነሱ መፈጠራቸውን በሚክዱት መዋዥቅ ውስጥ ሃራም ብለን፤ አክ እንትፍ ብለን ተጸይፈነውም የምንገኝ ዝምተኛ ልጆች አለናት ስለ እናታችን ዘብአደሮች ነን። ይህ በማይሻር ቃል በውስጣችን ለህትምት የበቃ ነው።
 
ከኳኳቴውም፦ ከሁካታውም ነጠል ብለን በራሳችን ቅይጥ ያልሆነ የጠራ ጎዳና የምንጓዝ የእትብቷ ፍሬወች አለን። ዝምታችን መንቀዥቀዥን ስለምንጠየፍ ብቻ ነው።
 
እናታችን ብትናፍቀን፤ ብታጓጓን እንጂ ፈጽሞ አትሰለችንም። ኢትዮጵያ ለእኛ ቀርቶ ለአፍሪካ፤ ኢትዮጵያ ለጥቁር ህዝብ፤ ኢትዮጵያ ለግሎባላይዜሽኑ #አንቱ ሊቀ - ትጉኃን ነው መንፈሷ። ተፈሪም። #የፊደል #ገበታ ናትም።
 
ለዚህም ነው እኔ ኢትዮጵያ የከበደችን ለሁላችንም ነው እምለው። ልጆቿ ሲያቃልሏታ፤ ሲያጣጥሏት ስለማስተውል። ሰንደቅ ዓላማዋን መልበስ ሳይሆን በክፋም በደጉም ዘመኗ የውስጥ መሃንዲሱ እና መሪው የተቀደሰው መንፈሷ እንዲሆን መፍቀድ ይገባል። በቋሚነት።
በምንም መንገድ ቢሆን የዘበጠ ዕይታ ስለ እናቴ ካለው መንፈስ ጋር ሥርጉተ ሥላሴ ዳማ ስትጫወት አትገኝም። መቼውንም። ሁሉም በመብቱ ልክ የሚሻውን መሆን ይችላል። እኔም የመብት እና የግዴታየ ካስማው የመፈጠሬ ምክንያታዊ #ጓል ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው። ዝንፍ ንቅንቅ አይልም ከዚህ አቋሜም። 
 
ወደ ቀደመው ስመለስ ያን ጸያፍ ውርዴ ስንኝ የተጠቀሙት ሙሁር የአንከር የሚዲያው ቋሚ ተንታኝ ሆነው አያቸዋለሁኝ። አዳምጫቸው አላውቅም። በባዕድ ስሜት የሚዳክርን መንፈስ ማዳመጥ መበክል ስለሆነ። 
 
እኒህ ሰው ምንአልባትም ወደፊት ተቃዋሚወች ለሚያስቡት የኢትዮጵያ አዲስ መንግሥታዊ አወቃቀር የብሄረሰብ ውክልና በሁነኛነት የሚታጩ ይሆናሉ። ይህ ገማና ነው ኢትዮጵያዊ ትውልዱን እንደ ግሎባሉ ዓለም አዲስ ትውልድ ዕድሉን፤ የዜግነት መብቱን፤ የእናት ፍቅሩን እየነጠቀ፦ #እያጓጎለ እያጎፈረም የሚገኘው። በዚህ መንፈስ ውስጥ ተስፋን አፈላልጉት። #ልሙጥ ነው። 
 
#ለኢሊቱ ኢትዮጵያ ምናቸው ናት? 
 
ይህን ጥያቄ አዲሱ ትውልድ ሊመረምረው ይገባል። በዚህ ልክ ላልተገኜ ሰብዕና ቅንጣት አቅም ሊባክን አይገባም። ከኢትዮጵያ ኢሊት ይልቅ የውጭ አገሩ የፖለቲካ፤ የታሪክ፤ የፍልስፍና፤ #የሥልጣኔ #ኢሊት አዲስ ቃል ነው ይሄ ኢሊቶች የበለጠ ኢትዮጵያ ይፈላሰፋባታል።
ልዑሉ ጀርመን በግዕዝ፤ በአማርኛ ቋንቋ ኢሊት መፍጠር ስለምን ፈለገ? ፖላንድን እማታስቡት አገር ነው። አማርኛ ቋንቋ ፕሮፌሽናቸው ነው። ለምን? ሚስጢርን እንደ ጣዝማ ከኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያዊነት ለመቅዳት ነው። ግን መጸሐፈ ፈውስ ለጀርመኖች ምን ውለታ ዋለላቸው? አንብቡ። ትዕዛዝ አይደለም። እህታዊ ዕይታ እንጂ።
 
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት የሚቃለል፤ የሚጣጣል፤ የትሜና የሚወረወር ክስተት አይደለም። #ኢትዮጵያዊነት #ዩንቨርስም ክስተትም ነው። ደፍሬ ነው እምናገረው። ያለኝን፤ የሰጠኝን፤ ያጎናጸፈኝን በሚገባ ጠንቅቄ ስለማውቀው። ኢትዮጵያዊነት እያንዳንዱ ዜጋ #ካሪክለም ተነድፎለት ሊማሩት የሚገባ ረቂቅ ክስተት ነው። 
 
ኢትዮጵያ ሳይንስ ናት።
ኢትዮጵያ ፍልስፍና ናት።
ኢትዮጵያ ህግ ናት!
ኢትዮጵያ ዩንቨርስ ናት!
ኢትዮጵያ ይሉኝታም ናት!
ኢትዮጵያ ፈርኃ እግዜብሄር፤ ፈርኃ አላህም ናት!
ኢትዮጵያ አክብሮት ናት!
ኢትዮጵያ ትህትና ናት!
 
አሁን ከሆነ ትናንት ያልነበሩ፤ ህወሃት መንበሩን ለቀቀብን ብለው በገፍ የመጡ ደራሽ ታጋዮች ሊያስፈራሩን፤ ሊያሸብሩን የሚፈልጉ ምርቃታቸውን አንድየ አማኑኤል በጥበቡ ያነሰባቸው ሰብዕናወች አሉ። #የነጠቡ። በሚያላግጡት - ያላግጡ። የሚያንጓጥጡትን - ያንጓጥጡ። 
 
ከማንም፤ ከምንም ዕሳቤ ጥገኛ ያልሆን በምንኖርበት አገር ቋሚ አሻራ ያለን #ጭምት ልጆች አሉት #ኢትዮጵያዊነት፤ ጭምት ልጆች አላት እምየ ኢትዮጵያ። በልካችን ስለልካችን እራሳችን ቀጥተን እና ከርክመን በእኛ ግድፈት የእናታችን ሥም እንዳይነሳ በበዛ ጥንቃቄ የምንኖር ልጆች #አለንላት - ኢትዮጵያ። 
 
ዝምታችን ከዳጥ እና ከመንጨባረቅ ጋር ሰብዕናችን እንዳይለካለክ ስለምንሻም ነው። አቲካራ አያስፈልግም። የሚያስፈልገው ቁምነገር የቁጥር ማሟያ ላለመሆን አቅማችን ቆጥበን እናስተዳድራለን። እኔ የማውቀውን ስንክሳር ለማድመጥ ቅንጣት አቅም አላባክንም። የምማርበት ሲሆን ብቻ አዳምጣለሁኝ።
 
የልጅ ፋሲል የእኔዓለምን ሚዲያ ፋኖ ዱር ቤቴ ከአለበት ዕለት ጀምሮ አዲሱ ቅኝቱን አዳምጬው አላውቅም። ተዋወቅን። የእኔ የሥርጉተ ሥላሴ ጆሮ መገለባበጫ ማትራስ አይደለም። 
 
ከእኔ አቅም በላይ፤ ከእኔ እውቀት በላይ የሆኑትን ምርጥ አድርጌ አዳምጣለሁ። በነገራችን ላይ ሚዲያውን ሥሙን እረሳሁት ኢኮኖሚስቱ አቶ ሙሼ ሰሙ ሰሞኑን የሰጡት ጠፈፍ ያለ ቃለ- ምልልስ አለ አዳምጡት። የተመጠነ፤ ብቁ ትንተና ነው። ለትውልድ የዕውቀት ስክነትም የሚረዳ። ከዛው ላይም ዕይታየን መጥኜ ሰጥቻለሁኝ። 
 
የሆነ ሆኖ በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ያለኝ አቋም ፍጹም የጸና ነው። ለምን? ኢትዮጵያ የሰጠችኝን አሳምሬ አውቃለሁኝ።
ቁጥቡ ሰብዕናየ የተቀዳው፤ የተቀረጸው በእሷ ቅዱስ መንፈስ፤ የመልካምነት እና የተፈጥሯዊነት አውደ ምህረት ነውና። በማናቸውም ሁኔታ አቅም ስመግብ ለእናት ኢትዮጵያ ክብር እና ልዕልና ይጠቅማል ወይ ብየ አስልቼ ነው። መዝኜ ነው። እንደ ዱሮው እንደ ወንዝ ዳር አሽዋ የሚዛቅ የአቅም ብክነት ከእኔ ቤት አሁን ላይ የለም። ወደፊትም አይኖርም።
 
አማራነቴም የሚቀዳው ምንጩ ከኢትዮጵያዊነቴ ነው። ሁለቱ ውህድ ናቸው። ህወሃት እያለ አማራ ነኝ ብሎ ወጥቶ ያልታገለ በዛ ተጋድሎ በደራሽነት ተመዝግብ ለክብር በቅቶ መነሻ መሠረቱን ተንጠራርቶ ሲያጣጥልም አስተውላለሁኝ። ማለቅም፤ መንጠፍጠፍም እንዲህ እና እንዲያም ያደርጋል። 
 
በዘመን ስጦታ በግሎባላይዜሽን ከኢትዮጵያዊነቴ መንፈስ ያፈነገጡ መንፈሶች ለፓን አፍሪካኒስቷ ኢትዮጵያ አይምጥንም። መብት እና ግዴታን ማወቅ ሙሉ ሰው ያደርጋል። 
 
አንድ ሰው የመብቱን ጣራ እና ግድግዳ በዕውነት እና በመርኽ ልክ ሊያውቀው ይገባል። ስደት ላይ ያለውም መኖሩ መሠረቱ እናት አገር ሆና፤ እሷን ተጠይፎ ከሆነ አይቀናውም። ለዚህም ነው ራዕዩ ሁሉ የዕንቧይ ካብ ሲሆን የኖረው።
 
የህወሃት ፈቅዶ ሥልጣኑን መልቀቅ ከሆነም ባለቤቱ #ዊዝደም እና ልዑል #እግዚአብሄር ብቻ ናቸው። ከዛ በኋላም ድንገቴ በረከቶች ምንጫቸው ከዛው ይቀዳል። ከላይኛው። የዊዝደም ፈጣሪም መሪም አማኑኤል ብቻ ነው። 
 
ያ ሁሉ ለቁጥር አታካች የፓርቲ መዋቅር፤ የሰበነክ ተቋማት ብዛት የትግሉን መቋጫ አላበጁትም። ዕውነቱ ይህ ነው። ለህወሃት እራሱ የተፈጠረው ነገር እንግዳ ነበር። ያን የማስተዳደር አቅም አልነበረውም። ሁነቱ የቀደመ ከሱ እጅ የወጣ ስለነበር።
 
ስለሆነም #ሳይባክኑ ሌላውንም ሳያባክኑ በስክነት አገርን ህግ ሳይጣስ፤ በሥርዓት ሊያስቀጥል የሚችል፤ ትውልድን በራስ መተማመን፦ በሞራል በሚያንጽ ትህትና እና ተፈጥሯዊነት ላይ አተኩሮ በተከታታይነት መስራት ይገባል። መግለብለብ /// መገለብን ያከናንባል።
ስክነት እና እርጋታ ግን አስተማማኝ ትውልድ ያበረክታል። መባረክ ከበረከተ ትውልዱ ለአፍሪካ ሮል ሞዴል የመሆን አቅሙን ይፈጠራል። የትውልዱ የመኖር ዋስትናው ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊሟላ ይገባል። የብልጽግና መንግሥት ይህ በኽረ ጉዳይ መብቱ ሳይሆን ግዴታው ነው። 
 
የእኔ ክብረቶቼ እንዴት አረፈዳችሁልኝ። ደህና ናችሁ ወይ? ደህና ዋሉልኝ። አሜን። 
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
27/08/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?