#መኖሬ #ካንፓሴ። መኖሬ #ኮንፓሴ።
ነገር ወጣቶች ሆይ! ዕድሜያችሁ የሚፈቅደውን ሃይማኖታችሁ፣ ትውፊታችን ባህላችን በሚፈቅደው ልክ የአጤ ወጣትነት ሥጦታ እንደ እኔ እንዳታባክኑት አደራየ ከውስጥ ነው፣ ከልቤ እና ከእውነቴ እግዚአብሄርም በሚያውቀው እንዲህ አምር እንደ ነበር #አላውቅም ነበር።
ለካንስ ወጣትነት ውበቱ ዲካ የለሽ እንዲህ ነበር። #ገርሞኛል። #የዕውነትም #ደንቆኛል። የፖለቲካ ህይወቴን ብቻ ነው እኔ እማውቀው። ሌላማ በወጣትነት ያለው ፈታ፤ ዘና ያለው የሳቅ እና የሰናይ ጊዜ ከወዴት አባቴ፤ የሚገርመው ዛሬም በዛው መቀጠሌ ነው።
የእምየ ሲዊዝሻ ረቂቅ #መንፈሳዊ #ጭምታዊ ድባብም ባልጠላውም፤ የወጣትነት ጊዜየን ባሳለፍኩበት #ክድን ባለ ህይወት እንዲቀጥልም ተጽዕኖ ያለው ይመስለኛል። በወጣትነት ፖለቲከኝነት ሌላው ቀርቶ የአማኑኤል ሥጦታ የሆነውን የደም ግባት እንኳን #እንዳታስተውሉት ግርዶሽ ይሠራል።
የእኔ ክብሮች ደህና ናችሁን? ኑሩልኝ።
ሥርጉትሻ። 26/08/025
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ