#ጦርነት #ቤርሙዳ #ትርያንግል ነው። #አስማጭ። "አሜሪካ ባቀረበችው የዩክሬን የሰላም ዕቅድ ላይ በሚደረገው ንግግር "ከፍተኛ መሻሻል" መታየቱ ተገለጸ" BBC
"አሜሪካ ባቀረበችው የዩክሬን የሰላም ዕቅድ ላይ በሚደረገው ንግግር "ከፍተኛ መሻሻል" መታየቱ ተገለጸ"
"አሜሪካ፤ የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነትን ለመቋጨት ያቀረበችውን የሰላም ዕቅድ በተመለከተ የሚደረገው ንግግር ላይ "ከፍተኛ መሻሻል" መታየቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ተናገሩ።
ሩቢዮ፤ የዩክሬን እና አውሮፓ ተደራዳሪዎች በሲውዘርላድ ጄኒቫ ከተማ ካደረጉት ስብሰባ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ነገር ግን "አሁንም፤ መከናወን ያለበት የተወሰነ ስራ አለ" ብለዋል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቭሎድሚር ዜሌንስኪ በበኩላቸው "የፕሬዝዳንት [ዶናልድ] ትራምፕ ቡድን [የምንናገረውን] እያደመጠን ስለመሆኑ የሚያመለክቱ ፍንጮች" እንደነበሩ ገልጸዋል።
በአሜሪካ የተዘጋጀው እና ለሩሲያ ያደላ ተደርጎ የታየው የሰላም ስምምነት ዕቅድ ሾልኮ ከወጣ በኋላ ዩክሬን እና አውሮፓውያን አጋሮቿ ስጋታቸውን አሰምተዋል። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደግሞ ዕቅዱ ለሰላም ስምምነት "መሠረት" እንደሚሆን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ፤ ዩክሬን "እጅግ ከባድ ምርጫን ልትጋፈጥ ትችላለች፤ ክብርን ማጣት ወይም ቁልፍ አጋርን የማጣት አደጋ [ያጋጥማታል]" በማለት እቅዱ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ሲገልጹ ተደምጠዋል።
ሩቢዮ፤ እሁድ ምሽት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በጄኔቫ የሚገኙት ተደራዳሪ ቡድኖች "በጣም ጥሩ ቀን" እንዳሳለፉ ተናግረዋል።
የንግግሩ ዋነኛ ዓላማ፤ 28 ነጥቦችን በያዘው የአሜሪካ የሰላም ዕቅድ ላይ የሚገኙ "ክፍት ጉዳዮችን" ለማጥበብ መሞከር እንደሆነ አስረድተዋል። በንግግሩ የተሳተፉ አካላትም ይህንን ግብ "ተጨባጭ በሆነ መልኩ" ማሳካታቸውን አስታውቀዋል።
አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማት በበኩላቸው የትኛውም የመጨረሻ የስምምነት ሰነድ ወደ ሩሲያ ከመላኩ በፊት በዩክሬን እና አሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ስምምነት ላይ ሊደረስበት እንደሚገባ አብራርተዋል። የሰላም ዕቅዱን ዝርዝር በተመለከተ አሁንም ቢሆን ሊሰራባቸው የሚገቡ የተወሰኑ ጉዳዮች እንዳሉም ጠቁመዋል።"
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ