እንኳን ደስ አለሽ ቅድስቴ ሲዊዚሻ።
እንኳን ደስ አለሽ ቅድስቴ ሲዊዚሻ።
የሲዊዝ ድንቆች በውብ ትዕይንት በበርሊን ስታዲዮ #ኢጣሊያንን 2 - ለ0 በሆነ ውጤት ለቀጣይ ዙር ጨዋታ የመጀመሪያው ቲም ሆነዋል።
ጨዋታቸው እጅግ ውብ፤ የተረጋጋ፤ ሥርዓት የነበረው ነበር። የሲዊዝ ቲም በአጨራረስ ላይ በነበረ ግድፈትብዙ #የግብ ዕድል አምልጧቸው ነው እንጂ ቢያንስ 4ቷን የማምጣት ዕድል ነበራቸው። ዛሬ ሲዊዞች ምንም ዓይነት ቢጫም፤ ማስጠንቀቂያም አልገጠማቸውም። በፍፁም የተረጋጋ መንፈስ ነበር የተጫወቱት።
ከረፍት በፊት የሲዊዘርላንድ ቲም በአንድ ግብ ለእረፍት ሲወጣ፤ ከረፍት መልስ በሰከንዶች ልዩነት ሁለተኛዋን ደገሙ እና የጣሊያን ቡድን ተስፋ ደመና አለበሱት።
የዕለቱ ዳኛ ፍፁም የተረጋጉ ስለነበረ ለዲስፕሊን ጨዋታ ምቹ ነበሩ። ከእረፍት መልስ እሜቴ ድንቡልቡል 65% በሲዊዝ ቲም ሥር ነበረች። ዕውነት ለመናገር ጎል ጠባቂ ሶመር ብዙም ሥራ አልነበረበትም ማለት ይቻላል።
የጣሊያን ቲም አመዛኙ ጊዜው በመከላከል፤ የሲዊዝ ቲም በማጥቃት እና በመከላከል ጥምር ቅልጥፍና ድፍረትም ታክሎበት በጥሩ ጨዋታ ለውጤት በቅቷል። የሲዊዝ የዕለቱ አሰላለፍ 3.4.3 ነበር ከጀርመን ጋር በነበረው ግጥሚያ አሰላለፋ የተለዬ ነበረ። ጀርመንን ሙሉ 90 ደቂቃ አንድ ለምንም የመራው የሲዊዝ ቲም በተጨማሪ ጊዜ ነበር ጀርመን አንድ ግብ በማስቆጠር ከምድቡ የመሪነቱን ቦታ ሳያስነካ ያጠናቀቀው። በዛ ጨዋታም የቅድስት አገር ሲዊዝ ቲም የጨዋታ ብልጫ ነበረው።
ጨዋታ እንዲህ ያልተጠበቀ ነጥብ እና ያልተጠበቁ ቡድኖች ወደፊት ሲመጡ ይማርካል። የአውሮፓ እግር ኳስ በዕለቱ ቀዝቀዝ ብሎ ቢጀምርም አሁን እዬተሟሟቀ ነው። የክሩ፤ የዩክሬን ቲም መሰናበታቸው ቢያስከፋም እንደ ሲዊዝ፤ እንደ ኦስትርያ ያሉ ቡድኖች ደግሞ ባልተገመተ ሁኔታ ከዚህ መድረስ ጨዋታውን እጅግ አጓጊ አድርጎታል።
ሥርጉትሻ።29/06/024
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ