ኧረ።
ኧረ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
እንዴት ሰነበታችሁ?
እባካችሁ ለፖለቲካ መሪወች፤ ለተፅዕኖ ፈጣሪወች፦ ብላችሁ ማህበራዊ ኑሯችሁን አታውኩ። የውስጥ ሰላማችሁንም
አትቀናቀኑ። # አናውቃቸውም።
መደገፍ መብት ነው፤ መሞገትም። ግን እነሱን አምናችሁ እና ተማምናችሁ ከጽኑ ወዳጃችሁ ጋር አትለያዩ። ትናንት ከብክበን መስክረንም ሌት ተቀን ተግተን መንበር ላይ ያወጣናቸው ዛሬ ኢትዮጵያን እስከመቀናቀን ደርሰዋል።
ማህፀንን እንደ ዱባ የሚቀረድድ መራር ሸክም። የሞግትናቸውንም // ከደገፍናቸው ጋር ስናነፃጽረው ግብረ መልሱ ከራሳችን ውጪ በፍፁም ልባችን ማንንም ማመን ምን ያህል ውስጥን እንደሚያቆስል እያዬሁ ነው።
ኧረ! ለሁላችን አምላካችን // አላሃችን ልብ ይስጠን። አሜን። ውዶቻችንም በማያዘልቅ አመክንዮ ብለን አንጣ። በተለይ የውስጥ ሰላማችን ለሌላ ሰብዕ ብለን አንጣ። #አንተዋወቅም። እኛ ላዩን እነሱ ውስጡ ለውስጥ ሲጓጓዙ ነው የኖሩት።
ሥርጉትሻ024/07/02
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ