ትዝብት።

 ትዝብት። 

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"


አንድ ግንኙነት ዲስፒሊን ሊኖረው ይገባል። አንድ ተቋምም ዲስፕሊን ሊኖረው ይገባል። እንኳንስ የፖለቲካ ድርጅት። እኔ ዛሬ ጓዶቼን ባገኝ፤ ለዓይነ ሥጋ ቢያበቃኝ እንደምን ሐሤት ባገኜሁ። ቃል ኪዳኑ ሰው ሠራሽ አይደለም እና። በወል፤ በጋራ የተከወኑ ተግባራት ለጎርፍ ሲሸለሙ ስመለከት ገረመኝ። ታማኝነት፤ ኪዳን፤ ውል፤ ቃል በኢትዮጵያ የፖለቲካ፤ የማህበራዊ ኑሮ መና ወና ሆኑ።

 በዚህ ውስጥ መሪነትን እሰቡት። ልሙጥ አልሆነባችሁም። የሚቀር ነገር የለም። የተዋጠ ቅቤ አይቀርም። ከምንጊዜም በላይ ክውን ብዬ በራሴ ራዕይ እና ግብ መትጋቴ የእኔ ሳይሆን የላይኛው እርዳታ መሆኑን ተገነዘብኩኝ። ተከርክሞ ክውን ብሎ ገድሞ መኖር በቢሊዮን ዶላር የማይገኝ ሥጦታ ሆኖ አገኜሁት።

 ሰው ከሰው ጋር ሲኖር፤ ሲሰራ፤ ሲወዳጅ እኮ ብዙ በጣም ብዙ ነገር ሊታወቅ ይችላል። ያን ጊዜ ጠብቆ የጥቃት ሚሳኤል ማድረግ ነውር ነው። #መጠበቅ//መጠበቅ እንደምን ያቅት። "አቤቱ ለአንደቤቴ ጠባቂ አዘጋጅ።" አሁን ሚዲያ ላይ የሚገኝ ህዝብ እኮ ገብያ ማለት ነው። ይፈታል። እና የተቋምን ቃልኪዳን ማፍሰስ? ሥርጉ2024/07/02

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።