የሰባዕዊነት #ሐዋርያዊት ቅድስት አገር #ሲዊዘርላንድ።

 

የሰባዕዊነት #ሐዋርያዊት ቅድስት አገር #ሲዊዘርላንድ
 
"አድርገኽልኛል እና አመሰግንኃለሁ።"
 No photo description available.May be an image of 1 person, playing soccer, playing football, crowd and textMay be an image of 1 person and playing soccerMay be an image of lake
 
 
እንደ አገር አስተዋይ አገር ብርክታዊቷ ሲዊዘርላንድ። እንደ ሕዝብም አስተዋይ ህዝብ ሲዊዛውያን። በብዙ አጋጣሚወች ብዙ ሲዊዛውያንን አግኝቻለሁ፤ የማድመጥ አቅማቸው፤ ልታይ ልታይ አለማለታቸው፤ ለሰው ልጅ ያላቸው ጥልቅ ፍቅር እና አክብሮት፤ ለመርዳት ያላቸው ፍጥነት፤ ለውሳኔ ቁጥብነታቸው ይገርማል። ይደንቃል። ያስተምራል። 
 
አንዱ ወይንም አንዷ ሲዊዛዊት በራሳቸው የትምህርት ተቋማት ናቸው። እንደ እኔ ሲዊዞች በተፈጥሯቸው ፖዘቲብ ቲንከር ናቸው። ካቀረቡ ከውስጣቸው፤ ሲለዩም በነበረው የፍቅር ደረጃን ሳያጓድሉ፤ ሳያስተጓጉሉ ነው። ሁልጊዜ በሚገጥሙኝ ዕድሎች ሁሉ ተምሬባቸዋለሁ። ልዩ ናቸው እና። 
 
መፃህፍት ሦስቱን በአንድ ላይ አሳተምኩኝ። ቤቴ አራተኛ ፎቅ ላይ ነው። መፃህፍቶችን በእሷ መኪና ጭነን አምጥተን ተሸክመን አመላልሰን ቤት አስገባነው። ጓደኛዬ ሲዊዛዊ የህክምና ዶር ናት። ይህ ትህትና፤ ይህ ታዛዥነት ለአንዲት ስደተኛ #ማንም#ምንም ለሌላት ባተሌ። ከጨረስን በኋላ ምን ነክቶን ነው ግን አጋዥ ሰው እኮ መቅጠር እንችል ነበር አለች እና ጅልነታችን ያስቃል አለች።
ሌላ ጊዜ ደግሞ የገዛሁት እና የመጣልኝ ዕቃ ትክክል አልሆን አለ። ክርክሩ በሙያ እንዲታገዝ አማካሪዬ ከቦታው ድረስ አብረውኝ ሄደው ከእኔ ጋር ሞገቱል። ሌላም ሌላም ነገር ማንሳት እችላለሁ። የትም ሄጄ #ተከፍቼ እምመጣበት ሁኔታ የለም። 
 
ጭምት - ቅን፤ ሰባዕዊ - ተፈጥሯዊ፤ አጽናኝ - ደግ፤ ሥልጡን - ሩህሩህ፤ ትጉህ - ታጋሽ፤ ድንቅ - ውብ፤ ፈርኃ እግዚአብሄር የሰከነባት፤ ዲሞክራሲ በሚዳሰስ በሚጨበጥ መልኩ #ዕውን የሆነባት ልዩ፤ ፍፁም ልዩ አገር ሲዊዘርላንድ።
 
ክውን - ጥንቁቅ፤ ፍፁም ሰላማዊ - ምድራዊ ገነት፤ ምሩቅ - ብሩክ አገር ቅኒት ሲዊዘርላንድ። የአይዟችሁ ሞዴል - ጥልቅ -የዊዝደም ባለቤት፤ ርጉ - ማራኪ፤ አጓጊ - በራሷ የምትተማመን ጌጥማ በዕት ሲዊዝሻ። ሞድርን ፅዱም!
 
በህይወት ኑሬ ሁሉን ባደርግልሽ፦ ውለታሽን ብመልስ እንዴት እግዚአብሄርን ባመሰገንኩ ነበር። ሥጦታዬም - ሽልማቴም ነሽ እና። ልቤ ቢከፈት አገሬ ኢትዮጵያ እና አንቺ እኩል ደረጃ ላይ ትገኛላችሁ። በፍፁም ርህራሄሽ ልቦናዬንም መንፈሴንም ገዝተሽዋልና። 
 
የሰው ልጅ ስለምን እንደተፈጠረ ሚስጥሩን ያነበብሽ፤ የተረጎምሽ ያመሳጠር ልዩ ፍፁም ልዩ አገር ሲዊዘርላንድ። ህግ አክባሪ ለሰው ልጆች ሁሉ ተጨናቂ፤ የመቻቻል አንከር ተደሟዊት ሲዊዝሻ ኑሪልኝ የእኔ ውድ የልቤ አልማዝ። 
 
በጽኑ ታምሜ ከጎኔ ያልተለዬሽ እናት ዓለም ሲዊዚሻ ዓርማዬ የህሊናዬ አሻራ፤ በእናቴ ጥልቅ ሃዘን ስጎዳ ሳትሰለችኝ፤ ሳትገፊኝ በለት ዕለት ህይወቴ ሳይቀር ያደረገሽልኝ ልዩ አትኩሮት በልቤም በህሊናዬም እንደ ታቦት ተቀርፆል። የሰባዕዊነት ፈላስፊት ሆይ፤ የሰዋዊነት ሳይንቲስቴ ሆይ አንች እኮ ለሰው ልጆች ከፈጣሪ ተባርከሽ የተሰጠሽ ሐሤቴ ነሽ። መውደድ ስለ አንቺ በጉነቱ ቃሉ አይገልጽልኝም፤ ማፍቀርም እንዲሁ ውስጤን አያብራራልኝም የሃይማኖቴ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፀሎቴ ነሽ። 
 
ፈፅሞ #አላጋነንኩትም የሆንሽልኝ ነው እምገልፀው። ማን እንደ አንቺ ለእኔ አለ እና። ያላደረግሽልኝ አንዳችም ነገር የለም። በአገሬ ዕንባ ባለመቆሙ ለትጋቴ ዋስ ጠበቃ መጠጊዬ ዕንቁዬ ነሽ ሲዊዝሻ ትርታዬ። አዬርሽ ፀዓዳ መንፈስሽ የእዮር ምርቃት የዘለቀው ሚስጢር ርግብዬ። ፋናዬ ብርሃኔም ነሽ። ያለሽኝ። ኑሪልኝ ለዘለዓለም። አሜን።
 
ብሩክ እና ቅዱስ አገር፤ #መምህር እና የመልካምነት የፊደል ገበታ አገር፤ ለተፈጥሯዊነት አናባቢ ተነባቢም አገር ሲዊዚሻ ኑሪልኝ። ሰው ወዳጁ፤ ቁጥቡ፤ የተረጋጋው ህዝብሽን እግዚአብሄር አምላክ ይጠብቅልኝ። አሜን።
 
"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ።" 
 
የዓለም ሊቃናት፤ የዓለም ሊህቃን አንቺ ለሰው ልጆች ያለሽን ክብር እና ጥልቅ ፍቅር ቢመራመሩበት ልቤ ይሽታል። የልብ ፈለግ አንቺን ፈጣሪ ለአምክንዮ እንደፈጠረሽ የምርምር ማዕከል ብትሆኚ ምኞቴ ነው። መኖር በአንቺ ውስጥ ዩንቨርስቲ ነውና። መዋዕለ ዕድሜን ገርቶ ሰው አድርጎ በሰባዕዊነት ዋልታ እና ማገር አድርጎ ይቀርፃል ረቂቁ ቅዱስ መንፈስሽ። ታድለሽ። 
 
እግዚአብሄር አምላክ ሁሉን #አትረፍርፎ የሰጠሽ የትህትና ልዕልት ነሽ እና። ፍፁም ቁጥብ። ከጣልቃ ገብነት እራስሽን ያቀበሽ አስተዋይ። ሰማያዊው እና ምድራዊውን አስተምህሮ አዋህደሽ የሆንሽ ማንጠግቦሽ ነሽ ለእኔ።
 
ምስጉን - የተመሰገንሽ፦ ክብርት የደግነት ንግሥት፤ የመልካምነት #ዘውድ - ለሰው ልጅ መፈጠር ምድራዊ ገነት አድርጎ አማኑኤል በእጁ የሠራሽ #ጠቢብ አገር ሲዊዚሻ። #ዕውነት ነሽ። #መርኽ ነሽ። ሲዊዘርላንድ ሆይ ሁለመናሽ ከሰው ልጆች ህሊና አቅም በላይነሽ የሚል ሙሉዑ መደምደሚያ ላይ ደርሻለሁ። 
 
ማህሌቴ
ሰላማዊቴ
ህሊናዊቴ
ክብርቴ
ቅድስቴ
ብርክታዊት
ቅኒት
ተደሟዊት
ዕድምታዊት
ሰዋዊት
ተፈጥሯዊት
መቻቻላዊት
ፊደላዊት
እንዴት ናችሁ ውዶቼ? ኑሩልኝ። አሜን። 
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
SerguteSelassie
02/07/024

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።