የዓድዋ ድል ሆይ #ይቅርበለን።
እኛነታችን በግርማ፤ በሞገሥ ያላቀ፤ የእኛነታችን ንጥረ ነገር ለዓለም የገለጸ #ራዲዮሎጂያችን የዓድዋ ድላችን።
"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"



የዓድዋ ጥንካሬ፤ ብርታት፤ መንፈስ፤ ህይወት፤ አቅም እና ክህሎት #ዊዝደሙን አክሎ ከእኛ ጋር ይሁን። አሜን።
አድዋ - ለእኔ፤
ዓድዋ - ለእኛ፤
ዓድዋ ለሁላችንም እኛነታችን የሰጠን፤ የማድረግ፤ የመሆን አቅማችን ለዓለም የገለጠ #ራዲዮሎጃችን ነው።
የስላቅ መደርደሪያ ካንፓስ ሆንበት። እኛ ለዓድዋ ለተፈጥሯዊ አቅሙ #እንቅፋት ሆንበት። ይህ እርግጥ እና ዕውነት ነው።
የአድዋን ክብር እና ልዕልና አብዝተን ተዳፈርነው። አንድነትን ዓድዋ ሰጠን። እኛ ግን ለመቆራረጥ ህግ አርቅቀን አጽድቀን #በአንቀጽ 39 ስንፎክር እንገናኛለን።
ጋዜጠኛ ሆኖ የአንቀጽ 39 ሞጋች ከመሆን በላይ ምን አሳፋሪስ፤ አንገት አስደፊ የታሪክ አሰርነት አለና?
ኢትዮጵያ አጀንዳዬ አዬደለችም ማለትስ ከማን ከዬት የተወረሰ #ቋቁሻዊ ዕሳቤ ይሆን????
በውነቱ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ፤ ልካችን ሳናውቅ በዓድዋ ድል #ክብር ዕውቀት የአመራር ክህሎት፤ ልቅና እና ልዕልና ልክ መሆን ላልቻልን የስንፍና #ግዞተኞች እግዚአብሄር አምላክ ማህሪ ነውና ምህረቱን ይላክልን። አሜን???
በውነት ተሳስተናል። በውነትም ከዊዝደማችን ጋር ፈቅደን #ተካክደናል። ፈጣሪ መርቆ ከሰጠን ከብልህነታችን ጋር ወደን #ተላልፈናል እና የዓድዋ ድል ሆይ! ይቅር በለን። አሜን።
የማከብራችሁ እጅግም የምትናፍቁኝ የአገሬ ልጆች እንኳን አደረሰን ለማለት፤ ለመባባል እንኳን #የንጽህናችን ልክ ምን ያህል ይሆን? ለድሉ #ድንግልናችንስ በምን ሁኔታ ላይ ይሆን?
ያን የድል መንበርን ዝቅ ብለን ይቅርታ ልንጠይቀው ይገባል። ቀና፤ ዘለግ፤ ገዘፍ ያደረገን የዕውነት፤ የፋክት #ሰንደቃችን ነውና።
#ፈላስፊት ኢትዮጵያ እንኳን ለንጹሁ ተፈጥሯዊው የድልሽ ዕለት ደረሽልን። አሜን።
ውብ ጊዜ ለማህበረ የዓድዋ ድል ልጆች እመኛለሁኝ። አሜን።
ዓድዋ ድሉ፤ ዓድዋ ክብሩ፤ ዓድዋ መንፈሱ ከእኛ ጋር ቢገናኝ፤ እንደ ሰው ቢጠይቀን፤ በፍርድ ቤት በዓለም አደባባይ ቢገትረን መልሳችን ምን ይሆን? ከአድዋ ድል ፊት ለመቆም አቅሙስ #ድፍረቱስ ይኖረናልን?
ለመሆኑ እኛን አስተካክሎ ለሰጠን የክብራችን ማዕረግ የሆነውን ቤተ - የዓድዋ ድልን ለመካስ ምን መሰናዶ ይኖረን ይሆን? ምንስ #ለካሳችን አዘጋጀን? የዓድዋ ድል ተበድሏል።
ነፃነትህን ለሰጠህ #ገድል ነፃ አውጪ ስታደራጅ፤ ነፃ ዓውጪን - ስትመራ፤ ያንን - ስትከበከብ ለቆዬህ ሁሉ ፈጣሪዬ ልብ ይስጥህ። አሜን።
የእኔ የምትለው #በቂነት እያለህ የትውስት #የፊደል ማንነት እርቦህ በዛ ውስጥ ያለህ ሁሉ ከቻልክ በቅንነት ከዓድዋ ድል ሥር እግር ሥር ወድቀህ ብርሃኔ እና ጌጤ የዓድዋ ድል ሆይ! ይቅር በለኝ ማለት ካለቀጠሮ ሊሆን ይገባል።
በትውስት የፖለቲካ ዕሳቤ #ሰሃ ተፈጥሯዊ ምሩቅ ማንነትን ክዶ ልጥፍ ማሰኜት የተገባ ባለመሆኑ ከግድፍት ወጥቶ፤ እራስን አርሞ እና ገርቶ ታሪክን #ሳይፈቀፍቁ በታሪኩ ልሳን ልክ መመስከር፤ መዘከር ይገባል። #በድንግልና እና በንጽህና።
ምንጊዜም የዓድዋ ድላችን ብርኃናችን!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02/03/2026
እኛን በእኛነት ተርጉሞ ለመቀበል ያብቃን። አሜን።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ