ዓለም ዓቀፍ #ሸላሚ ድርጅቶች ይህን ትጋት፤ ደግነት በትህትና ልግስና በትዕግሥት የደግነት ተግባር ሲጎመራ ምን ያደርጉ ይሆን???

 

ዓለም ዓቀፍ #ሸላሚ ድርጅቶች ይህን ትጋት፤ ደግነት በትህትና ልግስና በትዕግሥት የደግነት ተግባር ሲጎመራ ምን ያደርጉ ይሆን???
 
"እግዚአብሄር በአንድም በሌላም
ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።"
(ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱) 
 
 
 
 
ለትውልድ የሆነ #መሰጠት። ለአደራ ያበቃ #አጽናኝነት። ባለ አሻራ #አይዟችሁባይነት። ድንቅ - የሚያስቀና - የሚመስጥ ሰብዕና። ዕጣ ነፍስ #በይቻላል መንፈስ ችግርን የመጋፈጥ ልዩ ተጋድሎ። አንድ መጸሐፍ ይወጣዋል። የፕለይ ፀሐፊወች ይህን የዕውነተኛ ታሪክ ጭብጥ ትዘሉት ይሆን???
 
የእዮር #መሰጠት። ዓለም ዓቀፍ ሸላሚ ድርጅቶች አሜሪካ እና ካናዳ ያሉትም የኢትዮጵውያን ተቋማትም ይህን ብቃት #ባሊህ ይሉት ይሆን ወይንስ #ያገሉት??? እምናዬው ይሆናል።
 
አብነትትነት ይህ ነው። #አሻራ ይህ ነው። የአገር #ካስማነት ይህ ነው። #የትውልድ መሆን ይህ ነው። #ሰዋዊነት ይህ ነው። #ተፈጥሯዊነት ይህ ነው። 
 
 እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መክሊት ይዞ ይወለዳል። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #ጥሪ ይዞ ይወለዳል። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መልዕክት ይዞ ይወለዳል እላለሁ። መፃህፍቶቼ ላይም አበክሬ እገልፀዋለሁ። ይህ ጥሪ፤ ይህ ለደግነት ፖስተኝነት፤ ይህ ችግርን ተቋቁሞ ለመፍትሄው የመምራት የማስተዳደር ብቃት እንዳይሰወር ስለምሰጋ ነበር እንደዛ እምተጋው። 
 
እንዲህ በጥሪ ልክ ሆኖ መገኜት #መታደልም - #መመረቅም - #መሰጠትም ነው። አንድ ሰው ይህን ያህል ችግርን የመቋቋም አቅም ከዬት አገኜ? #ከእዮር #አደባባይ#ቅንነት የሰራው #ደግነት ነው። 
 
ሁሉም ለአንዱ ፦ አንዱም ለሁሉም እንዲህ በቅንነት ቢተጋ ድካማችን በቀነሰ ነበር። በሥጋ ብንለይም ነፍሳችን ሐሤት ባገኜች ነበር። ግን እኛ እና ደግነት ቀርቶ እኛ እራሳችን አሸንፈን ለትውልድ የመሆን የማክበር ሥርዓትን ለመፈፀም እኮ ምጣችን ነው። 
 
አክብሮ ለመሞገት፤ አክብሮ ለማድነቅ፤ አክብሮ ለመከራከር ተከባብሮ ተገናኝቶ ተከባብሮ ለመለያዬትም። 
 
የሆነ ሆኖ አዲስ ምዕራፍ፤ እሸት ክስተት ነው የሆነብኝ። የማቱሳላን ዕድሜ እመኛለሁ። የአገር ውስጥም የውጭም ሸላሚ ድርጅቶችም እሰቡበት። ከዚህ በላይ ልቅና፤ ከዚህ በላይ ልዕልና፤ ከዚህ በላይ ዊዝደምም የለም ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። መከታ፤ ጋሻ ጥላዬ ማለትም እችላለሁኝ። 
 
የእኔ ክብሮች እንዴት አደራችሁ። ደህና ናችሁን።
 
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02/08/024
መባረክም በረከትነትም እንዲህ ነው። #መታደል!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።