#አመድ አፋሹ አማራ … መጨረሻህ ናፈቀኝ …02/08/2021
#አመድ አፋሹ አማራ … መጨረሻህ ናፈቀኝ …
ከአቶ ሳልማን ማህመድ ፔጅ የተገኜ። ውዶቼ ዛሬ ከተለመደው ውጪ ነው እምሳተፈው። ባለመቻል። የሆነ ሆኖ የምችለውን ማድረግም መልካም ነው።
አቶ ሳልማን እንዲህ ይሉናል። ሳልማን የእሷ ፍቅር የሚባሉ ወዳጅ ነበሩኝ እኒህ አዲስ ናቸው፣ አፋርኛ ሥም ነው …… "እነሆ ጀግንነት. . . ከሃራ እስከ አላዉሃ ያልተነገረለት ግድል
_
የህወሓት ወራሪዎች ራያ ቆቦ ወረዳን በሸፍጥ ከተቆጣጠሩ በኋላ ያቀኑት ወደ ሀብሩ ወረዳ ነበር። እዛ ደግሞ የሚጠብቃቸው ሽርጣሙ ፣ ረመጡ ፣ ባለ አንድ እግራው የሀብሩ ሶዶማዎች ነው።
የሃራ እና አከባቢው ህዝብ ጠላት እየመጣ መሆኑ መረጃ ሲደረሰው ፈፅሞ ከተማውን ጥሎ አልሸሸም ፣ ከተማውን ድረስ እስኪመጡም አልጠበቀም ፣ የመከላከያንም ሆነ የአማራ ልዩ ሀይልን እርዳታ አልጠየቀም. . . .
ይልቁንም ከተማውን ከከባድ መሳሪያ ድብደባ እራሱንም ከባርነት ለማትረፍ የውጊያ ቀጠናውን ከሀራ ከተማ ወደ ሰሜን 3 km ወጣ ብሎ ቦታ ይዞ ጠበቃቸው እንጂ።
-
""ታሪክን ይሰሩታል እንጂ አምጠው አይወልዱትም"" እንዲሉ ሃራን ለመያዝ የመጣውን #ሁለት_ሻለቃ የጠላት ጦር በሶስት ቀን ውጊያ አፈር አበሉት።
ይህኔ ሃራን መያዝ ጉም እንደመጨበጥ የሆነበት የጠላት ሀይል ወደ ሃራ ሊያደርገው የነበረውን መስፋፋት በመተው ወደ አላውሃ ፈረጠጠ ጀግኖቹ ግን ጠላት ሸሸ ብለው ወደ ቤታቸው አልተመለሱም ይልቁንም እግር በእግር ተከትለው አላውሃ አከባቢ ሲደርስ አጋዥ ሀይል ያገኘው ፈርጣጭ የልብ'ልብ ተሰምቶት ፍርጠጣውን አቁሞ ፊቱን አዙሮ አንድ እግራዎቹን ገጠመ እንደ ሀራ ሁሉ አላውሃም ጠላትን ከዳችው የሞተው ሞቶ የቀረው ጠላት ""ወዲ ሽርጣም አይተኻአለን"" እያለ ወደ ምትመለከቱት ተራራ ፍርጠጣውን ቀጥሎ እናት ክፍለ ጦሩን ተቀላቀለ።
ይህ ሁሉ ሲሆን ስንቅም ሆነ ትጥቅ የረዳቸው የለም ፣ ከልዩ ሀይሉም ሆነ ከመከላከያ እርዳታ አላገኙም። ከሁሉም የሚሳያዝነው ደግሞ ይህ ሁሉ ሲሆን ቁስለኞቻችንን የሚያነሳ አንድም አምቡላንስ አልነበረም።
ይልቁንም የአከባቢው ህዝብ እና እናቶች በዚህ ተስፋ አስቆራጭ (despairing) ሁኔታ ሳይደናግጡ እንደ ህዝብ የገጠማቸውን ጠላት እንደ ህዝብ ከመግጠም ባሻገር ""ጥይት እና ስንቅ" በማዋጣት እነ **** *** (ስም መጥቀስ አልፈለኩም) በመሰሉ ቆራጥ ልጆቹ አማካኝነት ግንባር ድረስ በመኪና እየተከተሉና እያከፋፈሉ ነው በቆረጣ የመጣዉን #ሁለትሻለቃ ጠላት አፈር አስግጠው ከመስፋፋት የገቱት።
_
ከሃራ እና አከባቢው ህዝብ ብዙ ልንማር ይገባል
እነዚህ ጀግኖች ከተማቸውን ጠላት እንዲያወድማት ጥለውለት አልሸሹም ፣ በክብር መሞትን እየተቻለ ባርነትን መርጠው መኖርን መርጠውም እጃቸውን አጣጥፈው አልተቀመጡም ፣ ተመጣጣኝ የጦር መሳሪያ የለንም ብለው ብሬን እና ዲሽቃ የታጠቀን ሀይል በክላሽ ለመግጠም ቅንጣት ታክል አላመነቱም ፣ ለመዋጋት ሲወስኑም ጠላት ያሉበት ድረስ እስኪመጣ አልጠበቁም ይልቁንስ የውግያ ቀጠናውን ከከተማቸው 3 km ወጣ ብለው መግጠምን መርጠዋል ፣ እንደ ህዝብ የገጠማቸውን ጠላት እንደ ህዝብ ገጥመው ታሪክ የማይረሳው ገድል ፈፅመዋል።
የእነዚህን ጀግኖች የጦር ሜዳ ገድል በመፀሀፍ መልክ እኔ ራሴ በእጄ እፅፈዋለሁ።"
ህወኃት የልባቸውን እያደረሰላቸው ነው ለማህበረ ኦነግ። የዛሬ ዓመት ላደረሰው የበጎ ሰው ሽልማት ይጠብቀዋል። ህወኃት ግን ዕድሉን ካገኜ አንበርክኮ የኦህዴድን ባለሥልጣናት አዛባ ያስጠርጋል። ጠብቁት።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
02/08/2021
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ